Ardaita agricultural & TVT college communication/አርዳይታ ግ/ቴ/ሙ/ሥ ኮሌጅ ኮሙኒኬሽን

  • Home
  • Ethiopia
  • Gedeb
  • Ardaita agricultural & TVT college communication/አርዳይታ ግ/ቴ/ሙ/ሥ ኮሌጅ ኮሙኒኬሽን

Ardaita agricultural & TVT college communication/አርዳይታ ግ/ቴ/ሙ/ሥ ኮሌጅ ኮሙኒኬሽን Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ardaita agricultural & TVT college communication/አርዳይታ ግ/ቴ/ሙ/ሥ ኮሌጅ ኮሙኒኬሽን, Trade school, Gedeb.

Ardaita agricgricultural TVT college is one of the popular college that provide quality training on
👉 Cooperative Accounting and Auditing
👉 CoopBusiness Management
👉 Marketing
👉 Agricultural Machinery and Equipment Mechanics/Operations from level 1-4

በዛሬው ዕለት በኮሌጃችን በሶስቱም ዘርፎች በግማሽ አመቱ የተከናወኑ ሥራዎች አፈፃፀም ሪፖርት ተደረገ። የካቲት 20/2018 ዓ.ም🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹የኮሌጁ ዲን አቶ ጀማል ከዲር በተ...
27/02/2026

በዛሬው ዕለት በኮሌጃችን በሶስቱም ዘርፎች በግማሽ አመቱ የተከናወኑ ሥራዎች አፈፃፀም ሪፖርት ተደረገ።
የካቲት 20/2018 ዓ.ም
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የኮሌጁ ዲን አቶ ጀማል ከዲር በተገኙበት ከየስራ ዘርፉ በተወከሉ የሥራ ሀላፊዎች የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ተደርጓል። በሪፖርቱ
👉 ምክትል ዲኖች፣
👉 የሥራ አስፈፃሚዎች፣
👉 ቡድን መሪዎች፣
👉 ዴስክ ሀላፊዎች እና ባለሙያዎች ተገኝተዋል። በስፖርቱም ድክመቶች እና መሻሻል ያለባቸው በመገምገም እና የማሻሻያ ምክረ ሀሳቦች ከመድረኩ ተሰጥቶ፣ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ በመስጠትና መልካም ሥራ እና ጠንካራ ጎኖች ይበል ይቀጥል በሚሉ ገንቢ ሀሳቦች ተሰጥተው፤ በመጨረሻም በተደረገው ሪፖርት በአቶ ጀማል ከዲር የኮሌጁ ዲን ማጠቃለያ ሀሳብ መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የካቲት 20/2018 ዓ.ም
አርዳይታ ኮሌጅ ህዝ/ግ/ኮ/ሥራ አስፈፃሚ።

በኮሌጃችን በ"ISO 21001:2025 EOMS" ዋና አተገባበር ዙሪያ ውይይት ተደረገ። ✳✳✳✳✳✳✳✳✳✳✳የካቲት 12/2018 ዓ.ምእንደሚታወቀው በኮሌጃችን የ''ISO 21001:2025 EOMS...
20/02/2026

በኮሌጃችን በ"ISO 21001:2025 EOMS" ዋና አተገባበር ዙሪያ ውይይት ተደረገ።
✳✳✳✳✳✳✳✳✳✳✳
የካቲት 12/2018 ዓ.ም
እንደሚታወቀው በኮሌጃችን የ''ISO 21001:2025 EOMS" የትግበራና የሰነድ ዝግጅት ከተደመረ ከስድስት ወር በላይ ሆኖታል በነዚህ ወራት፦
🇪🇹 የሰነድ ዝግጅቶች፣
🇪🇹 የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናዎች፣
🇪🇹 ከሥራ አስፈፃሚዎች ጋር ውይይት የማድረግ ሥራ፣
🇪🇹 የቅድመ ትግበራና የሰነድ አጠቃቀም ሥልጠና ለባለሙያዎች፣ ቡድን መሪዎች ፀሐፊዎች እና ዴስክ ሃላፊዎች መስጠት፣
🇪🇹 የአስራ አምስት ቀን የሙከራ ትግበራ እና የክትትል ሥራ ተከናውኗል። በዚህም በትግበራውና ሰነድ ይዘት ላይ በሥራው ባለቤቶች የማስተካከያ ሀሳብና አስተያየቶች ተሰጥቶ በማስተካከል እና በማደራጀት ለዋናው ትግበራ ምዕራፍ መዘጋጀቱን ለማሳወቅ እና የማስጀመሪያ መርሐግብር ለማድረግ ዛሬ ማለትም የካቲት 12/2018 ዓ.ም የ"ISO 21001:2025 EOMS" የግብረ ኃይሉ ከኮሌጁ አስተዳደር ጋር ውይይት አድርጓል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የካቲት 12/2018 ዓ.ም
በኮሌጁ ህዝ/ግ/ኮ/ሥራ አስፈፃሚ ተዘጋጅቶ ቀረበ።

አርዳይታ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት እና ሥልጠና ኮልጅን ያውቁታል?ካላወቋት ትንሽ ልበላችሁ። 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹አርዳይታ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት እና ሥልጠና ኮሌጅ ...
25/01/2026

አርዳይታ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት እና ሥልጠና ኮልጅን ያውቁታል?
ካላወቋት ትንሽ ልበላችሁ።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
አርዳይታ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት እና ሥልጠና ኮሌጅ በፌዴራል የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ከሚተዳደሩት አምስቱ የግብርና ኮሌጆች አንዱ ነው።
👉 አመሰራረት፦ ኮሌጃችን አርዳይታ የግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ በ1976 ዓ.ም በኮለኔል መንግሥቱ ኃይለማሪያም "አርዳይታ የካቲት ፳፭ ኅብረት ሥራ ኢኒስቲትዩት" በሚል ስም የመሠረት ድንጋይ ተጥሎ በፍጥነት እና በጥራት ግንባታዎች ተገንብተው ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኑ።
👉 የተቋቋመበት ዓላማ አርሶአደሮች ዘመናዊ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት፣ የንግድ ሥራ አመራር እና ግብይት በአጭር ና በመደበኛ ሥልጠናዎችን ለመስጠትና ዘመናዊ አርሶአደሮች ማፍራት እና ሙያዊ እገዛ የሚያደርጉ የግብርና ባለሙያዎችን አሰልጥኖ ወደ አርሶአደሮች መንደር መላክ ነው።
👉 መገኛ፦ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን፣ ገደብ ሀሳሳ ወረዳ መነሻችሁን አዲስ አበባ በማድረግ በአሰላ አቅጣጫ ወደ ባሌ ሮባ ሲጓዙ ሀሳሳ ከተማን አልፈው ሰባት ኪሎሜትር እንደተጓዛችሁ በስተቀኝ 15 ኪሎሜትር የአሸዋ ጥርጊያ መንገድ ይጓዛሉ ከዛም ወደግራ አስፓልቱን ይዘው ሲጓዙ ኮሌጁን ያገኛሉ።
👉 አጠቃላይ ገለፃ፦
ኮሌጃችን ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 1994 ዓ.ም በተለያዩ የሙያ መስኮች ማለትም በኅብረት ሥራ ሂሳብ አያያዝ እና ቁጥጥር፣ በኅብረት ሥራ የንግድ ሥራ አመራር፣ በኅብረት ሥራ ግብይት በእንስሳት ሳይንስ እና በ እፅዋት ሳይንስ በመደበኛ እና በአጫጭር ሥልጠና በመስጠት በርካታ ቁጥር ያላቸውን ባለሙያዎች ከመላው ሀገሪቱ በመቀበል አፍርቷል። በመቀጠል ከ1994-2012 ዓ.ም ድረስ በሶስት የሥልጠና ዘርፎች በዲፕሎማ እና በመረጃ 4 ሲሰጥ ቆይቶ በ2012 ዓ.ም ከፌደራል የተፈጥሮ ሀብት እና ደን ሚኒስቴር በመወጣት ወደ ፌደራል ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ስር ገብቶ በዞኔሽንና ዲፍረነሴሽን የመንግሥት አቅጣጫ መሰረት
💻 በኅብረት ሥራ ሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት፣
💻 በኅብረት ሥራ የንግድ ሥራ አመራር፣
💻 በኅብረት ሥራ ግብይት እስከ 2015 ዓ.ም በመደበኛው የትምህርት ክፍለ ጊዜ እና በእረፍት ቀናት ቅዳሜና እሁድ ብቃት እና ሙያዊ ስነምግባር ያላቸውን ሙያተኞች አፍርቷል እያፈራም ይገኛል። ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ ሁለት የሥልጠና ክፍሎችን ማለትም፦
💻 የግብርና ማሽቸሪዎች እና መሳሪያዎች መካኒክ፣
💻 የግብርና ማሽቸሪዎች እና መሳሪያዎች አንቀሳቃሽ በመጨመር ሥልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል።
ከስልጠናው ባሻገር ኮሌጃችን አርዳይታ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት እና ሥልጠና ኮሌጅ ለአጎራባች ቀበሌ አርሶአደሮች ዘመናዊ የእንስሳት እርባታ፣ የወተት ላሞች ልማት እና የዶሮ እርባታ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና ሥልጠና በመስጠት የአርሶአደሩን ህይወት ለማሻሻል የበኩሉን ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
ነፃ የትምህርት ዕድል ለኮሌጁ ሰራተኛ ቤተሰቦች እና ለአካባቢው ማህበረሰብ በመስጠት የህዝብ ተቋም መሆኑን አሳይቷል።
👉 ምን ምን አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋሉ?
አርዳይታ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት እና ሥልጠና ኮሌጅ የሚከተሉትን አገልግሎቶች ለመስጠት ሁልጊዜ እናንተን ይጠብቃል
👉 በአምስቱ የሥልጠና አይነቶች በቅዳሜናእሁድ ሥልጠና መስጠት፣
👉 በመሰረታዊ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት፣ በመሰረታዊ አዋጭ የንግድ ሥራ ዕቅድ አዘገጃጀት፣ መሰረታዊ የእርሻ መሣሪያዎች ጥገና ሌሎች ክህሎቶችን በአጫጭር ሥልጠና ማሰልጠን፣
👉 እንቁላል፣ የደለቡ በጎች ሰንጋዎች በተመጣጣኝ ዋጋ መሸጥ፣

23/12/2025

Watch, follow, and discover more trending content.

Address

Gedeb

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ardaita agricultural & TVT college communication/አርዳይታ ግ/ቴ/ሙ/ሥ ኮሌጅ ኮሙኒኬሽን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category