03/05/2025
ይህንን ልጅ ካገናችሁ ወረታ ከፋይ ነኝ ይላል።
Public
03/05/2025
ይህንን ልጅ ካገናችሁ ወረታ ከፋይ ነኝ ይላል።
27/04/2025
27/04/2025
20/06/2022
19/06/2022
እኔ ወይም የእኔ ቡድን ብቻ ብሎ ማሰብ ለኢትዮጵያ አይሆንም !!
ህብረብሄራዊነት ባለበት ጽንፈኝነት የበለጠ አደጋ ነው !!!
በኢትዮጵያ በመሰረታዊነት መቀየር (Transformed) መሆን ከሚገቡ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ለዘመናት የተገነባው የፖለቲካ ልምምዳችን ነው። ፖለቲካችን በጽንፍ ወይም በዋልታ-ረገጥ ዕይታዎች የተወጠረ ነው።
በፖለቲካ ልሂቃን መካከል ጫፍ ና ጫፍ ቆሞ ገመድ መጓተት ፣ እልህ መጋባትና ማኩረፍ ፣ ብጥብጥ መፍጠርና የህዝብን ሠላም ማደፍረስ ፣ያለመደማመጥ ፣ እኔ /የእኛ ቡድን ብቻ ልክ ነን ፣ ፍፁም እውነተኛ ነን ብሎ ማሰብ፣የተለየ ሀሳብ የያዘን አካል እንደ ጠላት ማየት ፣ ስለሆነም የሀሳብ ልዩነት በሀይልና አውዳሚ በሆነ መንገድ የመፍታት አባዜ ውስጥ ቆይተናል። ይህ እጅግ ኋላቀር የፖለቲካ ልምምድ ጽንፈኝነት በከፍተኛ ሁኔታ እያቆጠቆጠ እንዲመጣ መነሻ ሆኗል። በፅንፈኝነት ምክንያት ዛሬ ላይ የኢትዮጵያ ሰላም ፣አንድነትና ልማት ፈተና ውስጥ ነው።
ስለ ጽንፈኝነት (Extremism)
በርካታ መዝገበ ቃላት ሲተረጎሙ ኢ- ምክንያታዊና በብዙሃኑ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው ርይኦተዓለም፣ ባህርይ፣ እምነትና ድርጊት እንደሆነ ያስቀምጣሉ ፡፡ አንዳንድ ምንጮች እንደሚገልጹት የጽንፈኝነት ተመሳሳይ ቃላት (ሃሳቦች) ዋልታ-ረገጥነት ፣ ዘረኝነትን፣ ሌላን ጥላቻ ፣ ያለመቻቻል፣ ኢ- ፍትሐዊነት፣ የሞራል ዝቅጠትና ልክ የለሽ ግለኝነት ናቸው፡፡
ጽንፈኝነት ዴሞክራሲያዊ አሰራርንና መንግስትን፣ የሕግ የበላይነትን፣ የግለሰቦች ነጻነትን፣ ልዩነቶችን ማክበርና ማስተናገድን፣ ችግሮችን በሕግና በውይይት መፍታትን፣ በመሬት ላይ ያለውን ማህበራዊ ስርዓት አይቀበልም፡፡
ጽንፈኝነት በሕብረተሰቡ ውስጥ ያለመረጋጋትን፣ ያለመተማመንንና ያለመተባበርን ይፈጥራል፡፡ በመሆኑም ሰላምና የልማት እንቅስቃሴ ይስተጋጎላሉ፡፡
የተባበሩት መንግስታት (2015) plan of action to prevent violent extremism በሚለው ዕቅድ/ ሰነድ እንደገለጸው ጽንፈኝነት የአንድን ቡድን ፍላጎት ለማሟላት፣ ሌለውን ወገን ለመጨቆንና ለማፈን፣ በወቅቱ ያለውን ማህበራዊና ፓለቲካዊ ስርዓት ለማናጋት፣ በአብዛኛው በሰዎችና በጾታዎች እኩልነት የማያምን አካሄድና ክስተት እንደሆነ ያመለክታል፡፡
ሰዎች ጽንፈኛ ሆነው አይወለዱም፣ በአንድ ቀንም ጽንፈኛ አይሆኑም ዘራቸው/ጎሳቸው ወይም ሃይማኖታቸውም ጽንፈኛ አያደርጋቸውም። ዕድገት፣ ኑሮ፣ ጓደኛ፣ ትምህርት፣ ሚዲያ፣ ውሎ፣ ወዘተ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡፡
የሳልታር (2004) ጥናት እንደሚያሳየው ጽንፈኞች የሰዎችን የእኩልነት መብት አይቀበሉም፣ የተለያዩ ብሔሮች ፣ ዘሮችንና ሃይማኖቶችን ይሳደባሉ አክብሮት የላቸውም፣ ጥላቻም ያንጸባርቃሉ ፣ዛቻና ማስፈራራትን ይጠቀማሉ፡፡
ጽንፈኝነት ሰላምን ያናጋል፣ ሰዎች ደህንነት እንዳይሰማቸው ያደርጋል፣ ለአገር ልማትም እንቅፋት ነው፡፡
ጽንፈኝነት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ግን በብዛቱም ሆነ በዓይነቱ በአውደሚነቱና የዜጎችን ሰላም በማወክ ረገድ ከፍተኛና አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ከዕለት ተእለት እንቅስቃሴ መረዳት ይቻላል ፡፡ ጽንፈኞች የፓለቲካ ፕሮጀክታቸው መጠቀሚያ የሚያደርጉት ብሔር እና ሀይማኖትን ነው። ለዚህም ነው ዛሬ በሀገራችን በብሔር እና በሃይማኖት ስም ዘግናኝ ድርጊቶች እየተፈፀሙ ያሉት።
ለኢትዮጵያ ጽንፈኝነት በፍፁም ሊሆን አይችልም። ኢትዮጵያ በብዛሀነት ያገጠች ስትሆን ፤ጽንፍኝነት ደግሞ ከብዛሃነት ጋር እሳትና ጭድ ነው። ይህ ሁኔታ መቀየር አለበት።
የአገራችን የፖለቲካ ዕይታና ተግባር አካታች እና አሳታፊ ፣ በሀሳብ በላይነት የሚያምን ወደ መሆን መሸጋገር የግድ የሚልበት ደረጃ ላይ ነን። ፖለቲካችን ከመጠላለፍ ፣መጠፋፋትና ሴራ ወጥቶ ወደ አድስ አቅጣጫ የአስተሳሰብ ሽግግር ማድረግ አለበት። በውይይት እና ድርድር ፣ በፉክክር እና ትብብር መካከል ሚዛን መጠበቅ ያስፈልጋል። በመብትና ግዴታ በዴሞክራሲ ባህል ግንባታና የሃገር ሰላም ፀጥታ መካከል ሚዛን መጠበቅ አለብን። ህብረተሰቡ በአጠቃላይ፣ መንግስት፣ ት/ቤቶች ሚዲያ፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራንና ለሰላምና ለአገር አንድነትና ዕድገት የቆሙ ኃይሎች በሙሉ ለጉዳዮ ትኩረት ሰጥተው ጽንፈኝነትን በጋራ መከላከል ተገቢ ነው።
ጽንፈኝነት ሄዶ ሄዶ አገር ያፈርሳል፣ ሰላም ያጠፋል ፣አዉዳሚ ነው።
የዛሬው ትውልድ ስለ ኢትዮጵያችን አንድነት ፣ ህዝቡ ሰላም ፣ ዕድገትና ብልፅግና ሲባል ጽንፈኝነትን በተባበረ ኃይል የመከላከል አገራዊ ኃላፊነት ወድቆበታል።
ኢትዮጵያ የጋራ ቤታችን ናት !!!
10/03/2022
በመሎ ጋዳ ወረዳ ጋዳ ከተማ ቀበሌ የ2013 ዓ.ም የበልግ እርሻ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2014 ዓ.ም የበልግ እርሻ ዕቅድ ላይ ንቅናቄ መድረክ ተካሄደ ። መጋቢት 30/06/2014 ዓ.ም
23/02/2022
💪የማይፈትናችሁ ነገር አይለውጣችሁም!🔥🔥🔥
👉በህይወት ብዙ ፈተናዎች ፣ ብዙ ችግሮችና ብዙ ውጣ ውረዶች ተከስተው ሊሆን ይችላል። ግን ፈተናዎቹ ሁሉ ወደ ተሻለ ልህቀትና እድገት ይወስዶታል እንጂ ህይወቶን አያጨልመውም።ህይወቶን የሚያጨልመው አለቀልኝ ብለው እጅ ከሰጡ ብቻ ነው።
👉ታዲያ ምንም እንኳን በብዙ ፈተናዎች ብታልፉም በፍጹም እጅ አትስጡ! ምክንያቱም እጅ የሰጣችሁ ጊዜ ያበቃላችኋል።
👉ህይወት ስትፈትንህ አልሸነፍ ባይ ሁን። የቀረቡልህንም ፈተናዎች ተጋፈጣቸው እንጂ አትሽሻቸው። ፈተናዎችህን መሸሽሽ ችግሮችህንአይፈታልህም!