20/06/2026
የአርሲዉ ደባ ሲጋለጥ
በአርሲ ዞን በአሰኮ ወረዳ በንጹኃን ዜጎች ላይ የደረሰው አሰቃቂ ጭፍጨፋ በፅንፈኞች የተቀነባበረ እና የተናበበ ሴራ መሆኑ ግልፅ ነው።
ይህ የጥፋት ኃይሎችን ፍላጎት የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ ራሳቸው በፈፀሙት ወንጀል ጉዳዩን ሌላ መልክ ለማስያዝ በሚሰሩት የሀሰት ፕሮፓጋንዳ “የብሔር ማጽዳት” እና “የኦሮሞ ማጥፋት” በሚሉ እርስ በርስ በሚጋጩ ትረካዎች በዲያስፖራና በአገር ውስጥ የሰሩትን የሴራ ጥልቀት ያሳያል። እነዚህ የጽንፈኞች ቡድኖች በሁለቱ ብሔር ስም በመነገድ እና የሕዝብን ደም በመጠጣት የሥልጣንና የገንዘብ ጥቅማቸውን ለማሳደድ ይሠራሉ። አንዱ ለሌላው ሽፋን በመስጠት የኢትዮጵያን ማኅበራዊ ትሥሥር ለመበተን የሚሰሩት እነዚህ የሞት ነጋዴዎች፣ በአንድ በኩል “የአማራ ደም” በሌላ በኩል ደግሞ “የኦሮሞ ደም” እያሉ ቢጮኹም፣ ማታ ማታ ግን በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ አብረው የጋራ ጠላቶቻችን መሆናቸውን ተረድተን በጋራ ልናወግዛቸው ይገባል።
እጃችሁን ከአሰኮ ሕዝብ ላይ አንሱ! / !