08/02/2023
# ማስታወቂያ
በ 2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ እና በመንግስት ተቋማት ገብታችሁ መማር የምትፈልጉ ተማሪዎች የተቋም ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ የካቲት 02/2015 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ማሳሰቢያ:-
በ 2015 የትምህርት ዘመን በልዩ ሁኔታ በአዳማ እና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዪኒቨርሲቲዎች መማር የምትፈልጉ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና የማይሰጥ መሆኑን አውቃችሁ መርጣችሁ መመደብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ የምትሹ (ተመሳሳይ ጾታ ያላችሁ መንትያዎች፣ እመጫቶች(በቅርቡ የወለዳችሁ እናቶች) ፣ ነፍሰጡር ተማሪዎች፣ በመንግስት ሆስፒታሎች ህክምና ቦርድ የተረጋገጠ ልዩ ክትትል የሚሻ ህመም ታማሚዎች … ወዘተ) ተማሪዎች ማመልከቻችሁን እና ደጋፊ ሰነዶቻችሁን በቀጣዩ ሊንክ
https://student.ethernet.edu.et
በኩል ብቻ እንድትልኩ እየገለጽን ምንም አይነት ማመልከቻ በአካል የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን።
ትምህርት ሚኒስቴር!
26/01/2023
ማስታወቂያ
ለ2014 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና ተፈታኞች በሙሉ
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት የተለቀቀ በመሆኑ ተፈታኞች ከዛሬ ጥር18 2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 5፡30 ጀምሮ፡-
• በዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ወይም
• በ6284 አጭር የጽሑፍ መልዕክት መላኪያ ላይ የምዝግባ ቁጥራቸውን (Registration Number) ብቻ በመላክ ወይም
• በቴሌግራም ላይ https://t.me/eaesbot
ማየት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ማሳሰቢያ፡-
• ማንኛውም ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች በአካል መምጣት ሳያስፈልግ እስከ ጥር 26/2015 ዓ.ም ድረስ በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ላይ Compliant የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ማቅረብ ይችላሉ፡፡
• የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አድራሻ ላይ ብቻ ይጠቀሙ፡፡ ከተመሳሳይ እና የተዛባ መረጃ ለማሰራጫት ከሚሞክሩ አካላት ራስዎን ይጠብቁ፡፡
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
ጥር 18/2015 ዓ.ም
05/11/2022
እንኳን ደስ አላችሁ !!!
ባይራ ኮይሻ ወረዳ በ2014ዓም በአጠቃላይ ትምህርት ሥራ የላቀ አፈፃፀም በማስመዝገብ ዋንጫና የእውቅና ሰርተፍኬት አግኝቷል ።
27/12/2021
በጤና ተቋማት የሚነሱ አገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመፍታት የባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ እንድሆነ ተጠቆመ
በቅሎ ሰኞ፤ ታህሳስ 18/2014 የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ የወባ በሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ፣ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ንቅናቄና የ5 ወራት ተግባር አፈጻጸም እየገመገመ ነው፡፡
መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ እንደገለጹት በጤና ዘርፍ ለህብረተሰቡ ቀልጣፋና ጥራት ያለውን አገልግሎትን ለመስጠት የአመራሩና የባለሙያዎች ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡
የዓለም አቀፍ ወረረሽን የሆነው የኮቭድ 19 በሽታው በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ በጤናና ስነልቦና እያስከተለ ያለው ተጽኖ ቀላል የማይባል እንዳልሆነም ገልጸዋል፡፡
የጤና አገልግሎት ተደራሽነት፣ ጥራትንና ፍታሃዊነትን ለማረጋገጥ የሴቶች ልማት ቡድን አደረጃጀቶችን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አሳምነው አይዛ አስታዉቀዋል፡፡
የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ጥራቱን የጠበቀ፣ ለሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች ተደራሽና የመክፈል አቅም የሌላቸውን አግልገሎት በመስጠት የህዝቡን ጤናና ድህነት ወዳ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ይሰራል ብለዋል፡፡
ፍታሃዊ የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነትና ተደራሽነት ለማረጋገጥ 18ቱ የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጅ በግለሰብ፣ በቤተሰብ፣ በማህበረሰብና በተቋማት ደረጃ ተግባረዊ ለማድረግ በ100 ቀናት ዕቅድ የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት ጉድለት መኖሩንና ይህንን ለማካካስ አመራሩ በትኩረት ልመራ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
በ100 ቀናት ዕቅድ ዙሪያ የነበሩ ጉድለቶችን በመገመገምና ክፍተቶችን በመለየት የቀጣይ አቅጣጫ ይቀመጠል ተብለው ይጠበቃል፡፡
በመድረኩ የዞኑ አጠቃላይ አመራር፣ የወረዳና ከተማ አስተዳዳሪዎች፣ የመንስግት ዋና እና ረዳት ተጠሪዎችና የጤና ጽ/ቤት ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
07/12/2021
በቃ!
የባይራ ኮይሻ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት አጠቃላይ የወረዳው መምህራንና ሠራተኞች በኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለውን የውጭ ሀገር ጫናን በመቃወም የ በቃ! ንቅናቄን ተቀላቀሉ።
በቅሎ ሰኞ፤ ህዳር 28/2014 ዓ.ም በወላይታ ዞን የባይራ ኮይሻ ወረዳ መምህራንና ሠራተኞች በኢትዮጵያ ላይ ያለውን የምዕራባውያን ጣልቃ ገብነትን ተቃወሙ። በተጨማሪም ለጀግናው ሀገር መከላከያ ሠራዊት በገንዘብ፣ በስንቅ ዝግጅትና በሞራል ድጋፍ አድርጓል።
ኢትዮጵያ በቅኝ አገዛዝን ስርዓት ውስጥ ለመግባት ፍቃደኛ ያልሆነች ጀግናና ኩሩ ህዝብ ያላት ድንቅ ሀገር እንደነበረች ምዕራባውያን ያውቋታል። ኢትዮጵያ ማድረግና መወሰን ያለባትን በራሷ ታውቅበታለች እንጂ የሌሎችን ጣልቃ ገብነት አትሻም። ኢትዮጵያ በራሷ ትጀምራለች፣ በራሷ ትጨርሳለች፣ በሀገር ክብር ላይ የመጣውን ማንኛውንም አካል የሚትለቅ ሀገር አይደለችም፣ በሀገር ሉዓላዊነት ላይ ሌሎች እንዲወስኑ እድል አትሰጥም፣ ታርክ ያለው ሀገር ደሙን አፍስሶ #በአድዋ ላይ ክብሩን ያስከበረው ሀገር #ከአጉዋ መሰረዙን አይፈራም።
መምህራንና ሠራተኞች በኢትዮጵያ ላይ ያለውን የውጭ ጣልቃ ገብነት ልቆም ይገባል፣ ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷ የተጠበቀ ሀገር ናት ስሉ ገልጿል። በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ላይ ያለውን እውነታን የማይገልጽ ሀሰተኛ መረጃን የሚያሰራጩ ሚዲያዎችና ግለሰቦች እያደረጉ ያሉት አካሄድ ከሚዛኑ ያፈነገጠ እንደሆነ ገልጿል። ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ከአሸባሪው ቡድን ጋር ያበሩ የውጭና የውስ ሚዲያዎች፣ የሀገርን ጉዳይ ከሀገርቱ ዜጎች በላይ እኔ አውቃለው የሚሉት አንዳንድ የምዕራባውያን መንግስታት ጣልቃ ገብነት በቃ! ልባል ይገባል አሉ።
አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያን ባስተዳደረበት ዘመን ሁሉ ለራሱ ጥቅምና ምቾት ስሰራ የቆየ ጨቋኝ አስተዳደር ስያራምድ የኖረ ክፉ ቡድን እንደሆነ በመግለፅ የዘመናት የህዝብ ጭንቅ ተደምሮ ያመጣውን ለውጥ ለመቀበል አሻፈረኝ ብሎ በህዝብ ላይ ጅምላ ጭፍጨፋ ማድረጉ ይህ ቡድን ከጅምር ጀምሮ አረመኔ እንደሆነ የሚያሳይ ነው ብሏል።
መምህራንና ሠራተኞች የኢትዮጵያ ክብር እንዲመልስና ብልፅግና እንዲሰፍን ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ከ50 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል። ድጋፉ ከዚህ በፍት በተለያየ ጊዜ ስደረገ መቆየቱን በማስታወስ በአስፈላጊው ሰዓት ሁሉ እንደሚቀጥሉ አስረድቷል።
በኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለው የምዕራባውያን ጣልቃ ገብነት ይቁም!
በቃ!
አከባቢውን ጠብቅ!
ወደ ግንባር ዝመት!
መከላከያን ደግፍ!
ህዳር 28/2014 ዓ.ም
በ/ሰኞ