አጣዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

አጣዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አጣዬ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ

የአጣዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለአረጋዊያንና አቅመ ደካሞች የምገባ ፕሮግራም አካሄደ፣‎🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬‎‎(ነሀሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም)‎‎የአጣዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2...
17/08/2026

የአጣዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለአረጋዊያንና አቅመ ደካሞች የምገባ ፕሮግራም አካሄደ፣
‎🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬

‎(ነሀሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም)

‎የአጣዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 በጀት አመት የክረምት እቅዶች ውስጥ አንዱ የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ መሳተፍ ነው።
‎ለዚህም በአጣዬ ከተማ አልማ አካባቢ ለሚገኙ ከ53 በላይ ለሚሆኑ አረጋዊያን የኮሌጁ ዲን አቶ እንድሪስ ሰይድ እና ም/ዲኖች አቶ አረጋኸኝ ጌታቸው፣ ወ/ሮ ባንችአምላክ አዳነ እና ባለሙያዎች በቦታው በመገኘት #የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም አድርጓል።

‎ከማዕድ ማጋራቱ በተጨማሪ #በኮሌጁ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር እሸቱ አባተ አሰልጣኝነት የተመረተ 26 ሊትር ፈሳሽ ሳሙና ድጋፍ አድርጓል። እንደ አቶ እንድሪስ ሰይድ ገለፃ አረጋዊያንን መደገፍ በጎ ተግባር በመሆኑ ግለሰብ እንዲሁም ተቋም ተጠናክሮ መያዝ ያለበት ተግባር መሆኑን ገልፀዋል።


‎መረጃው የኮሌጁ ህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ነው

የአጣዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ  ” በሚል የበጎ አድራጎት ዘመቻ ላይ ድጋፍ አደረገ፣‎⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳‎‎(ነሀሴ 08/2018 ዓ.ም)‎‎በኤፍራ...
14/08/2026

የአጣዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ” በሚል የበጎ አድራጎት ዘመቻ ላይ ድጋፍ አደረገ፣
‎⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳

‎(ነሀሴ 08/2018 ዓ.ም)

‎በኤፍራታና ግድም ወረዳ እየተካሄደ ባለው “አንድ ደርዘን ደብተር ለአንድ ተማሪ” የክረምት የበጎ አድራጎት ዘመቻ የመማሪያ ቁሳቁስ ማሟላት ለማይችሉ ተማሪዎች የሚውል የትምህርት ቁሳቁስ የማሰባሰብ ተግባር ላይ ኮሌጁም የበኩሉን ተወጥቷል።

‎በዚህም የአጣዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ #እንደ ኮሌጅ 10 ደርዘን ደብተር፣ 2 ፓኮ እስኪብርቶ እና የኮሌጁ ዲን አቶ እንድሪስ ሰይድ 2 ደርዘን ደብተር፣ የኮሌጁ ም/ ዲን አቶ አረጋኸኝ ጌታቸው 1 ደርዘን፣ ወ/ሮ ባንችአምላክ አዳነ 1 ደርዘን፣ አቶ ብርሀኑ ዘለቀ እና ወ/ሮ ውድነሽ በቀለ በጋራ 1 ደርዘን በጥቅሉ 15 ደርዘን ደብተሮችን በኮሌጁ ዲኖች አቶ እንድሪስ ሰይድ አማካኝነት ለኤፍራታና ግድም ወረዳ ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ለወ/ሮ ወርቅነሽ ጌታብሎ አስረክበዋል።

‎እንደ አቶ እንድሪስ ሰይድ ገለፃ እንደኮሌጅ ካሉ ክበባቶች ውስጥ አንዱ የበጎ አድራጎት ክበብ በመሆኑ እንደዚህ አይነቱ የበጎ አድራጎት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ግንዛቤ ፈጥረዋል።

‎የኮሌጁ ህዝብ ግንኙነት ባለሙያ

የአጣዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የውጭ አገር ስራ ስምሪት ስልጠና መስጠት ጀመረ፣‎==============================‎‎(ነሐሴ 06 ቀን 2018 ዓ.ም)‎‎የአጣዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ...
12/08/2026

የአጣዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የውጭ አገር ስራ ስምሪት ስልጠና መስጠት ጀመረ፣
‎==============================

‎(ነሐሴ 06 ቀን 2018 ዓ.ም)

‎የአጣዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2019 በጀት ዓመት የሁለተኛ ዙር ስልጠና ከነሐሴ 06/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ21 ቀን የሚቆይ የውጭ አገር ስራ ስምሪት የቤት ውስጥ አያያዝ Work # ስልጠናውን አስጀምሯል።

‎የኮሌጁ ዲን አቶ እንድሪስ ሰይድ እና ም/ዲን አቶ አረጋኸኝ ጌታቸው አጠቃላይ የ21 ቀን የስልጠና ቆይታ ምን ይመስላል በሚል ዙሪያ አጭር ግንዛቤ ፈጥረዋል።
‎ስልጠናው በኢንስትራክተር ሞላ ሹምዬ አማካኝነት ስለ ቅድመ ጉዞ ስልጠና የተጀመረ ሲሆን የሰራተኛ መለያ አሻራ ቁጥር አውጥተው በኦንላይን ለተመዘገቡ 195 ሰልጣኞች የሚሰጥ ነው።

‎የኮሌጁ ህዝብ ግንኙነት ባለሙያ

10/08/2026
10/08/2026
10/08/2026
‎በአጣዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ3R-4-CACE ፕሮጀክት አማካኝነት ለህፃናት ማቆያ ግንባታ ለመንባት የሳይት ርክክብ አካሄደ።‎➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖‎‎(ሐምሌ 01/2018 ዓ.ም...
07/08/2026

‎በአጣዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ3R-4-CACE ፕሮጀክት አማካኝነት ለህፃናት ማቆያ ግንባታ ለመንባት የሳይት ርክክብ አካሄደ።
‎➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

‎(ሐምሌ 01/2018 ዓ.ም)

‎በአጣዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግቢ ውስጥ በ3R-4-CACE ፕሮጀክት አማካኝነት የህፃናት ማቆያ ግንባታ ለመገንባት የሚያስችል የቦታ ርክክብ ተካሂዷል።

‎በርክክቡ ላይ የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ተመስገን ተስፋ፣ የኮሌጁ ዲን አቶ እንድሪስ ሰይድ እና ም/ዲኖች አቶ አረጋኸኝ ጌታቸው፣ ወ/ሮ ባንችአምላክ አዳነ፣ የአጣዬ ከ/አስተዳደር ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ጌጤነሽ ማሞ፣ የ3R-4-CACE ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ታሪኩ ገበየሁ፣ የግንባታው አሸናፊ ኮንትራክተር በለጠ ደምስ እና የግንባታው አስተባባሪዎች ተገኝተዋል።

‎ይህ የህፃናት ማቆያ ግንባታ በ2018 በጀት አመት ግንባታው ተጀምሮ በቀጣይ በጀት አመት ሙሉ በሙሉ ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ተገልጿል።

‎የኮሌጁ ህዝብ ግንኙነት ባለሙያ

‎የአጣዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የችግኝ ተከላ አካሄደ፣‎⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳‎‎(ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም) ‎‎የአጣዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የክረምት ዕ...
29/07/2026

‎የአጣዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የችግኝ ተከላ አካሄደ፣
‎⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳

‎(ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም)

‎የአጣዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የክረምት ዕቅዶች መካካል 🌹🌹"ተስፋን እንትከል"🌹🌹 በሚል መሪ ቃል ኮሌጁን ይበልጥ ውብና ማራኪ ሊያደርጉ የሚችሉ የተለያዩ የውበት እና የችግኝ ዝሪያ አይነቶችን የተከላ ፕሮግራም አካሂዷል።

‎በችግኝ ተከላው ላይ የኮሌጁ ዲን አቶ እንድሪስ ሰይድ፣ የኮሌጁ ም/ዲን አቶ አረጋኸኝ ጌታቸውና ወ/ሮ ባንችአምላክ አዳነ ፣ የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበበ በቀለ፣ የኤፍራታና ግድም ወረዳ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊዎች አቶ ሻንበል አረጋኸኝና ወ/ሮ አመዘን ጌታሁን እንዲሁም የኮሌጁ አሰልጣኞች እና የአስተዳደር ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

‎የተተከሉ ችግኞች የግራፊሊያ ዛፎች፣ የፖፖያ እና ሌሎች ችግኞች ሲሆኑ ይህ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ኮሌጁ በቀጣይ እጅግ በጣም ውበት እንዲኖረውና የሚያስደስት እንዲሆን ስለሚረዳ የተተከሉ ችግኞችን መንከባከብና መቆጣጠር እንደሚገባ በአፅንኦት በማሳሰብ ተጠናቋል።

‎የኮሌጁ ህዝብ ግንኙነት ባለሙያ

‎የአጣዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የውጭ አገር ስራ ስምሪት ምዘና መስጠት ጀመረ፣‎==============================‎‎(ሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም)‎‎የአጣዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ...
24/07/2026

‎የአጣዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የውጭ አገር ስራ ስምሪት ምዘና መስጠት ጀመረ፣
‎==============================

‎(ሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም)

‎የአጣዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ21 ቀን ያሰለጠናቸውን #የ2019 በጀት አመት የመጀመሪያው ዙር የውጭ አገር ስራ ስምሪት ምዘና በምግብ ዝግጅት እና የቤት ውስጥ ንፅህና አያያዝ Work # 160 የሲኦሲ ተመዛኞችን ከዛሬ ሀምሌ 17 ቀን ጀምሮ ምዘና በማስመዘን ላይ ይገኛል።

‎መረጃው የኮሌጁ ህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ነው

የአጣዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ሰልጣኞች ለ20ኛ ጊዜ አስመረቀ፣‎🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓‎‎(ሀምሌ 12 ቀን 2018 ዓ.ም)‎🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬‎‎...
19/07/2026

የአጣዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ሰልጣኞች ለ20ኛ ጊዜ አስመረቀ፣
‎🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓

‎(ሀምሌ 12 ቀን 2018 ዓ.ም)
‎🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬🧬

‎ኮሌጁ ለ20ኛ ዙር በተለያዩ የትምህርት መስኮች ከደረጃ 1-5 ያሰለጠናቸውን 100 ሰልጣኞች በዛሬው እለት በድምቀት አስመርቋል።

‎የአጣዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሌጁ ዲን አቶ እንድሪስ ሰይድ ለክቡር የወረዳችን አመራሮች፣ ለተመራቂዎች እንዲሁም ለተመራቂ ቤተሰቦች እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

‎በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የክብር እንግዳ በመሆን የተገኙት የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ተመስገን ተስፋ ፣ የኤፍራታና ግድም ወረዳ ተቀዳሚ አስተዳዳሪ አቶ አበራ መኮንን እና ሌሎችም የከተማውና የወረዳ አመራሮች ለተመራቂዎቹ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

‎በመቀጠል ለተመራቂዎች ቀጣይ የሥራ ሕይወታቸው የተማሩትን ዕውቀት ተጠቅመው ማህበረሰባቸውንና ሀገራቸውን በቅንነት እንዲያገለግሉ በማለት ከአጣዬ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት እና ከኤ/ግ/ወረዳ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊዎች ጋር የሰነድ ርክብክብ አድርገዋል።

‎በመጨረሻ ከየዲፓርትመንቱና ከየሌቭሉ ከ1 እስከ 3 ለወጡ ሰልጣኞች፣ ለተሻሉ ኢንተርፕራይዞች፣ ለዲጅታል አማራ ስልጠና በግንባር ቀደምነት ንቁ ተሳትፎ ላደረጉ እና ለተለያዩ የስራ አጋር ተቋሞች የምስክር ወረቀት የተሸለሙ ሲሆን በድጋሚ ከአጠቃላይ ከኮሌጁ ሰልጣኞች 1ኛ ለወጣው ሰልጣኝ #በፍቅር አሳምነው የዋንጫ ሽልማት በማበርከት የኤ/ግ/ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበራ መኮንን በድጋሚ ለተመራቂዎች መልካም ዕድል እንዲገጥመቸው ተመኝተው እንደ አጣዬ ከተማ ትልቁ የትምህርት ተቋም ይህ ኮሌጅ በመሆኑ ሁሉም የአካባቢው ማህበረሰብ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል የእለቱ የምርቃን ፕሮግራም ተጠናቋል።

‎መረጃው የኮሌጁ ህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ነው

Address

ለእውቅናዎ የአጣዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በአማራ ክልል በሰሜን ሽዋ ዞን አጣዬ ከተማ ይገኛል
Efeson

Telephone

+251336610308

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አጣዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share