ስራና ህይወት Work & Life

ስራና ህይወት Work & Life

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ስራና ህይወት Work & Life, Personal coach, Jijiga.

Photos from ስራና ህይወት Work & Life's post 25/08/2025

የመልካም አስተዳደር እቅድ



ክፍል 2፡ የእቅድ ዝግጅት

Photos from ስራና ህይወት Work & Life's post 25/08/2025

የመልካም አስተዳደር እቅድ



ክፍል አንድ የመልካም አስተዳደር መርሆዎች

Photos from ስራና ህይወት Work & Life's post 18/05/2025

Chat GPT Created operators of Work & Life
በቻት ጅፒቲ በኩል የተቀጠሩ የስራና ህይወት ሰራተኞችን እናስተዋውቃችሁ



ስራና ህይወት በልዩ አቀራረብ ቻት ጅፒቲን በመጠቀም ሊያገለግላችሁ ዝግጅቱን አጠናቋል በቅርቡ ይጠብቁን

10/05/2025

ስንቀየር የሚያስቸግሩን እነማን ናቸው...?



ለውጥ በሚከሰት ጊዜ በጥምረት የሚጓዙ ሁለት “አይጦች”ና ሁለት “ትንንሽ ሰዎች” እንደሚኖሩ ዶ/ር እስፔንሰር ጆንሰን “አይቤን ማን ወሰደው” በሚል በጻፉት አጭር ጽሁፋቸው አስፍረው እናገኛለን ለውጥህ በሚያብብ ጊዜ ምን አይነት ጥረት ውጤታማ እንዳደረገህ ግድ ሳይሰጣቸው ምንም አስተዋጽኦ ላላደረጉበትና ካንተ ተገኝቶ የተትረፈረውን የስኬት “አይብ” እንደመብታቸው በመቁጠር የሚጠቀሙ ገጸ ባሀሪዎች ናቸው
በጋራ ከሚንቀሳቀሱት ሁለቱ አይጦች አንዱ የሚፈልገው ነገር የት እንዳለ በማነፍነፍ የማወቅ ጸጋ ያለው ሲሆን አንዱ በፍጥነት ደርሰው እንዲጠቀሙ የሚመራ ነው በተቃራኒው የሚፈልጉት ነገር ሲጠፋም ደጋግመው ማሰብ ሳይጠበቅባቸው በፍጥነት ከዚያ ቦታ የሚሰወሩ ናቸው
እነዚህ ሰዎች በአይጦች የተወከሉት እንደ እንስሳ እንጅ እንደ ሰው ስለማያስቡ ነው አንዱ አነፍናፊ ሲሆን አንዱ በፍጥነት ደራሽ ነው ስለለውጥህና ከመጣው ለውጥ ለመጠቀም የሚችሉበትን የተሟላ ሁኔታ ማንም ሳነግይራቸው ማወቅ የሚችሉ ሰዎችን ይወክላል ካንተ ለሚያገኙት ነገር እንጅ ላንተ ምንም ግድ ስለሌላቸው ያገኙትን ነገር ባጡበት ቅጽበት ከጎንህ የሉም
ትንንሽ ሰዎች አእምሮአቸውን የሚጠቀሙ ነገር ግን በመወንጀል በመውቀስና በማሳበብ የሚታወቁ ሲሆን “እሱ ነው” እና “እንዴት አደረገው” በሚል ስም ተወክለው ይገኛሉ ካንተ የሚያገኙት ፍርፋሪ “አይብ” እየቀረ እንደሆነ ሲያስቡ አስቀርቶታል ብለው የሚሉትን ሰው ፈልገው በማጥቃትና ማናቸውንም አይነት እርምጃ በመውሰድ ለመመለስ የሚሞክሩ ሲሆን የሚከሰስ ባይኖርም ከመላምት ወደሗላ የማይሉና ለውጡን ማመን ባለመቻል ራሳቸውን እስከመጉዳት የሚሰርሱ ሰዎችን ባህሪ ይወክላል
በመጻህፍ ቅዱስ የእየሱስ ክርስቶስን ታሪክ ስንመለከትም ከቱሩፋቱ በተገኘ መቅደሱና መንግስቱ የሚተዳደሩ ትንንሽ የመጻህፍት መምህራንና ነገስታት ለውጡን ሲሰሙ ስልጣናቸው እንዳስጨነቃቸውና ስልጣናቸውን ለማትረፍ ክርስቶስን ወንጅለው በመውቀስና በማሳበብ ለሞት እንደዳረጉት እንዲሁም በእጁ የዳኑና በተአምራቱ የተመገቡ ህዝቦች መያዙን ሲመለከቱ እንደ እንስሳ እንደካዱት እንመለከታለን
እንደ እንስሳ የሆኑ ሰዎች ካንተ የሚያገኙትን ጥቅም ካጡ ላንተ እንደሆኑት ለሌላውም በመሆን ተጠቃሚነታቸውን ያስቀጥላሉ...
ፍቅረኛየ ያልካት፥ ጓደኛህ፥ አገልጋይህ፥ በማንኛውን አጋጣሚ የቀረበህ ሰው ትሰጠው የነበረውን ጥቅም ባቋረጥክበት ቅጽበት ወይም ካንተ የተሻለ የሚጠቅመው ባገኘ ጊዜ ሲከዳ ማየት የተለመደ ነው እንዲያውም ለሌላ አግዞ ሊወነጅልህና በፈጠራና በውሸት ስምህን ሊያጠፋም ይችላል እንደ ሰው ቆጥረሀቸው ብሽሽቅ ውስጥ ባትገባ ጥሩ ነው ትተሃቸው እለፍ መንገድህን ቀጥል ለክርስቶስ ያልተመለሱ መሆናቸውን አትርሳ
ጥቅም ፈልገው የሚወነጅሉህና ሊያጠቁህ የሚፈልጉ ሰዎችን እንደ ክርስቶስ አምላክ ካልሆንክ በስተቀር ፊት አትስጣቸው...
በሃይልና በማስፈራራት ጥቅም የምትሰጠው ሰው ካለ አሁኑኑ ማስተካከል አለብህ ሲጎዳህ አንተም እንደምትጎዳው አውቆ እንዲፈራህና በምትፈልገው መንገድ ሲሄድ ብቻ እንደምትጠቅመው እንዲያውቅ አድርግ አለበለዚያ አንድ ቀን በዚህ ሰው ልትጠፋ እንደምትችል አትጠራጠር አንተ ደግሞ አምላክ ስላልሆን ከሞትክ እንደክርስቶስ ልትነሳ አትችልምና አትቀልድ

10/05/2025

ለውጥ ምንድን ነው?



ነግቶ ከመንቃታችን ጀምሮ መሽቶ እስከምንተኛ ድረስ ለውጥን ከማስተዋል አንቦዝንም ለውጥ ተፈጥሮአዊም ሰው ሰራሽም፥ ፈጣንም ዘገምተኛም ሁሉንም ነው የተፈጥሮ ሳይንስና የማህበራዊ ሳይንስ ምሁራን ስለለውጥ ብዙ የምርምር ስራዎችን አቅርበዋል ጽፈዋል እነዚህን ጽንሰ ሃሳቦች መገንዘብ ነባራዊ ሁኔታን ለመተንተንና ማንኛውንም የስራ እቅድ እና የለውጥ እንቅስቃሴ ስናስብ ግምት ውስጥ ልናስገባቸው የሚገቡ በመሆናቸው እንደሚከተለው ጠቅለል አድርገን ጠቅሰናቸዋል ሆኖም በደንብ ለመረዳት የተዛማጅ ጽሁፎችን በጥልቀት ማንበብና መዳሰስ አስፈላጊ ነው
...ጥያቄ ሃሳብና አስተያየታችሁን ኮሜንት ላይ ማስቀመጥ ትችላላችሁ...

የተፈጥሮ ሳይንስ ብያኔ

ለውጥ የጀመረው በታላቁ ፍንዳታ ወይም “Big Bang” ሲሆን ከዛን ጊዜ ጀምሮ የምናየውም የማናየውም የተፈጥሮ አካል ካለመኖር ወደ መኖር የመጣበት፤ ዘመን መቁጠር የተጀመረበትና ረዘም ባለ የዝግመተ ለውጥ ሂደት ዛሬ ያለንበት ሁኔታ ላይ ልንደርስ እንደቻልን ይገልጻል
እኛ ሰዎች ልጅ እያለን ቤተሰቦቻችን የምንፈልገውን እንደሚሰጡን እኛም እንደምንቀበል መኖሪያችንና ንብረቶችን ተጋርተን ወደ ለውጥ እንደምንገባው ሁሉ ህይወት ያለውና የሌለው አካል ወደ ለውጥ የሚገባበት ጊዜ በውስጡ ባለው የንጥረ-ነገር (Element) ይዘት መስጠት መቀበል እና መጋራት ሁኔታ ተመስርቶ ወደ ለውጥ ይገባል ይህ ሁኔታ ህይወት ባለው አካል ውስጥ በዘረመል ቀመር መሰረት የሚተዳደር ሆኖ ሰውነታችን ውስጥ እድገትና ለውጥ እንዲከሰት መሰረታዊ መነሻ ነው በሌሎች እንስሳትና በእጽዋትም ጭምር ለውጡ ይህን መንገድ በመከተል ይከናወናል
ለምሳሌ ያህል ወደ ወጣትነት ስንሸጋገር ለውጡ ጉልህ ሆኖ በድምጻችን መጎርነንና መቅጠን፥ የመራቢያ አካሎቻችን መዳበርና ስሜታችንን ሙሉ ለሙሉ በመቀየር ይገለጽና ከልጅነታችን ጠባብ አለም አጣልቶ የህይወትን ጥልቀት ለመዳሰስ በሚጓጓ ማንነት “የገሃነም ቁልቁለት” ይተካና ለውጣችን በግልጽ የሚታይ ይሆናል
ባጠቃላይ የሰው ልጅ ህይወት በሰባት ቅመሞች (ፍላጎቶቹ) ላይ የተገነባ የመሆንና አለመሆን ስልተ-ምት ነው (Clear, 2023) ለውጥ እነዚህን ፍላጎቶች ለማሳካት የሚደረግ እንቅስቃሴ ውጤት ነው
1. ምግብና መጠጥ
2. ሀይልና ቁጠባ
3. ፍቅርና ዘር መተካት
4. ከሌሎች ጋር መዛመድና ጥምረት መፍጠር
5. ማህበራዊ ተቀባይነትና ማረጋገጫን ማቸነፍ
6. ደረጃንና ክብርን ማስጠበቅ
7. ስጋትንና ጥርጣሬን መቀነስ ናቸው

የማህበራዊ ሳይንስ ብያኔ

የሰው ልጅ በምድር ላይ በጋራ መኖር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ አምስት ዋና ዋና ሀይሎች ለውጥን እንደሚወስኑለት ይታወቃል
1. ፖለቲካዊ ፦ ወደ ስልጣን የሚመጣ ሃይል ወይም አስተሳሰብ ሲኖር ከተስማማን በመደገፍ ካልተስማማን በመቃወም ለውጥ ውስጥ እንድንሳተፍ እንገደዳለን አያገባንም ብንል እንኳ የመጣው ሃይል የሚያደርሰው ጥቅምና ጉዳት በየቤታችን መግባቱ አይቀርም፤ በተለይ ከፖሊሲ ማውጣት እስከ ማስፈጸም ያሉ ዋንኛ የመንግስትን አቅሞች የሚወስን አካል እንደመሆኑና ሲመጣም ቃል የሚገባለት የህብረተሰብ ክፍል ስለሚኖር ብዙ ድርጅቶች ትልልቅ ባለሃብቶች እንዲፈርሱና አዳዲሶች እንዲወጡ ምክንያት ይሆናል
2. ኢኮኖሚያዊ፦ ሰዎች “ሀብት ሲመጣ ብር ሲይዙ ተቀየሩብኝ” ይላሉ ኢኮኖሚ (የመክፈል አቅም) የምንመኘውን ለውጥ ለማሳካት መንገዱን ቀለል ያደርግልናል ወይም አለመኖሩ ደግሞ ያከብድብናል
3. ማህበራዊ፦ ሁሉም ማህበረሰብ እምነቱን ባህሉንና የኑሮ ዘይቤውን ይወዳል ይጠብቃል ሰው ከአንድ ማህበረሰብ ጋር ሲኖር መመሳሰል ይጠበቅበታል አልያ ግን ጉዳትን ማስተናገዱ አይቀርም
4. ቴክኖሎጅያዊ፦ ቴክኖሎጅ ዋነኛ የለውጥ መሳሪያ እየሆነ እንደመጣ ይነገራል እኔ ይህን ሃሳብ ለማዘጋጀት የቻልኩት በዩ-ቲዩብ እና ፌስ ቡክን በመሳሰሉ የማህበራዊ ሚዲያዎች ለእናንተ ተደራሽ እንደሚሆን በማሰብ ነው ይህ ቴክኖሎጅ ባይኖር ለማዘጋጀት አልደክምም ነበር ይህንና የመሳሰሉ የስራ ማቅለያ ቴክኖሎጅዎች አንዱን ድርጅት ከፍ አንዱን ዝቅ የማድረግ እድል አላቸው ለምሳሌ የተሻለ ማሽነሪ ተጠቅሞ የሚሰራ ፋብሪካ ከሱ ተመሳሳይ ከሆነና ዝቅተኛ ማሽነሪ ከሚጠቀምና ጭራሽ ከማይጠቀም ድርጅት የተሻለ መሆኑ ጥርጥር የለውም
5. አካባቢያዊ፦ ጎንደር ከተማ መኖርና በዙሪያው በሚገኝ ገጠር ወይም የበለጠ በሰለጠነ የአውሮፓ ከተማ መኖር አንድ አይነት ሰው እንድንሆን አያደርገንም ይህም ከአካባቢያዊ የመሰረተ ልማት ምቹነት ጋር በተያያዘ ህይወታችን ቀለል የማለት ከፍ ያለ ተደራሽነት እንዲኖረን የማድረግ ነገር ይኖረዋል
6. ህጋዊ፦ በአንድ ሀገር እየኖረ ያለ ሰው የዛን ሀገር ህግ ማክበር እንዳለበት ይታወቃል ህጎች ሲሻሻሉም ህይወቱና ኑሮው ላይ ተጽእኖ ይኖራቸዋል

Photos from ስራና ህይወት Work & Life's post 09/05/2025
Want your school to be the top-listed School/college in Jijiga?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Website

Address

Jijiga
00251