The holy land of lalibela peoples

The holy land of lalibela peoples This is the lalibela peoples talking page and we will share our Everything about lalibela

እንኳን ለቸሩ አምላካችን  #ለመድኀኔዓለም ክብረ በዓል (ለመጋቢት 27 ጥንተ ስቅለት ልዋጭ በዓል) እና   ክብረ በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ፡፡
06/11/2025

እንኳን ለቸሩ አምላካችን #ለመድኀኔዓለም ክብረ በዓል (ለመጋቢት 27 ጥንተ ስቅለት ልዋጭ በዓል) እና ክብረ በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ፡፡

16/10/2025

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Ayal Tasew Lal, Bereket Addisse, Adonaye Eyesoss, Getu Eshetu, Sisay Temesgen Tsegaw, Yihune Assefa, Belaye Mesganaw, Meseret Aweke, Yawkal Tesfaw, Ytayh Kinde

07/09/2025

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Lidetu Mulu, Tilahun Abate, እንየው የእናቱ ልጅ, Mekonen Abera, እማ ክፉሽን አልስማ, Emuye Awash, Haymanot Belay, Gietu Tegaye Assefa, Belay Tefera, Ŵĩž Ñãĥøm Wagaw, Hani Marr, Fasikaw Zena, Letsatsi Tsotetsi, Emabate Wedaju, አይቸዉ አይቸዉ አለልኝ, Etalem Gadissa, Adebabay Galo, Endau Endau, HAbtamu Tadesse, Weynuwa Kedir, Tagay Mamo, hirut kasaye, Peka Top, Adisu Ketema, Melkamu Sisay, Fanaye Fantaye, ኤልያስ አይናለም, Birhanu Belay, Yohanise Fkeru, ftsum, Awoke Kitaw, hiwi, Mahletasefa Mahlet, Yemaryam Yemaryam, Melkamu Yeshanew, Mengistu Alehegn, Mamshaye Getahun, Awulachew Shifets, Ayda Worku, Bezualem Dessie

ሰኔ 12 የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል!የቅድስት አፎሚያ እና የቅዱስ ላሊበላ እረፍት ነው!በቀሲስ መ/ር ሄኖክ ወ/ማርያምሰኔ 12 ቀን ቅዱስ ሚካኤል ደገኛዋን ቅድስት አፎሚያን ከሰይጣን ተንኮ...
19/06/2025

ሰኔ 12 የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል!

የቅድስት አፎሚያ እና የቅዱስ ላሊበላ እረፍት ነው!

በቀሲስ መ/ር ሄኖክ ወ/ማርያም

ሰኔ 12 ቀን ቅዱስ ሚካኤል ደገኛዋን ቅድስት አፎሚያን ከሰይጣን ተንኮል የታደገበት ዕለት እንደሆነ ድርሳኑ መዝግቦልናል፡፡

ቅድስት አፎሚያ አስተራኒቆስ የተባለ ደግ ባል ነበራት፡፡ ይህ ሰው ሊሞት ሲል የቅዱስ ሚካኤልን ስዕል አዘጋጅቶ በመስጠት፤በየወሩ በቅዱስ ሚካኤል ቀን ለድሆች፣ለጦም አዳሪዎች ምጽዋት እንድትሰጥ፤መስጠት ብቻ ሳይሆን ወደ ፈጣሪዋ አጥብቃ ከመጸለይ እንዳታቋርጥ ነግሯት ያርፋል፡፡

ቅድስት አፎሚያም ይሄንን ርህራሄና ሰብአዊነት የተመላበት በጎ ሥራ አጥብቃ መስራት ጀመረች፡፡ የበጎ ነገር ጠላት የሆነው ሰይጣን የቸርነት ሥራዋን ተመልክቶ ወደ ቅድስት አፎሚያ መጣ፡፡ አዛኝ በመምሰልም ‹‹ለምን ገንዘብሽን ታባክኛለሽ፤ይልቁንስ ገንዘብሽ ከማለቁ በፊት ባል አግብተሽ አትኖሪም ባልሽ እንደሆነ ጸድቋል ምጽዋት አያስፈልገውም›› አላት፡፡

ሰይጣን የአስተራኖቆስን መጽደቅ የተናገረው አፎሚያን ለማስደሰት ሳይሆን እንደ አዳምና ሔዋን ለማሳት ነው፡፡ ዘፍ 3÷1-8

ቅድስት አፎሚያም ‹‹ሌላ ባል ላላገባ ከፈጣሪዬ ጋር ቃል ኪዳን ገብቻለሁ›› አለችው፡፡ ሰይጣንም የሚያስትበት የጥፋትና የተንኮል መንገድ ብዙ ነውና መነኩሴ በመምሰል ብዙ ቢዘበዝባትም አፎምያ ግን ለሥጋዊ ምክሩ ቦታ ሳትሰጠው እንቢኝ አለችው፡፡

ሰይጣንም በዚህ ሳያበቃ ያስትልኛል፣አፎሚያን ያሳምንልኛል ያለውን ሐሳብ እያመጣ ቢነግራትም በእንቢታዋ ጸናች፡፡ ለሰይጣን ውሸት የየዕለት ሥራው ስለሆነ ይባስ ብሎ ቅዱስ ሚካኤል ነኝ ብሎ እርፍ አለው፡፡ ሰይጣን በአምሳለ መልአክ ሰውን እንደሚያስት ያወቀው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ሰይጣን ራሱን የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣል›› ብሎ ነግሮናል፡፡ 2ኛ ቆሮ 11÷14

ስለዚህ አፎምያ በቅዱስ ሚካኤል ተመስሎ ቢነግራትም አልቀበልም አለችው፡፡ ወዳጆቼ እስቲ እራሳችንን እናስብ ስለ እውነት እኛ ብንሆን ይህንን ፈተና እናልፍ ነበር? ይህ የአፎሚያን የእምነት ጥበብ የሚያሳይ ነው፡፡

ሰይጣንም አሉኝ የሚለውን ሰይጣናዊ ማሳመኛ ጥበብ ተጠቀመ፡፡ አፎሚያም ምንም ይበል ምንም አለተቀበለችውም፡፡ ምክንያቷ ደግሞ ንግግሩና ገጽታው ስላልተካከለ፡፡

በአፎምያ መንፈሳዊ ቆራጥነት የተበሳጨው ሰይጣንም ዓይኑን አፍጥጦ፣ጥርሱን አግጥጦ አንቆ ሊገላት ሲል ቅዱስ ሚካኤል ብርሃናዊ ክንፉን እያማታ በቅጽበት ደረሰላት ከሰይጣንም እጅ አዳናት፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም ስለ እረፍቷ ‹‹ብጽዕት አፎሚያ ሆይ ሄደሽ የቤትሽን ሥራ አዘጋጂ፣ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ትለያለሽ፣እነሆ እግዚአብሔር ዓይን ያላየውን፣ጆሮም ያልሰማውን፣በሰው ልብ ያልታሰበውን አዘጋጅቶልሻል›› ብሎ የምስራቹን ነግራት ከእሷ ተሰወረ፡፡

ቅድስት አፎምያም የቅዱስ ሚካኤልን የበዓሉን ዝግጅት ከፈጸመች በኃላ ወደ ኤጲስቆጶሱና ወደ ካህናቱ መልዕክት ላከች እነሱም መጡ፡፡ ለእነሱም ቀሪ ገንዘብዋን ለድሆች ለጦም አዳሪዎች ይሰጥዋቸውም ዘንድ አስረከበቻቸው፡፡

ከዚህ በኃላ ተነስታ ጸለየች፣የከበረ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልንም ሥዕል አንስታ አቅፋ ሳመችው/አፎሚያ ለሰይጣን ይህንን ስዕል ስታሳየው ነው አሳች መልኩ ወደ ሰይጣንነት የተቀጠረው/ ያን ጊዜም ቅድስት ነፍሷ ከሥጋዋ ተለየች፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም የከበረች ነፍሷን በብርሃናዊ ክንፉ አቅፎ ደግፎ የፈጣሪውን መንግስት እንድትወርስ አድርጓታል፡፡

ከቅድስት አፎምያ ሁለት ነገር እንማራለን፡፡ አንደኛው ጥቅም አዘል ፈተናን አልፋ ሰይጣንን ድል መንሳትዋ ሲሆን ሁለተኛው አፎምያ ጽድቅ ሰርታ የሥጋ ፈተናዋን ድል ነስታ፣ሰይጣንን ማሸነሽ
የቻለችው ጫካ ገብታ ሳይሆን በዓለም ሆና ነው፡፡ ስለዚህ ጽድቅ ሰርቶ ለመጽደቅ ሥራ እንጂ ቦታ እንደማይወስነው ታሪክዋ አስተማሪ ነው፡፡

፨ ሰኔ 12 ቀን እረፍቱ ለቅዱስ ላሊበላ ፨

ቅዱስ ላሊበላ በነገሠ ጊዜ እኔ ንጉሥ ነኝ ብሎ ድሆችን ሳይንቅ፣በአገዛዙ ሰዎችን ሳያስጨንቅ የኖረ ጻድቅ ነው፡፡ ጌታችን ቅዱስ ላሊበላን የፍቅሩን ጽናት በማየት መልአኩን ላከለት፡፡ መልአኩም ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማይ ነጠቀው፡፡ በዚያም ቤተ ክርስትያንን እንዴት እንደሚያንጽ ጥበብን ገለጠለት፡፡

ቅዱስ ላሊበላም ሥጋ የለበሱ ሰዎች ሳይሆኑ ቅዱሳን መላእክቶች በስውር እየተራዱት እነዛን አስደናቂ፣ለውጭ ጥበበኞች አጨቃጫቂ የሆኑትን ፍልፍል አብያተ ክርስትያናትን አንጿል፡፡

ጌታችንም ሰኔ 12 ቀን በብርሃን ሰረገላ ተቀምጦ፣የሚያስፈራ መብረቅን ተጎናጽፎ ቅዱሳን መላእክትን አስከትሎ ወደ ቅዱስ ላሊበላ መጣ፡፡ ጌታም ‹‹ወዳጄ ላሊበላ ሆይ ሰላም ላንተ ይሁንልህ፡፡ እኔ በማይታበል ቃሌ እነግርሃለሁ፤ማደርያህ በክብር ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ጋር ይሁን፡፡ በጸሎትህና በቃል ኪዳንህ ለሚታመን እምነቱ እንደ ጴጥሮስና ጳውሎስ ደም መፍሰስ ይሆንለታል፡፡

ወደ ቤተ መቅደስህ የሔደ ኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መቅደስ እንደ ሄደ ይሆንለታል፡፡ መቃብርህንም የተሳለመ የሥጋዬን መቃብር እንደተሳለመ ይሆንለታል፡፡ በየወሩ የተራቡትን እያበላ፣የተጠሙትን እያጠጣ መታሰብያህን ለሚያደርግ እኔ የተሰወረ መና እመግበዋለሁ፤የህይወትንም ጽዋንም አጠጣዋለሁ፡፡ በመታሰብያህ ቀን ዕጣን ወይም ስንዴ የሚያገባውን እኔ በኢየሩሳሌም ሰማያዊት በውስጠኛው መጋረጃ አስቀምጬ ከተቆረሰው ሥጋዬ አቆርበዋሁ፤በአማላጅነትህም እየታመነ የገድልህን መጽሐፍ የሚጽፈውን ያንተ ስም በተጻፈበት ቦታ እኔ ስሙን እጽፋለሁ፡፡፡ በፍጹም ልቡ ለሚያምን ይህን የማይታበል ቃል የተናገርኩ የህያው እግዚአብሔር ልጅ እኔ ኢየሱስ ነኝ›› አለው፡፡

ቅዱስ ላሊበላም ይህንን ቃል ኪዳን ስለሰጠውና ስላጸናለት ጌታችንን እያመሰገነ እግሩ ላይ ወድቆ አመሰገነው፡፡ ሰኔ 12 ቀንም አረፈ፡፡ ቅድስት ነፍሱንም ቅዱሳን መላእክት ይዘው የዘላለም ማረፍያው አስገቡት፡፡

፨ የቅዱስ ሚካኤል የወር በዓላት ከነምክንያት ፨

መስከረም 12 ፦ ቅዱስ ፋሲለደስን በመከራው ሰዓት የረዳበት እና የሰማዕትነት ተጋድሎውን ከፍጻሜ እንዲያደርስ ከጎኑ ተገኝቶ ያጸናበት

ጥቅምት 12 ፦ ነብዩ ሳሙኤል ዳዊትን ቅብዐ መንግስት እንዲቀባው የነገረበት ቀን ነው፡፡ ቅዱስ ዳዊትም ከቅዱሳን መላእክት ረድኤት በደንብ ስለተጠቀመ ክብራቸውን በመዝሙሩ በደንብ መዝግቧል፡፡

ህዳር 12 ፦ የቅዱስ ሚካኤል በዓለ ሲመቱ ነው፡፡ በዚህ ቀን እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ አደርጎ ሾመው፡፡ የመላእክት ሹመት እንደ ሰው በተጽእኖ አይደለም፡፡ ሰው በሰው ላይ የሚሾመው ለመገልገል ነው፡፡ የመላእክት ሹመት ግን ለማገልገል ነው፡፡ እንደ ሰው አንዱ መልአክ አንዱን መልአክ አያገለግልም፡፡ አገልግሎታቸው እግዚአብሔርንና ሰውን ነው፡፡

በዚህም ቀን ለሰው ልጆች ከፈጣሪው ምህረት የሚለምንበት እና በቃል ኪዳኑ ነፍሳትን ከሲኦል የሚያወጣበት ቀን ነው፡፡ ለነዌ ልጅ ለኢያሱ በታላቅ ክብር በንጉሥ ጭፍራ አምሳል የታየበት ቀንም ነው፡፡

ታህሳስ 12 ፦ ዱራታኦስና ቴዎብስትያን የረዳበት ቀን ነው፡፡

ጥር 12 ፦ ያዕቆብን ከኤሳው፣ተላፊኖስን ከአመጸኛው ያዳነበት ቀን ነው፡፡

የካቲት 12 ፦ አንድ ችግረኛ ሰው ያለ ሥራ ቁጭ ብሎ ቅዱስ ሚካኤል ምግብ እንዲያመጣለት በመነዝነዝ ያስቸግረው ስለነበረ ቅዱስ ሚካኤልም ወደ ችግረኛው ሰው በመሄድ ‹‹ወይ እርሻ ኖሮህ አልባረኩልህ፣ወይ ገንዘብ ኖሮክ ንግድህን አልባረኩልህ ዝም ብለህ ለምን ታስቸግረኛለህ›› ብሎት ወቅሶት በቅዱስ ሚካኤል ገንዘብ ነግዶ ተአምር የሰራለት ቀን ነው፡፡

መጋቢት 12 ፦ ኢአማኒ የነበረውን ቂሶንን ወደ ክርስትና የመለሰበት ቀን ነው፡፡

ሚያዝያ 12 ፦ ነብዩ ኤርሚያስን በአመጸኛው ሴዴቅያስ ከተጣለበት የቆሻሻ ጉድጓድ ያወጣበት ቀን ነው፡፡

ግንቦት 12 ፦ ወደ ነብዩ ዕንባቆም ተልኮ ዕንባቆምን በባቢሎን ዳንኤልን በአንበሳ ጉድጓድ በተጣለበት ጊዜ ምግብ እንዲያደርስለት ከምድረ ፍልስጥኤም በተአምር ተሸክሞ ፋርስ አውርዶት ዳንኤልን የረዳበት ቀን ነው፡፡

ሰኔ 12 ፦ ቅድስት አፎሚያን ከሰይጣን የታደገበት ቀን ነው፡፡ ባሕራንንም የሞቱን ደብዳቤ አጥፍቶ፣በሠርግ ተክቶ ተአምር እንደሰራለት ድርሳኑ ይነግረናል፡፡

ሐምሌ 12 ፦ እግዚአብሔር የይሁዳ ንጉሥ የሕዝቅያስን ጸሎት ሰምቶ ቅዱስ ሚካኤልን ልኮለት ከሰናክሬም መቅሰፍት ኢየሩሳሌምንና የይሁዳ ሰዎችን ያዳነበት ቀን ነው፡፡

ነሐሴ 12 ፦ ንጉሡ ቆስጠንጢኖስን የረዳበት፤አርባ ዘመን ቤተ ክርስትያንን ሲያቃጥሉ ክርስትያኖችን በእሳት ሲማግዱ፣በሰይፍ ሲያርዱ የነበሩትን ዲዮቅልጥያኖስንና መክስምያኖስን ከምድረ ገጽ ያጠፋበት ቀን ነው፡፡

ሺህ በክንፉ ሺህ በአክናፉ ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል በብርሃናዊ ክንፉ አቅፎ ደግፎ ከክፍ ነገር ይሰውረን፡፡ የቅድስት አፎሚያ፣የቅዱስ ላሊበላ ጸሎት በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡

ቤተሰብ ገብታቹህ Like እና subscriber አድርጉ
10/06/2025

ቤተሰብ ገብታቹህ Like እና subscriber አድርጉ

ቅዱስ ላልይበላ ሌላኛው ድንቅ ነገር ተገኝቷል።ይህ የምትመለከቱት ትሬንች ከቤተ ማርያም ወደ ቤተ ጊወርጊስ ፀበሉና ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ የሚሄድ ሲሆን በተለያየ ወቅት ተደፍኖ አሁን ላይ በዘላቂ...
13/03/2025

ቅዱስ ላልይበላ ሌላኛው ድንቅ ነገር ተገኝቷል።
ይህ የምትመለከቱት ትሬንች ከቤተ ማርያም ወደ ቤተ ጊወርጊስ ፀበሉና ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ የሚሄድ ሲሆን በተለያየ ወቅት ተደፍኖ አሁን ላይ በዘላቂ ላሊበላ ፕሮጀክት አፈሩ ሲወጣ ከቡድን ሶስት በቀራኒዮ አድርጎ ወደ ቡድን አንድ የሚወስድ የዋሻ በር ተገኝቷል።
የላ/ከ/አስ/ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት 2017 አ.ም

04/03/2025

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Bereket Ayele, Eyayaw Mesay, Mak Bela, Wubshet Adane, የእናቴ ምርኮኛ, Emebet Emebet, Kidest Zemen

28/02/2025
16/02/2025

ቅዱስ ላልይበላ
❤❤❤❤❤❤

Address

Lalibela

Telephone

+251982048064

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when The holy land of lalibela peoples posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to The holy land of lalibela peoples:

Shortcuts

Share