Wolaita Laamiya Qaatta

Wolaita Laamiya Qaatta

Share

Energize, Motivate and Change the Life of Voiceless Lives

24/03/2026

Big shout-out to my newest top fans! Eshau Shay

11/03/2026

Anne ubbaykka Shemppuwa maaro gitte😭😭😭😭😭😭

27/02/2026

╱◥██████◣
│∩│🌄▤│▤▤│
ስልካችሁ ኦሪጂናል ከሆነ እስኪ እሄን ቤት ኮፒ አድርጉ!

24/02/2026

በሳይንስ የተረጋገጡ የቡና የጤና ጥቅሞች!

1. ለልብ እንክብካቤ ይረዳል

· በመጠን የሚጠጣ ቡና የልብ ክትትልን በማሻሻል ለልብ ሕመም ተጋላጭነትን እንደሚቀንስ ጥናቶች ያመለክታሉ።

2. የስኳር በሽታ የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል

· በየቀኑ ቡና መጠጣት አይነት 2 የስኳር በሽታን (Type 2 Diabetes) የመጋለጥ እድልን ዝቅ ሊያደርግ እንደሚችል ጥናቶች ያሳያሉ።

3. አልዛይመር እና ፓርኪንሰን በሽታን ይከላከላል

· ቡና በአእምሮ ላይ ተጠባባቂ ሆኖ በመስራት እንደ አልዛይመር እና ፓርኪንሰን ያሉ የአእምሮ መበላሸት በሽታዎችን ለመከላከል ይረዳል።

4. ጉበትን ይጠብቃል

· ቡና ለጉበት ጤና ጠቃሚ ነው። በተለይም የጉበት ካንሰር፣ ሲሮሲስ (Cirrhosis) እና የስብ ክምችት (Fatty Liver Disease) የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል።

5. የስሜት ሁኔታን ከፍ ያደርጋል እና ድብርትን ይከላከላል

· ቡና ውስጥ ያለው ካፌይን የነርቭ ስርዓትን በማነቃቃት ስሜትን ከፍ ለማድረግ እና የመንፈስ ጭንቀት (ድብርት)ን ለመቀነስ ይረዳል።

6. ፀረ-ኦክሲደንት (አንቲኦክሲዳንት) ይዟል

· ቡና ከፍተኛ መጠን ያለው አንቲኦክሲዳንት ይይዛል። እነዚህ ንጥረ ነገሮች ሴሎችን ከመጎዳት በመከላከል እርጅናን ለማዘግየት እና ካንሰርን ለመከላከል ይረዳሉ።

7. የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ያሻሽላል

· ካፌይን አድሬናሊን (Adrenaline)ን ከፍ በማድረግ ሰውነትን ለከፍተኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያዘጋጃል። በዚህም የስፖርት አፈጻጸምን ሊጨምር ይችላል።

8. የረጅም ዕድሜ ኑሮ እንዲኖር አስተዋጽኦ ያደርጋል

· በመደበኛነት ቡና መጠጣት ለተለያዩ በሽታዎች የመጋለጥ እድልን ስለሚቀንስ፣ በአጠቃላይ የሟችነት መጠንን ዝቅ ለማድረግ እና ረጅም ዕድሜ ለመኖር እንደሚረዳ ጥናቶች ያሳያሉ።

#ማሳሰቢያ

ከላይ የተዘረዘሩት ጥቅሞች በአብዛኛው የሚገኙት ያለስኳር እና ያለ ከፍተኛ መጠን ወተት በሆነ ቡና ነው።

ከመጠን ያለፈ ቡና መጠጣት፦

* እንቅልፍ የማጣት ችግር

* የጨንጓራ ህመም ያመጣል

* የልብ ምት የመጨመር ችግር እና

* የሆድ ምቾት የማጣት ችግር ያስከትላል። ስለዚህ ቡናን በመጠን መጠጣት ተገቢ ነው። የጨንጓራ ህመም ያለባቸው ሰዎች ቡና እንድጠጡ አይመከርም፡፡

16/02/2026

👌🫂𝗕𝗥𝗘𝗔𝗞𝗜𝗡𝗚 𝗡𝗘𝗪𝗦...
ሩሲያ 100% ውጤታማ የተባለውን የካንሰር ክትባት ይፋ አደረገች

ሩሲያ "ኤንቴሮሚክስ" የተሰኘው አዲሱ የካንሰር ክትባቷ በክሊኒካዊ ሙከራዎች ላይ 100 በመቶ ስኬታማ መሆኑንና ለክሊኒካዊ አገልግሎት እንዲውል መፈቀዱን አስታውቃለች። የካንሰር በሽታ ውስብስብነትና ዓይነቱ የበዛ በመሆኑ፣ ማንኛውም "ሙሉ በሙሉ ስኬታማ ነው" የሚል የሕክምና ግኝት የዓለምን ትኩረት መሳቡ አይቀሬ ነው። ይህ ክትባት በሽታ የመከላከል ስርዓትን በማነቃቃት የካንሰር ሴሎችን እንዲያጠቃ ወይም የካንሰር ምልክቶችን ለይቶ እንዲመታ ተደርጎ የተሰራ መሆኑ ተገልጿል።

ይሁን እንጂ በኦንኮሎጂ (የካንሰር ሕክምና) ዘርፍ "100 በመቶ ስኬት" የሚለው አገላለጽ አብዛኛውን ጊዜ ለአንድ የተወሰነ የካንሰር ዓይነት፣ ደረጃ ወይም ለተወሰኑ የሙከራ ተሳታፊዎች እንጂ ለሁሉም የካንሰር ዓይነቶች ላይሆን እንደሚችል ይገመታል። ክትባቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነትን ለማግኘት ዝርዝር መረጃዎቹ በገለልተኛ አካላት መፈተሽ፣ በሳይንሳዊ መጽሔቶች መታተምና የረጅም ጊዜ የደህንነት ክትትል ውጤቶቹ መታወቅ ይኖርባቸዋል።

ይህ ግኝት በገለልተኛ ወገኖች ተረጋግጦ እውነትነቱ ከተረጋገጠ፣ በካንሰር ሕክምና ታሪክ ውስጥ ትልቅ ለውጥ የሚያመጣ ስኬት ይሆናል። ሆኖም የሙከራው ውጤት በዓለም አቀፍ የሳይንስ ማህበረሰብ በዝርዝር ተተንትኖ ይፋ እስኪሆን ድረስ፣ እንዲህ ያሉ ሰፊ የሕክምና ስኬት መግለጫዎችን በጥንቃቄና በተስፋ መጠባበቅ ተገቢው አካሄድ ነው።

መረጃው ;- የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ነው

20/12/2025

የመ/ሰራተኞች የረዥም ጊዜ የመልካም አስ/ር ጥያቄ የነበረው የ 9 ወር JEG ክፍያ በ2018 ዓ. ም በሚደረገው ሀገራዊ ምርጫ እንቂፋት እንዳይሆን ብልጽግና ፓርቲ እየመረመረ እንዳለ ስንቶቻችን እናቃለን?

09/12/2025

የመስከረም ወር ውዝፍ ደሞዝ በአስቸኳይ ይከፈልላቸው!!!

19/11/2025

ማናቸው!!! የአብዲ ራዋ የእስካሁኑ ታሪክ በአጭሩ
******************

የ2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዋንጫ በተነሳበት ሁሉ ወላይታ ዲቻን እና አብዲ ራዋን አለማንሳት ፈጽሞ የማይቻል ነው። ወላይታ ዲቻ እንዲታወስ ያደረጉት አብዲ ራዋ ታሪካቸው ከታች ተያይዟል።

አብዲ ዉልደቱ ዎላይታ ሶዶ ነው። 1964 ዓ.ም ነሃሴ 29 ተወለደ። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን ለመከታተል ወደ ታሪካዊው ኦተና አንደኛ ደረጃ ት/ት ቤት የተጓዘው ብላቴናው አብዲ የህይወቱ ጥሪ ከሆነው ስፖርት እና እግር ኳስ ጋር የተዋዋቀው ገና በለጋነት ዕድሜው ነበር፥ በኦቶና እና መዝጊድ አፈራማ ሜዳዎች ከዕድሜ እኩዮቹ ጋር የጨርቅ ኳስ በማንቀራቀብ ከእግር ኳስ ጋር በህይወት ዘመን ወደማይፋታው ትዉዉቅ እና ፍቅር የገባ ው አብዲ በአጭር ግዜ ዉስጥ ይህ የእግር ኳስ ተስዕጦው በለጋ ዕድሜው በ1977 እና 78 ዓ.ም ወደ ከፍተኛ 01 እና 02 ቀበሌዎች ወክሎ የመጫወት ዕድል አስገኘለት።

በዎላይታ ሶዶ ዉስጥ በዛን ግዜ በነበሩት 2 ከፍተኛዎች በወቅቱ በትምህርት ቤቶች እና በከፍተኛዎች የነበሩትን በርከታ የእግርኳስ ታለንት ከነበራቸው ወጣቶች ጋር ተፎካክሮ መመረጥ አስቸጋሪ በነበረበት ዘመን በ1979 የሲዳሞ ክፍለ አገርን በመወከል በያቤሎ አሬሮ በሚደረገው የስፖርታዊ ዉድድር ላይ ወላይታን በመወከል በጠረጴዛ ቴኒስ ለመወዳደር ከወላይታ አዉራጃ በመመረጥ የመጀመሪያውን የስፖርት ክፍለ አገር አቀፍ ዉድድር ላይ የመሳተፍ ዕድል አግኝቷል።

የ16 አመት ለግላጋ ወጣት እና የ10ኛ ክፍል ተማሪ የነበረው አብዲ የያቤሌ አሬሮ ዉድድሩን ለ17 ቀናት ካካሄደ በሁዋላ በህይወት አጋጣሚ በ ቦረና - ያቤሎ ሞሚንቶ ምግብ ቤት እንደ ስፖርተኛ ቁርስ እና ምሳውን በኩፖን እየተመገበ በህይወት መንገድ ላይ የህይወት ዘመን የትዳር አጋሩ ከልጆቹ እናት ሶፊያ ጋር እንደዛሬው ስልክ ፣ ፌስ ቡክ እና ኢንስታግራም በሌለበት የኤሮግራም ደብዳቤ ዘመን አድራሻ በመቀበል እንደ የዛኔዎቹ አራዳዎች ቀልጠፍ ያለው ወጣት ለመተዋወቅ ለመግባባት እና በሁዋላም በሰመረ በትዳር የተቋጨውን ግንኙነት ለመመስረት በቅቷል።

ይህ ጥንስስ ተሳክቶ ከጥቂት ግዜ በሁዋላ በታዳጊዎች የሩጫ ዉድድር ለመሳተፍ ወደ ወላይታ ሶዶ ከመጣቸሁ እና ስለሷ አዉርቶ ከማይጠግበው ጸባዬ ሰናይዋ ሶፊያ ጋር በ1979 በትዳር በመጣመር 5 ልጆችን ወልዶ ለወግ ለቁምነ ነገር የማብቃት የህይወት መስመር ዉስጥ ለመግባት ችሏል።

ወጣቱ አብዲ 1980 በግዜው ከመላው ኢትዮጵያ በትምህርት ዉጤታቸው ከፍተኛ የሆኑት ብቻ የመግባት ዕድል የሚያገኙበትን በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው የጀነራል ዊንጌት ትምህርት ቤት ከወላይታ ከተመረጡ ምርጥ 3 ተማሪዎች አንዱ በመሆን በዛን ግዜ እንደ ብርቅ የሚታየውን የጀነራል ዊንጌት ትምህርት ቤት መቀላቀል ችሏል።

ትምህርት ቤቱንም በመወከል የነፍስያውን ጥሪ የሆነውን ስፖርት መለየት ያልቻለው ወጣቱ አብዲ ለጀነራል ዊንጌት የእግር ኳስ፣ የመረብ ኳስ፣ የቮሊቦል ቡድኖች በመጫወት እና ብቃቱን በማስመስከር በወቅቱ የአዲስ አበባ ሻምፒዮና ከፍተኛ 25 በመወከል በእግር ኳስና በመረብ ኳስ ለመመረጥ የበቃ ሲሆን በወቅቱ ታዋቂ ለነበረው የሜታ ቢራ የመረብ ኳስ ክለብ የተመለመለ ቢሆንም ከትምህርቱ ጋር አብሮ የማይሄድ በመሆኑ ዕድሉን ሳይጠቀምበት ቀርቷል።

ሆኖም የወላይታ የስፖርት አባት በአቶ ተሾመ አምዴ እና በጤና ስፖርት ታዋቂ በነበረው ግርማ ቸሩ አሰልጣኝነት በአዲስአ አበባ

22/08/2025

CAF ተሳትፎ ታሪክ
#የወላይታ ዲቻ እውነተኛ ታርክ እና አመጣጥ !!
ከ28 ዓመታት በፊት ከደቡብ በአፍሪካ መድረክ በመሳተፍ ቀዳሚዎቹ የጦና ንቦች ለ3ኛ ጊዜ ሊሳተፉ ነው‼️

የዛን ጊዜ ወላይታ ቱሳ ተብለው የሚጠሩት የጦና ንቦቹ በ1989ዓም ከ28ዓመታት በፊት የመጀመሪያውን በማንሳት #ከደቡብ ኢትዮጵያን በአፍሪካ መድረክ በመውከል #የመጀመሪያው ክለብ ሆነው ነበር!

በ2001 ዓም ስያሜው ከወላይታ ቱሳ ወደ ወላይታ ድቻ ተቀይሮ እንደ አዲስ ከተቋቋመ በኋላ በ2009 ዓም ለ2ኛ ጊዜ በማንሳት አፍሪካ መድረክ የግብፁን ሀያል ክለብ በማሸነፍ በኢትዮጵያ ክለቦች ታሪክ አዲስ ሪከርድ አስመዝግቧል!

ወላይታ ድቻ በዘንድሮ ሲዳማ ቡናን በፎርፌ በመርታት የ2017ዓም 3ኛ ጊዜ በማንሳት ታርክ ሰርቷል!

👊😎
🎯 የደቡብ መጠሪያ ባለታሪክ ወላይታ ድቻ
🎯 ከደቡብ ለመጀመሪያ ጊዜ ያነሳ ወላይታ ድቻ!
🎯 ከደቡብ በCAF confederation የመጀመሪያ ተሳታፊ ወላይታ ድቻ
🎯 ከኢትዮጵያ ክለቦች በCAF confederation እስከ 2ኛ ዙር ወደ 16 ክለቦች የገባ #የመጀመሪያው እና #ብቸኛ ክለብ ወላይታ ድቻ ነው!

❤❤❤❤❤ክለቡ ወላይታ ድቻ ነው‼️

20/08/2025


የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ካረፉ እነኾ 13 ዓመታት ተቆጠሩ። ነፍሳቸውን በአፀደ ገነት ያኑር!!🙏🏾

እርስዎ ግን አቶ መለስን በምን ያስታውሷቸዋል? አስተያየትዎን በአጭሩ ቢገልፁልን?

Want your school to be the top-listed School/college in Sodo?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address

Main Road
Sodo