Hossana Polytechnic college

Hossana Polytechnic college HPTC is dedicated to provide efficient, demand driven and project based high quality ethiopian occup

በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ቢሮ የሠልጣኝ፣ አሰልጣኝ፣ አመራር ልማትና ተቋማት አቅም ግንባታ ዳይሮክቶሬት አዲስ ወደ አመራርነት ለመጡ ዋናና ምክትል ዲኖች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና መስ...
03/02/2020

በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ቢሮ የሠልጣኝ፣ አሰልጣኝ፣ አመራር ልማትና ተቋማት አቅም ግንባታ ዳይሮክቶሬት አዲስ ወደ አመራርነት ለመጡ ዋናና ምክትል ዲኖች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና መስጠቱ ተገለፀ፡፡
=================================
በቢሮው የሠልጣኝ፣ አሰልጣኝ፣ አመራር ልማትና ተቋማት አቅም ግንባታ ዳይሮክቶሬት እንዳስታወቀው አዲስ ወደ አመራርነት ለመጡ ከ70 ለሚበልጡ
የኮሌጅ ዋናና ምክትል ዲኖች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና በቡታጅራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከጥር ግቢ ለተከታታይ 5 ቀናት መስጠቱ ተገለፀ፡፡ በተያያዘም ሥልጠናው በዋናነት አዲስ ወደ ቴ/ሙያ አመራሪነት የመጡ ዲኖችና ምክትል ዲኖች የቴ/ሙ/ት/ሥ/ ዘርፉን በብቃት፣ በዕውቀት እና በክህሎት እንድመሩ 15 ያህል የሥልጠና ሞጁል ተዘጋጅቶ መሰጠቱ የተገለፀ ስሆን ሁሉም ወደዬ ኮሌጆቻቸው ስመለሱ ለኮሌጁ ማህበረሰብ በማውረድ በስትራቴጅው መሠረት ከመምራትም ባሻገር የሥርዓቱን ዘላቅነት ለማረጋገጥ የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባቸዋል ተብሏል፡፡ ቢሮው ያዘጋጀውን ሥልጠና ካሰለጠኑት አሠልጣኞች መካከል አቶ አረጋ ታመነ
ከወራቤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሪጂስትራል አስተባባሪ በበኩላቸው ቢሮው ዋና ዲኖችንና ምክትል ዲኖችን በጋራ ከማሰልጠንም በተጨማሪ ሴት አሠልጣኞችን
ወደ አመራርነት እንድመጡ አድርጎ በርካታ ሴቶች እንድሳተፉ ማድረጉ ሥልጠናውን ለየት እንደሚያደርግ ገልፀው የሥልጠናው ዋና ዓላማም አመራሮች በሰው ሀይል፣ በፋይናንስና ንብረት አስተዳደር፣ በሥርዓተ ትምህርትና ቲቲኤልኤም አዘገጃጀትና አተገባበር፣ በIDP & DAC አዘገጃጀት፣ በካይዘን አተገባበር ወዘተ በአጠቃላይ በቴ/ሙ/ት/ሥ/ስትራቴጂ ላይ የጠራ
አመለካከትና ግንዛቤ በመያዝ ኮሌጆችን በብቃት፣ በዕውቀትና በክህሎት ለመምራት የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡ ከስልጠና ተሳታፊዎች መካከል ወ/ሪት ሰርካለም እሸቱ በሣውላ ፖሊ ቴክኒክ
ኮሌጅ የሠልጣኝ፣ አሰልጣኝ፣ አመራር ልማትና ተቋማት አቅም ግንባታ አስተባባሪ እና ምክትል ዲን የሆኑት በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት አብዛኞቻቸው በሠልጣኝና አሠልጣኝነት በሥርዓቱ ውስጥ አልፈው የመጡ ብሆኑም እንደዚህ ዓይነት ሥልጠና በመሪነት ሚናቸው ላይ ግንዛቤ በመፍጠርና አቅምን በማሳደግ የሚፈጥረው አወንታዊ ተጽዕኖ የጎላ መሆኑን ገልፀው
ለውጤታማነትም የሚችሉትን ሁሉ ለማድረግ መነሳሳታቸውን አስታውቀው ሥልጠናው በስኬት መጠናቀቁን የቢሮው ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮ ዳይሬክቶሬት ዘግቧል፡፡

እንኳን ደስ አለንኢትዮጵያ ETRSS-1 የተሰኘችውን የመጀመሪያ የመሬት ምልከታ ሳተላይት ወደ ህዋ ልካለች
20/12/2019

እንኳን ደስ አለን
ኢትዮጵያ ETRSS-1 የተሰኘችውን የመጀመሪያ የመሬት ምልከታ ሳተላይት ወደ ህዋ ልካለች

የሆሳዕና ፖሊ-ቴክኒክ መሠረታዊ መምህራን ማህበር ዛሬ ታህሳስ 9/2012 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ  የ2011 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀምን በመገምገም የ2012 ዓ.ም ዕቅድን አፅድቋል።መምህራን ማህበ...
19/12/2019

የሆሳዕና ፖሊ-ቴክኒክ መሠረታዊ መምህራን ማህበር ዛሬ ታህሳስ 9/2012 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የ2011 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀምን በመገምገም የ2012 ዓ.ም ዕቅድን አፅድቋል።መምህራን ማህበሩ ከዚህ ስብሰባ ጎን ለጎን በአገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ የሚገኘውን የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር 70ኛ የምስረታ በዓልን በድምቀት አክብሯል።

የሆሳዕና ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች በአገር አቀፍ ደረጃ  ዘንድሮ ለ15ኛ ጊዜ እየተከበረ ያለውን አገር አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን በተለያዩ አዝናኝ እና አስተማሪ ...
13/12/2019

የሆሳዕና ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች በአገር አቀፍ ደረጃ ዘንድሮ ለ15ኛ ጊዜ እየተከበረ ያለውን አገር አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን በተለያዩ አዝናኝ እና አስተማሪ ዝግጅቶች እንዲሁም በፓናል ውይይት የኮሌጁ ኃላፊዎች በተገኙበት በኮሌጁ አዳራሽ በድምቀት ተከብሯል።

South Tvet Magazine
12/12/2019

South Tvet Magazine

የጉዞ ማስታወሻየሆሳዕና ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ ዲፓርትመንት ተጠሪዎች እና የአስተዳደር ሰራተኞች ለተሻለ ልምድ ልውውጥ በአሁን ሰዓት ወደ አዲስ አበባ ጉዞ እያደረጉ ይገኛሉ።
12/12/2019

የጉዞ ማስታወሻ
የሆሳዕና ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ ዲፓርትመንት ተጠሪዎች እና የአስተዳደር ሰራተኞች ለተሻለ ልምድ ልውውጥ በአሁን ሰዓት ወደ አዲስ አበባ ጉዞ እያደረጉ ይገኛሉ።

10/12/2019
የደቡብ ክልል ቴ/ሙ/ት/ስ ቢሮ ያዘጋጀው ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነረው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በዛሬው ዕለት ተጠናቀቀ። የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ የቀረቡ ሰነዶች የአመራሩን አቅምከመ...
07/12/2019

የደቡብ ክልል ቴ/ሙ/ት/ስ ቢሮ ያዘጋጀው ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነረው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በዛሬው ዕለት ተጠናቀቀ። የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ የቀረቡ ሰነዶች የአመራሩን አቅም
ከመገገንባት አንፃር ሚናው የጎላ እንደሆነ ተሳታፊዎች ገልፀዋል። በውይይቱ ማጠቃለያ ላይም የዘርፋ ኃላፊዎች ከተሳታፊ ለቀረቡ ጥያቄዎች ተገቢውን
ምላሽ በመስጠትና የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ የዕለቱ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ህዳር 27/2012 ዓ/ም መጠናቀቁ የቴ/ሙ/ት/ስልጠና
የቢሮው ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ገልፀዋል።

የክልሉ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ቢሮ ለዞንና ለልዩ ወረዳ ቴ/መ/ት/ስ መምሪያና ፅ/ቤት አመራርና ለዋና ሥራ ሂደት አስተባባሪዎች የግንዛቤማስጨበጫ መድረክ በሆሳዕና ከተማ እያካሄደ መ...
06/12/2019

የክልሉ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ቢሮ ለዞንና ለልዩ ወረዳ ቴ/መ/ት/ስ መምሪያና ፅ/ቤት አመራርና ለዋና ሥራ ሂደት አስተባባሪዎች የግንዛቤ
ማስጨበጫ መድረክ በሆሳዕና ከተማ እያካሄደ መሆኑን ገለፀ። ለሁለት ቀናት የሚቆየው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ የቴክኒክና ሙያ እስትራቴጂ ፣የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ትግበራ ፣የሥራ ግንኙነት ተግባር፣ የካውንስል አደረጃጀትና ኮማንድ ፖስትና ስለ ስርዓተ ፆታና ስለ HIV ADSና የሰው ኃይል አስተዳደር ላይ የመወያያ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት እንደሚደረግ
የቢሮው የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ገልፀዋል።

Welding Technology
06/12/2019

Welding Technology

የጀርምን መንግስት በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ   ድጋፍ አድርጓል፡፡በቅርቡ የጀርመን መንግስት በKFW አማካኝነት የትብብር ስልጠናውን ለማበረታታት የተለያዩ 29 ተሸከርካሪዎችን ...
05/12/2019

የጀርምን መንግስት በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ ድጋፍ አድርጓል፡፡
በቅርቡ የጀርመን መንግስት በKFW አማካኝነት የትብብር ስልጠናውን ለማበረታታት የተለያዩ 29 ተሸከርካሪዎችን ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

ኢትዮጵያ ለግብርና ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት የሚሆኑ ከሰላሳ በላይ ትራክተሮችና ማሽነሪዎች ድጋፍ ከጀርመን መንግስት አገኘች፡፡*************************************...
03/12/2019

ኢትዮጵያ ለግብርና ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት የሚሆኑ ከሰላሳ በላይ ትራክተሮችና ማሽነሪዎች ድጋፍ ከጀርመን መንግስት አገኘች፡፡
************************************************
በኢትዮጵያ እና በጀርመን መካከል በትምህርት መስክ ያለው ትብብር ከአርባ ዓመታት በላይ አስቆጥሯል፡፡ ጀርመን ለኢትዮጵያዊያን እስከ 3ኛ ዲግሪ የሚደርስ
የትምህርት እድል በመስጠት እያስተማረች ሲሆን በርካታ ቁጥር ያላቸው የጀርመን ፕሮፌሰሮችም በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች በማስተማር ላይ ይገኛሉ፡፡
ሀገራችንም ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠናን በአዲስ መልክ ስታዋቅር ሞዴል ያደረገችውም የጀርመንን የትምህርት ስርዓት ነው፡፡ ይህንኑ የሁለትዮሽ ግንኙነት የሚያጠናክር የትራክተሮች እና ማሽነሪዎች ድጋፍ ርክክብ በፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት ቅጥር ግቢ
ተካሂዷል፡፡ ርክክቡ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስትር፣ የጀርመን የኢኮኖሚ ትብብር
ሚንስትር፣ የጀርመን የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚንስትር፣ በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር እና ሌሎችም ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት
ተከናውኗል፡፡ ፕ/ር ሒሩት ወ/ማርያም በርክክብ ሥነሥርዓቱ ላይ እንደገለፁት ‹‹ጀርመን ወደ
ሀያ ለሚጠጉ ዓመታት የሀገራችንን የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ በቴክኒክና በፋይናንስ ስትደግፍ ቆይታለች፡፡ አሁን ደግሞ የትራክተሮችና ማሽነሪዎች ድጋፍ አድርገውልናል፡፡ እነዚህን ማሽነሪዎች መጠቀም ግብርናውን ዘመናዊና ምርታማ የሚያደርጉ ባለሙያዎችንና ቴክሽያኖችን ለማፍራት ያግዛል››፡፡ ሀገራዊ ለውጡን ለመደገፍም ያለውን ከፍተኛ ሚና በማስታወስ፡፡ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ የተደራጁ ወርክ ሾፖች የስልጠና
ቁሳቁሶች የሚጠይቅ በመሆኑ የተግባራዊ ስልጠናችን በሚፈለገው ደረጃ ተለውጧል ማለት አያስችልም ያሉት ፕ/ር ሒሩት ይህ ድጋፍ ክፍተቱን ለመሙላት ትልቅ ድርሻ እንደሚኖረው ያስረዳሉ፡፡ ከ80 በመቶ በላይ በግብርና የሚተዳደር ህዝብ ላላት ኢትዮጵያ ዘርፉን
ለማዘመን የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ወሳኝ መሆኑን የጠቀሱት ደግሞ የጀርመን የኢኮኖሚ ትብብር ሚንስትሩ ዶ/ር ገርል ሙለር ናቸው፡፡ የሀገራቸው ድጋፍም በዋናነት የኢትዮጵያን ግብርና ለመደገፍና ለማሳደግ ያለመ ነው ብለዋል፡፡ ድጋፉም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡ በመጨረሻም የኢንስቲትዩቱን በጀርመን መንግስት የቁሳቁስ ድጋፍ የተደራጁ የስልጠኛ ክፍሎችን ተዟዙረው ጎብኝተዋል፡፡

Address

Gombora, 3KM On Wolkite Road
Hossana
09HOSSANATVET

Telephone

+251465552680

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hossana Polytechnic college posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category