22/08/2026
የራያ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዘዳንት ፕሮፈሰር ታደሰ ደጀኔና አዲሱ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋ ዓፈራ ለዩቨርሲቲው ማህበረሰብ መልእክት አስተላለፉ ።
ራያ ዩኒቨርሲቲ፣ ነሐሴ 16/2018 ዓ.ምላለፉት አስር ዓመታት ከዩኒቨርሲቲው ምስረታ ጀምሮ በፕሬዚዳንትነት ሲያገለግሉ የቆዩት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ የጡረታ ጊዜያቸው በመድረሱ፣ የራያ ዩኒቨርሲቲ የፕሬዚዳንትነት ኃላፊነት ለአዲሱ ፕሬዚደንት ያስረከቡት ፕሮፈሰር ተደሰ ደጀኔና አሁን አዲስ ፕሬዝደንት ሁነው የተሾሙት ዶክተር ነጋ ዓፈራ ለራያ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ መልእክት አስተላልፏል ።
መልእክት ያሳተላለፉ የራያ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ፣ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በመተሳሰብ፣ በመተባበርና ለጋራ ራዕይ በአንድነት በመቆም የተጀመሩትን መልካም ሥራዎች በማጠናከር የዩኒቨርሲቲውን ቀጣይ የልማትና የተቋማዊ ሥራዎች በተቀናጀ መልኩ እንዲያፋጥኑ እና ለበለጠ ውጤት በቁርጠኝነት እንዲሰሩ መልዕክትና ምክር ሰጥተዋል።
በተለይም የዩኒቨርሲቲው የወደፊት ስኬት በአንድ አካል ብቻ ሳይሆን፣ በመላው የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ የጋራ ትብብር፣ ተጠያቂነትና ቁርጠኝነት እንደሚመሠረት አስገንዝበዋል።
አዲሱ የራያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር ነጋ ዓፈራ በበኩላቸው፣ በቀድሞ አመራርና በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የተጀመሩ መልካም ሥራዎችን በማስቀጠልና በማጠናከር፣ ዩኒቨርሲቲውን ወደ ተሻለ የልማት፣ የትምህርት፣ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ደረጃ ለማድረስ ከመላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ጋር በአንድነትና በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
ዶ/ር ነጋ አክለውም፣ በጋራ ራዕይ፣ በተቀናጀ አመራርና በተጠናከረ የሥራ ባህል በመመራት የራያ ዩኒቨርሲቲን ተልዕኮ በበለጠ ለማሳካትና ዩኒቨርሲቲውን የላቀ ውጤት ወደሚያስመዘግብበት ደረጃ ለማድረስ ያላቸውን ጽኑ እምነት ገልጸዋል።
ራያ ዩኒቨርሲቲ ለፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ ላበረከቱት የአስር ዓመት አገልግሎት ከፍተኛ ምስጋና በማቅረብ፣ ለዶ/ር ነጋ ዓፈራ በአዲሱ የአመራር ዘመናቸው ስኬትና የላቀ ውጤት ይመኛል።
==================================
ዕውቀት ለማህበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
*****//*****
የዩኒቨርሲቲያችን መረጃዎች ለማግኘት እነዚህን አማራጮች መጠቀም ይችላሉ፡፡
Facebook: https://www.facebook.com/RayaUniversityofficial
YouTube: https://www.youtube.com/
Linked ln: https://www.linkedin.com/in/raya-university-89075a347/