Guasa Industrial Business-GIB-s.c

Guasa Industrial Business-GIB-s.c Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Guasa Industrial Business-GIB-s.c, Educational Research Center, Addis Ababa, Ethiopia . P. o. box, Gewasa.

01/05/2026
11/04/2026

25/08/2018 እንዳይረሳ

07/04/2026
27/03/2026

https://ee.kobotoolbox.org/x/2jxyxUn1 ይህንን መጠይቅ እንድትሞሉልን በአክብሮት እንጠይቃለን።

Queued records, except those marked as draft , are uploaded automatically, in the background, every 5 minutes when the web page is open and an Internet connection is available.

የ   ውልደት እና ቀደምትነት ከዘመኑ ቀድመው የነቁት የመንዝ ግለሰቦች በ 1953 አመተ ምህረት አዲስ አበባ   የመንዝ መረዳጃ እድር ብለው በጥቂት ሰዎች መሰረቱት ።በዚህን ወቅት ለኢንደለስ...
20/03/2026

የ ውልደት እና ቀደምትነት

ከዘመኑ ቀድመው የነቁት የመንዝ ግለሰቦች በ 1953 አመተ ምህረት አዲስ አበባ የመንዝ መረዳጃ እድር ብለው በጥቂት ሰዎች መሰረቱት ።

በዚህን ወቅት ለኢንደለስትሪ ልማት በሚል 20,000 ካሬ ሜትር መሬት ከንጉሱ ተሰጥቶት ነበር ። ለ25 አመታትም ግብር በመክፈል ፣ ቤቶችን በመስራት በይዞታነት ተጠቅሞ ነበር ።

ከዚያም በ 1959 ራሱን በማሻሻል ፣ አባላቶችን በማሳደግ ወደ የመንዝና ግሼ ትራንስፖርት ና መንገድ ስራ ድርጅት በማለት ተደራጀ ።

በወቅቱ አቶ የተባሉ ግለሰብን መኪና በመከራየት ከአዲስ አበባ ሞላሌ ፣ መሀል ሜዳ እና ግሼ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ጀመረ ።

በ1961 አመት ምህረት ደግሞ አቶ የተባሉ ግለሰብን መኪና በመከራየት የበለጠ ማህበረሰቡን ማገልገል ጀመረ ።

በ1965 ስሙን የትራንስፖርት እና መንገድ ስራዎች አክሲዮን ማህበር ወደሚል በማስተካከል በሰፊው ለመስራት ዝግጅቱን አጠናቆ ሲደራጅ ፣ የመንግስት ለውጥ በመምጣቱ ባሰበው ልክ መቀጠል አልቻለም ነበር ።

የደርግ መንግስት መምጣቱን ተከትሎ እንደገና የመንዝና ግሼ አውራጃ ትራንስፖርት ማህበር በሚል በመንዝ የትራንስፖርት ስራውን ጀመረ ።

በወቅቱ የንጉሱን መውደቅ ተከትሎ በመንዝ ደርግን በመቃወም ከፍተኛ ጦርነት ተከሰተ ስለዚህ ጦርነት ( በሌላ ) ርእስ እመጣለሁ ።

ይህንን ተከትሎ ማህበሩን ለማጠናከር እና የትራንስፖርት ክፍተቱን ለመጠቀም ፣ በመጀመሪያ ከአካባቢው ነጋዴዎች ገንዘብ በመሰብሰብ ነበር የተጠናከረው ፣ ሆኖም እየቆየ የነጋዴዎች ፍላጎት ሲቀንስ ማህበረሰቡ ድርጅቱን ወደ ራሱ ለመግዛት ተገዷል ።

#ከዚያስ ? የሚለውን ይዤ እመለሳለሁ ፣ ከ 1970 በሗላ ምን ተፈጠረ ? ድርጅቱ ምን ገጠመው ፣ እድገቱ፣ ውድቀቱ ፣ መነሳቱ ወዘተ ይቀጥላል

Yitina Gebre Mamo

Erkyihun Desalegn

Aytenew Sidlele

Shewamene Tesfaye

Daniel Asaye Teshome

Tesfaye Mengistu Yirga

Giŕefe Getañeh

Aki Man Z Menz

Talbachew Bekele

07/03/2026

ኑ ነጋችንን በጋራ እንገንባ!!!
ዛሬ ለደረስንበት ደረጃ ትላንት አባት እናቶቻችን ውድ ዋጋን ከፍለዋል። ያ የተከፈለ ዋጋ እኛ ቢያንስ እነሡ ከነበሩበት ዘመን "በተሻለ ደረጃ" እንድንገኝ መሠረት ጥሏል። ያ የነሡ ዘመን ልክ እንዳሁኑ በደቂቃዎች ሽርፍራፊ በመገናኘት ሀሳብ ለሀሣብ መለዋወጥ የማይቻልበት: እንኳን ስልክ ደብዳቤ እንኳን ባልነበረበት በዚያ የመረጃ "ጨለማ" ዘመን አባቶቻችን የመንዝን ችግር ለነገስታቱ ለማስረዳት ስንቃቸውን በአህያ ጭነው አቅም ያለው በበቅሎ አቅም የሌለው በእግሩ አስከመናገሻ ከተማ ድረስ ለበርካታ ቀናት ተጉዘው በአካባቢው የትምህርት ተቋማት የጤና ተቋማት እንዲሁም ሌሎች የልማት ተቋማት እንዲከፈቱ ብርቱ ትግልን አድርገዋል። እነሱ በዘመናቸው የትምህርት የጤና እንዲሁም የመንገድ መሠረተልማት እና የትራንስፓርት ችግር ወርቅ በእሳት እንደሚፈተነው ፈትኗቸዋል። ወደኋላ የአባቶቻችንን ዘመን መለስብለን ላፍታ ብናስበዉ እውነት ምን ያልፈተናቸው ነገር ይኖር? ትምህርት አልፈተናቸው ይሆን? በቀደመው ዘመን መንዝ ላይ ዘመናዊ ት/ቤት ባልነበረበት ዘመን እድል የገጠመው አዲስ አበባ ከቤተሰብ እርቆ ካልሆነም አብነት ትምህርት በሚማሩበት በዚያ ዘመን በነበረው የትራንስፓርት ችግር ተማሪው ቶሎ ቶሎ ከቤተሰቡ የሚገናኝበት ዘዴ ስላልነበረ
" ተማሪ በሞተ በሰባት አመቱ
ተምሮ ይመጣል ትላለች እናቱ" እየተባለ በስነቃል የሚነገርበት ያ እናት የልጇን መሞት እንኳን መርዶ የማትሰማበት የጭንቅ ዘመን::
# በዚያ የመኪና መንገድም ሆነ መኪና በሌለበት ዘመን ሩቅ ሀገር ያሉ ወገኖቻቸውን ለመጠየቅ ስንቃቸውን በአገልግል ውሃቸውን በቅል ይዘው ለሳምንታትና ለወራት ካሰቡበት ለመድረስ በባዶ አግራቸው ሲባክኑ የነበሩት አባቶቻቸን
# እኒያ አንድም የጤና ተቋም ባልነበረበት ዘመን በበሽታ የተሰቃዩት በወረርሽን የተቆሉት መድሐኒትን ከተፈጥሮ እጽዋትና ማእድናት በመቀመም ህዝባቸውን ለመታደግ የማሰኑት
እኒያ በኔ በአላዋቂው ከንቱ ሰው ተዘርዝረው በማያልቁ ይልቁንም በእድሜ ቀደም ያሉት በሰላ ብእራቸው ከትበው ለመጭው ትውልድ ቢያስቀምጧቸው ትልቅ ትምህርት በሚሰጡ መልከ ብዙ ችግሮች የተፈተኑ የመንዝ አባቶች ለፈተናዎቹ እጅ ሳይ ሰጡ ለችግሮቻቸውም ሳይንበረከኩ ችግሮቻቸውን የሚፈቱበትን ብልሐት ከዚያው ከችግሩ መካከል እየመዘዙ ለአሁኑ ትውልድ ችግር የሚፈታባቸውን በርካታ አደረጃጀቶችን እና አሠራሮችን ትተው አልፈዋል።
❤️❤️❤️ የትምህርትን ችግር በመፍታት ሀገር ለማንቃት ጥንታዊውንና 78 አመታትን ያስቆጠረውን " የአቤቶ ነጋሢ ክርስቶስ ወረደ ቃል ት/ቤትን ሚያዚያ 7ቀን 1940 ንጉሰ ነገስቱን መንዝ ድረስ በአካል አምጥተው እንዲከፈት በማድረግ ታሪክ ሰርተዋል።
❤️ የገጠማቸውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍም እናቶቾ ከመቀነታቸው ፈተው; አባቶቾ የበግና የፍየል ሙክቶቻቸውን ሸጠው አዋጥተው መኪና በመግዛት የማህበረሰቡን ችግር ፈተዋል::
@ ያ እነሡ ትላንት ችግር የፈቱበት ድርጅት ዛሬ ላለንበት መሠረት ሆኖን እኛን እዚህ አድርሶናል ያንን ድርጅት መነሻ አድርገን ዛሬ ላይ እኛም ስራ ሰርተን ከመጭው ትውልድ ጋረ የምንተሳሰርበት ጓሳ ኢንዱስትሪያል ቢዝነስ አክሲዮን ማህበርን መስርተናል።
❤️ ጓሳ ኢንዱስትሪያል ቢዝነስ አክሲዮን ማህበርም ነገን መስራት የሚያስችለንን የቆጵሮስ አካዳሚ አህት ኩባንያን ይዞልን ብቅ ብሏል።
❤️ ቆጵሮስ አካዳሚ የነገ ሀገር ተረካቢ ዘርፈ ብዙ ሙያተኞች በእውቀትና በስነምግባር ተኮትኩተው የሚያድጉበት የነገ የሀገር ተስፋ ሆኖ በ2017 መመሐል ሜዳ እና በሞላሌ ከተማ ሁለት ቅርንጪፎችን ከፍቶ

ጓሳ ኢንዱስትሪያል ቢዝነስ አ/ማህበር የአክስዮን ሽያጭ በአባላት ውሳኔ እየሸጠ መሆኑን ስንገልጽላች በከፍተኛ ደስታ ነው፡፡ የአንድ አክስዮን ዋጋ 1000 (አንድ ሺህ) ብር ሲሆን ዝቅተኛ የአ...
25/02/2026

ጓሳ ኢንዱስትሪያል ቢዝነስ አ/ማህበር የአክስዮን ሽያጭ በአባላት ውሳኔ እየሸጠ መሆኑን ስንገልጽላች በከፍተኛ ደስታ ነው፡፡ የአንድ አክስዮን ዋጋ 1000 (አንድ ሺህ) ብር ሲሆን ዝቅተኛ የአክስዮን ሽያጭ 10 (አስር) ነው፡፡ ለዚህ ሽያጭ የአገልግሎት ክፍያ በአንድ አክስዮን 60 (6%) ሲሆን ለጠቅላላ ዝቅተኛ የአክስዮን ሽያጭ 600 (ስድሰት መቶ ብር) ይከፈላል ማለት ነው፡፡ ይህ ክፍያ ለተከፈለባቸው እና ለመክፈል ቃል የተገባባቸውንም ጭምር በአንድ ግዜ የሚከፍል ሲሆን አክስዮኖቹ ለግለሰቦች፤ ለድርጅቶች እና ሕዝብ እንደሚሸጥ ሲገልፅ በታላቅ ደስታ ነው፡፡ ይህንን የአክስዮን ሽያጭ ለካፒታል ገበያ ባለስልጣን በማሳወቅ እና የሽያጭ ግዜውም የሚጀምርበት ቀን የካቲት 01/2018 ሲሆን የሚያበቃት ግዜ ሰኔ 30/2018 ዓ.ም ነው፡፡ስሆነም በዚህ ግዜ ውስጥ የሚከናወነው የአክስዮን ሽያጭ 5 ሚሊዮን(አመስት ሚሊዮን ብር) ወይም አመስት ሺህ (5000 እጣ ብቻ ነው)፡፡ ይህንን ለነባር እና ለአዲስ አባለት ከፍት የተደረገ ሽያጭ ስለሆነ ሁ

ጓሳ ኢንዱስትሪያል ቢዝነስ አ/ማህበር የአክስዮን ሽያጭ በአባላት ውሳኔ እየሸጠ መሆኑን ስንገልጽላች በከፍተኛ ደስታ ነው፡፡ የአንድ አክስዮን ዋጋ 1000 (አንድ ሺህ) ብር ሲሆን ዝቅተኛ የአ...
25/02/2026

ጓሳ ኢንዱስትሪያል ቢዝነስ አ/ማህበር የአክስዮን ሽያጭ በአባላት ውሳኔ እየሸጠ መሆኑን ስንገልጽላች በከፍተኛ ደስታ ነው፡፡ የአንድ አክስዮን ዋጋ 1000 (አንድ ሺህ) ብር ሲሆን ዝቅተኛ የአክስዮን ሽያጭ 10 (አስር) ነው፡፡ ለዚህ ሽያጭ የአገልግሎት ክፍያ በአንድ አክስዮን 60 (6%) ሲሆን ለጠቅላላ ዝቅተኛ የአክስዮን ሽያጭ 600 (ስድሰት መቶ ብር) ይከፈላል ማለት ነው፡፡ ይህ ክፍያ ለተከፈለባቸው እና ለመክፈል ቃል የተገባባቸውንም ጭምር በአንድ ግዜ የሚከፍል ሲሆን አክስዮኖቹ ለግለሰቦች፤ ለድርጅቶች እና ሕዝብ እንደሚሸጥ ሲገልፅ በታላቅ ደስታ ነው፡፡ ይህንን የአክስዮን ሽያጭ ለካፒታል ገበያ ባለስልጣን በማሳወቅ እና የሽያጭ ግዜውም የሚጀምርበት ቀን የካቲት 01/2018 ሲሆን የሚያበቃት ግዜ ሰኔ 30/2018 ዓ.ም ነው፡፡ስሆነም በዚህ ግዜ ውስጥ የሚከናወነው የአክስዮን ሽያጭ 5 ሚሊዮን(አመስት ሚሊዮን ብር) ወይም አመስት ሺህ (5000 እጣ ብቻ ነው)፡፡ ይህንን ለነባር እና ለአዲስ አባለት ከፍት የተደረገ ሽያጭ ስለሆነ ሁላቸሁም በዚህ የአክስዮን ሽያጭ ግዜ ሰሌዳ ውስጥ እንድትገዙ ተጋብዛችኋል፡፡

30/01/2026

ጓሳ ኢንዱስትሪያል ቢዝነስ ግሩፕ አክሲዎን ማኅበር እንደ ማኅበር መመስረትን ማደግን መውደቅን መነሳትን መንስኤ እና ውጤትን የምንማርበት የመንዝ ሕዝብ የኅብረት እና ንግድ ሥራ እንቅስቃሴ ማመሳከሪያ ዋቢ መጽሐፍ ሆኖ ይቀጥላል።
አክሲዎን ማኅበሩን ከድንዛዜ አላቀው አሁን በሚታይበት የማንሰራራት ምዕራፍ ላይ ያደረሱት እንደነ ዶክተር ይጥና ገብረ ማሞ ያሉት እንቁ የመንዝ ምሁራን የእውቀት የታጋሽነት የአለኝታነት ልክ ላሳደጋቸው ላስተማራቸው ማኅበረሰብ ያሳዩበት ከመሆኑም ባሻገር ከውድቀት ማንሻ ሥልት አቀያዬስ ችሎታቸው እንደ ተግባራዊ ተሞክሮ የወሰድንበት ታሪካዊ የአክሲዎን ማኅበሩ ትንሳኤ አብሣሪዎች ሆነው በታሪክ እንድወሱ የሚያደርግ ሲሆን ሂደቱን ለተረዳ ልብወለድ እንጅ እውነተኛ ክዋኔ የማይመስል ገራሚ የጋሃዱ አለም ነጸብራቅ እምነት እና ክህደት የተፋጠጡበት እጅን በአፍ የሚያስጭን ድራማ መሰል ታሪካዊ ጉዞ የተደረገበት አክሲዎን ማኅበር ነው ።
የመሐል ሜዳ የድርጅቱ ቅርንጫፍ ተወካይ የሆኑትን አቶ እሸቱ ወዳጄነህ አዝብጤን አለማመስገን ከፍተኛ ንፉግነት ይሆናል ። አቶ እሸቱ ለዚህ ሕዝባዊ አገልግሎት ሰጭ ማኅበር የሥራ ዘመኑን በኮሚቴነት የጡረታ ዘመኑን በሥራ አስኪያጅነት ሙሉ ጊዜውን መስዋት ስላደረገልን ልናመሰግነው ይገባል ።
የድሮው ርዕሰ ነገር በደጋግ ወንድሞቻችን እና አባቶቻችን እንደተዘጋው ዶሴ ሆኖ ዳግመኛ ላይከፈት ተከርችሟል ።
ካሁን በኋላ አዲስ ርዕሰ ነገር ተከፍቷል ። ሁሉ ነገሩ አዲስ ሆኗል የድሮውን እያነሱ ጊዜ ማጥፋት የለም ።አክትሟል።
ዛሬ ላይ የሚጠበቅብን ቢያንስ ዝቅተኛውን የአክሲዎን ሽያጭ ቢያንስ በብር 10,000.00 መግዛት የአገልግሎት ክፍያ ብር 600.00 መክፈል ።ከፍተኛ 2 ሚሊዩን ብር አክሲዎን ገዝተው የአካባቢው ሃብት በአካባቢው ባላክሲዎኖች እንድያዝ ባለማድረጋችን ምክንያት የተሳትፎ እና የሃብት ማነስ ክፍተት ተፈጥሮ ይሄ መነሻ ሃብት ወደ ወሎ ወይም ጎጃማ ተሻግሮ ከጎጃም ወይም ከወሎ መጥተው እኛ እያለን ማልማት ስንችል እያልን አልሆነ ቁጭት ውስጥ ገብተን ትዝብት ውስጥ እንዳንወርቅ ሁላችንም አክሲዎን ለመግዛት እንዘጋጅ !! በተክለማርያም በላይ

Address

Addis Ababa, Ethiopia . P. O. Box
Gewasa
33112

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Guasa Industrial Business-GIB-s.c posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Guasa Industrial Business-GIB-s.c:

Shortcuts

Share