Openo Children Academy

Openo Children Academy openo

የንባብ ባህልን ለማጎልበት በትናንትናው ዕለት የተከፈተው የመፅሐፍት አውደ ርዕይ በኦፔኖ ህፃናት አካዳሚ በተለያዩ መርሃግብሮች እንደቀጠለ ነው።በዛሬው ዕለትም የተማሪዎች የጎዳና ላይ ሩጫ ውድ...
14/04/2024

የንባብ ባህልን ለማጎልበት በትናንትናው ዕለት የተከፈተው የመፅሐፍት አውደ ርዕይ በኦፔኖ ህፃናት አካዳሚ በተለያዩ መርሃግብሮች እንደቀጠለ ነው።

በዛሬው ዕለትም የተማሪዎች የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ተካሂዷል።

ከጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት (ሚያዝያ 06/2016 ዓ.ም)

በኦፔኖ ህፃናት አካዳሚ አዘጋጅነት "ፍኖተ ንባብ" በሚል መሪ ቃል በትናንትናው ዕለት የተከፈተውን የመፅሐፍት አውደ ርዕይ ምክንያት በማድረግ የተማሪዎች የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ተካሂዷል። '

በውድድሩ ላይ የኦፔኖ ህፃናት አካዳሚ ተማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ውድድሩ መነሻውን መቱ ማዞሪያ አድርጎ በኦፔኖ ህፃናት አካዳሚ ውስጥ ተጠናቋል።

የሩጫ ውድድሩ ተማሪዎች በስፖርት ጤናቸውን እንዲጠብቁና በአካልና በአዕምሮ ዝግጁ እንዲሆኑ የሚያስተምር እንደሆነ ተገልጿል።

ከዚህ ባሻገር በተማሪዎች መካከል ያለውን መቀራረብና የእርስ በእርስ ግንኙነት እንዲዳብርም ውድድሩ የራሱን አስተዋጽዖ ያበረክታል ተብሏል።

በወንዶች ውድድር ሙይ ኡባንግ፣ ቸደጆክ አቺዲና ናትናኤል ተፈራ እንዲሁም በሴቶች መስታወት አሸናፊ፣ መሰረት መልካሙና ፀደይ ገላይ ከአንድ እስከ ሶስት በመውጣት ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

በኬጂ ተማሪዎች ውድድር ፋሩቅ ሲሳይ፣ ናታን ተስፋዬና ምትኩ ዮናስ ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ይዘዋል።

በዚህ ውድድር ከአንድ እስከ አምስት ለወጡ ተማሪዎች የመፅሐፍ ሽልማት ተበርክቷል።

Grade 8 students
17/09/2023

Grade 8 students

የፊታችን ነሐሴ 15/ 2015 ዓ/ም የተማሪዎች ምዝገባ እንጀምራለን።
17/08/2023

የፊታችን ነሐሴ 15/ 2015 ዓ/ም የተማሪዎች ምዝገባ እንጀምራለን።

01/03/2023
ደረጃቸውን የጠበቁ የመማሪያ ክፍሎችን አዘጋጅተናል።
02/10/2022

ደረጃቸውን የጠበቁ የመማሪያ ክፍሎችን አዘጋጅተናል።

28/09/2022

ውድ የተከበራችሁ ተማሪዎች
ት/ቤታችን የ2015 ዓ/ም የመማር ማስተማር ስራ ዛሬ ቀን 18/01/2015 ዓ/ም የጀመረ መሆኑን ከወዲሁ እናስታውቃለን።
ማሳሰቢያ:-
የትራንስፖርት ተጠቃሚዎች ቁጥር አንድ ት/ቤት የአስተዳደር ቢሮ በመቅረብ እንዲትመሰገቡ እናሳስባለን።
ከት/ቤቱ

ት/ቤታችን በ2014 ዓ.ም ለ8ኛ ክፍል ተፈታኞች የሽኝት ፕሮግራም በማዘጋጀት ከክልሉ 2ኛ ጀረጃ በመዉጣታቸዉ የምስክር ወረቀት አበረከተላቸው።                      መልካም የትምህ...
21/09/2022

ት/ቤታችን በ2014 ዓ.ም ለ8ኛ ክፍል ተፈታኞች የሽኝት ፕሮግራም በማዘጋጀት ከክልሉ 2ኛ ጀረጃ በመዉጣታቸዉ የምስክር ወረቀት አበረከተላቸው።
መልካም የትምህርት ዘመን

16/09/2022

🎉Congratulations🎉
ለኦፔኖ አካዳሚ ወላጆችና ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ! ት/ቤታችን በ2014 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ክልላዊ ፈተና ያስፈተናቸው ተማሪዎች ከክልሉ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ 2ኛ ደረጃ በመሆን ሙሉ በሙሉ ወደ ቀጣዩ ክፍል ተዛውረዋል።

15/09/2022

የሀገራችንን የትምህርት ጥራት የሚያረጋግጥ ትውልድ ለማፍራት እንተጋለን!!!

ኦፔኖ የህፃናት አካዳሚ
ጋምቤላ

👑👑👑🌹Congratulation🌹🌹☀️☀️                እንኳን  ደስ አላችሁየዕውቅና የምስክር ወረቀት  በክልሉ መንግስት ተበርክቶልናል።በ2014  የትምህርት ዘመን ብቁ ተማሪዎችን በ...
13/09/2022

👑👑👑🌹Congratulation🌹🌹☀️☀️
እንኳን ደስ አላችሁ
የዕውቅና የምስክር ወረቀት በክልሉ መንግስት ተበርክቶልናል።
በ2014 የትምህርት ዘመን ብቁ ተማሪዎችን በማፍራት ከክልሉ የግል ት/ቤቶች የዕውቅና የምስክር ወረቀት በክልሉ መንግስት ስለተበረከተልን ትልቅ ደስታ ተሰምቶናል።
🙏የክልሉን መንግስት እናመሰግናለን።🙏

HAPPY NEW YEAR            2015
10/09/2022

HAPPY NEW YEAR
2015

01/09/2022

Address

Gambella Town Baro Mado
Gambela

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Openo Children Academy posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Openo Children Academy:

Shortcuts

Share