Samara-Logiyi Ma/Xii Qaadaay Wacaysir Kee Qafar Afih Gaddalosiyyi K/Buxa

  • Home
  • Ethiopia
  • Logya
  • Samara-Logiyi Ma/Xii Qaadaay Wacaysir Kee Qafar Afih Gaddalosiyyi K/Buxa

Samara-Logiyi Ma/Xii Qaadaay Wacaysir Kee Qafar Afih Gaddalosiyyi K/Buxa Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Samara-Logiyi Ma/Xii Qaadaay Wacaysir Kee Qafar Afih Gaddalosiyyi K/Buxa, School, Semera Logiy, Logya.

የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ለሰመራ-ሎግያ ከተማ  የዲጂታል አድራሻ ስርዓትን ሊተገብር ነው።   ሰመራ ፣ሚያዝያ 21 ፤2018 ( አፋ.ብ.መ.ድ )      ሚያዚያ 21 ቀን 2...
29/04/2026

የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ለሰመራ-ሎግያ ከተማ የዲጂታል አድራሻ ስርዓትን ሊተገብር ነው።

ሰመራ ፣ሚያዝያ 21 ፤2018 ( አፋ.ብ.መ.ድ )

ሚያዚያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከሰመራ-ሎግያ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር የዲጂታል አድራሻ ስርዓት ለመዘርጋት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱን የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ በላቸው ፀሐይ እና የሰመራ- ሎግያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብዱ ሙሳ ፈርመውታል፡፡

በስምምነቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ በላቸው ፀሐይ በዲጂታል-ኢትዮጵያ 2030፤ የዲጂታል አድራሻ ሥርዓት ትግበራ በማሳደግ ከዲጂታል አገልግሎቶች ጋር በማቀናጀት ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን በማድረግ ሂደት ውስጥ የአስቻይነት ሚና እንዳለው እና በቀዳሚነት የአድራሻ ሥርዓት የሚያስፈልጋቸው ሴክተሮች ጋር ተግባራዊ እንዲደረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ም/ዋና ዳይሬክተሩ አክለው የዲጂታል አድራሻ ስርአቱ (eDAS) አስተዳደራዊ፣ ዲጂታል ኢኮኖሚያዊ፣ ለSmart-City ግምባታ እና ማህበራዊ አገልግሎቶችን ቀልጣፋ እና ተደራሽ ለማድረግ፣ ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገትን፣ የከተሞችን ምቾት እና የዜጎችን ሁለንተናዊ ደህንነት ለማረጋገጥ ዓይነተኛ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።

የሰመራ-ሎግያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብዱ ሙሳ በኢንስቲትዩቱ ለከተማው አስተዳደሩ ለተሰጠው እድል ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን ዲጂታል አድራሻ ከተማችንን በማዘመን ለኑሮ፣ ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ተመራጭ የሚያደርግ በመሆኑ አጠቃላይ ስራው እስኪጠናቀቅ ድረስ አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ለስራው ስኬታማነትም የከተማ መስተዳድሩ አስፈላጉውን ሀሉ ትብብርና እገዛ በማድረግ ሀላፊነቱንበአግባቡ ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን ከንቲባው ጨምረው ገልጸዋል።

የዲጂታል አድራሻ ስርአቱ (eDAS) በ73 የኢትዮጵያ ከተሞች ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልፀው የሰመራ-ሎጊያ ከተማ አስተዳደር የዲጅታል አድራሻ ስርዓት ፕሮጅክት በአጭር ጊዜ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ስራው ተጠናቆ አገልግሎት ላይ የሚውል እንደሆነ በኢንስቲትዩቱ የዲጂታል የአድራሻ ስርዓት ኘሮጀክት ማናጀር አቶ አግማሴ ገበየሁ ገልፀዋል።

አፋር ብዙሀን መገናኛ ድርጅት

29/04/2026
 #አፋርን የዓለም የሳይንስና የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የታለመው ታላቅ ፕሮጀክትሚያዚያ 9፣ 2018 — የሰው ልጅ የታሪክ መጽሐፍ ቀዳሚ ምዕራፍ ተደርጋ በምትወሰደው አፋር፣ የሰው ልጅን አጀ...
17/04/2026

#አፋርን የዓለም የሳይንስና የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የታለመው ታላቅ ፕሮጀክት

ሚያዚያ 9፣ 2018 — የሰው ልጅ የታሪክ መጽሐፍ ቀዳሚ ምዕራፍ ተደርጋ በምትወሰደው አፋር፣ የሰው ልጅን አጀማመር
በዝርዝር የሚተርክ ዘመናዊ ሙዚየም ሊገነባ ነው።

የአፋር ክልል በተለይም የአዋሽ ተፋሰስ እንደ ሉሲ (ሄሎ መሊ)፣ አርዲ እና ሰላም ያሉ የዓለምን ሳይንሳዊ እይታ የቀየሩ የሰው ልጅ ቅድመ አያቶች ቅሪተ አካላት የተገኙበት ስፍራ መሆኑ ይታወቃል።

ምንም እንኳን ክልሉ በዓለም የሳይንስ ሊቃውንት ዘንድ የሰው ዘር መገኛ የሚል ደማቅ ስም ቢኖረውም፣ እስካሁን ድረስ እነዚህን ታላላቅ ግኝቶች በዝርዝር የሚያሳይና ታሪካቸውን በዘመናዊ መልክ የሚተርክ ማዕከል በአካባቢው ሳይኖር ቆይቷል። ይህንን ክፍተት ለመሙላት የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን በ 329 ሚሊየን ብር ወጪ ሙዚየሙን ለመገንባት በይፋ ወደ ሥራ ገብቷል።

💠 የሙዚየሙ ዘርፈ-ብዙ ፋይዳዎች

ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት ከግንባታ ባለፈ ለሀገርና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚሰጠው ጥቅም በበርካታ ዘርፎች የሚገለጽ ነው፦

🔬 ለሳይንሳዊ ምርምርና ዕድገት፦

⩩ ለሀገር ውስጥና ለዓለም አቀፍ ተመራማሪዎች ምቹ የምርምር ማዕከል ሆኖ ያገለግላል።

⩩ ተመራማሪዎች ቅሪተ አካላቱ በተገኙበት ስፍራ ሆነው ጥናት እንዲያደርጉ ዕድል ይፈጥራል።

⩩ ኢትዮጵያውያን ሳይንቲስቶች ከዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ጋር ልምድ የሚለዋወጡበት መድረክ ይሆናል።

🌍 ለማህበራዊና አካባቢያዊ ልማት፦

⩩ የአፋር ማህበረሰብ የታሪኩ ባለቤት መሆኑን በተግባር የሚያረጋግጥና ለማንነት ኩራት ምንጭ ይሆናል።

⩩ የአካባቢው ተማሪዎችና ወጣቶች ስለ ሰው ልጅ ታሪክ በተግባር የታገዘ ትምህርት እንዲያገኙ ያስችላል።

🏨 ለቱሪዝም ዘርፍ መነቃቃት፦

⩩ የቱሪዝም ሞተር በመሆን የጎብኝዎችን ቁጥር ከመጨመር ባለፈ፣ ቱሪስቶች በአካባቢው የሚቆዩበትን ጊዜ እንዲያራዝሙ ያደርጋል።

⩩ ለሆቴሎች፣ ለትራንስፖርትና ለሀገር በቀል የእጅ ጥበብ ውጤቶች ሰፊ ገበያ ይፈጥራል።

🇪🇹 ለሀገር ገጽታ ግንባታና ዲፕሎማሲ፦

⩩ ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ መሆኗን በዓለም መድረክ ይበልጥ ለማስተዋወቅ ትልቅ የዲፕሎማሲ መሣሪያ ይሆናል።

⩩ ቅርሶችን በሳይንሳዊ መንገድ ጠብቆ ማቆየት ሀገሪቱ ለዓለም አቀፍ ቅርሶች የምትሰጠውን ትኩረት የሚያሳይ ነው።

📌 ማጠቃለያ

ይህ ሙዚየም የሰው ልጅ ሁሉ መነሻ የሆነችውን ምድር አንድነትና የኢትዮጵያን ጥንታዊነት የሚያጎላ የሰላም ተምሳሌት ነው። ግንባታው ሲጠናቀቅ አፋርን የዓለም የሳይንስና የቱሪዝም ማዕከል በማድረግ፣ ታሪክን በክብር ጠብቆ ለትውልድ ለማስተላለፍ ትልቅ አቅም ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።

17/04/2026
12/04/2026

Qafar Rakaakayak Samara Logiyi Magaalal Qado Dirrik 24, Baaxo Milaaguy Geytime Daddos Mayso Faatit Tekke Qokol Soolo Wagsiisak Samara Logiy Magaalah Xiinissok Naharsi Saqalah yan Maskaxxale Cajji Qabdu M***a Hussen Tatruse farmo..

Samara - Logiy Magaalah Xiinissok kantibah kutbeh buxa

የድጋፍ ሰልፍ ጥሪ የተከበሩ ሃጂ አብዱ ሙሳ ሁሴን የሰመራ ሎጊያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ለሰመራ ሎጊያ ከተማ ማህበረሰብ በሙሉየሰመራ ሎጊያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ እና ከሁለቱም ክፍለ ከተ...
08/04/2026

የድጋፍ ሰልፍ ጥሪ የተከበሩ ሃጂ አብዱ ሙሳ ሁሴን የሰመራ ሎጊያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ለሰመራ ሎጊያ ከተማ ማህበረሰብ በሙሉ

የሰመራ ሎጊያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ እና ከሁለቱም ክፍለ ከተሞች እና የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ጋር በመሆን " በሀገራዊ ለውጡ የተመዘገቡ የልማትና የብልፅግና ስኬቶችን እውቅና ለመስጠት ያለመ መጋቢት 24 የጨለማው መጋረጃ ተገፎ የሀገራችን የከፍታ ብርሃን የታየበት ታሪካዊ ቀን" በሚል መሪ ቃል በቀን 1/9/2018 ሀሙስ ነገ ጠዋት 12/ሰአት ጀምሮ ታላቅ የድጋፍ ስልፍ ስላለን የሰመራ ሎጊያ ከተማ አስተዳደር የከተማችን ማህበረሰብ በሙሉ ማንም ሳይቀር የድጋፉ ሰልፍ ተሳታፍ አንድትሆኑ በአክብሮት እንጠይቃለን የሰመራ ሎጊያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሃጂ አብዱ ሙሳ ሁሴን

የሰመራ ሎጊያ ከተማ አስተዳደር የከተማችን ማህበረሰብ እና የመንግስት ሰራተኞች እና ወጣቶች እንዲሁም አባቶችና እናቶች በዚህ ታሪካዊ የድጋፍ ሰልፍ ላይ በነቂስ በመውጣት የለውጥ አጋርነታችሁን እንድታሳዩ ጥሪውን የሰመራ ሎጊያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ ሃጂ አብዱ ሙሳ ሁሴን አስተላልፈዋል።

መጋቢት 30/8/2018
Samara - Logiy Magaalah Xiinissok Kantibah Kutbeh Buxa

የሠመራ-ሎግያ ከንቲባ በ100 ሄክታር መሬት ላይ ያለማውን የስንዴ ምርት ሰበሰበ።   ሰመራ ፣ መጋቢት 28፣ 2018 (አፋ.ብ.መ.ድ)የሰመራ-ሎግያ ከተማ ከንቲባ በቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸ...
06/04/2026

የሠመራ-ሎግያ ከንቲባ በ100 ሄክታር መሬት ላይ ያለማውን የስንዴ ምርት ሰበሰበ።

ሰመራ ፣ መጋቢት 28፣ 2018 (አፋ.ብ.መ.ድ)

የሰመራ-ሎግያ ከተማ ከንቲባ በቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው አማካኝ ተገምብቶ ስራ ለጀመረው ብርሃን ዳቦና ዱቄት ፋብሪካ ግብአት እንዲሆን በ100 ሄክታር መሬት ላይ ያለማውን ስንዴ ምርት መሰብሰብ ጀመረ ።

በመርሃ-ግብሩ ላይ የከተማ መስተዳድሩ ከንቲባ አብዱ ሙሳን ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

በዚህ ወቅትም የከተማ መስተዳድሩ ከንቲባ አቶ አብዱ ሙሳ እንደገለጹት መንግሥት ሰው ተኮር በሆኑ የልማት ስራዎቹ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ከእነዚህም ውስጥ በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ሰመራ ከተማን ጨምሮ በተለያዪ ከተማዎች ተገምብተዉ ወደአገልግሎት ያስገቧቸው የዳቦና ዱቄት ፋብሪካዎች አንዱና ዋነኞቹ ናቸው

በሰመራ ከተማ ተገምብቶ ወደ አገልግሎት የገባው ይህ የዳቦ ፋብሪካ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ ዳቦና ዱቄት እያቀረበ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህን አማራጭም የበለጠ አስተማማኝ በሆነ አግባብ ለማስቀጠል ከክልሉ ባገኘው 500 ሄክታር መሬት ላይ በመጀመሪያው ዙር 100 ሄክታር መሬት ላይ ያለማውን የስንዴ ምርት መሰብሰብ መጀመሩን ተናግረዋል።

ይህም ከዚህ በፊት ሲገጥሙት የነበሩ የግብአት አቅርቦት ችግር በመቅረፋ የዳቦና ዱቄት ምርቱን ዘላቂነትባለው መልኩ በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቱን ለህብረተሰቡ ለማቅረብ እንደሚስችለው ጠቁመዋል።

መሀመድ አሊ
አፋር ብዙሀን መገናኛ ድርጅት

Address

Semera Logiy
Logya

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Samara-Logiyi Ma/Xii Qaadaay Wacaysir Kee Qafar Afih Gaddalosiyyi K/Buxa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category