Garda Marta Woreda Education Office

Garda Marta Woreda Education Office This is official page of Garda Marta Woreda Education Office

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በበይነ መረብ ብቻ ይሰጣልጋርዳ ማርታ፣ የካቲት 2፣ 2018 (ጋርዳ ማርታ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት) የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀ...
09/02/2026

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በበይነ መረብ ብቻ ይሰጣል

ጋርዳ ማርታ፣ የካቲት 2፣ 2018 (ጋርዳ ማርታ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት) የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተናን መቶ በመቶ በበይነ መረብ ለመስጠት የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ነው አለ የትምህርት ሚኒስቴር፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እንዳሉት÷ በተያዘው በጀት ዓመት የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ሙሉ በሙሉ በበይነ መረብ ይሰጣል፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት ፈተናው በወረቀትና በበይነ መረብ ሲሰጥ እንደረበር አንስተው÷ በዚህ ዓመት ፈተናውን በበይነ መረብ ብቻ ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

ለዚህም የተለያዩ ግብዓቶች ለክልሎች ድጋፍ እየተደረገ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ÷ በፈተና ጣቢያዎች በቂ የኢንተርኔት አቅርቦት እንዲኖር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በትብብር ይሰራል ብለዋል።

ክልሎች በዚህ ሒደት የሚያጋጥሙ ችግሮች እንዳይኖሩ በቂ ኮምፒዩተር፣ ኔትዎርክና አማራጭ የሀይል አቅርቦት እንዲኖር ልዩ ትኩረት ሰጥተው መዘጋጀት አለባቸው ነው ያሉት፡፡

ለተማሪዎች በቂ ሥልጠና መስጠት አስፈላጊ መሆኑንም ሚኒስትሩ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ መጠየቃቸውን ሚኒስቴሩ ለፋና ዲጂታል ገልጿል።

ትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ምዘናና ፈተና አስተዳደር ሥርዓት ውስጥ ያጋጠሙ ስብራቶችን ለማስቀረት የተለያዩ የሪፎርም ተግባራትን ቀርጾ ፈተናን ከስርቆትና ኩረጃ በፀዳ መልኩ ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል።

ባለፈው ዓመት የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናን በበይነ መረብ የወሰዱ ተማሪዎች ቁጥር 134 ሺህ 828 ሲሆን፤ ይህም ከአጠቃላይ ተፈታኞች አንጻር 23 ነጥብ 2 በመቶ ነበር።
ምንጭ Ministry of Education

በጋሞ ዞን ትምህርት መምሪያ የተረጋጋ የመማር ማስተማር ሂደትን ለማስቀጠልና የትምህርት ብክነትን ለመቀነስ አጋዥ ነው የተባለ ምክክር እየተካሄደ ነውጋርዳ ማርታ፦ ጥር 22/2018 ዓ.ም (ጋር...
30/01/2026

በጋሞ ዞን ትምህርት መምሪያ የተረጋጋ የመማር ማስተማር ሂደትን ለማስቀጠልና የትምህርት ብክነትን ለመቀነስ አጋዥ ነው የተባለ ምክክር እየተካሄደ ነው

ጋርዳ ማርታ፦ ጥር 22/2018 ዓ.ም (ጋርዳ ማርታ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት)

በጋሞ ዞን ትምህርት መምሪያ አዘጋጅነት የተረጋጋ የመማር ማስተማር ሂደትን ለማስቀጠልና የትምህርት ብክነትን ለመቀነስ አጋዥ ነው የተባለ የባለድርሻ አካላት ምክክር መድረክ በቦረዳ ወረዳ ዘፍኔ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በመድረኩ መክፈቻ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር አዲሱ አዳሙ ሀገራችን የገጠማትን የትምህርት ስብራትን ለመጠገን የተለያዩ ሥራዎችን በመሥራት ላይ መሆኗን ገልጸዋል።

ትምህርት የበርካታ አካላት ተሳትፎ የሚጠይቅ መሆኑን የተናገሩት ኃላፊው በተለይም የትምህርት ሴክተር ማናጅመንት አካላትና የመምህራን ሚና የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል ብለዋል።

ባለፉት ወራት በዞኑ ባሉ በአንዳንድ ት/ቤቶች በተለያዩ ምክንያቶች የትምህርት ብክነት ጎልቶ መታየቱን የጠቆሙት ዶ/ር አዲሱ አሁን ስላለፈው ጊዜ ከመናገር ይልቅ በቀሪ ወራት የተሻለ ነገር ተሠርቶ በዓመቱ መጨረሻ የተሻለ ውጤት ለማምጣት መረባረብ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የቦረዳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሸናፊ ሻሌ በበኩላቸው በቦረዳ ወረዳ ለሌሎች ወረዳዎች ተሞክሮ የሚሆኑ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

በትምህርት ዘርፍ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ኃላፊነት መወጣት እንዳለባቸው ያስገነዘቡት ዋና አስተዳዳሪው ትምህርት ላይ መሥራት የነገን ሀገር ዕጣ ፋንታ መወሰን በመሆኑ ልዩ ትኩረት ያስፈልጋል ብለዋል።

ለትምህርት ብክነት ምክንያት የሚሆኑ የተለያዩ ጉዳዮች ያሉ ቢሆንም ትውልድን የሚቀርጹ መምህራን ሁሌም ከመደበኛ ሥራቸው መነቀል እንደሌለባቸውም አስተዳዳሪው አስገንዝበዋል።

በአሁኑ ሰዓትም ለውይይት የመነሻ ሰነድ በመቅረብ ላይ ያለ ሲሆን ቀጥሎም ሰፋ ያለ ውይይት እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

በመድረኩ የጋሞ ዞን ትምህርት መምሪያ ማናጅመንት አባላት፣ የጋሞ ዞን መምህራን ማህበር ሥራ አስፈፃሚ አካላት፣ የሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች የትምህርት ጽ/ቤቶች ኃላፊዎች እና የሁሉም መዋቅር የመምህራን ማህበር ሰብሳቢዎች ተገኝተዋል።

በመላኩ ማሞ

 :-በጋርዳ ማርታ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በተለያዩ ትምህርት ቤቶች በ2018 ዓ.ም ትምህርት ዘሜን 8ኛ ክፍል ድጋሚ ለመፈተን ተማሪዎችን ተቀብሎ እየመዘገበ መሆኑ ይታወቃል። ይሁን እንጂ ከዚ...
28/01/2026

:-
በጋርዳ ማርታ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በተለያዩ ትምህርት ቤቶች በ2018 ዓ.ም ትምህርት ዘሜን 8ኛ ክፍል ድጋሚ ለመፈተን ተማሪዎችን ተቀብሎ እየመዘገበ መሆኑ ይታወቃል። ይሁን እንጂ ከዚህ በታች በዝርዝር የቀረባችሁ ተማሪዎች ፋይዳ መታወቂያ ባለመኖራችሁ ምክንያት ጽ/ቤቱ መረጃውን በኦንላይን ሞልቶ ለሚመለከተው ክፍል ሪፖርት ለመላክ ተቸግሯል።
ስለሆነም ባላችሁበት በመሆን ፋይዳ መታወቂያ (Pin) መረጃ በመላክ እንድትመዘገቡ ጽ/ቤቱ አጥብቆ ያሳውቃል።
የት/ቤት ር/መ/ራን፣ሱ/ሮች፣መ/ራን፣ተማሪዎችና ባለድርሻ አካላት መረጃ በማድረስ ትብብር እንድታደርጉም ጭምር ያሳውቃል።
ጥር 20/2018 ዓ.ም
ጋርዳ ማርታ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት
ጎጋሌ

ጋርዳ ማርታ ታህሳስ 4/2018 ዓ.ም:- የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ከአርባ ምንጭ ትምህርት ኮሌጅ የቦርድ አመራር እና ማናጅመንት አባላት ጋር የትውውቅ እና የአፈጻጸም ግምገማዊ ውይይት ...
14/12/2025

ጋርዳ ማርታ ታህሳስ 4/2018 ዓ.ም:- የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ከአርባ ምንጭ ትምህርት ኮሌጅ የቦርድ አመራር እና ማናጅመንት አባላት ጋር የትውውቅ እና የአፈጻጸም ግምገማዊ ውይይት አደረጉ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ በክቡር አቶ አብዮት ደምሴ የተመራው ቡድን ከኮሌጁ ቦርድ አመራርና ማኔጅመንት አባላት ጋር ታኅሳስ 4/2018 ዓ/ም የትውውቅ እና የአፈጻጸም ግምገማዊ ውይይት አካሂደዋል፡፡ በዕለቱም እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን ዞረው ምልከታ አድርጓል፡፡

ለውይይትና ግምገማ መነሻ የሚሆኑ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ቅድሚያ እንዲሠጣቸው በቦርድ አቅጣጫ የተቀመጠላቸውን የአፈጻጸም ሪፖርት የኮሌጁ ዋና ዲን ዶ/ር እንግዳ እንድሪያስ ያቀረቡ ሲሆን በተነሱ ሀሳቦች ላይ ተጨማሪ ውይይት በማድረግ በአጭር ጊዜ ውስጥ በሂደት ላይ ያሉ ሥራዎች እንዲጠናቀቁ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ አብዮት ደምሴ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት በቦርዱ ፈጥነው እንዲሰሩ አቅጣጫ የተቀመጠላቸው ስራዎች በቂ ትኩረት እንዲሰጣቸው አሳስበዋል፡፡

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ም/ኃላፊና የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ኃላፊ ክቡር አቶ ኢሳያስ እንድሪያስ እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ም/ኃላፊና የአስተዳደርና ፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ እንዲሁም የኮሌጁ ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ታምሩ ቡራይና ኮሌጁ ለትምህርት ጥራት እየሰጠ ያለውን ጥረት አድንቀው በቀጣይም እየታየ ያለው ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡

እንደክልል የበጀት ውስንነት እንዳለ የገለጹት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ም/ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ምህረቱ አሰፋ በበኩላቸው ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮች ተለይተው ደረጃ በደረጃ ሊሰሩ እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡

በመጨረሻም ኮሌጁን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ በውይይቱ የተገኙ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡ ቃል ገብተዋል፡፡

ምንጭ:-AMCE ነው።

በአርባምንጭ ከተማ ከ23 ሚሊዮን ብር በላይ የተገነባው የጋሽ አሰፋ ጫቦ መታሰቢያ ፩ኛና መካከለኛ ደረጃ  ትምህርት ቤት ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ ጋርዳ ማርታ ፣ታህሳስ 2/2018 ዓ/ም...
11/12/2025

በአርባምንጭ ከተማ ከ23 ሚሊዮን ብር በላይ የተገነባው የጋሽ አሰፋ ጫቦ መታሰቢያ ፩ኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

ጋርዳ ማርታ ፣ታህሳስ 2/2018 ዓ/ም (ጋርዳ ማርታ ትምህርት ጽ/ቤት)

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የደቡብ ክልል ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ተማሪዎች የነገ ሀገር ተረካቢ በመሆናቸው መንግስት በትምህርት ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

በተማሪዎች ውጤት ላይ ለውጥ እንዲመጣ አስፈላጊ ማቴሪያሎችን ለማሟላት የሁሉ ሰው ርብርብ ይጠይቃል ሲሉም ተናግረዋል።

አድስ የሚገነባው G+2 ህንጻ ደረጀውና ጥራቱ የተጠበቀ ሊሆን እንደሚገባ ተናግረው ህንጻው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንዲችል ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ በመውጣት ከመንግሥት ጎን ሊቆም ይገባል ብለዋል።

የአርባምንጭ ከተማ ከንቲባ ዶ/ር መስፍን መንዛ የከተማው አስተዳደሩ በትምህርት፣በጤናና በሌሎች ማህበራዊ ትስስር የሚያጎለብቱና ኢኮኖሚያዊ እድገትን የሚያሳልጡ የሴክተር የመሠረተ ልማት ግንባታና የማስፋፊያ ሥራዎችን በትኩረት እየሰራ ሲሆን በርካታ አበረታች ውጤቶችም ተመዝግበዋል ሲሉ ገልጸዋል።

የተማሪ ጥምርታ ለማሻሻል ተብለው በከተማው በርካታ ማስፋፊያዎች እየተሰሩ እንዳሉም ከንቲባው ተናግረዋል።

በከተማ የተጀመሩ በርካታ የልማት ሥራዎች እንዳሉ ገልጸው የከተማውን ዕድገት ለማፋጠን በገቢ አሰባሰብ ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በከተማው ላይ የሚሰሩ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ለሀገር ባለውለታ በሆኑ ሰዎች በስማቸው ስሰየም እጅግ የሚያስደስት ነው ሲሉም ገልጸዋል።

የጋሞ ዞን ዋና አስተዳደር ዶ/ር ደምስ አድማሱ ለትምህርት ቤቱ ግንባታ አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላትን አመስግነው አሁን ለተገነባው ት/ቤት ለ5 ክፍሎች የሚሆን የተማሪ መቀመጫ ወንበር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።

የአቶ አሰፋ ጫቦ መታሰቢያ 1ኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት 2 ብሎክና 10 ክፍሎችን የያዜ ሲሆን ከ600 በላይ ተማሪዎችን ማስተናገድ እንደሚችል ተገልጿል።

በመርሃግብሩ የተገኙት የጋሼ አሰፋ ጫቦ ቤተሰቦች ት/ቤቱ በጋሽ አሰፋ ጫቦ ስም በመሰየሙ እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው ይህንን ያስተባበሩ አካላትን አመስግነዋል።

በመጨረሻም በት/ቤቱ ግንባታ የላቀ አስተዋጽኦ ላደረጉት አካላት ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።

አስደሳች_ዜና_ለጋርዳ_ማርታ_ወረዳ በ2018 ትምህርት ዘመን በግብርናው ዘርፍ በተለያዩ ትምህርት ዓይነት ከዞኑ በመጣው ኮታ መሠረት ተወዳድሮ በፈተና ያለፉ ተማሪዎችና የሚማሩበት ኮሌጅ ምደባ ...
06/12/2025

አስደሳች_ዜና_ለጋርዳ_ማርታ_ወረዳ

በ2018 ትምህርት ዘመን በግብርናው ዘርፍ በተለያዩ ትምህርት ዓይነት ከዞኑ በመጣው ኮታ መሠረት ተወዳድሮ በፈተና ያለፉ ተማሪዎችና የሚማሩበት ኮሌጅ ምደባ ይፋ ሆኗል።
በዚህም መሠረት:

1) ተማሪ አረጋሽ አበራ ➡️ ተፈጥሮ ➡️ አገርፋ ኮሌጅ
2) ተማሪ መርድክዮስ ማርትዛ ➡️ተፈጥሮ ➡️አገርፋ ኮሌጅ
3) ተማሪ ጌታሁን ገዛሃኝ ➡️ መስኖ ➡️ አገርፋ ኮሌጅ
4) ተማሪ አድማሱ ጌታቸው ➡️ መስኖ ➡️አገርፋ ኮሌጅ
5) ተማሪ ትዝታ ፊልሞን ➡️ ሰብል ➡️ አገርፋ ኮሌጅ
6) ተማሪ ጠብቀው ጣሰው ➡️ ሰብል ➡️ አገርፋ ኮሌጅ
7) ተማሪ ሄርና ሄጳ ➡️እርባታ ➡️አገርፋ ኮሌጅ
8) ተማሪ ደመቀች ሳፋለ ➡️ ሰብል ልማት ➡️ ጋዋኔ ግ/ቴ/ኮሌጅ
9) ተማሪ ወካዩ ምከለ ➡️ እርባታ ➡️ ጋዋኔ ግ/ኮሌጅ
10) ተማሪ መላኩ ሞሶሎ ➡️ መካናይዜሽን ➡️ አርዳይታ ኮሌጅ
ተማሪዎችንና የተማሪ ቤተሰቦች እንኳን ደስ ያላችሁ!
እንኳን ደስ አላችሁ!!

በወረዳችን ውስጥ ያላችሁ ሁሉም የትምህርት ቤት አመራሮች ማለትም ሱ/ሮች፣ር/መ/ራን፣ም/ር/መ/ራን እንድሁም መ/ራን ተግባሩን በጥንቃቄ እንድትፈፅሙና አፈፃፀሙን ለጽ/ቤታችን እንድታሳውቁ ይሁን...
23/11/2025

በወረዳችን ውስጥ ያላችሁ ሁሉም የትምህርት ቤት አመራሮች ማለትም ሱ/ሮች፣ር/መ/ራን፣ም/ር/መ/ራን እንድሁም መ/ራን ተግባሩን በጥንቃቄ እንድትፈፅሙና አፈፃፀሙን ለጽ/ቤታችን እንድታሳውቁ ይሁን።

ሴት ተማሪዎች አርቴፊሻል ነገር ማድረግ አይችሉም!📌ሴት ተማሪዎች የጥፍር፣ የፀጉርና የከንፈር ቀለም መቀባት፣ ቅንድብ መቀንደብና መኳኳል፣ አላስፈላጊ ጌጣ ጌጦችን አድርጎ ወደ ትምህርት ቤት መ...
20/11/2025

ሴት ተማሪዎች አርቴፊሻል ነገር ማድረግ አይችሉም!

📌ሴት ተማሪዎች የጥፍር፣ የፀጉርና የከንፈር ቀለም መቀባት፣ ቅንድብ መቀንደብና መኳኳል፣ አላስፈላጊ ጌጣ ጌጦችን አድርጎ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ የሚከለክል መመሪያ ትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጀ፡፡

| ትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎችን ሥነ ምግባር ለመቆጣጠር ያዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ማንኛውም ተማሪዎች ከተፈጥሮ ጸጉራቸው በስተቀር አርቴፊሻል ፀጉር መቀጠል አይችሉም ተብሏል፡፡

ከዚህ ባለፈም በትምህርት ቤት ውስጥ አላስፈላጊ የሆኑ የኢትዮጵያዊነት ባህልን የማይገልፁ በዓላት በተለይም እንደ ክሬዚ ዴይ፣ ኦልድ ዴይ፣ ቤቢ ዴይ፣ ቶማቶ ዴይ፣ ከለር ዴይ፣ ቫላንታይን ዴይ እና ሌሎችም የበዓል ቀናቶች ተብለው የሚከበሩ በዓላት ማክበር በመመሪያው ተከልክሏል፡፡

በትምህርት ቤት የደንብ ልብስ በተገቢ መንገድ መልሰብ ሲል ባወጣው መመሪያ ስር ሴቶች ጉርድ ቀሚስ ከባት በታች የሆነ ቁመት ያለው ለብሶ መገኘት አለባቸው ተብሏል፡፡

ከደንብ ልብስ ውጪ ቢሆን ከአካባቢው ባህል ጋር የማይቃረን አለባበስ መልበስ ይጠበቅባቸዋል ይላል ረቂቅ መመሪያው፡፡

ትምህርት ቤት ውስጥ መፈፀም የተከለከሉ ድርጊቶች ብሎ ከዘረዘራቸው መካከል ደግሞ የትምህርት ቤቱን መምህራን፣ የትምህርት አመራር፣ ሠራተኞችና ሌሎች የትምህርት ማህበረሰብ አካላትን መዝለፍ፣ መስደብ፣ ማንቋሸሽና አካላዊ ጥቃት መፈጸም ቅጣት የሚያስከትል ተግባር ነው ተብሏል፡፡

ተንቀሳቃሽ ስልክ ወይም ሞባይል እና የሙዚቃ ማዳመጫ መሣሪያዎችን ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ይዞ መገኘት ረቂቅ መመሪያው ከልክሏል፡፡

በቃል፣ በምልክትም ሆነ በጽሑፍ ፀያፍ ነገሮችን መግለፅ፤ ጨዋነት የጎደላቸውን እንዲሁም ሐይማኖታዊና ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን ምስሎችና ጽሑፎች በትምህርት ቤት ውስጥ ይዞ መገኘትና ማሰራጨት አይፈቀድም፡፡

በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ የማንኛውንም ዓይነት የኃይማኖት አምልኮ ሥርዓትና የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን ማካሄድ ይከለክላል፡፡

ማንኛውም ተማሪ አገራዊ እሴት ያልሆኑና መጤ የሆኑ ነገሮችን በሰውነት ላይ ምልክት ማድረግ፤ ከአገራዊ እሴት ጋር የሚቃረኑ አሉታዊ መጤ ምልክቶችን በሰውነት ላይ መነቀስ፣ ማሳየት፣ ማድረግ፣ መጠቀም ፍፁም የተከለከለ ነው ብሏል ረቂቅ መመሪያው፡፡

ከ9 እስከ 12ተኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች አንድ ተማሪ በሥነ-ምግባር ጉድለት እጅ ከፍንጅ ከተያዘና የመማር ማስተማሩን ሂደት የሚያውክ ሆኖ ከተገኘ ውሳኔ እስኪሰጠው ከትምህርት ቤት ሊታገድ እንደሚችልም በመመሪያው ሰፍሯል፡፡

ተማሪዎች ተደጋጋሚ ጥፋት አጥፍተው ሲገኙ በተለይም ከ7 እስከ 12ተኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች እስከ 1 ዓመት ድረስ እንደ ጥፋቱ መጠን ታይቶ ከትምህርት ሊታገዱ ይችላልም ሲል ረቂቅ መመርያው አስቀምጧል፡፡

በሌላ በኩል በትምህርት ቤቶችና አካባቢ የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ለሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበ ረቂቅ ደንብ ተሰናድቷል፡፡

በዚህ ረቂቅ ደንብ ትምባሆ(ሲጋራ፣ ሺሻ)፣ ጫት፣ አልኮል የናርኮቲክ እና ሳይኮትሮፒክ ዝርያ ያላቸው አደገኛ ህገ ወጥ መድኃኒቶች እና ሱስ አስያዥ ዕፆች ትምህርት ቤት አካባቢ መሸጥም ሆነ ይዞ መገኘትን ይከለክላል።

የአልኮል መሸጫ እና ማከፋፈያ ቤቶች፣ የሲጋራ መሻጫ ሱቆች፣ ሺሻ ቤቶች፣ ጫት መሸጫና መቃሚያ ቤቶች፣ ጭፈራ ቤቶች፤ ቁማር ቤቶች፤ የእንግዳ ማረፊያ ቤቶች እና የሰውነት መታሻ ወይም ማሳጅ ቤቶች በትምህርት ቤቶች በ500 ሜትር ርቀት ውስጥ መክፈት አይቻልም፡፡

ፊልም ማጫዎቻ ቤቶች፣ ፕሌይ ስቴሽን ቤቶች፣ ዲ.ኤስ.ቲቪ ቤቶች፣ ከረንቡላ፣ ፑል፣ ጆተኒ፣ ቢንጎ እና የስፖርት ቁማር መጫወቻ ቤቶችም በትምህርት ቤት አቅራቢያ መክፈትን ከልክሏል ሲል ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል።

የጋርዳ ማርታ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት "በሰቆጣ ቃል ኪዳን" ፕሮግራም የተሰራ የሴት ተማሪዎች ንፅህና መጠበቂያ ክፍል እና በምገባ ፕሮግራም ለታቀፉ ትምህርት ቤቶች የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገጋርዳ...
13/11/2025

የጋርዳ ማርታ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት "በሰቆጣ ቃል ኪዳን" ፕሮግራም የተሰራ የሴት ተማሪዎች ንፅህና መጠበቂያ ክፍል እና በምገባ ፕሮግራም ለታቀፉ ትምህርት ቤቶች የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

ጋርዳ ማርታ፣ ህዳር 4፣2018፣ (ጋርዳ ማርታ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት) ፣

በመርሐግብሩ ላይ የተገኙት የጋርዳ ማርታ ወረዳ የዋና አስተዳዳሪ ልዩ አማካሪ አቶ ምኞት ማቴዎስ "የሰቆጣ ቃል ኪዳን" ዋና ዓላማ በህጻናት ላይ የሚታየውን የመቀንጨር ችግር ማስወገድ መሆኑን ገልጸው ይህንንም ለማሳካት እንደ ትምህርት ተቋም የተማሪዎችን ሥነ-ምግብ፣ ጤና እና የትምህርት ጥራት ማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተሾመ ታመነህ በ"ሰቆጣ ቃል ኪዳን" ፕሮግራም በበጀት ዓመቱ የተለያዩ ተግባራትን ጽ/ቤቱ እንዳከናወነ ጠቁመው በተጨማሪም የተማሪዎችን ሥነ-ምግብ እና ንጽህና ለማሻሻል በወረዳው በጎጋሌ ፩ኛ ደረጃ ት/ቤት የሴት ተማሪዎች ንፅህና መጠበቂያ ክፍል እንዲሁም በምገባ ፕሮግራም ለታቀፉ ትምህርት ቤቶች የቁሳቁስ ድጋፍ ጽ/ቤቱ ማድረጉን ገልጸዋል።

መርሐግብሩ የጋርዳ ማርታ ወረዳ የዋና አስተዳዳሪ ልዩ አማካሪ አቶ ምኞት ማቴዎስ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተከናውኗል።

Gamo Zone Garda Marta Woreda Education Office

ለትምህርት ፈላጊዎች የወጣ ማስታወቂያጋሞ ዞን ጋርዳ ማርታ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም በቅድመ አንደኛና በድፕሎማ መርሀ-ግብር ትምህርት ፈላጊዎችን አወዳድሮ መላክ ይፈልጋል።በዚህም...
04/11/2025

ለትምህርት ፈላጊዎች የወጣ ማስታወቂያ
ጋሞ ዞን ጋርዳ ማርታ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም በቅድመ አንደኛና በድፕሎማ መርሀ-ግብር ትምህርት ፈላጊዎችን አወዳድሮ መላክ ይፈልጋል።
በዚህም መሠረት ከዚህ በታች በቅድመ ሥራ ሥልጠናና ዕጩ መምህራን ምልመላና መረጣ መስፈርት ይፋ አድርገዋል።
ስለሆነም በተገለፀው መስፈርት መሠረት በጋርዳ ማርታ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ላይ በመገኘት እንድትመዘግቡ ያሳውቃል።
መልካም ዕድል ለሁሉም ተወዳዳሪዎች እንድሆንም ይመኛል።
ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም
ጋ/ማ/ወ/ት/ጽ/ቤት

የማጠናከሪያ ትምህር በዕቅድና በትኩረት እንዲመራ ትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ               -------------------- // --------------------‎(ጥቅምት 09/2018...
19/10/2025

የማጠናከሪያ ትምህር በዕቅድና በትኩረት እንዲመራ ትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ
-------------------- // --------------------

‎(ጥቅምት 09/2018 ዓ.ም) የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት አየለች እሸቴ ከክልልና ከከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በበይነ መረብ ውይይት ባደረጉበት ወቅት እንደገለጹት በአጠቃላይ ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ በተለይም ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርትን በዕቅድና በትኩረት እንዲሰራ አሳስበዋል።

የተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ መምህራን፣ የትምህርት ቤት አመራሮች፣ ወላጆች እንዲሁም የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተማሪዎች ጊዚያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ ከወዲሁ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚጠበቅባቸው ክብርት ወ/ሮ አየለች አስገንዝበዋል።

‎የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች በበኩላቸው የማጠናከሪያ ትምህርት ለተማሪዎች ውጤት መሻሻል ጠቀሜታው የላቀ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።


‎የትምህርት ፕሮግራሞች ጥራትና መሻሻል መሪ ስራ አስፈጻሚ ዩሀንስ ወጋሶ(ዶ/ር) የማጠናከሪያ ትምህርትን በተመለከተ መነሻ ስትራቴጂ እቅድ ያቀረቡ ሲሆን የተያዘው ግብ እንዲሳካ ከወዲሁ የዕቅድ ክትትልና ድጋፍ ሥራዎች ሊጠናከሩ ይገባል ብለዋል።


‎በበይነ-መረብ በተደረገው በዚሁ ውይይት ላይ የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችን ፣ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) እና ሌሎችም የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

Address

Garda Marta
Gimbichu
EDU.COM

Opening Hours

Monday 02:30 - 11:30
Tuesday 02:30 - 11:30
Wednesday 02:30 - 11:30
Thursday 02:30 - 11:30
Friday 02:30 - 11:30

Telephone

+251926404684

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Garda Marta Woreda Education Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category