Union Academy

Call Website Contact the school

Union Academy A private school from KG - 12 found in Hawasa English Medium, Equipped with modern facilities!

12/09/2026

በርካቶች የዛሬ ማንነታቸውን የሰሩበት፣ ስብዕናቸውን የገነቡበት፣ ሀሳባቸው የተደመጠበት፣ በነፃነት ህልማቸውን የቀረፁበት ዩኒየን አካዳሚ። በ2019 የትምህርት ዘመን በራሳቸው የሚተማመኑ ፣ አቅማቸውን ለማሳደግ ፣ ዝንባሌያቸውን ለማዳበር ፣ ተሰጥዎአቸውን ለማውጣት የሚፈልጉ ተማሪዎችን ባሉት ቀሪ ውስን ቦታዎች ያለምንም ቅድመሁኔታ ለታላቅነት፣ ለአሸናፊነትና ለስኬት ሊያዘጋጃችሁ ይጋብዛል። እኔም ሆንኩ ጓደኞቼ አብራችሁን እንድትማሩ እንጋብዛለን።
ዩኒየን አካዳሚ በታላላቆቻችን መሰረት ላይ ቆመን የስኬት አሻራቸውን እናስቀጥላለን።

08/09/2026

እንኳን ለ2019 የትምህርት ዘመን አደረሳችሁ። ብዙዎችን ከህልማቸው ያገናኘው ዩኒየን አካዳሚ ከአፀደ ህፃናት እስከ 12ኛ ክፍል ምዝገባ አጠናቆ ውድ ተማሪዎቻችንን እየጠበቅን እንገኛለን። በቀሩት ጥቂት ቀናት አዲስ ተማሪዎችን እንድትቀላቀሉን እንጋብዛለን።

ይህ የተቋሙ ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል ነው።
04/09/2026

ይህ የተቋሙ ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል ነው።

A school located in HAWASSA KG -12

እንኳን ደስ አላችሁ
31/08/2026

እንኳን ደስ አላችሁ

የተከበራችሁ የዩኒየን ኮሌጅ የቦርድ አባላት፣ አስተዳደር ሰራተኞች፣ የተከበራችሁ የወላጆችና የክብር እንግዶች፣ እንዲሁም የዛሬው እለት ታላላቅ ባለታሪኮች—ውድ የ2018 ዓ.ም. ተመራቂ ተማሪዎ...
22/08/2026

የተከበራችሁ የዩኒየን ኮሌጅ የቦርድ አባላት፣ አስተዳደር ሰራተኞች፣ የተከበራችሁ የወላጆችና የክብር እንግዶች፣ እንዲሁም የዛሬው እለት ታላላቅ ባለታሪኮች—ውድ የ2018 ዓ.ም. ተመራቂ ተማሪዎቻችን፤ እንኳን ለዚህ የክብር እና የስኬት ቀን በሰላም አደረሳችሁ!በዛሬው እለት በዚህ አዳራሽ ውስጥ ተገኝተን የበርካታ ዓመታት ጥረት፣ ፅናት እና ትጋት ፍሬ ሲያፈራ በማየታችን ኮሌጃችን ታላቅ ደስታና ኩራት ይሰማዋል። ዩኒየን ኮሌጅ በርካታ ሺዎችን ከህልማቸው ያገናኝ፣ አንጋፋና ስመጥር ተቋም ነው፡፡ እናንተም የዚህ ታላቅ ኮሌጅ የታሪክ ተጋሪ በመሆናችሁ ኩራት ሊሰማችሁ ይገባል፡፡ ውድ ተመራቂዎች፤ ዛሬ በእጃችሁ የምትቀበሉት ዲግሪ ወይም ዲፕሎማ ምስክር ወረቀት ብቻ አይደለም። የዛሬው ምርቃታችሁ የትላንት ልፋታችሁ፣ የሌሊት እንቅልፍ ማጣት፣ የጥናት ድካም፣ የመታገስ እና የማሸነፍ ምልክታችሁ ነው። በዩኒየን ኮሌጅ ቆይታችሁ የቀሰማችሁት እውቀትና ክህሎት ለወደፊት ህይወታችሁ ጠንካራ መሰረት እንደሚሆን ሙሉ እምነት አለን። የወደድነውን ፣ የመረጥነውንና ያከበርነውን የትምህርት ስራ ተማሪዎቻችንን በሚያሳድግና በሚያበቃ መልኩ፣ በፍፁም ነፃነት፣ በተመረጡ ድንቅ መምህራን፣ በተደራጀና በተሙላ ሁኔታ በመስጠት ስናገለግላችሁ ቆይተን ዛሬ ለዚህ ክብር በቅታችኋል፡፡ እንኳን ደስ አላችሁ፡፡ አለም በየቀኑ በከፍተኛ ፍጥነት እየተለወጠች ነው። ዛሬ ወደ ስራው አለም ስትቀላቀሉ እውቀታችሁን ብቻ ሳይሆን ሙያዊ ስነ-ምግባራችሁን፣ የመሪነት ብቃታችሁን እና ችግር ፈቺነታችሁን ማሳየት ይጠበቅባችኋል። ኮሌጃችን ያስጨበጣችሁን እውቀት በመጠቀም በማህበረሰባችሁ እና በሀገራችን ላይ በጎ እና ዘላቂ ለውጥ እንደምታመጡ አንጠራጠርም። የሰው ልጅ ሀብቱ ትጋቱ ነው እንደሚባለው ሳይማር ያስተማራችሁን ማህበረሰብ በታማኝነት እንድታገለግሉ ፈጣሪ ይርዳችሁ፡፡የተከበራችሁ ወላጆች እና አሳዳጊዎች፤ ልጆቻችሁ ለዚህ ማዕረግ እንዲበቁ ላደረጋችሁት የማይተካ መስዋዕትነት፣ ላሳያችሁት ድጋፍ እና በኮሌጃችን ላይ ላኖራችሁት እምነት በራሴና በኮሌጁ ስም የላቀ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። የዛሬው ስኬት የጋራ ፍሬያችን ነው።ውድ የመምህራን እና የአስተዳደር አባላት፤ እነዚህን ወጣቶች ኮትኩታችሁ ለዛሬው የበቃ ማንነትና ክብር እንዲበቁ ላደረጋችሁት ያልተቆጠበ ድካም እና ሙያዊ አገልግሎት ምስጋናዬ የላቀ ነው።ተመራቂዎቻችን፤ መማር በምረቃ አይጠናቀቅም፤ ይልቁንም አዲስ የመማር እና የመበልፀግ ምዕራፍ ይጀመራል። የታመናችሁ፣ በትጋት የምታገለግሉ እና ለለውጥ ዝግጁ የሆናችሁ ዜጎች ሁኑ። በሄዳችሁበት ሁሉ የዩኒየን ኮሌጅ አምባሳደሮች መሆናችሁን አትርሱ። ስለሰጠናችሁ መልካም ነገር እየመሰከራችሁ፣ ያጎደልነውን እየሞላችሁ፣ የተሳሳተውን እያረማችሁ ለተተኪ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ገፅታችንን እንድትገነቡ የሙሉ ስልጣን አምባሳደሮቻችን መሆናችሁን እያሳወኩ በቀሪ ዘመናችሁ የአምላክ እገዛና ጥበቃ አይለያችሁ፡፡ በነበረን ቆይታ ሰለነበራችሁ በጎነት፣ ስላሳያችሁት መልካም ስነምግባር፣ ሰላከናወናችሁት አመርቂ አስተዋፅዎ፣ ስለሁሉም ነገር በድጋሚ አመሰግናለሁ፡፡ በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ! የወደፊት ህይወታችሁ በስኬት እና በበረከት የተሞላ ይሁን!
ኢዮብ ጽጌ

ዩኒየን ኮሌጅ በዲፕሎማ እና በመጀመሪያ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በደማቅ ሁኔታ ዛሬ ያስመርቃል።
22/08/2026

ዩኒየን ኮሌጅ በዲፕሎማ እና በመጀመሪያ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በደማቅ ሁኔታ ዛሬ ያስመርቃል።

20/08/2026

https://unionacademy.edu.et/
የትምህርት ቤታችን ድረገፅ።
የonline ፈተና መስጫና መጻሕፍት እና ሌሎች አጋዥ የመማሪያ ግብዓት ይገኛሉ። የፈተና መለማመጃ ፣ የሞባይል አፕሊኬሽን አውርደው ይጠቀሙ።

በጠራ ራዕይ፣ በታደሰ ቃልኪዳን፣ በተሟላ ብቁ የሰው ሀይል፣ በተደራጀ መልኩ ለ2019 የትምህርት ዘመን ተሰጥዖ ፣ እውቀትና ክህሎት ላይ መሰረት ያደረገ ጥራት ያለው የትምህርት አገልግሎት ለመ...
20/08/2026

በጠራ ራዕይ፣ በታደሰ ቃልኪዳን፣ በተሟላ ብቁ የሰው ሀይል፣ በተደራጀ መልኩ ለ2019 የትምህርት ዘመን ተሰጥዖ ፣ እውቀትና ክህሎት ላይ መሰረት ያደረገ ጥራት ያለው የትምህርት አገልግሎት ለመስጠት ምዝገባ እያጠናቀቅን ሲሆን ባሉን ውስን ቦታዎች ፈጥነው እንዲመዘገቡ እድል አመቻችተናል።
በምንወደውና በምትወዱት ዩኒየን አካዳሚ የምንሰራውን እንናገራለን፤ የተናገርነውን እንሰራለን።
ኑ! የመረጡንን የተመረጡ እናደርጋለን።

29/06/2026

በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለተፈታኞች የማይፈቀዱ ቁሳቁስ…

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከነገ ጀምሮ እስከ ሐምሌ 16 ቀን 2018 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ በ607 የፈተና ማዕከላት በስድስት ዙር ይሰጣል፡፡

ለፈተናው 306 ሺህ 456 የተፈጥሮ ሳይንስ እንዲሁም 257 ሺህ 45 የማህበራዊ ሳይንስ በድምሩ 563ሺህ 501 ተፈታኞች መመዝገባቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል፡፡

አገልግሎቱ ለፈተናው የሚያስፈልጉ ሁሉንም ዝግጅቶች ማጠናቀቁንና የፈተና አስፈጻሚዎችን ወደ ፈተና ማዕከላት ማሰማራቱን ገልጿል።

ተፈታኞች ወደ ፈተና ማዕከላት ሲቀርቡ የመፈተኛ መግቢያ ካርዳቸውን (አድሚሽን ካርድ)፣ የተማሪ ወይም ህጋዊ መታወቂያ፣ በፈተና አስተዳደሩ የተፈቀደ እስክሪብቶ እና ባዶ ወረቀት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

ሞባይል ስልክ፣ ስማርት ሰዓት፣ ብሉቱዝ፣ ጆሮ ማዳመጫ፣ ፍላሽ ዲስክ፣ ሜሞሪ ካርድ፣ የግል ላፕቶፕ ወይም ታብሌት እና ሌሎች ያልተፈቀዱ መሳሪያዎችን ይዞ ወደ ፈተና ክፍል መግባት አይፈቀድም።

ፈተናው በበይነ መረብ በ6 ዙር የሚሰጥ ሲሆን፣ በወረቀት የሚፈተኑ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከሐምሌ 1 እስከ 3፣ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ደግሞ ከሐምሌ 6 እስከ 8 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚፈተኑ ተገልጿል።

የትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም ተፈታኞች መልካም እድል እየተመኘ ፈተናውን በመረጋጋት፣ በሥነ ምግባርና በራስ መተማመን እንዲወስዱ ጥሪ አቅርቧል።

2018 የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ማስታወሻ
29/01/2026

2018 የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ማስታወሻ

Address

Hawassa
1138

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Union Academy posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Union Academy:

Shortcuts

Share

Category