ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ/Poly Technic Collage

ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ/Poly Technic Collage Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ/Poly Technic Collage, Education, Durame.

02/01/2026
19/10/2025
የክልሉን ፀጋዎች በመጠቀም ውጤታማነትን ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር ይገባል:- ዶላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር)(ሆሳዕና፣ ግንቦት 22/2017)የስራና ክህሎት ሚኒስቴር የሱፐርቪዥን ቡድን በማ...
30/05/2025

የክልሉን ፀጋዎች በመጠቀም ውጤታማነትን ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር ይገባል:- ዶላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር)

(ሆሳዕና፣ ግንቦት 22/2017)

የስራና ክህሎት ሚኒስቴር የሱፐርቪዥን ቡድን
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ያካሄደውን የመስክ ምልከታ አስመልክቶ ለሚመለከታቸው የክልሉ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች የቃል ግብረ መልስ ሰጠ።

በግብረ መልስ መድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት በብልፅግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር)፣ የተካሄደው ሱፐርቪዥን ወቅታዊ መሆኑን ጠቅሰው፣ በግብረ መልሱ በግበዓትነት የተወሰዱ ነጥቦችን በ2018 በጀት አመት ዕቅት በማካተት የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የክልሉን ፀጋዎች በመጠቀም ለውጤታማነት መስራት እንደሚገባ ያመላከቱት ኃላፊው በተሞክሮነት የተለዩትን አጠናክሮ በማስቀጠል፣ ጉለቶችን በተቀናጀ መንገድ በፈጠነ ጊዜ በማረም በክልሉ ብልፅግናን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

በስራና ክህሎት ሚኒስቴር የሱፐርቪዥን ቡድን የተሰጠውን ግብረ መልስ በግብዓትነት በመውሰድ በክልሉ ሁለንተናዊ ብልፅግና እንዲረጋገጥ በቅንጅት መስራት ይገባል ሲሉም ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) አሳስበዋል።

የስራና ክህሎት ሚኒስቴር የሱፐርቪዥን ቡድንን የመሩት ሚኒስትር ድኤታ ሰለሞን ሶካ፣ ምልከታ በተደረገባቸው ዘርፎች ላይ በዝርዝር የቃል ግብረ መልስ የሰጡ ሲሆን፣ በክልሉ ያደረጉት ቆይታ ደስ የሚልና ስኬታማ መሆኑን ገልፀው፣ በተካሄደው ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን በየደረጃው ግብረ መልስ እየተሰጠ ስለመመጣቱ ገልፀዋል።

በክልሉ በክህሎት ልማት፣ በስራ ዕድል ፈጠራ፣ በኢንተርፕራይዞች ልማት፣ በኢንዱስትሪ ልማት እንዲሁም በሰላማዊ ኢንዱስትሪ እየተሰሩ የሚገኙ ተግባራት ተስፋ ሰጪና አበራታች መሆናቸውን ገልፀው ጅምር ስራዎቹን ይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

ለሚመለከታቸው የክልሉ ተቋማትና ለብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የጽሁፍ ግብረ መልስ በቀጣይ እንደሚሰጥም አቶ ሰለሞን አመላክተዋል።

ግብረ መልሱን የክልሉ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና፣ የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት እንዲሁም የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች አድምጠዋል።

የተቋማቱ የስራ ኃላፊዎች በምልከታው በጥንካሬ የተሰጡትን አጠናክሮ ለማስቀጠል፣ በጉድለት የተለዩትን ደግሞ በቀጣይ በማረም ለውጤታማነት እንደሚሰሩም ቁርጠኝነታቸውን ገልፀዋል።

29/05/2025
29/05/2025
12/03/2025

የምዝገባ እና የፈተና ቀናት ተራዝመዋል።

ለደረጃ 7 (2ኛ ዲግሪ) የNGAT አመልካቾች ምዘገባ መጋቢት 01/2017 መጠናቀቁ እና ፈተናው መጋቢት 05/2017 ከ3፡00 ጀምሮ እንደሚሰጥ መገለጹ ይታወሳል።

ይሁንና በተፈታኞች ጥያቄ መሰረት ምዝገባው እስከ መጋቢት 04/2017 ዓ.ም እስከ ምሽቱ 12:00 የተራዘመ ሲሆን ፈተናው ደግሞ መጋቢት 12/2017 ከ3:00 ጀምሮ ይሰጣል።

በዚሁ መሰረት በተለያየ ምክንያት ምዝገባ ያመለጣችሁ አመልካቾች ምዝገባችሁን ቀደም ሲል በተገለጸው ሊንክ https://ngat.ethernet.edu.et/registration በመግባት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ፈተናውን ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ስዓት በምትመደቡበት የፈተና ማዕከላት ተገኝታችሁ እንድትፈተኑ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-
1. ተፈታኞች ወደ ፈተና ማዕከል በምትሄዱበት ወቅት ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ መያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡
2. ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናው ከመጀመሩ 30 ደቂቃ በፊት በፈተና ማዕከል መገኘት ይጠበቅበታል፡፡
3. የሞባይል ስልክ ይዞ በፈተና ማዕከል መገኘት ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡
4. የፈተና ማዕከላት ምደባ በምዝገባ ፕላትፎርም የሚገለጽ ይሆናል፡፡

06/03/2025

Address

Durame
DURAMEPOLY

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ/Poly Technic Collage posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category