Outshine Academy Hawassa-አውትሻይን አካዳሚ ሀዋሳ

Outshine Academy Hawassa-አውትሻይን አካዳሚ ሀዋሳ Outshine Academy is privately owned school in Hawassa Ethiopia. It has 4 branches in the city.

Permanently closed.
ለመላው ሙስሊም የአውትሻይን አካዳሚ ቤተሰቦች እንኳን ለኢድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ!! 🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌መልካም በዓል!!
20/03/2026

ለመላው ሙስሊም የአውትሻይን አካዳሚ ቤተሰቦች እንኳን ለኢድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ!!
🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌
መልካም በዓል!!

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ አውትሻይን አካዳሚ በዓሉ የሰላም፣የደስታ፣የፍቅር፣የመተሳሰ...
07/01/2026

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ አውትሻይን አካዳሚ በዓሉ የሰላም፣የደስታ፣የፍቅር፣የመተሳሰብ፣የጨዋታ እናም ዘመድ ከዘመድ የሚጠያየቅበት ጥሩ እና ያማረ ጊዜን ከውድ ቤተሰቦቻችሁ ጋር እንድታሳልፉ መልካም ምኞታችንን ለመግለፅ እንወዳለን።

አውትሻይን አካዳሚ መልካም በዓል!!!!!

ላለፉት ዓመታት በፍቅር እና መተሳሰብ ስናከብረው የቆየነው የብሄር ብሄረሰቦች  በዓል በሀገሪቱ ህግ መሰረት  ዛሬ ህዳር 29/03/ 2018 ዓ.ም እለተ ሰኞ በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች ታስቦ ...
09/12/2025

ላለፉት ዓመታት በፍቅር እና መተሳሰብ ስናከብረው የቆየነው የብሄር ብሄረሰቦች በዓል በሀገሪቱ ህግ መሰረት ዛሬ ህዳር 29/03/ 2018 ዓ.ም እለተ ሰኞ በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች ታስቦ እና ተከብሮ ይውሏል።

ታዲያ እኛ አውትሻይን አካዳሚ እንደ አንድ ሀገር ወዳድ ትውልድ ማፍለቂያ ተቋም እንደመሆናችን እውቀት እና ስነ-ምግባርን በማስጨበጥ ውስጥ የሀገርን ፍቅር , ተስፋ, ክብር , ሀላፊነት እና አደራ ማስተማራችን ነገ በስስት የሚኖሩባትን ኢትዮጵያን ለመረከብ ያስችላቸው ዘንድ ነው።

ዛሬ የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን ስናከብር ለልጆቻችን የምንሰጠው የባህል፣የአኗኗር፣የአስተሳሰብ እና የቋንቋ ልዩነቷ ለአንድነቷ መሰረት ከመሆን ባለፈ ጉራማይሌያዊ የውበት ምስጢር ያደላት እንቁ የብዙ ብሄር ብሄረሰቦች መኖሪያ ሀገር እንዳለቻቸው በፍቅር እና መከባበር መኖር ምን ያህል ዋጋ እንዳለው በማሳየት በልዩነት ውስጥ ያለውን አብሮነት አጉልቶ በማንጸባረቅ ነው።

ልጆቻችን በተለያዩ ብሄሮች አልባሳት አሸብርቀው ትምህርታዊ እንዲሁም የተለያዩ የጥበብ ስራዎች አዝናኖትን ባዘለ መልኩ ደስ በሚል ሁኔታ በምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት ማክበር ተችሏል።

ዛሬ ለነበረን ቆይታ ከመምህራን እንዲሁም ሌሎች የተቋሙ ባለ ድርሻ አካላት ቀጥሎ ለውድ ወላጆች ተማሪዎቻችንን አምረው እና ደምቀው እንዲገኙ ስላረጉ የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

አውትሻይን አካዳሚ በአንድነቱ የሚኮራ ጉራማይልርያዊ ውበትን የሚያከብር እና የሚያንፀባርቅ ትውልድን እናፈራለን!!!!!!!

የትምህርት ዘርፉ ስብራት የቱ ጋር ነው? ክፍተቶችን በመለየትስ ምን አይነት መፍትሄዎችን ማምጣት ይጠበቃል? የሚሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ያስችል ዘንድ ትምህርት ሚኒስቴር "የመምህራን አቅም ማ...
20/10/2025

የትምህርት ዘርፉ ስብራት የቱ ጋር ነው? ክፍተቶችን በመለየትስ ምን አይነት መፍትሄዎችን ማምጣት ይጠበቃል? የሚሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ያስችል ዘንድ ትምህርት ሚኒስቴር "የመምህራን አቅም ማጎልበቻ ስልጠና የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ለሚከናወኑ ስራዎች አጋዥ ነው።" በሚል መፈክር በሁሉም የሀገራችን የትምህርት ተቋማት መምህራን የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑ ይታወቃል።

ይህም በመሆኑ እንደ አንድ የእንቁ ትውልድ መፍለቂያ ተቋም በዕውቀት የዳበረ በስነምግባር የጎለበተ ዕውቀተ ምሉዕ ሀገር ተረካቢ ለመፍጠር ትምህርት ወሳኙን ድርሻ እንደሚይዝ ማሳያ የሆነው ትምህርት ቤታችን
OUTSHINE ACADEMY

በብቁ ባለሙያዎች አጋዥነት የተቋሙ ከፍተኛ ባለስጣናት እንዲሁም በሶስቱም ቅርንጫፎች ስር የሚገኙ መምህራንን ጨምሮ ያሳተፈ ስልጠና ለሁለት ተከታታይ ቀናት
7/2/2018 እና 08/02/2018 አከናውኗል።

ስልጠናውም የትምህርት ጥራት ማምጣት የሚችሉ strategy ያተኮረ ሲሆን በዋና አጀንዳነት የመምህራንን አቅም ማጎልበት ነው። ይህም የትምህርት ይዘት እና የማስተማር ስነ-ዘዴን ይመለከታል። ስልጠናው በአዲሱ የስርአተ ትምህርት ይዘት ላይ በቂ ግንዛቤን የሚያስጨብጥ እንዲሁም የመማር ማስተማር ሂደቱን ጥሩ እና የተሳለጠ እንደሚያደርገው ስልጠናውን የወሰዱት መምህራን ገልፀዋል።

14/10/2025
14/10/2025

የዛሬ የሠንደቅዓላማ ቀን አከባበር
አውትሻይን_አካዳሚ ቁ-2

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

02/10/2025

Celebrating my 4th year on Facebook. Thank you for your continuing support. I could never have made it without you. 🙏🤗🎉

14/09/2025

ለት/ቤታችን የተማሪዎች ወላጆች በሙሉ
🌼🏵️🌼🏵️🌼🏵️🌼🏵️🌼🏵️🌼🏵️

እንኳን ለ2018 ዓ.ም ትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ እያልን ትምህርት የሚከፈትበትን ቀን በቴሌግራም ቻናላችን እንደምንገልፅ በነገርነው መሰረት ትምህርት ቤቱ የተለያዩ ግንባታዎች እና የማሻሻያ ስራዎችን እያካሄደ በመቆየቱ ቀሪ የፅዳት ስራዎችን ከፊታችን ባለው ሳምንት ስለሚያከናውን ትምህርት የሚከፈትበትን ቀን ለአንድ ሳምንት ያራዘምን መሆኑን እያሳወቅን በመዘግየታችን ይቅርታ እንጠይቃለን።
በመሆኑም የትምህርት ዘመኑ የመጀመሪያ ቀን በ12/01/2018 ዓ.ም መሆኑን በትህትና እንገልፃለን።

🌼🌼🌼 ውድ የአውትሻይን አካዳሚ ቤተሰቦች 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼መልካም አዲስ ዓመት 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼2018 ዓ.ም🌼🌼🌼🌼
10/09/2025

🌼🌼🌼 ውድ የአውትሻይን አካዳሚ ቤተሰቦች 🌼🌼🌼

🌼🌼🌼🌼መልካም አዲስ ዓመት 🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼2018 ዓ.ም🌼🌼🌼🌼

Address

Hawassa Next To Street Gebriel School
Hawassa

Telephone

+251911965083

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Outshine Academy Hawassa-አውትሻይን አካዳሚ ሀዋሳ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Outshine Academy Hawassa-አውትሻይን አካዳሚ ሀዋሳ:

Shortcuts

Share

Category