30/03/2026
ቀን 21/07/2018
የትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጥን የሚመለከት አስቸኳይ መልእክት
=========
ለተከበራችሁ ወላጆች/አሳዳጊዎች :-
ትምህርት ቤታችን በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍም ሆነ በሀገራችን የተከሰተውን የነዳጅ እጥረት በተቻለ መጠን ተቋቁሞ እስካሁን ድረስ የትራንስፖርት አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱ ይታወቃል።
ሆኖም ግን፣ በአሁኑ ሰዓት ተጨማሪ ናፍታ ማግኘት ባለመቻሉ እና የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት መምሪያ ችግሩን ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት ቢያደርግም የሚፈለገውን ነዳጅ ማግኘት ባለመቻሉ ፤ ከፊታችን ረቡዕ (23/07/2018) ጀምሮ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት የማንችል መሆኑን እንገልጻለን።
ስለሆነም ፣ ተማሪዎች በትምህርታቸው ላይ መስተጓጎል እንዳይገጥማቸው ወላጆች ይህንን አስገዳጅ ሁኔታ ተረድታችሁ ከረቡዕ (23/07/2018) ጀምሮ ሌሎች አማራጭ የትራንስፖርት መንገዶችን እንድትጠቀሙ እያሳወቅን ፤ ችግሩ ተቀርፎ ነዳጅ ማግኘት ስንጀምር አገልግሎቱን ወዲያውኑ የምንቀጥል መሆኑን እየገለጽን ፣ ያጋጠመው ችግር ከት/ቤቱ አቅም በላይ ስለሆነ ይቅርታ እንጠይቃለን።
ት/ቤቱ