12/03/2025
🗨️💬
“ በክርስቶስ ላላችሁ ለሁላችሁ ሰላም ይሁን። አሜን።” 1ኛ ጴጥ. 5፥14
በክርስቶስ የተወደዳችሁ ወንድሞች እና እኅቶቻችን የአጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤት አመራሮች፤የቀጠና አደረጃጀት ሰብሳቢዎች በሙሉ በየሰ/ት/ቤቶቻችሁ የመረጣችኋቸውን ወካዮቻችሁን የተሰጣችሁ የማሳወቂያ ቀን እስከዛሬ 03/07/2017 ዓ.ም {ዕተለ ረቡዕ} ስለሆነ በቀጠና ሰብሳቢዎቻችሁ አማካኝነት እንድታሳውቁ ስንል በጥብቅ እናሳውቃለን።
#ማሳሰቢያ፦ከቀጣዩ የቅዳሜ ጉባኤ በኋላ በአንድነቱ ጠቅላላ ጉባኤ ተወካይ ያላቸው አባል ሰ/ት/ቤቶች ብቻ በመዋቅሩ ታቅፈው የሚቀጥሉ ይሆናል።
#ስለሆነም ይኼንን ዕድል እንደቀላል እንዳታዩት አጽንዖት ለመስጠት እንወዳለን።
#ይኼንን ዕድል መጠቀም ለማትፈልጉ ሰ/ት/ቤቶች አንድነቱ ሓላፊነት የማይወስድ መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን።
“እግዚአብሔር ይማረን ይባርከንም፥ ፊቱንም በላያችን ያብራ፤” መዝ. 67፥1
የአዘዞ ወረዳ ቤተክህነት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መጋቢት ፫,፳፻፲፯ ዓ.ም
አዘዞ፣ጎንደር፣ኢትዮጵያ