13/09/2024
በቦዲቲ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት መሪነት የ2017 ዓ.ም የጊፋታ በዓል በደማቁ ለማክበር የሚያስችል ንቅናቄ መድረክ ተካሄደ
ቦዲቲ ፤ መስከረም ፤ 3/2017 ዓ.ም በወላይታ ዞን በቦዲቲ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት መሪነት የ2017 ዓ.ም የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ የ"ጊፋታ" በዓልን በድምቀት ለማክበር የሚያስችል ንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል።
መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የቦዲቲ ከተማ ከንቲባ አቶ ጳውሎስ በቀለ እንደገለፁት ወላይታ ለአለም ህዝብ የሚያካፍላቸው መልካም የሆኑና የምንኮራባቸው በርካታ ባህሎች መኖራቸውን ለውይይቱ ተሳታፊ ወጣቶች አብራርተው "ጊፋታ" ከእነዚህ ውስጥ አንዱና ዋነኛው መሆኑን ተናግረዋል።
አቶ ጳውሎስ አክለውም መስቀል በዓል በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበር ሀይማኖታዊ በዓል እንደሆነና "ጊፋታ" የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ የሆነ ታሪካዊና ባህላዊ ልዩ በዓል ነው ሲሉ አስረድተዋል።
ስለዚህ ይህንን የማንነታችን መገለጫ የሆነውን በዓላችንን ለአለም ህዝብ ከማሳወቅ አኳያ ይህ ትውልድ አሻራቸውን በሚገባ ማሳረፍ አለበት ብለዋል።
አቶ ፍሰሃ ሳሙኤል በቦዲቲ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ዋና ተጠሪ በበኩላቸው ወጣቱ ትውልድ የራሱን ቱባ ባህል ጠንቅቆ ማወቅ እንዳለበት ተናግረው በዚሁ ልክ ሌሎችንም በሚገባ የማሳወቅ ኃላፊነት እንዲሁም ግዴታም እንዳለባቸው አስረድተዋል ።
ጊፋታ ከጥንት አባቶቻችን ጀምሮ በድምቀት ስከበር የመጣ የማንነታችን ልዩ መገለጫ እንደሆነ ያነሱት አቶ ፍሰሃ በዓሉ ምንም አይነት ግንኙነት ከሀይማኖት ጋር እንደሌለው አብራርቷል።
በአሁኑ ጊዜ ጊፋታ በአለም ቅርስነት የማስመዝገብ ስራ ወደ መጠናቀቁ ደረጃ እየደረሰ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ፍሰሃ ጥረቱ ዳር እንዲደርስ አሁንም ከፍተኛ ስራን ስለሚጠይቅ ወጣቱ የእራሱን አሻራ በተለያየ መንገድ ማሳረፍ ያስፈልጋል ብለዋል።
አቶ ታረቀኝ መንግስቱ በቦዲቲ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ እንደተናገሩት የወላይታ ህዝብ ለብዙ ዘመናት የራሱን የማንነት መገለጫ የሆነውን ቋንቋውን ፥ ባህሉንና ታሪኩን ጠብቆ የቆየ ጀግና ህዝብ እንደሆነ አስረድተው ባህሉን ለአለም ህዝብ ማስተላለፍ ደግሞ የሁላችንም ኃላፊነት ነው ብለዋል።
አቶ ታረቀኝ አክለውም ወጣቱ ትውልድ ታሪኩን ፡ ባህሉን እና ወጉን አውቀው በመኖር ሌሎች እንዲያውቁ የበኩላቸውን ለወጡ እንደምገባ አሳስበው "ጊፋታ "በዓል በሀይማኖት ተቋም ስም የሚከበር ሳይሆን የወላይታ ማንነት መገለጫ ከዘመን ዘመን መሸጋገሪያ ድልድይ የሆነ ታሪካዊ በዓላችን ነው ሲሉ አብራርተዋል።
አቶ አሸናፊ አፋቶ በቦዲቲ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት ኃላፊ በንግግራቸው የማንነታችን መገለጫ የሆነውን "ጊፋታ" በዓል አከባበር በአለም ታሪካዊ ቅርስነት እንዲመዘገብ ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ ናቸው ብለዋል።
ይህንን የወላይታ ብሔር ልዩ መገለጫ የሆነውን ጊፋታ በአለም ቅርስ መዝገብ ላይ በደማቅ ብዕር ተጽፎ እንድቀር የወጣቱ ሚና የጎላ መሆን እንደሚገባም ተናግሯል።
04/09/2024
የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓል አከባበር ዙሪያ ከወጣት አደረጃጀቶች ጋር ንቅናቄ መድረክ በመካሄድ ላይ ነው
ወላይታ ሶዶ፤ነሓሴ 29/2016 የ2017 ዓ.ም የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓልን በልዩ ድምቀት ለማክበር ከወጣት አደረጃጀቶች ጋር የንቅናቄ መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
"ጊፋታ" በጉጉት እና በከፍተኛ ዝግጅት በየዓመቱ የሚከበር የወላይታ የዘመን መለወጫ በዓል ነው።
ጊፋታ የዕርቅ፣ የሰላም እንዲሁም ለታላቅ የሚሰጥ በዓል ሲሆን በወላይታ ባህል የመጀመሪያው ወርም 'ጊፋታ' ተብሎ ይጠራል።
በጊፋታ በዓል ወጣቶች በሰኔ ወር ማብቅያ አካባቢ ለ" #ጉሊያ” (ደመራ) የሚሆን እንጨት ወደ ጫካ በመዉረድ ቆርጦ በህብረት እየዘፈኑ ጉሊያ ለማቃጠል ወደተወሰነለት ቦታ ይጎትታሉ፣ጊዜዉ ሲደርስ ጉሊያ ያቆማሉ፣” #ዞኪያ” ይጫወታሉ።
በጊፋታ ወቅት ለማገዶ አገልግሎት የሚዉል እንጨት ፈልጠዉ እና ሳር አጭደዉ ይከምራሉ።
በመጨረሻዉም ቀን ከአባቶቻቸዉ ጋር ሥጋ ወደሚታረድበት ደጃፍ ይሄዳሌሉ፣ቅርጫዉ ተከፋፍሎ እስከሚያልቅ የበሬዉን ፊኛ ነፍተዉ እንደ ኳስ ይጫወታሉ፣በመጨረሻም በዕጣ የደረሳቸዉን ሥጋ ከቀርከሃ (ከጭራሮ እንጨትና ሀረግ) በተሠራ አዲስ ቅርጮ (በዘንቢል) አደርገዉ ወደቤት ይወስዳሉ።
ጊፋታ በዓል በወላይታ ህዝብ ዘንድ በጉጉት የሚጠበቅና የማንነት መገለጫ ነው።
20/07/2024
Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Bedilu T Jara, Tekle Tadwos, Yakob Kalose, Damte Harkiso, Worku Anjulo, Âķě Mĕķĩ, Zade Love Elsa, Tamrat Shamebo, Eshe Ermi, Tadese Nageso, Muse Polis, Tamirat Asfachew Adaro
15/07/2024
በክረምት ወራት ወጣቶች በጎ ተግባር በመንገድ ደህንነትና ትራፍክ አገልግሎት መስክ ለሚሰማሩ ወጣቶች ተጨማሪ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
ቦዲቲ ፤ ሐምሌ ፤ 08/2016 ዓ.ም በወላይታ ዞን በቦዲቲ ከተማ አስተዳደር 2016 ዓ.ም በክረምት ወራት ወጣቶች በጎ ተግባር በመንገድ ደህንነትና ትራፍክ አገልግሎት መስክ ለሚሰማሩ ወጣቶች ተጨማሪ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በከተማው ትራፊክ ፖሊሶች አማካኝነት ተሰጥቷል።
ስልጠናው በተለያየ አጋጣሚ በሰውና በንብረት ላይ የሚደርሰውን የትራፊክ አደጋን ከመከላከል አንፃር ወጣቶች እውቀት አግኝተው ህብረተሰቡን እንዲያስተምሩና እንዲያገለግሉ በእጅጉ ይረዳል ተብሏል።
ለወጣቶቹ ተጨማሪ የግንዛቤ ስልጠና የሰጡት የሰጡት ረዳት እንስፔክቴር ሰብሌ ሰለሞን ፤ ሳጂን አለሙ አብሮ እና ኮ/ል ደሰለኝ ታደሴ ናቸው።
18/05/2024
የቦዲቲ ከተማ ወጣት ማህበር ስራ አስፈፃሚዎች በቀን 10/09/2016 ዓ.ም እስካሁን ያለውን የማህበር ስራ አፈፃፀም ገምግመዋል።
12/05/2024
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መርሐ ግብር ይፋ ሆነ
ቦዲቲ፣ ግንቦት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2016 ትምህርት ዘመን የ2ኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና መርሐ ግብር ይፋ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል፡፡
የፈተና መርሐ ግብሩ በወረቀትና በበይነ መረብ የሚሰጠውን የፈተና የሚወስዱ ከትግራይ ክልል ውጭ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ላሉ ተፈታኞች ነው ይፋ የተደረገው፡፡
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ተፈታኞች እና የሚመለከታቸው አካላት ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡
የፈተና መርሐ ግብሩ ከታች ባለው ሰንጠረዥ ቀርቧል ፡-