Horn History

Horn History If you say every thing is possible, it will be possible!

ወ/ሮ  #ደስታ  #ገብሩ በኢትዮ ሶማሊያ ድንበር ቶጎ ውጫሌ ጦር ግንበር በ1956 ዓ.ምወ/ሮ ደስታ ገብሩ ከታዋቂው አባታቸው ከከንቲባ ገብሩ ደስታና ከእናታቸው ከወ/ሮ ካሣዬ የለምቱ በ1913...
15/08/2026

ወ/ሮ #ደስታ #ገብሩ በኢትዮ ሶማሊያ ድንበር ቶጎ ውጫሌ ጦር ግንበር በ1956 ዓ.ም

ወ/ሮ ደስታ ገብሩ ከታዋቂው አባታቸው ከከንቲባ ገብሩ ደስታና ከእናታቸው ከወ/ሮ ካሣዬ የለምቱ በ1913 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ አባታቸው ከንቲባ ገብሩ አጼ ምኒልክ ዘውድ ከመጫናቸው ከዛሬ 145 አመት በፊት በሚሲዮናውያን አማካኝነት ከበጌምድር ወደ ውጭ ተልከው ከፍተኛ ት/ት ከተከታተሉት ጥቂት ኢትዮጵያውያን መካከል አንዱ ናቸው፡፡ ከአጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት ጀምሮ እስከ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የመጀመሪያዎቹ የስልጣን ዘመንም በከፍተኛ ኃላፊነት አገራቸውን አገልግለዋል፡፡

ወ/ሮ ደስታ ገብሩ በአዲስ አበባ የስዊድን ሚሽን ት/ቤትና በእቴጌ መነን አዳሪ ት/ቤት ከመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ፓርላማ ሴት አባል እህታቸው ወ/ሮ ስንዱ ገብሩ ጋር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ በመቆየት ፋሺስት ኢጣሊያ በ1928 ዓ.ም ኢትዮጵያን ሲወር ትምህርታቸውን አቋርጠዋል፡፡ የፋሺስት ኢጣሊያን ወረራ ተከትሎ፣ አባታቸው ከንቲባ ገብሩ ቤተሰቡን ይዘው ወደ ነቀምትና ጎሬ በመሄድ በራስ እምሩ የሚመራውን የጥቁር አንበሳ አርበኞች ቡድን ተቀላቅለዋል፡፡

ይህንን ተከትሎም ፋሺስት መሸሻና ደበበ የተባሉትን የከንቲባ ገብሩን ወንድ ልጆች እአአ በየካቲት 1937 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከገደለ በኋላ፣ ከንቲባ ገብሩን ከቀሪ ቤተሰቦቻቸው ጋር በመያዝ ወደ ኢጣሊያ አገር አዚናራ እስር ቤት እስከ ነጻነት ድረስ አስሮ አቆይቷቸዋል፡፡ ወ/ሮ ስንዱ ገብሩ ከኢጣሊያ ከእስር ተለቀው እንደመጡ በአዲስ አበባ የእቴጌ መነን ት/ቤት በመምህርነት አገልግለዋል፡፡

ወ/ሮ ደስታ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበርንም ከተመሰረተበት ከ1928 ዓ.ም ጀምሮ ከ30 አመት በላይ በበጎ ፈቃደኝነት አገልግለዋል፡፡ ወ/ሮ ደስታ የኢትዮጵያ ሴቶች በጎ አድራጎት ድርጅትን በም/ፕሬዚዳንትነት መርተዋል፡፡ የወታደር ሚስቶች የበጎ አድራጎት ማህበርንም በ1956 ዓ.ም በማቋቋም ማህበሩን በፕሬዚዳንትነት አገልግለዋል፡፡

ወ/ሮ ደስታ በቶጎ ውጫሌ ግንባር የሶማሊያ ጦርን ለመመከት ኮ/ል አብዲሳ አጋን ጨምሮ በ1956 ዓ.ም ለዘመተው የኢትዮጵያ ጦር በጦር ግምባሩ በመገኘት በበጎ አድራጎት ስራ ተሳትፈዋል፡፡ ወ/ሮ ደስታ ገብሩ የታዋቂው ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ የሌ/ጄኔራል ከበደ ገብሬ ሚስትና በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳም የሚገኙት ፕያኖ ተጫዋቿ መነኩሴ የእማሆይ ጽጌ ማርያም እህት ነበሩ፡፡

ምንጭ፣ ቆፍጣናው ወታደር ሌ/ጄኔራል ከበደ ገብሬ፣ ከ1910-1967 ዓ.ም፣ በታምራት ከበደ/ሺበሺ ለማ፣ 2007 ዓ.ም

በአስተያየት መስጫው ላይ የተቀመጠው የከንቲባ ገብሩና የቤተሰቦቻቸው ምስል ሲሆን፣ ፎቶግራፉ በ1920ዎቹ እንደተነሳ ይታመናል፡፡

የአዲስ አበባ አናጺዎችበዮሐንስ መኮንን ---------------(የግል አስተያየ)አዲስ አበባ የተገነባችው በአንድ ወይም በሁለት ብሔሮች ብቻ ሳይሆን ከመላዋ ኢትዮጵያ በተሰባሰቡ ብሔሮች (ኦሮ...
15/08/2026

የአዲስ አበባ አናጺዎች
በዮሐንስ መኮንን
---------------
(የግል አስተያየ)

አዲስ አበባ የተገነባችው በአንድ ወይም በሁለት ብሔሮች ብቻ ሳይሆን ከመላዋ ኢትዮጵያ በተሰባሰቡ ብሔሮች (ኦሮሞ፣ አማራ፣ ሶማሌ፣ ጉራጌ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ዶርዜ፣ ወላይታ፣ ሲልጤ፣ ከምባታ፣ ሀዲያ... ወዘተ) ላብ እና ወዝ መሆኑን በርካታ ጥናቶችን ማጣቀስ ይቻላል። ለሰሞነኛው "የይገባኛል" ጥያቄ ማስታወሻ እንዲሆን የጥቂቶቹን ከታሪክ ምስክር ጋር አቀርባለሁ።

ሶማሌ
ፒተር ጋሬትሰን (Peter Garretson) ለ3ተኛ ዲግሪ ማሟያ "A History of Addis Abäba from Its Foundation in 1886 to 1910" በሚል ርእስ ባዘጋጁት ጽሑፍ፤ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመን የከተማዋ የመጀመሪያው ዘመናዊ የፖሊስና የጥበቃ ኃይል ሲደራጅ የሶማሌ ማኅበረሰብ አባላት በግንባር ቀደምነት ተሳትፈዋል ይላሉ። እነዚህ የፖሊስ አባላት በወቅቱ «ሶማሌ ፖሊስ» በመባል ይታወቁ የነበረ ሲሆን፣ የቤተ-መንግሥቱን፣ የአራዳን ንግድ ማዕከልና የከተማዋን ሰላም በማስከበር ረገድ ትልቅ ድርሻ ነበራቸው።

(በተጨማሪም በ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ በሊቢያ (ትሪፖሊ) ሰልጥነው የመጡ የአዲስ አበባ ጥበቃ አባላት "ትሪፖሊ" ከሚለው የከተማዋ ስም በመነሳት በሕዝብ አነጋገር ተለውጦ "ጥሩምቡሌ" ወይም ትሩምቡሌ በመባል ይታወቁ ነበር።)

ጉራጌ
ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት (Richard Pankhurst) "Economic History of Ethiopia" በሚል ርእስ ባዘጋጁት ጽሑፍ ደግሞ፤ የጉራጌ ማኅበረሰብ አዲስ አበባ ከተቆረቆረችበት ጊዜ ጀምሮ በቤት ግንባታ፣ በድንጋይ ጥርብ፣ በመንገድ ሥራ፣ በግንባታ ቁሳቁስ አቅርቦትና በትራንስፖርት (በጋሪና በሸክም) የከተማዋ ግንባታ የጀርባ አጥንት ሆኖ ማገልገሉን ይገልጻሉ።

ትግራዋይ
ፓንክረስት "History of Ethiopian Towns" በሚለው ሌላ ሥራቸው ደግሞ፤ ከትግራይ የመጡ የእጅ ባለሙያዎች፣ የድንጋይ ጠራቢዎችና አናጢዎች በከተማዋ የሚገኙ አበይት ቤተ-መንግሥቶች፣ ቤተ-ክርስቲያናት (ለምሳሌ የእንጦጦ ማርያምና የቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል) እና የቀደሙት ሕንጻዎች ግንባታ ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ እንደነበራቸው ይጠቅሳሉ።

ኦሮሞ
ፕ/ር ባህሩ ዘውዴ "A History of Modern Ethiopia" በሚለው ጽሑፋቸው፤ አዲስ አበባ ከመቆረቆሯ በፊት በአካባቢው ይኖሩ የነበሩት የኦሮሞ አባወራዎች (በተለይም የቱለማ ኦሮሞ) ለከተማዋ ምስረታና እድገት መሬታቸውን፣ የውኃ ምንጮቻቸውንና የተፈጥሮ ሀብታቸውን መስጠታቸውን ጽፈዋል። የከተማዋ ነዋሪ ቁጥር እየጨመረ ሲመጣ ከእንጦጦ፣ ከሱልልታ፣ ከአቃቂና ከቡራዩ አቅጣጫ እህል፣ እንጨት፣ ወተት፣ ቅቤና የቁም እንስሳትን በማቅረብ የከተማዋን ዕለታዊ ሕይወትና የገበያ እንቅስቃሴ ደግፈው አቁመዋል።

አማራ
ፕ/ር ባህሩ ዘውዴ "Pioneers of Change in Ethiopia" በተሰኘ ሌላ መጽሐፋቸው፤ የከተማዋ የመጀመሪያዎቹ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ የጽሕፈት ሥርዓት፣ የፍርድ ቤትና የአስተዳደር መዋቅሮች ሲዘረጉ የነበረውን የቢሮክራሲ፣ የሕግና የጽሕፈት መሠረት የጣሉት የጎንደር፣ የወሎና የሸዋ አማራ ማኅበረሰብ መሆናቸውን ያብራራሉ።

ጋሞ
ዴና ፍሪማን እና አሉላ ፓንክረስት (2003) "Peripheral People: The Excluded Minorities of Ethiopia" በተሰኘ ጽሑፋቸው፤ የጋሞ ማኅበረሰብ አዲስ አበባ ከተቆረቆረችበት ጊዜ ጀምሮ የሀገር ባህል አልባሳት (ነጠላ፣ ጋቢ፣ ቀሚስና ቡልኮ) በማምረት ረገድ ዋናው ባለድርሻ መሆናቸውን ያትታሉ። በከተማዋ የሽመና ኢንዱስትሪን (የእጅ ሽመናን) በመመራት የከተማዋን ነዋሪዎችና የውጭ ሀገር ዜጎችን የልብስ ፍላጎት በማሟላት ትልቅ የባህልና የኢኮኖሚ አሻራ አኑረዋል። እንደ ሺሮ ሜዳ ያሉ ታዋቂ የከተማዋ አካባቢዎች የጋሞ ማኅበረሰብ የባህል፣ የንግድና የእጅ ጥበብ ማዕከል ሆነው እንዲደራጁ እና የከተማዋ የቱሪዝም እና የንግድ የስበት ማዕከል እንዲሆኑ አድርገዋል።

ጎፋ
ቀደም ባሉት ዘመናት ከደቡብ ኢትዮጵያ ወደ አዲስ አበባ በሚደረጉ የንግድ መስመሮች አማካኝነት የቅመማ ቅመም፣ የእህል እና የቁም እንስሳት አቅርቦት ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ አድርገዋል።

ዶርዜ
በሽመና ጥበብ፣ በባህላዊ የቤት አሠራር ውበት እና በካፒታል ማከማቸት (በዕቁብና ማኅበራዊ ትስስር) በኩል በከተማዋ የፋይናንስና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጥረዋል።

ሲዳማ
የቡና እና የቅመማ ቅመም ንግድን ከደቡብ ወደ አዲስ አበባ ዋና ገበያ (አራዳና መርካቶ) በማስገባት፣ አዲስ አበባ የሀገሪቱ የቡና ወጪ ንግድ ማዕከል እንድትሆን በመደገፍ ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል።

ወላይታ፣ ሀዲያ እና ከምባታ
በከተማዋ ዘመናዊ መሠረተ-ልማቶች ግንባታ፣ በኢንዱስትሪዎች፣ በአገልግሎት ዘርፍ፣ በትምህርትና በጤና ተቋማት እንዲሁም በንግድ ውስጥ በከፍተኛ ቁጥር በመሰማራት የከተማዋን የሰው ኃይል እና የኢኮኖሚ እድገት ደግፈዋል።

(ዶ/ር ቢሻው መኮንን በ1991 "Internal Migration and Urbanization in Ethiopia" በሚል ርእስ ባዘጋጁት ጥናት ደግሞ የሚከተሉትን ማኅበረሰቦች ያነሷቸዋል፦)

• ካፋ፦ የቡና መገኛ ከሆነው አካባቢ የመጡ የካፋ ነጋዴዎችና ባለሙያዎች፣ የቡና ምርትንና የባህል እሴቶችን ወደ ከተማዋ በማምጣት ለንግዱ እድገት አስተዋጽኦ አድርገዋል።

• ስልጤ፦ بالمርካቶ እና በከተማዋ የንግድ ማዕከላት ውስጥ በአነስተኛ፣ በመካከለኛና በከፍተኛ ንግድ፣ በትራንስፖርትና በጅምላ አቅርቦት የከተማዋን የንግድ ዝውውር ከሚመሩት ዋና ዋና ማኅበረሰቦች አንዱ ናቸው።

• ሐረሪ፦ ከጥንታዊቷ የሐረር ጁጎል ከተማ የመጡ የሐረሪ ነጋዴዎች በወርቅ፣ በጨርቃ ጨርቅና በቅመማ ቅመም ንግድ አዲስ አበባን ከምስራቁ የንግድ መስመር ጋር በማስተሰረር ትልቅ ሚና ተጫውተዋል።

ማጠቃለያ
ከላይ የጥናት ወረቀቶች እና ልዩ ልዩ መጻሕፍት እንደሚመሰክሩት አዲስ አበባ የጠቀስኳቸው እና ያልጠቀስኳቸው ከምስራቅ እስከ ምዕራብ እና ከሰሜን እስከ ደቡብ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በጋራ ያፈሰሱት ላብ፣ እውቀት፣ ንግድና የባህል ቅይጥ ውጤት ናት። ይህ የታሪክ እውነታ አዲስ አበባ የማንም ብቸኛ ግዛት ሳትሆን የሁላችንም የጋራ ቤታችን መሆኗን ያረጋግጣል።

---------------
ቀጣይ ጥያቄ፦
አዲስ አበባን የመሰለ አንድ የፌደራል ዋና ከተማን ለአንድ በብሔር ለተደራጀ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ ከተማነት መስጠት ተገቢ ነው? የከተማ ዕቅድ (Urban Planning) ሳይንስን እና ዓለም አቀፍ ልምዶችን መሠረት አድርጌ ሀሳብ ለማካፈል በቀጣይ እመለሳለሁ።

(ይቀጥላል...)
Moktarovich Osmanova

አፄ ዮሐንስ ህይወቱን በሱዳኖች ያጣው ለግብፅ እና ለእንግሊዝ ሲል ነበር።ነገሩ እንዲህ ነው።በሙሀመድ አህመድ የሚመራው የሱዳን መህዲስት ጦር ሱዳንን የወረረውን የግብፅ ጦር አሸንፎ በከሰላ አ...
14/08/2026

አፄ ዮሐንስ ህይወቱን በሱዳኖች ያጣው ለግብፅ እና ለእንግሊዝ ሲል ነበር።

ነገሩ እንዲህ ነው።

በሙሀመድ አህመድ የሚመራው የሱዳን መህዲስት ጦር ሱዳንን የወረረውን የግብፅ ጦር አሸንፎ በከሰላ አማዲድ እና በኤርትራ ሰንሂት ላይ ከበውት ነበር። ግብፅ ደግሞ በጊዜው የእንግሊዝ የሞግዚት ግዛት ወይንም ተዘዋዋሪ ቅኝ ግዛት ስር ነበረች። እናም በሱዳን ጦር የተከበበውን የግብፅ ጦር ለማውጣት እንግሊዝ መላ ቢጠፋባት አፄ ዮሐንስን ማሸማገል ፈለገች። ግብፅና ኢትዮጵያ ጦርነት ላይ የነበሩ ቢሆንም እንግሊዝ አስታርቃ የኢትዮጵያ ጦር የተከበቡትን የግብፅ ጦር እንዲያወጡ ለማድረግ ዲፕሎማቷን ዊሊያም ሂወትን ወደ አስመራ ከዚያም ወደ አድዋ ላከች።

እናም አፄ ዮሑንስ በሶስት መስፈርት የግብፅን ጦር ከከበባ ለማውጣት ተስማሙ።
የመጀመሪያው ኢትዮጵያ የምፅዋ ወደብን እንዲትጠቀም
ሁለተኛው ግብፅ ጳጳሳቶቿን ወደ ኢትዮጵያ መላኳን እንዲትቀጥል
ሶስተኛ ግብፅ የያዘቺውን የቦጎት ግዛት ለኢትዮጵያ እንዲትመልስ ነበር።

አፄ ዮሐንስ የግብፅን ጦር ካስመለጠ በሗላ እንግሊዝ ለዮሐንስ የገባችለትን ቃል አፈረሰች። እናም ምፅዋን ከኢትዮጵያ ነጥቃ ለኢጣሊያ ( ጣልያን) ሰጠቻት። ግብፅ የለቀቀቻቼውን የኤርትራ መሬቶችም ኢጣልያ ተቆጣጠረቻቼው።

ከስምምነቱ ሌላ አደገኛ ከግብፅም የባሰ ጠላት እንጅ ምንም ያላተረፈው የአፄ ዮሐንሱ የኢትዮጵያ ጦር የግብፅን የተከበበ ሰራዊት ከሱዳን ከበባ አውጥቶ ለግብፅና እንግሊዝ አስረከበ። ሱዳን በዚህ ጊዜ እንደት ለግብፅ አግዛ ትወጋኛለች በማለት ኢትዮጵያ ላይ ጦርነት አወጀች።
ፕሮፌሰር ያቆብ አርሳኖ "Theory and Practice of Diplomacy" ን ሲያስተምሩን ክስተቱን ሲገልፁት " ዮሐንስ በአንፃራዊነት ትንሹን ጠላት ታርቆ ከትልቁ ጠላት ጋር ተላተመ" ነበር ያሉን። በርግጥ ሱዳን ከግብፅ የበለጠ አስፈሪ ነበልባል ሀይል አደራጅታ ነበር።

ምእራብ ኢትዮጵያን ጀምሮ ሱዳን እያጠቃች እስከ ጎንደር ድረስ ከፍተኛ ውድመት አደረሰች። ለአመታት የሱዳን ጦር የኢትዮጵያ ግዛቶች እያጠቃ ቤተክርስቲያን እያወደመ የበቀል በትሩን እያሳረፈ ከቆየ በሗላ ጦርነቱን ከመግጠም ውጭ አማራጭ ያልነበራቸው አፄ ዮሐንስ የሱዳንን ጦር መተማ ላይ ጥራቸውን እየመሩ ገጠሙ። የሱዳን ጦርም ዮሐንስን አንገቱን ቆርጦ በመውሰድ አሸናፊነቱን ደመደመና በቀሉን አጣጣመ።

አፄ ዮሐንስ ይህን ያደረጉት ከግብፅ ጳጳሳት እንዲላኩላቸውና ምፅዋን እንዲጠቀሙ ከግብፅና እንግሊዝ በቀረበላቸው ግብዣ ነበር።
አፄ ዮሐንስ ከግብፅ ጳጳስ ካልመጣ ሀገሪቱ አደጋ ላይ እንደምትወድቅና የርሳቸው የስልጣን ሄጋዊነትም ጥያቄ ውስጥ እንደሚገባ ያስቡ ነበር።
ግብፅ በጳጳሳቶቿ አማካኝነት ለሺህ አመታት የኢትዮጵያን ፖለቲካ ስትዘውር መኖሯ የሚያስገርም እውነታ ነው።

ቴሌግራም Seid Mohammed
👉

ጎረቤቶቻችን ስራ እየፈቱ ነው !!እውቁ የኬኒያ የሕግ ጠበቃ የሆነው አቶ ዶላ እንድዲስ፣ ኢየሱስን የገደሉትን የእስራኤልን እና የጣሊያን መንግስት ሠራዊቶችን ጨምሮ በወቅቱ የነበሩ የመንግስት ...
11/08/2026

ጎረቤቶቻችን ስራ እየፈቱ ነው !!

እውቁ የኬኒያ የሕግ ጠበቃ የሆነው አቶ ዶላ እንድዲስ፣ ኢየሱስን የገደሉትን የእስራኤልን እና የጣሊያን መንግስት ሠራዊቶችን ጨምሮ በወቅቱ የነበሩ የመንግስት ገዥዎችን በአለም አቀፍ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት በአካል ቀርቦ የወንጀል ክስ መስርቶባቸዋል። ጉዳዩንም በትኩረት እየተከታተለ እንደሚገኝ ጠበቃው ገልፆል።

የደቡብ አፍሪካውን ጥቁር ጠል ፍረጃና ጭፍጨፋ ለማውራት የተሳነው የማይበላውን ቅማል ስያክ ያበሳጫል።

08/08/2026

The Concept of Eternal Life (After Life) or Heaven among ancient Kush-Kemet people.

Thousands of years before the story of life after death and eternal life (heaven) was copied and rewritten into Abrahamic mythology, the ancient Africans used to believe that there is life after (eternal life) or heaven. They referred to it as the Garden of Osiris (Asur) where the soul of people who lived a life of balance, order, and truth would enjoy the eternity.

Ancient Kushetic-Kemet people believed that there are two distinct aspects of human life. They called them Ba (physical body) and the Ka (the soul). When one dies, the soul separates from the body to go and appear in front of the judge for negative self confession. Based on the 42 law of MAAT (moral codes), the soul confesses that it has lived by virtue, lived by truth, by honoring animals with reverence, holding purity in high esteem, achieving with integrity, by embracing all…etc.
Following self confession, the soul weighs against a feather. If the weight of the soul and feather are equal, then the soul considered pure and will be admitted into the Garden of Osiris (heaven). If the soul weighs heavier than the feather, then it considered sinful and would devoured by the Crocodile 🐊 deity called Amit.

The Biblical 10 commandments are believed to be copied from the ancient Kush-Kemet Book of Dead,

The Ritual of Judgment
* The Scale: The jackal-headed god Anubis guides the scales in the Hall of the Truth (Duat), measuring the heavy inner ledger of a person's life choices.
* The Heart: Believed to record every good and bad deed, the physical heart acts as the sole witness and test of character.
* The Feather: Representing Ma'at, the goddess of truth, balance, and order, it establishes the ultimate baseline of a pure, unburdened existence.

The Outcome
* Lighter or Balanced: If the heart is as light as or lighter than the feather, the soul achieves eternal peace and enters paradise in the Field of Rushes.
* Heavier: If the heart is weighed down by selfishness, lies, and wrongdoings, it is immediately cast down and consumed by Ammit, the dread Devourer of Souls.

They built magnificent Pyramids with internal decorated with text messages meant to guide the deceased to the afterlife. The deceased had to overcome various obstacles on their way to the afterlife. This included demons, snakes or knife-wielding gatekeepers. The text, therefore, reveals spells and methods used to overcome each obstacle and successfully reach the after life.

The Concept of Eternal Life (After Life) or Heaven among ancient Kush-Kemet people. Thousands of years before the story ...
06/08/2026

The Concept of Eternal Life (After Life) or Heaven among ancient Kush-Kemet people.

Thousands of years before the story of life after death and eternal life (heaven) was copied and rewritten into Abrahamic mythology, the ancient Africans used to believe that there is life after (eternal life) or heaven. They referred to it as the Garden of Osiris (Asur) where the soul of people who lived a life of balance, order, and truth would enjoy the eternity.

Ancient Kushetic-Kemet people believed that there are two distinct aspects of human life. They called them Ba (physical body) and the Ka (the soul). When one dies, the soul separates from the body to go and appear in front of the judge for negative self confession. Based on the 42 law of MAAT (moral codes), the soul confesses that it has lived by virtue, lived by truth, by honoring animals with reverence, holding purity in high esteem, achieving with integrity, by embracing all…etc.
Following self confession, the soul weighs against a feather. If the weight of the soul and feather are equal, then the soul considered pure and will be admitted into the Garden of Osiris (heaven). If the soul weighs heavier than the feather, then it considered sinful and would devoured by the Crocodile 🐊 deity called Amit.

The Biblical 10 commandments are believed to be copied from the ancient Kush-Kemet Book of Dead,

The Ritual of Judgment
* The Scale: The jackal-headed god Anubis guides the scales in the Hall of the Truth (Duat), measuring the heavy inner ledger of a person's life choices.
* The Heart: Believed to record every good and bad deed, the physical heart acts as the sole witness and test of character.
* The Feather: Representing Ma'at, the goddess of truth, balance, and order, it establishes the ultimate baseline of a pure, unburdened existence.

The Outcome
* Lighter or Balanced: If the heart is as light as or lighter than the feather, the soul achieves eternal peace and enters paradise in the Field of Rushes.
* Heavier: If the heart is weighed down by selfishness, lies, and wrongdoings, it is immediately cast down and consumed by Ammit, the dread Devourer of Souls.

They built magnificent Pyramids with internal decorated with text messages meant to guide the deceased to the afterlife. The deceased had to overcome various obstacles on their way to the afterlife. This included demons, snakes or knife-wielding gatekeepers. The text, therefore, reveals spells and methods used to overcome each obstacle and successfully reach the after life.

ከዋክብት ይረግፋሉ፣ የኢትዮጵያ ትንሣዔስ.. እውን ይሆናል?〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️በበኩሌ በዚህች የዛሬዋ ዓለም ላይ በይፋ ሠይጣንን የሚያመልኩ ሁለት እምነቶችን አ...
03/08/2026

ከዋክብት ይረግፋሉ፣ የኢትዮጵያ ትንሣዔስ.. እውን ይሆናል?
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️

በበኩሌ በዚህች የዛሬዋ ዓለም ላይ በይፋ ሠይጣንን የሚያመልኩ ሁለት እምነቶችን አውቃለሁ።

አንደኛው ኢራቅ ውስጥ ይገኛል። አምላኪዎቹም ያዚዲዎች ይባላሉ። በእነሱ እምነት አምላክ ይቺን ዓለም ፈጥሮ ሥራውን ጨርሶ ሲሄድ፣ ምድሪቱን በአደራ ያስረከባት ለሰባት መላዕክታት ነው። የመላዕክታቱ አለቃ ደሞ የጣዖስ ወይም የpeacock መልክ ያለው "መለክ ጣዎስ" ነው። በአምላክ ላይ ያመፀውም እሱ ነው።

ግን ያዚዲዎች አምላክ ሠይጣንን ይቅር ብሎ ወደ ቀደመ ክብሩና የዚህች ዓለም ገዢነት ሥልጣኑ መልሶታል ብለው ያምናሉ። የዚህች ዓለም ገዢ እሱ ነው ስለሚሉም ያመልኩታል። በእርግጥ ያዚዲዎች እኛ ሠይጣንን ("ኢብሊስን") አናመልክም ይላሉ።

ኢብሊስ ለአዳም አልሰግድም ያለው ከትዕቢቱ የተነሳ ነበር፣ መለክ ጣዎስ ግን ፈጣሪ ለማንም አትስገድ ስላለው ለአዳምም አልሰግድም አለ። በዚህ የተነሳም አምላክ በመላዕክታት ላይ አለቃ አድርጎ የምድር ገዢም አድርጎ ሾመው። ያዚዳኒዝም የሚያመልከውም መለክ ጣዎስን (ፒኮኩን መልዓክ) እንጂ አመፀኛውን ኢብሊስን ወይም ሰይጣንን አይደለም፣ ስለዚህ ከሰይጣኒዝም ጋር አታምታቱን ይላሉ።

ሌላኛው በግልፅ ሠይጣንን ለማምለክና ክርስትያኖችን ለመቃረን ሆን ተብሎ የተጀመረው ሐይማኖት ሠይጣኒዝም ነው። መሥራቹም አሜሪካዊው አነቶን ላቬይ ነው። አንቶን ላቬይ ሐይማኖተኛ ነበር። ከዚያ በአንድ የጥምቀት በዓል ላይ የቸርች ፒያኖ ዜማ ተመስጬ እየሰማሁ ሠይጣን ተገለፀልኝና ደቀመዝሙሩ እንድሆን፣ ይቺን ዓለምና ሕዝቦቿንም ከአምላክ ጨካኝ አገዛዝ ነፃ እንዳወጣ አጨኝ ነው የሚለው።

አንቶን ላቬይ በ1969 እኤአ (በእኛ አቆጣጠር 1961 ዓ/ም ላይ — ማለትም ከ60 ዓመታት ገደማ በፊት) "ሠይጣናዊ ቅዱስ መፅሐፍ" ("The Satanic Bible") የሚለውን የሠይጣን አምልኮት መፅሐፍ አሳትሟል። በሽፋኑም ላይ (በውስጡም) ሠይጣን ባፎሜት ሲገለፅለት የሰጠውን ባለ አምስት ኮከብ የሠይጣን ባፎሜት ማህተም አሳትሞ አውጥቶታል። ከዚያም ወዲህ ይህ የሠይጣን ኮከብ የሠይጣኒዝም ዋና ምልክትና በቤተ መቅደሶቻቸውና ድርሳኖቻቸው ሁሉ ላይ የሚቀርፁት ዋናው መለያ ምልክታቸው ነው።

በሠይጣኒዝም እምነት መሠረት የሰውልጅ ራሱን ዝቅ ዝቅ እንዲያደርግና በባርነት እንዲገዛለት፣ ሰውነቱንና ሰዋዊ ስሜቶቹን እንዲጨቁን፣ ገንዘብንና የበላይነትን እንዲጠላ፣ የዚህችን ዓለም ወርቅና አልማዝ እንዲፀየፍ፣ እንዲፈራና እንዲንቀጠቀጥለት የሚፈልገውን ፈላጭ ቆራጭ አምባገነን አምላክ ሳይሆን፣ ይህን ፈላጭ ቆራጭ አምላክና መንግሥቱን አስወግዶ ለሰው ልጅ እንዳሻው እንዲቦርቅ ነፃነቱን ሊያጎናፅፈው ሲል በአምላክ ላይ ያመፀውን ታላቁን አዋቂና የሰውልጅ ተቆርቋሪ ሠይጣንን እናመልካለን የሚል አስተምህሮ አለው።

በተለይ ሠይጣኒዝም የሚቃረነው ክርስትናን ነው። ዝሙትን ያበረታታል፣ እንዲያውም ዝሙት በአምልኮ ወቅት መፈፀም አለበት ወደ ታላቅድስና የሚወስደንም የህይወት መንገድ ነው ብሎ ያምናል። በመታበይም ያምናል፣ የሰልጅ ባለውበሚያገኘው ነገር እስካፍንጫው መኩራትና መንጠባረር መብቱ ነው። የሰውልጅ ባርያ ስላልሆነ ለአምላክ የመገዛትም ግዴታ የለበትም ይላል። ተፈጥሮን ማምለክ ግን መብቱ ነው።

የሠይጣኒዝም የተቀደሰ ዓላማም አምላክ በሠይጣን ታላቅ ተጋድሎ የተነጠቀውን ይቺን ምድርንና የሰውልጅን ሊወስድ/ሊቀማ ዳግም በሚመጣበት ወቅት፣ ከሠይጣን ጋር ወግኖ አምላክንና ታማኝ ጭፍሮቹን የሚዋጋ ሠይጣናዊ ሠራዊትን መገንባትና ማብዛት ነው።

ሠይጣኒዝም በግልፅ ዓላማችን በዳግም ምፅዓት ሊገዛንና ዐደ ገሃነም እሳት ሊወረውረን የሚመጣውን ጨካኝ አምላክ መዋጋትና ድል ማድረግ፣ ወደመጣበትም አሳፍረን መመለስ ነው ይላል። ተዘጋጁ የፍፃሜ ጦርነት ደርሳለች እያለም አማኒዎቹን ያተጋ ነበረ ራሱን የሠይጣኒዝም ላዕላይ ጳጳስ ነኝ ብሎ የሾመው አንቶን ላቬይ።

ላቬይ አምላክን ለመፋለም ከፍተኛ አምሮት ያደረበት የሠይጣኒዝም ካህን ቢሆንም፣ አምላክን ሳይዋጋ ቀላል በሽታ ገደለው። በሆስፒታል ንስሃ እንዲገባ ሲጠየቅ፣ ኮከቤን ብቻ ስጡኝ ብሎ ኮከቡን እንደታቀፈ አሸለበ።

ብዙም በወጉ ያልተዘመረለት የኢትዮጵያችን ሠዓሊ፣ ፀሐፊና ገጣሚ የነበረው መስፍን ሀብተማርያም — ኢህአዴግ ለአርቲስቶች ባንዲራው ላይ የሚለጠፍ ብሔራዊ አርማ እንዲያመጡ ጨረታ ሲያወጣ፣ ይህንን የባፎሜትን ኮከብ ስሎ አስገባ። በወቅቱ እንደ ታላቁ አፈወርቅ ተክሌ ጭምር በውድድሩ ተሳትፈው እንደነበረ ይነገራል።

በዚያ ውድድር የመስፍን ሀብተማርያም ኮከብ አለፈ። ትርጉሙንም የብሔብሔረሰቦች እኩልነት የተረጋገጠባት፣ እንደ ጎጆ ቤት ሁላችንንም በእኩልነት ያስጠለለችውን እናት ሀገር ይወክላል ብሎ ማቅረቡን ይናገራሉ። የጨረታው ሰነድም ግልፅ የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነትን፣ ተስፋን፣ አብሮ ተያይዞ ማደግን ወዘተ የሚናገር ነበረ። አሸነፈና አለፈ የመስፍን ሀብተማርያም ይሄ የባንዲራው በቢጫ መስመሮች የተሠራ ሰማያዊ ኮከብ።

ኢህአዴግ በወቅቱ ይሄ የቀረበለት ኮከብ የሠይጣን ባፎሜት የማምለኪያ ማኅተም መሆኑን ያውቅ ነበር ወይ? ብለን በንፁህ ልብ ከጠየቅን በወቅቱ የኢህአዴግ ሰዎች ይህንን የሚያውቁበት ዕድል ከ0.1% ያነሰ ይመስለኛል። ባጭሩና በቀላሉ የሠይጣን ባፎሜትን አርማ ባንዲራው ላይ አርማቸው አድርገው የማውጣት ሃሳቡም ፍላጎቱም የነበራቸው አይመስልም።

ሠዓሊው መስፍን ሀብተማርያምስ? በግሌ የደረስኩባቸው መረጃዎችና ማስረጃዎች አውቆ ሆን ብሎ የሠይጣንን ኮከብ ለኢህአዴግ ሰዎች አርማችሁ ነው እንኩ ብሎ አውቆ ሰጥቷል ወይ? የሚለውን በሙሉ ልብ የሚያረጋግጡልኝ አይደሉም። ግን አርቲስቱ መስፍን፣ ያ ኮከብ የሠይጣኒዝም ኮከብ እንደሆነ ሊያውቅ የሚችልበት ዕድል በጣም ሰፊ ነው።

የባኔዲራው ኮከብ መሠረታዊ ዲዛይንም ቁርጥ የባፎሜትን መሠረታዊ ቅርፆች ይዞ መገኘቱ፣ የመስፍን ጓደኞች እንደሚከራከሩት፣ ተራ አጋጣሚ ብቻ ነው ብሎ መገመት፣ እጅግ የበዛ የዋህነትን የሚጠይቅ ድምዳሜ ነው።

መስፍን የባኔዲራውን አርማ ከሠራ በኋላ በወጣት ዕድሜው ባጭር ታምሞ መሞቱ ይታወቃል። በህይወት እያለ ግን ባንዲራው መነካት እንደሌለበት በማሳሰብ፣ "ባንዲራው እንዳይነካ" የሚል ርዕስ ሰጥቶ በሶስቱ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ቀለማት የሠራውን የታላቁን ሠዓሊና ገጣሚ የገብረክርስቶስ ደስታን ሥዕል አሳምሮ ያውቀው ነበር። ያውቀው ነበር ብቻ ሳይሆን፣ ራሱን ከዚህ ባንዲራው እንዳይነካ ከሚለው ሥዕል ጋር አብሮ አድርጎ የራሱን ምሥል ስሏል!!

ይሄ ማለት ምን ማለት ነው? መስፍን ባንዲራው እንዳይነካ ያለውን የገብረክርስቶስን ግዝት ጥሰው ባንዲራውን ሊነኩ በፈለጉት ኢህአዴጎች ላይ ሠይጣናዊ ምልክትን እንኡኩ የሚገባችሁ ምልክት ይሄ ነው ባንዲራውን ደፍራችኋልና - የሚል ጥበባዊ ምሥጢር ያለውን ኪናዊ ቅኔ በሥዕል ዲዛይኑ ቋጥሮ ሰጥቷዋል ወይ? ወይስ ባንዲራው መርከስ አለበት፣ ዘመኑም የሠይጣን ዘመን ነው ብሎ አምኗል?

መስፍን ለኢህአዴጎቹና ለኢትዮጵያ፣ ለተቋቋመው የነገዶች ሥርዓት የነበረውስ አመለካከት ምን ይመስል ነበር? I think እነዚህ ነገሮች በጥልቅ መጠናት ያለባቸው ይመስለኛል። ግን ይሄ ባንዲራው ላይ የተለጠፈው ኮከብ የሠይጣን ባፎሜት ኮከብን ራሱኑ መሆኑ ምንም ጥርጥር ያለው አይደለም። የሠይጣንን ምልክት ነው ለባንዲራው የሰጣቸው ቢባል ይህን ለመሟገት የሚቻል አይመስለኝም። ኮከቡ የራሱ የአንቶን ላቬይ ሠይጣኒዝም ኮከብ ቅጂ ስለሆነ!

ለማንኛውም ይሄ ኮከብ የተለያየ የቀልድ ስላቅ ሲያርፍበትና የቁምነገር ስሞታም ሲቀርብበት ኖሯል። የወያኔ አምባሻ ነውም እየተባለ ተስቆበታል። አርቲስቱም ዛሬ ሃሳቡን ለማስረዳት በመካከላችን በህይወት የለም።

ከወያኔዎቹ መሐል ጥቂቶች የማይባሉትን ልሂቃን በትግል ዘመናቸው ለሚያምኑበት የሶሻላዝም ኮከብ የቀረበ የኮከብ ምልክት መኖሩ ሳያስደስታቸው አልቀረም። በደርግም ዘመን የተሠራው የኢህዲሪ አርማ ኮከብ ነበረው። የኢህአፓ አርማ ኮከብ ነበረ። የዚያ ዘመን አብዮተኞች ሁሉ ኮከብን ከሰውልጅ በላይ ከፍ አድርገው አምልከዋል። ለኮከብ ተጋድለዋል። ምናልባትም ያንን ትውልድ ከኋላ ሆኖ የሚጋልበው ሠይጣን ባፎሜት ራሱ ይሆንም ይሆናል። ምን ይታወቃል?

አሁን የባንዲራው አርማ ይቀየር ወይ? የሚል ጥያቄ እኔደ አዲስ ሲነሳ ሰማሁ ሰምኑን ደሞ። መቀየር እንዳለበት ጥርጥር የለውም። በግሌ አመለካከት መቀየር ሳይሆን መጥፋት ነው ያለበት። ባንዲራው መነካት የለበትም። ልሙጡ ባንዲራ ብለው ስም ያወጡለት ልሙጥ ሰዎች፣ የማያልፍ ባንዲራ ላይ የሚያልፉ አርማዎችን በማንጋጋት የባለጊዜነት እርካታ የሚሰማቸው ተራ ሰዎች ናቸው። ባንዲራው በራሱ በቂ ነበር።

በበኩሌ የአርማ አስተያየት የለኝም፣ እንዲኖረኝም አልፈልግም። ግን በባንዲራው ሌላ አርማ ካስፈለገ በመንግሥት ተቋማት ሁሉ ውስጥ የሚውለበለብ የሥርዓቱ አርማ ከኮከብ በስተቀር ምንም ቢሆን ግድ አይሰጠኝም።

የቡና ዘለላዎችን አርማ ብናደርግ ምናልባት በዓለም ላይ በተውለበለበ ቁጥር ሀገራዊ ብራንድ ይፈጥራል ብዬ አስባለሁ። ኢትዮጵያ የቡና መገኛ መሆኗንም ለዓለም ሁሉ ያውጃል። ከያንዳንዱ የቡና ጣዕም ጋር አብረን በሰዎች እዝነ ህሊና ውስጥ ሰተት ብለን እንገባለን።

ከሠይጣኒዝም የኮከብ አርማ ውጭ ማንኛውም ሌላ ምልክት (ለምን ሙቀጫና ዱባ አይሆንም) አርማ ሆበኢትዮጵያ ሠማይ ሥር ቢውለበለብ ለሁላችንም የመንፈስ እፎይታ ይመስለኛል።

ኢህአዴጎቹም አንዴ አርማችን ብለው ከያዙት በኋላ ገግመው ይዘውት ቀሩ እንጂ፣ መጀመሪያ ላይ አውቀውና ሆን ብለው የሠይጣንን ኮከብ አርማቸው ለማድረግ አስበው ያደረጉት አይመስለኝም። ሠዓሊው መስፍንም በመካከላችን የለምና ምን አስቦ ይህን ኮከብ እንደተዋሰ ሊነግረን አይችልም።

አልባሳትንና አርማን በመቀያየር የሚመጣ የተለየ ፅድቅ እኔደሌለ ግን ልናሰምርበት የሚገባ ሃቅ ይመስለኛል። ሥዕሎችን በመቀያየርና በማሳመር የሚመጣ ተዓምር የለም። አርማው የሠይጣንን አዚም በአናታችን ላይ ጭኖብን ከሆነ ይገፈፍልንና እንየው የሚፈጠረውን። አዚማችን ግን በውጪ በሚዌለበለበው ባንዲራ አርማ ላይ ሳይሆን፣ በውስጣችን እንዳይሆን ትልቅ ሥጋት አለኝ።

ፈጣሪ ከዚህ የሠይጣን ኮከብ ሁላችንንም ይፍታን!

የመጨረሻው የትንሣዔ ዘመን መቃረብ ምልክት በዮሐንስ ራዕይ እንደተገለፀው፣ የከዋክብት መርገፍ ይመስለኛል። እነዚህ የሠይጣን ባፎሜት ከከቦች ከየተሠቀሉበት የሀገራችን ሠማይ ላይ የሚረግፉበት የኢትዮጵያችን ትንሣዔ ዘመንም ቀርቦ ይሆናል። ማን ያውቃል?

ስለ አርማው ያላችሁን አስተያየት እስቲ በጨዋነት አድርሱኝ።

መልካም የትንሣዔ ዘመን ይሁንልን!

ሸጋ ሳምንት!
በ Assaf Hailu
🙏🏿👌

አሳዛኝ  ዜና መሠረት፡ የ25 ዓመቷ ሴት አዱት ዲሞ ኡቻላ የተባለች ሴት፣ የስድስት ዓመት ፍቅረኛዋ ሌላ ሴት ሊያገባ ነው ባለች ምክንያት የወንድ ፍቅረኛዋን ብልት በመቁረጧ እንደታሰረች ተዘገ...
30/07/2026

አሳዛኝ ዜና መሠረት፡ የ25 ዓመቷ ሴት አዱት ዲሞ ኡቻላ የተባለች ሴት፣ የስድስት ዓመት ፍቅረኛዋ ሌላ ሴት ሊያገባ ነው ባለች ምክንያት የወንድ ፍቅረኛዋን ብልት በመቁረጧ እንደታሰረች ተዘገበ።

ዘገባዎች እንደሚያሳዩት፣ አዱት ዲሞ ከሌክ ስቴት ወደ ዋው ተጉዛ፣ ፍቅረኛዋ ደንግ ዌክ በሮዝ ሆቴል ያደረበትን ሌሊት አሳለፈች። ለእሱ የሚያንቀላፋ ንጥረ ነገር ከሰጠች በኋላ ቢላዋ ተጠቅማ ጥቃቱን እንደፈጸመች ተጠርጠሯል።

Mekuac Deng

 👇👇👇👇የወላይታ የመጨረሻ ንጉስ ካዎ ጦና ጋጋ ማናቸው? ካዎ ጦና ጋጋ ከአባታቸው ከቦሻሻ ጋጋ ጎቤ እና የዘር ሀረጋቸው ከአርሲ ኦሮሞ ማዳልቾ ከሚባል ጎሳ ከሚመዘዙ እናታቸው ከአቤንቶ ዎርቄ ...
29/07/2026

👇👇👇👇
የወላይታ የመጨረሻ ንጉስ ካዎ ጦና ጋጋ ማናቸው?

ካዎ ጦና ጋጋ ከአባታቸው ከቦሻሻ ጋጋ ጎቤ እና የዘር ሀረጋቸው ከአርሲ ኦሮሞ ማዳልቾ ከሚባል ጎሳ ከሚመዘዙ እናታቸው ከአቤንቶ ዎርቄ ጎባና በ1858 ዓ.ም በጊዜው ዳልቦ ጋሩዋ/ካዎ ጎቤ ጋሩዋ/ተብሎ በሚጠራው ቦታ ተወለዱ፡፡ ጦና የቦሻሻ ጋጋ የመጀመሪያ ልጅ ሲሆኑ ዴሌ፣ሀሉ እና አላምቦ የሚባሉ ሦስት ወንድሞች እና ቴማሜ እና ቡንአሬ የሚባሉ ሁለት እህቶች በአጠቃላይ አምስት ወንድምና እህት ነበሯቸው፡፡

ካዎ ጦና በልጅነታቸው እንደማንም የነገስታት ልጅ በአያታቸው በካዎ ጎቤ ቤተመንግስት የፈረስ ጉግስ፣ አደን፣ ባህላዊ የእርሻ አሠራር፣ የለቅሶ፣ የሰርግና ሌሎችን ባህላዊ ሥርዓቶችን በሞግዚታቸው አቶ ባዳቾ(በኋላ ግራዝማች) አማካይነት ሙሉ እውቀት በማግኘት በድሎትና በእንክብካቤ እንዳደጉ ይታወቃል፡፡ ካዎ ጦና ከልጅነታቸው ጀምሮ በጣም ንቁ እና ነገሮችን የመረዳት ችሎታቸው ከፍተኛ በመሆኑ በሽማግሌዎች ዘንድ ለወደፊት ጠንካራና ትልቅ ኃላፊነት ሊረከቡ የሚችሉ መሆናቸውን ገና ከጥዋት ጀምሮ ያስመሰክሩ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ጦና ከልጅነታቸው ጀምሮ ከእድሜ እኮዮቻቸው ጋር ትግል(Baaxiyaa) የመግጠም ጨዋታን የሚወዱና በዚህም የአካባቢውን ወጣቶች በትግል ከማሸነፍ የማይመለሱ በመሆኑ ጦና አሸናፊ ነው(Xooni Xooniyaaga) እየተባለ ይዘመርላቸው እንደነበር ይነገራል፡፡

ከዎ ጦና በነበሩበት ዘመን ዘመናዊም ሆነ የቤተክርስቲያን ትምህርት ወደ አካባቢው ያልገባ በመሆኑ ትምህርት ለመማር ዕድል ያላገኙ ቢሆንም በጊዜው ለነገስታት ልጆች የሚሰጠውን የሕይወት ክህሎት ትምህርት በጥብቅ ሥነ-ሥርዓት ተከታትለዋል፡፡ ይህም የዎላይታ ባህላዊ የአስተዳደር ሥርዓት፣ባህላዊ ህጎችንና ደንቦችን፣ የጦር ስልትን፣ አደንና የውሃ ዋናን የእርሻ አሠራርን፣ ባህላዊ የዳኝነት ሥርዓትን እንዲሁም የንግድ ሥርዓትን ከሽማግሌዎችና ከባለሙያዎች በጥንቃቄ እንደተማሩ ይነገራል፡፡

በ1885 መጨረሻ አካባቢ አያታቸው ካዎ ጎቤ በጠና በመታመማቸው አስተዳደራዊ ሥራውን በሚገባ መፈጸም ባለመቻላቸው የወላይታ ሁሉንም ጎሳዎች የሚወክሉ ሽማግሌዎች ተሰብስበው ወደ ቤተመንግስት/ካዎ ጋሩዋ/ በመምጣት ንጉሱ ቀጣዩን አዲስ ንጉስ እንዲያስታውቋቸዉ ይጠይቃሉ፡፡ በዚህን ጊዜ ካዎ ጎቤ ልጃቸውን ሀዳሮን እንዲያነግሱ ይነግሯቸዋል፡፡ ነገር ግን የዎላይታ ሽማግሌዎች በመሉ ድምጽ የታላቅ ልጅ እያለ ታናሽ አይነግስም በማለት ጦናን ከንጉስ ጎቤ ይውንታ ውጪ በሕዝብ ፍላጎት ብቻ በመስከረም/ግፋታ/ ወር 1866ዓ.ም የንግሥና ቀለበት በማጥለቅ አነገሷቸው፡፡

ነገር ግን ጦና ገና የ12ዓመት ልጅ ስለነበሩ 20 ዓመት እስኪሞላቸው በዎንቤቶ(መስፍን) ሶራቶ ሞግዝትነት ሲመሩ ቆይተው ከ7ዓመታት የሞግዝት አስተዳደር በኋላ በሙሉ ኃላፊነት አገር መምራት እንደጀመሩ የብሔሩ አፈታሪክና የተጻፉሁፍ መረጃዎች ይገልጻሉ፡፡

የቅድመ አያታቸው ማለትም የንጉስ ዳሞቴ አስተዳደር በብዙ መልኩ ለህዝቡ ምቹ ስላልነበረ ሰላማዊና ዲሞክራሲዊ በሆነ ተቃውሞ ህዝቡ ካዎ ዳሞቴን ከሥልጣን ካስወገደ በኋላ ልጃቸውን ማለትም የንጉስ ጦናን አያት ንጉስ ጎቤን አነገሰ፡፡ የአያታቸው የንጉስ ጎቤ ዘመን ወላይታ ላይ እጅግ የተረጋጋ የብልጽግና ዘመን ነበር፡፡ ይህ ጊዜ ቀደም ሲል በአጉራባች ህዝቦች ተወርሮ የነበረውን የወላይታን መሬት የማስመለስ ዘመቻ ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀበትና ዎላይታ አሁን ያለውን የድንበር ቅርጽ የያዘበት ዘመን ስለነበር የጎቤ ዘመን በዎላይታ ታሪክ ውስጥ ህዝቡ በተሟላ ሰላም የኖረባቸው አርባ ሶስት ዓመታት ነበሩ፡፡

የንጉስ ጦና የሥልጣን ዘመን እንደ አያታቸው ካዎ ጎቤ ሁሉ ለሕዝቡ የተትረፈረፈ እህልና ሀብት የነበረበት የጥጋብና የብልጽግና ዘመን ቢሆንም ወቅቱ አብሲኒያዎች በሥልጣን ሽኩቻና በድንበር መስፋፋት የተወጠሩበት ጊዜ በመሆኑ በተለይም የአፄ ዮሐንስን ሞት ተከትሎ የሸዋው ንጉስ ምኒልክ በ1881 ዓ.ም ራሳቸውን ንጉሰ ነገስት ዘኢትያጵያ በማለት ዘውድ ከጫኑ በኋላ፡፡

ቀደም ሲል በሸዋ የጀመሩትን የድንበር ማስፋፋት ዘመቻ አጠናክሮ በመቀጠል ተካታታይ ጦርነቶችን ዎላይታ ላይ የከፈቱበት ጊዜ በመሆኑ የዎላይታ ሉአላዊነትና የግዛት አንድነት ትልቅ ስጋት ላይ የወደቀበት ወቅት በመሆኑ የንግሥና ዘመናቸው በውጫዊ ግፊት ምክንያት በከፍተኛ ጫና ላይ የወደቀበት ወቅት ነበር፡፡

ይሁን እንጂ ካዎ ጦና መላውን የዎላይታ ህዝብ አንድ በማድረግ ለሰባት ዙሪ የመጣዉን የምኒልክን ሠራዊት ፍጹም በማይታመን ሁኔታ በጊዜው ኃያላን መንግሥታት እንኳን ያላሰቡትን “ባዮሎጂካል” የጦር መሳሪያ ማለትም ፈንጣጣን እና ንብን ጭምር በመጠቀም ዎላይታን እንዲወጋ ከዳግማዊ ምኒልክ የተላከውን ሠራዊት በተለያየ ጊዜ አፈር ከመሬት በማልበስ መልሷል፡፡

ነገር ግን በ1887ዓ.ም ዘመናዊ የጦር መሳሪያና ሁሉንም የምኒልክ የጦር መሪዎችንና ሚንስተሮቻቸውን እንዲሁም ምኒልክ እራቸው በአካል በተሳተፉበት የመጨረሻ ዙር ጦርነት የጦናን የጦር ስልት ከአንዳንድ አገርንና ህዝብን ከከዱ ሰዎች አማካይነት መበውስድ ከብዙ ደም መፋሰስ በኋላ ጦናን በጥይት በማቁሰልና በመማረክ ወደ አዲስ አባባ በመውስድ ፊት በር ተብሎ በሚጠራው ከታላቁ ቤተመንግሥት ፊት ለፊት በሚገኘው ቦታ በግዞት እንዲቀመጡ ተደረገ፡፡

አንዳንድ የጽሁፍ መረጃዎች ንጉስ ጦና በአዱዋ ጦርነት ወቅት ከግዞት በመውጣት ንጉሰ ነገሥቱ ሁሉንም ሹማምንቶች ይዘዉ ወደ ጦርነቱ ሲሄዱ ሀገሪቱ ውስጥ የአስተዳደር ክፍተት እንዳይፈጠር ኃላፊነት እንደሠጧቸው የሚገልጹ ቢኖሩም (አካሉ ወልደማሪየም ሩሕ መጽሔት ታህሳስ 1985 ገጽ 10-11 ይመልከቱ) ነገር ግን ጦና በአድዋ ጦርነት ሠራዊት የመምራት ሚና ተሰጥቷቸው በጦርነቱ እንደተሳተፉ በርካታ መረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል፡፡

ዳግማዊ ምኒልክ ከብዙ ማግባባት በኋላ ጦናን ክርስትና በማስነሳት በ1895ዓ.ም መልሰው የወላይታን አውራጃ እንዲገዙ ከጦና ጋር የጠበቀ ዝምድና በመሻት ከሸዋንግዥት(ሾንግቴ) ጋር (Political Merge) የፓለቲካ ጋብቻ እንዲፈጽሙ በማድረግ እንዲሁም ስድስት መቶ ጠብመንጃና ብዙ ጋሻ መሬት በጉልት መልክ በመስጠት ወደ ወላይታ ላኩዋቸው፡፡ የዎላይታ ህዝብ በሸዋን ግዥት ጋብቻ ዙሪያ ደስተኛ ስላልነበረ “Shonggitee Wolayitta Bayzzida Badame” በማለት ስለእሰቸው ቅሬታውን ይገልጽ ነበር፡፡

ጦናም ከምኒልክ በተሰጣቸው የጦር መሳሪያ ከምኒልክ ጋር ስዋጋ አልረዳችሁኝም በማለት አጎራባች ህዝቦችን በመውጋታቸው ከንጉሰ ነገስቱ እውቅና ውጪ ጦርነት ከፍታሃል በመባል ከሥልጣን እንዲወርዱ ተደርገው እንደገና ለግዞት ወደ አንኮበር እንደተላኩ ይነገራል፡፡ በዚህም ምክንያት ጦና በምኒልክ ሥር ዎላይታን ያስተዳደሩበት ጊዜ እጅግ አጭር ነበር፡፡

በመጨረሻም ንጉስ ጦና ከግዞት በመውጣት ወደ አዲስ አበባ በመመለስ በ1909ዓ.ም ተፈጥሯዊ ሞት በመሞት አሁን በአዲስ አበባ ከተማ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያ አጠገብ በሚገኘው ባለወልድ ቤተክርስትያን ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል፡፡ በአሁኑ ሰዓትም መቃብራቸው በዚያ ቤተክርስቲያን ይገኛል፡፡ ንጉስ ጦና በህይወት ዘመናቸው የዎላይታን ህዝብ አንድ አድርጎ በመምራት ለፈጸሙት ተግባር የህዝቡ አንድነት ተምሳሌት ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡ንጉስ ጦና በዘመናቸው በማህበረሰቡ ነባር ሥርዓት በማደግና በማለፍ የራስን አስተዳደር በመምራት፤ ብሔራዊ ኩራት በመሆን፣ ወጣት ሠራዊት በማደራጅትና በመምራት በተከታታይ የመጣውን የጠላት ጦር መክቶ በመመለስ ጀግንነታቸውን አስመስክረዋል፡፡

በዘመኑ የሰዎች የፈጠራ ሥራ እንዲያድግና የዕደ-ጥበብ ባለሙያዎች የምርታቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማደረግ ለዕደ-ጥበብ ሥራ ልዩ ትኩረት በመስጠት ሁሉንም ባለሙያዎችን አንድ ቦታ በማሰባሰብ የጎጆ እንዱስትሪ ለማስፋፋት ያደረጉት ጥረት ቀላል የሚባል አይደለም፡፡

/ህይወት ታሪክ/

Address

Sodo

Telephone

+251913352851

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Horn History posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share