01/01/2026
Newton's and Einstein's laws of gravity
ቀደም ባለው ትምህርታችን ውስጥ የኒውተን ስበት ህግ ከአንስታይን የህዋ ጊዜ መታጠፍ ግኝት በኋላ ስበት የሚባል ነገር እንደሌለ ገልጨላችኋለሁ። ስለዚህ ስለ ህዋ ጊዜ መታጠፍ ማወቅ የለብንም ነው የምትሉን ሰዎች?
ኳስ ወደ ላይ ስንወረውር ተወርውሮ አይቀርም ወደ ምድር ይመለሳል። ጨረቃ ምድርን ባላት በሌላት ሃይል ምድርን እየዞረች ትከተላለች። ወደ ጥቁር ቀዳዳ Black hole የተጠጋ ማንኛውም ነገር ተጨማዶ እና ተጨፍልቆ ወደ ውስጧ ይሰምጣል። ታዲያ የስበት ሃይል ከሌለ ይህ ድርጊት የተፈጸመው ያለው እንዴት ነው? አንስታይን የኒውተንን ስበት ህግ አፍርሶ የራሱን የህዋ ጊዜ መታጠፍ ህግ ተክቷል። እስቲ ለአንስታይን እድሉን እንስጠውና ህጉን ያስረዳን እሱም ቢሞትም ስራው አልሞተምና።
እንግዲያው የአንስታይን መንፈስ ቢመጣ ኖሮ ምን ይለን ነበር?
ሰላም ይለን ነበር። ኒውተን አልተሳሳተም፤ ዝም ብሎ ሙሉውን ምስል አላየም ነበር። እኔ የገለጥኩት ምስጢር ይሄ ነው።
የተወጠረው ሸራ ምሳሌ
አንድ ትልቅ እና ጠንካራ ሸራ በአራቱም ማዕዘን ተይዞ እንደተወጠረ አድርጋችሁ አስቡ።
ይህ ሸራ የህዋ ጊዜ Spacetime ነው።
አሁን አንድ ከባድ የብረት ኳስ ለምሳሌ ምድርን በሸራው መሃል ላይ አስቀምጡ። ምን ይሆናል?
ኳሱ በክብደቱ ሸራውን ወደ ታች ያጎብጠዋል።
ኳሱ ለምን ተመለሰ?
አሁን አንድ ትንሽ ጠጠር ኳስ ወደ ላይ ብትወረውሩት። ኳሱ ከምድር የፈጠረችውን የሸራው ጎድጓዳ ለማምለጥ ይሞክራል። ጉልበቱ ሲያልቅበት ግን ተመልሶ ወደ ጎድጓዳው ይንከባለላል። እኛ ይህንን ስናይ የስበት ሃይል ሳበው እንላለን። እንደ እውነቱ ከሆነ ኳሱ እየተከተለ ያለው የታጠፈውን የሸራውን መንገድ ብቻ ነው።
ጨረቃ ለምን ትዞራለች?
ጨረቃም ልክ እንደዛው ናት። እሷ በምድር ዙሪያ በጣም በፍጥነት እየተጓዘች ያለች ጠጠር ናት። ነገር ግን ምድር በፈጠረችው ጥልቅ የህዋ ጊዜ ጎድጓዳ ውስጥ ታስራለች። ፍጥነቷ ከጎድጓዳው ለማምለጥ በቂ አይደለም። በጣም ቀርፋፋም ስላልሆነች ወደ ውስጥ አትወድቅም። ስለዚህ ለዘላለም በዚያ የታጠፈ መንገድ ላይ ለመዞር ትገደዳለች። እኛ ይህንን ስናይ የስበት ሃይል በምህዋር አቆይቷታል እንላለን።
Black hole ምንድን ነው?
ጥቁር ቀዳዳ ደግሞ የመጨረሻው ጫፍ ነው። እሱ በሸራው ላይ የተፈጠረ ጎድጓዳ ሳይሆን ሸራው ራሱ የተበሳበት መጨረሻ የሌለው ቀዳዳ ነው።
ማንኛውም ነገር ወደዚህ ቀዳዳ ጠርዝ ከተጠጋ መውጫ የለውም። መንገዱ ራሱ ወደ አንድ አቅጣጫ ብቻ ነው የሚያመለክተው። ወደ ውስጥ።
እኛ ይህንን ስናይ የስበት ሃይሉ በጣም ጠንካራ ከመሆኑ የተነሳ ብርሃን እንኳን አያመልጠውም እንላለን።
አንስታይን ያስተማረን ነገር ይሄ ነው። በአጽናፈ ሰማይ ውስጥ የመሳብ ሃይል የሚባል ነገር የለም።
ያለው ነገር ቢኖር በቁስ አካል አማካኝነት የሚፈጠር የህዋ ጊዜ መታጠፍ ነው።
ነገሮች በሙሉ የሚጓዙት በቀጥተኛ መስመር ነው። ነገር ግን የሚጓዙበት መንገድ ራሱ የታጠፈ ነው።
ስለዚህ በግልፅ አማርኛ የህዋ ጊዜ መታጠፍ ማለት የሚዛን ጉዳይ ነው ማለት ነው። አሁን ለምሳሌ ሶላር ሲስተማችን ውስጥ ያሉት ፕላኔቶች በሙሉ ከፀሃይ ውጭ ከምድር ጋር መጥቶ ብላተሙ ምን ይፈጠራል? ከፀሃይ የበለጠ ግዙፍ የሆነ ፕላኔት፣ ስለዚህ ምድር እንደ ፀሐይ ሴንተር ቦታ ላይ ትሆናለች ፀሐይ እንደ ላሎቹ ፕላኔት ምድር እንደ ፀሐይ እንድ ቦታ ላይ ሆና ፀሀይ ምድርን መዞር ትጀምራለች። ከላይ የገለፅኩላችሁን የሸራ ምሳሌ ድጋሚ በጨርቅ ምሳሌ እንመልከት፣ ዙሪያው የተ