የሲቀላ ቀበሌ ታክስ ማዕከል

የሲቀላ ቀበሌ ታክስ ማዕከል

Share

29/03/2023

👉የቀን ገቢ ግምት መርህ👈
***
👉 “ገቢ” ማለት በክልሉ የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 165/2009 አንቀጽ 2/14 መሠረት መደበኛ ያልሆነ ገቢን ጨምሮ ከማንኛውም ምንጭ በጥሬ ገንዘብ ወይም በዓይነት የተገኘ ወይም በማንኛውም መንገድ ለግብር ከፋዩ የተከፈለው፣በስሙ የተያዘለት ወይም የተቀበለው ማንኛውም የኢኮኖሚ ጥቅም ነው፡፡

👉 “የቀን ገቢ” ማለት አንድ ግብር ከፋይ በቀን ዕቃ ሸጦ ወይም አገልግሎት ሰጥቶ የሚያገኘው አማካይ ዕለታዊ ገቢ ነው፡፡ ይህ በቀን የሚገኘዉ የሽያጭ ገቢ የተሸጠውን ዕቃ የተገዛበት (የተመረተበት)፣ የሥራ ማስኬጃ ወጪዎችን እና ለሥራው ዋስትና ለማሰጠት እንዲሁም ከንግድ ሥራው የሚያገኘውን ትርፍ ያካትታል፡፡

👉 የቀን ገቢ ግምት በሚከናወንበት ጊዜ የሚወሰደው የግብር ከፋዩ አማካይ ዕለታዊ ገቢ እንጂ የተጣራ ትርፍ እንዳልሆነ በገማች ኮሚቴም ሆነ በአጣሪ ቡድኑ ግንዛቤ መወሰድ ይኖርበታል፡፡

👉 በሣምንት በተወሰኑ የገበያ ቀናት ብቻ እየሰሩ በሌሎች ቀናት ድርጅታቸውን ዘግተው የሚቆዩ ግብር ከፋዮች በሚያጋጥሙበት ጊዜ በሰሩበት ቀናት ያገኙትን የሽያጭ ገቢ በመደመርና ለሰባት ቀናት በማካፈል አማካይ የዕለት ሽያጭ ገቢያቸው ይወሰዳል፡፡

👉 ግብር ከፋዩ በታክስ ከፋይነት ያልተመዘገበ ወይም ተመዝግቦ የጸና የንግድ ሥራ ፈቃድ ሳይኖረው በዕቃ ሽያጭ ወይም በአገልግሎት መስጠት ሥራ ላይ የተሰማራ እስከሆነ ድረስ የቀን ገቢ ግምት ሥራው መከናወን ይኖርበታል፡፡

👉 ግብር ከፋዩ ከአንድ በላይ በሆነ የንግድ ወይም የአገልግሎት መስጠት ሥራ ላይ የተሰማራ ከሆነ ባከናወነው የዕቃና የአገልግሎት ሽያጭ ዓይነት የቀን አማካይ ሽያጭ ገቢ ተለይቶ መገመት ያለበት ስለሆነ ግብር ከፋዩ በየሥራ ዘርፉ በአማካይ የሚያገኘው የዕለት ሽያጭ ገቢ ይዘትና ስፋት ለመገመት አመላካች የሆኑ ታሳቢዎችን ሁሉ በጥልቀት በማጤን ተመጣጣኝ የሆነ ግምት ሊገመት ይገባል፡፡

22/03/2023

የጋሞ ልማት ማህበር ''ደሬ ጋሞ ልማትና ቢዝነስ ኮርፖሬሽን" በሚል ስያሜ ዋና ጽ/ቤቱን በአርባምንጭ ከተማ ያደረገ ኮርፖሬሽን ፈቃድ አገኘ።

ኮርፖሬሽኑ በስሩ በርካታ የንግድ ዘርፎችን በመያዝ ቀጣይነት ያለው ገቢ የሚያመነጭ ተቋም መሆኑም ተገልጿል ።

አርባምንጭ ፡ መጋቢት 12/2015 ዓ.ም የተጀመሩ የልማት ስራዎች ለማስቀጠል በአካባቢው የሚገኙትን ሀብት ለልማት የማሰባሰብ እና ገቢ የሚያመነጭ" ደሬ ጋሞ ልማትና ቢዝነስ ኮርፖሬሽን ተመስርቷል ።

ኮርፖሬሽኑ በውስጡ ከያዛቸው ስምንት የንግድ ዘርፎች መካከል "የአርባምንጭ ግብርና ልማት ኃላፊነቱ የተወሰነ ማህበር" ፣ " ጉጌ እንስሳት እርባታ ኃ/የተወሰነ ማህበር" እና " ነጭ ሣር የሆቴል አገልግሎት የተወሰነ ማህበር " የPLC ፈቃድ አግኝተዋል።

የአክስዮን ሽያጭ የጀመረው የሠላም ማይክሮ ፋይናንስ አክስዮን ማህበርን ጨምሮ ፣ የማዕድን ዘርፍ እና የደረጃ አራት የኮንስትራክሽን እና ሌሎች ዘረፎችን ወደ ሥራ ለማስገባት የጥናትና ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቋል።

"ደሬ ጋሞ ልማትና ቢዝነስ ኮርፖሬሽን" ከቀድሞው አደረጃጀት በተሻለ ለበርካታ ሰዎች የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ ፣ ከአርሶአደር እስከ ምሁር ተጠቃሚ ያደርጋል በንግድ ሕግ መሠረት ትልልቅ ሥራዎችን ይሰራል።

ኮርፖሬሽኑ በመመሪያና ደንብ የሚተዳደር እና በሥራ አመራር ቦርድ የሚመራ መሆኑ በየዓመቱ ከሚያገኘው ትርፍ የመንግስትን ግብር በመክፈል ለልማት ማህበሩ የሀብት ማግኛ ምንጭ መሆኑን ተገልጿል።

የጋሞ ልማት ማህበር ላለፉት ዓመታት ልማቱን ለማስቀጠል በገቢ ማስገኛ ስራዎች ቢሰማራም ልማቱ የሚጠይቀውን የሀብት መጠን ማሟላት ይቻል ዘንድ ተጨማሪ 8 የቢዝነስ ተቋማትን በማደራጀት ለልማት ስራው እንዲደጉም በማቀድ በማህበሩ ቦርድ ተወስኖ አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶች ሲከናወኑ ቆይቷል።

በቀጣይም የልማት ማህበሩ የተቋቋመበትን ዓላማና ተግባራት በብቃት የሚወጣው ሲሆን በአንጻሩም ኮርፖሬሽኑ ትርፋማነትን መሠረት አድርጎ ማህበረሰቡን ሆነ ልማት ማህበሩን በበርካታ የሚደግፍ ተቋም መሆኑን ከጋሞ ልማት ማህበር የተገኙ መረጃዎች ያመላክታሉ።

22/01/2023

👉🏻የታክስ/ግብር አስገራሚ እውነታዎች 👈🏻(2)
***
🫳 በአሜሪካ አንድ የታክስ ማጭበርበርን ያጋለጠ/ሪፖርት ያደረገ/ ሰው በመጠቆሙ ከሚሰበሰበው 30 /ሠላሣ/ በመቶ የሚሆነውን ድርሻ ያገኛል ወይም ይሰጠዋል፤

🫳 በአትላስ ሸርጅድ (Atlas shrugged) ላይ የሚገኙ አጠቃላይ የቃላት ብዛት 645ሺህ፣ መጸሐፍ ቅዱስ ደግሞ ወደ 700ሺህ ቃላት ሲኖራቸው የአሜሪካው የፌደራል ታክስ ኮድ 3 ማሊዮን 700ሺህ ቃላትን ይዟል፤

🫳የአሜሪካ ባለኃብቶች ከመካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ዜጎች ይልቅ ከፍተኛውን ታክስ/ግብር ይከፍላሉ፡፡ የባለኃብቶቹ ብዛት ከአጠቃላይ ሕዝብ አንድ በመቶ ብቻ ቢሆንም አጠቃላይ ማህበረሰቡ ከሚያገኘው ገቢ 19 በመቶ የሚያገኙ ናቸው፡፡ ከሚሰበሰበው አጠቃላይ የገቢ ግብር አኳያ ግን 37 በመቶውን የሚሸፍኑት እነርሱ ናቸው፤

🫳ኤክሳይዝ ታክስ/ግብር በአሜሪካ “የኃጢያት ግብር (Sin tax)” የሚል ተቀፅላ መጠሪያ ተሰጥቶታል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት በአልኮል/ በሲጋራ እና በቁማር ላይ የሚጣል ታክስ/ግብር በመሆኑ ነው፤

🫳እንግሊዝ ከመኖሪያ ቤት ጋር ተያይዞ የሚከፈልን ታክስ/ግብር በ1691 ስታስከፍል የነበረው ቤቶቹ ባላቸው የመስኮት ቁጥር እና መጠን ነበር፡፡ ይህን ተከትሎ ነዋሪዎቿ የሚከፍለውን ግብር መጠን ለመቀነስ ሲሉ አዲስ በሚገነቧቸው ቤቶች ላይ የሚያኖሯቸውን መስኮቶች ብዛት በቁጥር አነስተኛ ያደርጉ ነበር፡፡ በፊት ከገነቧቸውም ቤቶች የመስኮት ቁጥሪቸውን በማሸግና በመድፈን ይቀንሱ ነበር፡፡ በዚህ የተነሳ ግን በንፁህ አየር እጥረት ለተለያዩ የጤና ችግሮች ይጋለጡ ነበር፡፡ ይህን የተረዳው መንግሥት ታዲያ በ1851 ሕጉ እንዲሻሻል አድርጓል፡፡

🫳 በ1705 የሩሲያው ገዥ የነበረው ታላቁ ፒተር በፂም ላይ ታክስ ጥሎ ነበር፡፡ የገዢው ይሄን ያደረገው በምዕራብ አውሮፖ ታዋቂ የነበረው ፂምን ተላጭቶ እና አምሮ የመታየትን ባሕል ለማስረፅ ሲል ነበር፤

Photos from የሲቀላ ቀበሌ ታክስ ማዕከል's post 18/01/2023

ለከተማ እድገት ሀብት፣ ቴክኖሎጂ፣ የማህበረሰብ ጉልበት፣ ጊዜንና የአመራር ቁርጠኝነት የጎላ ድርሻ እንዳለው ተጠቆመ

ጥር 10/2015 ዓ.ም_ ለከተማ እድገት ሀብት፣ ቴክኖሎጂ፣ የማህበረሰብ ጉልበት፣ ጊዜንና የአመራር ቁርጠኝነትን የሚጠይቅ በመሆኑ በዚህ ረገድ ትኩረት ሊደረግ እንደሚገባ የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ም/ቤት ቋሚ ኮሚቴ የአዳማ ከተማን የእድገት ግስጋሴ በመጎብኘት የልምድ ልውውጥ አድርጓል።

የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኃይሉ ጀልዱ በልምድ ልውውጡ ላይ እንደገለጹት፥ ያሉ መልካም አጋጣሚዎችን በመለየት ለከተሞች እድገት ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠርና ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል።

በዚህ ረገድም በአዳማ ከተማ ማህበረሰቡን፣ ባለሀብቱን፣ አመራሩን በማሳተፍና በማቀናጀት ተጨባጭ ለውጥ መምጣቱን ገልጸዋል።

በተለይም የገቢ አቅምን ከማሳደግና የመሬት ልማትን ከማስተዳደር አኳያ ሰፊ ስራ መሠራቱን ጠቁመው፥ አርባምንጮችም ከመልካም ጅማሯችን ጥሩ ልምድ ይቀስማሉ ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ጠቁመዋል።

የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ማርቆስ ማቴዎስ በበኩላቸው የአዳማ ከተማ በዲጅታል ቴክኖሎጂ በመታገዝ ሰፊ ስራ መስራቱ የሚደነቅ ነው።

በተለይም ከተማን ለማሳደግ ሀብት፣ ቴክኖሎጂ፣ ጊዜንና ቁርጠኝነትን የሚጠይቅ በመሆኑ አቅም ያለው ባለሀብት፣ ዕውቀት ያለው ወጣት፣ ጉልበት ያለው ማህበረሰብና ቁርጠኛ የሆነ አመራርን መፍጠር ከተቻለ በአዳማ ከተማ የታየውን ተሞክሮ በአርባምንጭ ከተማ መድገም አያቅትም ብለዋል።

እንደዚሁም በህብረተሰብ ተሳትፎ የሚሰሩ ስራዎችን በማስፋት የተሻለ ዕድገትና ልማት ማምጣት እንደሚቻል ከአዳማ ከተማ ልምድ መቀመራቸውን ተናግረዋል።

የአከባቢን ሰላም በማስጠበቅና የህብረተሰብ ተሳትፎን በማጠናከር በተሰራው ስራ በአዳማ ከተማ አይነተኛ ለውጥ ተመልክተናል ያሉት ደግሞ የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ስንታየሁ አበረ ናቸው፡፡

በከተማዋ ያየነውን ልምድና ተሞክሮ ወደ ከተማችን በማውረድ ለተሻለ ለውጥ ልንተጋ ይገባል ብለዋል።

የከተማዋ ነዋሪና ባለሀብቱ ለአርባምንጭ ከተማ እድገት እና ለውጥ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል።

09/01/2023

ከሽያጭ ታክስ/ Turn over tax/ ክፍያ ነፃ ግብይቶች

• ቢያንስ ሁለት ዓመት ያገለገለ የመኖርያ ቤት ሽያጭ እና የመኖርያ ቤት ኪራይ
• የፋይናንስ አገልግሎቶች
• ለሳንቲሞችና መዳልያዎች ጥናት አገልግሎት ከሚውሉት በስተቀር የአገር ውስጥና የውጭ አገር ገንዘቦች እና የዋስትና ሰነዶች ማሰራጨት
• በሃይማኖት ድርጅቶች የሚሰጡ የእምነት ወይም ከአምልኮ ጋር የሚገናኙ አገልግሎቶች
• የሕክምና አገልግሎቶች እና አግባብ ባለው የመንግስት መሥርያ ቤት በሚወጣ መመርያ መሠረት ነፃ የተደረጉ አገልግሎቶች
• በትምህርት ተቁዋማት የሚሰጡ የማስተማር አገልግሎቶች እንዲሁም ለሕፃናት ጥበቃ በመዋእለ ሕፃናት የሚሰጡ አገልግሎቶች
• ለሰብአዊ ዕርዳታ የሚውሉ ዕቃዎችና አገልግሎቶች፣ የኤሌክትሪክ፤የኬሮሲን እና የውሃ አቅርቦት፣ የትራንስፖርት አገልግሎቶች
• ማንኛውም የስራ እንቅስቃሴ ለማከናወን ለሚስጥ ፈቃድ ለመንግስት የሚሰጥ ክፍያ
• ከ60% በላይ ሠራተኞቹ አካል ጉዳተኞች የሆኑበት አካል ጉዳተኞችን ቀጥሮ የሚያሰራ ድርጅት የሚቀርባቸው ዕቃዎችና አገልግሎቶች
• መፃሕፍት( ወደ ሀገር የሚገቡ፣ በሀገር ውስጥ የሚሸጡ እና መጻህፍትን ወቅታዊ ለማድረግ የሚወጡ እትሞች )
• የምግብ እህል (ጤፍ፤ ስንዴ፣ ገብስ፣ በቆሎ፣ ማሽላ፣ ዘንጋዳ ፣ዳጉሳ ፣ አጃ፣ እንዲሁም የነዚህ ዱቄት ከጥራጥሬ አተር ፣ባቄላ፣ምስር ፣አኩሪ አተር፣ሽንብራ ፣ግብጦ ፣ጓያ )
• የቅባት እህሎችም ሆኑ ፕሮሰስ የተደረጉ ምግቦች፣ ፉርሽካም ጭምር የታክስ መነሳት አይመለከታቸውም ፡፡

07/01/2023

የአርባ ምንጭ ከተማ ከንቲባ አቶ ማርቆስ ማቲዮስ ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት (ገና) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

ከንቲባው በመልዕክታቸው ለመላው የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎችና የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን አደረሳችሁ በማለት በዓሉን በጋራ፣ በአንድነትና በመተጋገዝ እንዲያሳልፉ ገልፀዋል።

መልካም በዓል!

Photos from የሲቀላ ቀበሌ ታክስ ማዕከል's post 04/01/2023

የአርባምንጭ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት ከዝህ በታች በዝርዝር የገለፃቸውን የሺያጭ መመዝገቢያ ማሺን ተጠቃሚ ነጋዴዎች የማሺን እድሳት እንድያደረጉ በተገለፀው ጊዜ በመቅርብ የማሽን እድሳት እንድታደረጉ ያሳስባል።
የአርባምንጭ ከተማ ገቢዎች

Photos from የሲቀላ ቀበሌ ታክስ ማዕከል's post 21/12/2022

የማዕከላችን በተግባራቸው ግንባር ቀደም የሆኑ በገቢ አስባስብ ስርዓቱን በማዘመን የሚታወቁት የሲቀላ ታክስ ማዕከል ባለሞያዎች ከሚኖሩበት አከባቢ የምርጫ ጣቢያ በመሄድ አድሱን የደቡብ ኢትዮጲያ ክልል'' መመስረት የምያስችለውን የመራጭነት ካርድ በመውሰድ ድምፅ በመስጠት ዴሞክራሲያዊ መብታችሁን በመጠቀም ግዴታቸውን ለመውጣት ካርድ ወስደዋል።

Photos from የሲቀላ ቀበሌ ታክስ ማዕከል's post 18/12/2022
10/12/2022

አርባምንጭ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት ባወጣው የቅጥር ማስታውቂያ መስርት የፈተና ቀን ስለማሳውቅ ይሆናል
________________
መ/ቤታችን በቀን 16_3_2015 ዓ.ም ባወጣው የቅጥር ማስታወቂያ ላይ የተመዘገባችሁ አመልካቾች ፈተና የሚሰጠው በቀን 4_4_2015 ዓ.ም መሆኑን እየገለጽን ወደ ፈተና ስመጣ ማንነታችሁን የምገልጽ መታወቂያ እንድትዙ እያሳሰብን ነገር ግን ስልክ ይዞ መግባት በፍጹም የተከለከለ መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን ። የአርባምንጭ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት

Photos from የሲቀላ ቀበሌ ታክስ ማዕከል's post 06/12/2022

በአርባምንጭ ከተማ በገቢ ጸ/ቤት አዘጋጅነት ከ6ቱ ቀቤሌ ለተወጣጡ ለሴቶች እና ወጣቶች አደረጃጀቶች በግብር እና በታክስ ግንዛቤ ማሳደጊያ ስልጠና ተሰጠ ፡፡
**********************************************

መስሪያ ቤቱ ግብር እና ታክስ ሥርዓቱ ላይ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የተለያዩ ተግባራትን አከናውኗል።

ከዚህ በመነሳት በተለያዩ አደረጃጀቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች የተሰጡ ሲሆን ከሴቶች አደረጃጀቶች እና ከወጣቶች አደረጃጀቶች ጋር የሚደረገው ውይይት ካላቸው ተደራሽነት አንፃር እና ከሚያከናውኑት የገብይይት ሲተያይ ከፍተኛ ስለሆነ ለይት ያደርገዋል ፡፡

በመሆኑም ይህ ስልጠና በከተማ አቀፍ ደረጃ ከ12 ቀጠናዎች ለተወጣጡ የአደረጃት ክፍሎች የተሰጠ ስሆን በቀጣይ በተዋረድ በየቀጠናወ ስልጠናው በወሰዱ ሰልጣኞች አማካይነት የሚሰጥ ይሆናል ፡፡ በስልጠናው ወቅት ከሰልጣኞች ጥያቄዎች ተነስቶ በሚመለከተታቸው የሥራ ኃላፊዎች ምላሽ ተሰጥቷል ፡፡

Photos from የሲቀላ ቀበሌ ታክስ ማዕከል's post 21/11/2022

ሕገወጥ ደረሰኞችን እንዴት በቀላሉ መለየት እንችላለን?
***
ግብይት በምናካሄድበት ጊዜ ደረሰኝ የመቀበል ልምዳችን መዳበር የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡ ነገር ግን የምንቀበለው ደረሰኝ ሕጋዊነቱን ማጣራት እና ማወቅ ደግሞ ያስፈልገናል፡፡
አንዳንድ ጊዜ በሕገወጥ ደረሰኞች ግብይት የሚካሄድ ሲሆን ይህም በገዢው ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እና ከዛም ባለፈ በሕግ እስከመጠየቅ የሚያደርስ ጉዳይ ነው፡፡
ለመሆኑ ሕገወጥ ደረሰኞች እንዴት ወዲያውኑ መለየት እንችላለን
ምንግዜም ግብይት ሲያደርጉ በመጀመሪያ
1. በእጅ ስልክዎ ጎግል ላይ ገብተው e-trade gov et በማለት ሰርች ያድርጉ፣
2. በመቀጠል የንግድ ድርጅት መረጃ ያጣሩ የሚለውን ይጫኑ
3. ቀጥሎ በመጣው ሰሌዳ ላይ የንግድ ፈቃድ ማጣሪያ ከሚለው ስር የፈቃድ ወይም የግብር ከፋይ ስም በሚለው ቦታ ላይ የግብር ከፋዩን TN No ያስገቡ
4. ቀጥሎ በመጣው ሰሌዳ ላይ የንግድ ድርጅትን ሙሉ መረጃ በሚገባ ማይት ይችላሉ፡፡

የሊንኩ ቅደም ተከተል በፎቶግራፍ ከዚህ በታች እንደቀረበው ነው፡፡

ራስዎንም ሆነ ሌሎችን ከሕገወጥ የደረሰኝ ዝውውር ይከላከሉ፡፡

Want your school to be the top-listed School/college in Adama?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address

Df
Adama