በረከት አለማየሁ

በረከት አለማየሁ

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from በረከት አለማየሁ, Sodo.

Photos from በወላይታ ዞን የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት- Wolaita Zone Prosperity Party Branch office's post 11/12/2025
01/12/2025

በወላይታ ዞን 3ኛ ዙር የአመራር ስልጠና ለመስጠት በቂ ዝግጅት መጠናቀቁን የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር አማረ አቦታ አስታወቁ

‎​ወላይታ ሶዶ፣ህዳር 22/2018 በወላይታ ዞን 3ኛ ዙር የአመራር የአቅም ግንባታ ስልጠና ለመስጠት በቂ ዝግጅት መጠናቀቁን የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር አማረ አቦታ ገልፀዋል።

ስልጠናው ‎"በመደመር መንግስት እይታ፤ የዘርፎች እመርታ" በሚል መሪ ሀሳብ በብልጽግና ፓርቲ ተዘጋጅቶ የሚሰጥ መሆኑንም አስታውቀዋል።

ስልጠናው በመደመር መንግስት እይታ የግብርናና የገጠር የመዋቅራዊ ትራንስፎርሜሽን ጉዞ፣ የኢንዱስትሪ ዘርፍ፣ የከተማ ልማት እንዲሁም የቱሪዝም ዘርፍ እመርታ በሚል ርዕሶች በብልፅግና ፓርቲ ተዘጋጅቶ የሚሰጥ ነው ብለዋል።

የአመራሩን የመፈጸምና የማስፈጸም አቅምን ለመገንባት ስልጠናው እጅግ ወሳኝ መሆኑን በመገለጽ፥ በአመራሩ ዘንድ የቁጭትና የተነሳሽነት ስሜት የሚፈጥር እንደሆነም አስገንዝበዋል።

ስልጠናው በአመራሮች መካከል የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን በመፍጠር የሀገራችን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ የሚተጋ ቁርጠኛ አመራርን ለመፍጠር የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል።

ስልጠናው የአመራሩን ግንዛቤ ከፍ የሚያደርግ፣ ክህሎትና አቅም የሚገነባ እንደሆነም አንስተዋል።

ሰልጣኝ አመራሮች ከስልጠናው ባሻገር እርስ በእርስ ልምድ የሚለወጡበትና የሚቀስሙበት ነው ያሉት ኃላፊው፥ ሰልጣኞች ስልጠናውን ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ዲስፕሊን መከታተል እንደሚገባቸውም አሳስበዋል።

በስልጠናው ከዞን ማዕከል፣ ከክልል ተቋማት፣ ከወረዳና ከከተማ አስተዳደር የተወጣጡ ከ1100 በላይ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች እንደሚሳተፉም አስታውቀዋል።

ስልጠናው ዛሬ ከሰዓት የሚጀመር መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፥ ስልጠናው ለተከታታይ 9 ቀናት የሚሰጥ እንደሆነም አስታውቀዋል።

30/11/2025
Want your school to be the top-listed School/college in Sodo?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address

Sodo