ደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ /Dessie College Of Teachers Education

ደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ /Dessie College Of Teachers Education

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ /Dessie College Of Teachers Education, College & University, Dessie, Dessie.

Photos from ደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ /Dessie College Of Teachers Education's post 10/05/2026

የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በገራዶ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የ110 ሺህ ብር ድጋፍ አደረገ

ደሴ (ግንቦት 02/2018 ዓ.ም)

የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ የማህበረሰብ አገልግሎት ድርሻውን ለመወጣት በገራዶ አካባቢ ለሚገኙ ተፈናቃዮችና ወላጅ አልባ ሕፃናት የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።

ኮሌጁ ሚያዚያ 28 እና 29 ቀን 2018 ዓ.ም ባከናወነው በዚህ የድጋፍ መርሃ-ግብር ላይ ከ110 ሺህ ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸውን የምግብ ፍጆታዎችና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን አበርክቷል።

ድጋፉን ያስረከቡት የኮሌጁ የአካዳሚክ ም/ዲን ወ/ሮ መምበረ ላቀው እና የልማትና አስተዳደር ም/ዲን አቶ ደምሰው አሰፋ እንደገለጹት፤ ኮሌጁ ከመማር ማስተማር ስራው በተጓዳኝ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣትና ለተቸገሩ ወገኖች አለኝታነቱን ለማሳየት በትኩረት እየሰራ ይገኛል።
የቀረበው ድጋፍም ፓስታ፣ ማካሮኒ፣ ፈሳሽ ሳሙና፣ ሶፍት እና ኦሞን ያካተተ ሲሆን፤ ይህም በተፈናቃዮችና በሕጻናቱ ላይ የሚታየውን መሰረታዊ ፍላጎት በከፊል ለመሸፈን ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።

በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የኮሌጁ የማህበረሰብ አገልግሎት አስተባባሪ አቶ አሸብር ወሰንና የኮሌጁ አመራሮች ተገኝተው ድጋፉን ለተወካዮች አስረክበዋል። እርዳታውን የተቀበሉት ግለሰቦች ኮሌጁ ላደረገላቸው ወቅታዊና አስፈላጊ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ መሰል ሰብአዊ ድጋፎችንና የማህበረሰብ አገልግሎት ተግባራትን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም በዚሁ ወቅት ተመላክቷል።

Photos from ደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ /Dessie College Of Teachers Education's post 01/05/2026

የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ከ"ላይት ኢትዮጵያ" ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ

ደሴ፦ ሚያዝያ 23 ቀን 2018 ዓ.ም

የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ከተለያዩ አገር በቀል ድርጅቶች ጋር ያለውን አጋርነት ለማጠናከር በሚያደርገው እንቅስቃሴ፣ ዛሬ ሚያዝያ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከ"ላይት ኢትዮጵያ" አገር በቀል ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር የጋራ የሥራ መግባቢያ ሰነድ (MoU) ተፈራርሟል።

በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ኮሌጁን በመወከል የኮሌጁ ዲን ዶክተር ሀሰን ወርቁ የተገኙ ሲሆን፣ በ"ላይት ኢትዮጵያ" በኩል ደግሞ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ መላኩ በመገኘት ስምምነቱን አጽድቀዋል።

የኮሌጁ ዲን ዶክተር ሀሰን ወርቁ ለኮሌጁ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል እንደገለጹት፣ ይህ የመግባቢያ ሰነድ በዋናነት በአራት ቁልፍ ዘርፎች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፦
በትምህርትና ስልጠና፣
በጥናትና ምርምር፣
በሥራ ፈጠራ እንዲሁም
በማኅበረሰብ አቅም ግንባታ ዙሪያ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።

ይህ በሁለቱ ተቋማት መካከል የተደረገው ስምምነት ከዛሬው የፊርማ ዕለት ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት የሚጸና መሆኑ ተገልጿል።

ስምምነቱ በኮሌጁ የመማር ማስተማር ሂደት ላይ ተጨማሪ አቅም ከመፍጠሩም በላይ፣ ተማሪዎችና መምህራን በምርምርና በሥራ ፈጠራ ዘርፎች ሰፊ ዕድል እንዲያገኙ መንገድ የሚከፍት መሆኑም ታምኖበታል።

ደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ!

Photos from ደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ /Dessie College Of Teachers Education's post 29/04/2026

የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ የስፖርት ውድድር ፍጻሜ፦ የሒሳብ ትምህርት ክፍል የሁለቱም ዘርፎች የዋንጫ ባለቤት ሆነ
ደሴ፦ ሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም

በደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በስፖርት ክበባት አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየውና ሁሉንም የትምህርት ክፍሎች ያሳተፈው ዓመታዊ የስፖርት ውድድር በዛሬው ዕለት በደመቀ ሁኔታ ፍጻሜውን አግኝቷል። በውድድሩ የሒሳብ ትምህርት ክፍል በእግር ኳስና በቮሊቦል ዘርፎች ድርብ ድል በማስመዝገብ የዓመቱ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል።

የታየው ብቃትና የውጤት መረጃ
በጉጉት ሲጠበቅ በነበረው የእግር ኳስ የፍጻሜ ጨዋታ፣ የሒሳብ ትምህርት ክፍል ከሥነ-ጥበባት ትምህርት ክፍል ጋር ተገናኝተው የሒሳብ ትምህርት ክፍል ተጫዋቾች ባሳዩት ድንቅ ብቃት ተጋጣሚያቸውን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ የዓመቱን ዋንጫ በኩራት አንስተዋል። በተመሳሳይ በቮሊቦል ረገድም የሒሳብ ትምህርት ክፍል ሌላኛውን ድል በማስመዝገብ የሁለቱም ዘርፎች ሻምፒዮን መሆን ችሏል።

የሥነ-ጥበባትና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ክፍል ኃላፊ አቶ ይማም አራጌ እንደገለጹት፤ ውድድሩ የወንዶችን ተሳትፎ ብቻ ሳይሆን ከሁሉም ትምህርት ክፍሎች የተውጣጡ ሴት ተጫዋቾች በቮሊቦል የታዩበት ነበር። ኃላፊው አክለውም በቀጣይ ዓመታት የሴቶችን ተሳትፎ ይበልጥ በማጠናከር ተስፋ ሰጪ ስራዎች እንደሚሰሩ ጠቁመዋል።

ለውድድሩ ስኬት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦች በኮሌጁ ምክትል ዲኖችና በትምህርት ክፍሎች ተጠሪዎች አማካኝነት የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል። የአሸናፊው ቡድን የድል ዋንጫ ደግሞ በኮሌጁ ዲን ዶ/ር ሀሰን ወርቁ እጅ ተሰጥቷል።

የዕለቱ ኮከቦች፦
በውድድሩ ላይ የግል ብቃታቸውን ላሳዩ ተጫዋቾች ልዩ እውቅና የተሰጠ ሲሆን፦

አንዋር ሲራጅ፦ የእግር ኳስ ኮከብ ተጫዋች፤

መህዲ ጀማል፦ የውድድሩ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ፤

ታዲዎስ አሰፋ፦ የቮሊቦል ኮከብ ተጫዋች በመሆን ተሸልመዋል።

የዕለቱን የፍጻሜ ጨዋታ በዳኝነት የመሩት የኮሌጁ አንጋፋ መምህር አቶ አበበ ደሴ ሲሆኑ፣ ውድድሩ ፍጹም ስፖርታዊ ጨዋነት በታየበት ሁኔታ ተጠናቋል።

Photos from ደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ /Dessie College Of Teachers Education's post 26/04/2026

በደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለሁለት ቀናት ሲሰጥ የነበረው የጥናትና ምርምር ስልጠና ተጠናቀቀ
(ደሴ፤ ሚያዝያ 18/2018 ዓ.ም)

የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ የመምህራኑንና የሰራተኞቹን የጥናትና ምርምር አቅም ለማሳደግ ትላንት ሚያዝያ 17/2018 ዓ.ም የጀመረው ጥልቅ ስልጠና ዛሬ በስኬት ተጠናቋል። ስልጠናው በተለይም በዘመናዊ የቁጥር መረጃ ትንተና (Quantitative Data Analysis Software) ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነበር።

በወሎ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ በሆኑት በዶ/ር ግሩም ታረቀኝ የተሰጠው ይህ ስልጠና፤ ተሳታፊዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመራጭ የሆኑ የጥናት ሶፍትዌሮችን በመጠቀም እንዴት ጥራት ያለውና ሳይንሳዊ ምርምር ማካሄድ እንደሚችሉ ግንዛቤ ያስጨበጠ ነው።

የስልጠናው ዋና ዋና ነጥቦች፦
የቴክኖሎጂ ትግበራ፦ በጥናትና ምርምር ስራዎች ወቅት የሚገጥሙ ውስብስብ የቁጥር መረጃዎችን (Quantitative data) በሶፍትዌር የታገዘ ፈጣንና ትክክለኛ ትንተና መስጠት የሚያስችል ክህሎት ማስጨበጥ።

ለትምህርት ጥራት ያለው ፋይዳ፦ ኮሌጁ በምርምር የታገዘ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖረውና የትምህርት ጥራትን በሳይንሳዊ መንገድ ለማጎልበት የዲጂታል ምርምር መሣሪያዎች ያላቸውን ሚና መተንተን።
ተግባራዊ ልምምድ፦ ሰልጣኞች ላለፉት ሁለት ቀናት በንድፈ-ሃሳብና በተግባራዊ ልምምድ፣ አሁን ላይ ዓለም እየተጠቀመባቸው ባሉ ሶፍትዌሮች ዙሪያ ሰፊ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ተደርጓል።

ዶ/ር ግሩም ታረቀኝ በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ እንደገለጹት፣ ተቋማት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ከሚከተሏቸው መንገዶች አንዱና ዋነኛው መምህራንና ሰራተኞች በዘመናዊ የምርምር ስልቶች ራሳቸውን እንዲያበቁ ማድረግ ነው።

የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው፣ ላለፉት ሁለት ቀናት የወሰዱት ስልጠና ወቅታዊና ለስራቸው እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው፤ በተለይም በሶፍትዌር የታገዘ የምርምር ስልት መለመዱ የመረጃዎችን ተአማኒነትና የጥናቶችን ደረጃ ከፍ እንደሚያደርገው ገልጸዋል። ሰልጣኞቹ በቆይታቸው በንቃት በመሳተፍ ለወደፊት ስራዎቻቸው ግብዓት የሚሆን ልምድ አካብተዋል።
ይህ ስልጠና ኮሌጁ ለልማትና ለለውጥ የጀመረውን ጉዞ የሚያጠናክር ከመሆኑም ባለፈ፣ በምርምር ዘርፍ ያለውን ተወዳዳሪነት ከፍ እንደሚያደርገው ይጠበቃል።
የደሴ መምህራን ኮሌጅ !

Photos from ደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ /Dessie College Of Teachers Education's post 25/04/2026

የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት መምህራንና አመራሮች ስልጠና ሰጠ

(ደሴ፤ ሚያዝያ 17/2018 ዓ.ም)

የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት መምህራንና አመራሮች በተማሪዎች ልዩ ተሰጥኦና በተቋማዊ ውጤታማነት ዙሪያ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥቷል።

የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ሀሰን ወርቁ እና የአስተዳደርና ልማት ምክትል ዲን አቶ ደምሰው በሰጡት በዚህ ስልጠና፤ በተለይ የአዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ልዩ ተሰጥኦ መሰረት ያደረገ የማስተማር ስነ-ዘዴን መከተልና በማስረጃ ላይ የተመሰረተ የትምህርት ማሻሻያ (Evidence-based reform) ማካሄድ በሚቻልባቸው ስልቶች ላይ ሰፊ ግንዛቤ ተፈጥሯል።

ይህ ስልጠና በዋነኝነት የደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት አመራርና መምህራን ራሳቸውን ከሌሎች አገር በቀልና ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች ጋር በማነፃፀር፣ ያለባቸውን ክፍተት እንዲሞሉና አሰራራቸውን እንዲያስተካክሉ ለማስቻል የተዘጋጀ የግንዛቤ ማሻሻያ መድረክ ነው።

በስልጠናው ወቅት የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
የተሰጥኦ ማበልጸጊያ ስልቶች፦ መምህራንና አመራሮች ከተለመደው የአካዳሚክ ትምህርት ጎን ለጎን የተማሪዎችን ተፈጥሮአዊ ዝንባሌ መለየትና ማሳደግ በሚችሉባቸው ተግባራዊ መንገዶች ላይ ተሞክሮዎች ቀርበዋል።

ተቋማዊ ንጽጽር (Benchmarking)፦ ትምህርት ቤቱ ራሱን በሀገር ውስጥ ካሉ እንደ ቃለሚኖ፣ ኃይሌ ሚናስ እና የኦሮሚያ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ካሉ ተዛማጅ ተቋማት ጋር በማነፃፀር፣ ክፍተቶችን በመሙላት ተወዳዳሪ መሆን በሚችልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጓል።
ተቋማዊ ገቢን ማሳደግ፦ ተቋማት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የውስጥ ገቢ አቅማቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው ተመላክቷል። ለዚህም የኮሌጁ “ሀረጎ የንግድና የማማከ ኢንተርፕራይዝ” በኃላፊው አቶ ሙላት አገኝ አማካኝነት በእንስሳት እርባታና በትምህርት ዘርፍ እያከናወናቸው ያሉ የገቢ ማመንጫ ስራዎች ለሌሎች ተቋማት እንደ ጥሩ ተሞክሮ ተጋርተዋል።

ይህ ስልጠና የደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት መምህራንና አመራሮች የተማሪዎቻቸውን ሁለንተናዊ ብቃት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስና ተቋማዊ አሰራራቸውን ለማዘመን የሚያስችል አቅጣጫ አመላካች ሆኖ መጠናቀቁ ተገልጿል።

የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ!

04/10/2024
Photos from ደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ /Dessie College Of Teachers Education's post 24/09/2024

የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለመምህራንና ሰራተኞች የ2017 ዓ.ም የመሪ ዕቅድ ትውውቅ አደረገ፡፡

14/01/2017 ዓ.ም ፡- ደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ :-

የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በዛሬው ዕለት ለመምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች የዕቅድ ትውውቅ ያደረገ ሲሆን በኮሌጁ የእቅድ ዝግጅትና ሀብት አፈላላጊ ኦፊሰር አቶ መሀመድ አህመድ የዕቅድ ትውውቁ ሲቀርብ ከተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄወችና አስተያየቶችም በመድረኩ ላይ ተነስተዋል፡፡

የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ሀሰን ወርቁ በቀረው የዕቅድ ትውውቅ ላይ ለተነሱት ጥያቄወች ማብራሪያና የማጠቃለያ ሀሳብ ሰጥተዋል፡፡

እቅዱ በተሰጠው አስተያየት መሰረት ተስተካክለው ወደ ክልል ትምህርት ቢሮ የሚላክ ሲሆን የኮሌጁ ትምህርት ክፍሎችና የተለያዩ የስራ ሂደት ክፍሎች ከኮሌጁ እቅድ በመነሳት የራሳቸውን ዝርዝር እቅድ እስከ ትግበራ መርሀ-ግብር በማውጣት ወደስራ እንደሚገቡ በማጠቃለያ ንግግር ላይ ዶ/ር ሀሰን ወርቁ ሀሳብ የሰጡበት ሲሆን በተጨማሪም ለሚከወኑ ስራወችም ከዚህ በፊት ከነበረው በተሻለ የድጋፍ ክትትል እንደሚደረግም ገልጸው ፕሮግራሙ እንዲጠቃለል ሁኖአል፡፡

የኮሌጁ የሕዝብ ግንኙነት
መስከረም 2024 ዓ.ም

Photos from ደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ /Dessie College Of Teachers Education's post 18/09/2024

የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለትምህርት ቤቶች ድጋፍ አደረገ

08/01/2016 ዓ.ም ደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ፡-

የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በያዝነው አመት የትምህርት ግብአት ለመግዛት የአቅም ውስንነት ላለባቸው ተማሪወች የደብተርና የ እስክርቢቶ እገዛ አደረገ፡፡

በትላንትናው ዕለት በኩታበር ወረዳ ለሚገኘው ዶሽኝ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ 75 ተማሪወች ለእያንዳንዳቸው ሰባት /7/ የመማሪያ ደብተርና አምስት /5/ እስክርቢቶ በድምሩ 576 ደብተር እና 375 እስክርቢቶ በኮሌጁ ዲን ዶ/ር ሐሰን ወርቁ አማካኝነት ለትምህርት ቤቱ ር/መምህር ለ አቶ መሰረት አሰፋ ያበረከተ ሲሆን በዛሬው እለትም ደሴ ለሚገኘው ለአዲስ ፋና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ለ 75 ተማሪወች መማሪያ የሚሆን በተመሳሳይ 576 ደብተር እና 375 እስክርቢቶ የኮሌጁ ዲን ለ ት/ቤቱ ር/መምህር ለአቶ የሱፍ ሙሔ አበርክቷል፡፡

ኮሌጁ ለሁለቱም ትምህርት ቤቶች አጠቃላይ ለ150 ተማሪወች የደብትርና የእስክርቢቶ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ይህ አስተዋጽኦ በገንዘብ ሲሰላ አጠቃላይ 85,775 ብር ፈጅቷል፡፡

የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለትምህርት ቤቶች በተለያየ መስክ ድጋፍ እያደረገ ያለ ኮሌጅ ሲሆን ከዚህ በፊትም እንደሚያደርገው የትምህርት ጥራትን ለማምጣት የተለያዩ የት/ቤቶችን ር/መምህራንንና መምህራንን የአቅም ግንባታ ስልጠናወችን በመስጠት የበኩሉን ሚና እንደሚወጣ የ ኩታበር ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኡመር አሊ እና የ ደቡብ ወሎ ዞን የትምህርት ባለሙያ አቶ ቴወድሮስ ክፍሌ በተገኙበት የኮሌጁ ዲን ለትምህርት ቤቶች መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የደሴ መምህርን ትምህርት ኮሌጅ የሕዝብ ግንኙነት!

Photos from ደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ /Dessie College Of Teachers Education's post 05/07/2024

የአራተኛው ዙር አገር አቀፍ የሪሰርች ኮንፈረንስ በደሴ በመምህራን ትምህርት ኮሌጅ ተካሄደ

28/10/2016 ዓ.ም ደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ፡-

አራተኛው ዙር አገር አቀፍ የኮሌጆች የጥናትና ምርምር ሲምፖዚየም “Educational Research for Improving Educational Practices” በሚል መሪቃል በደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ አዘጋጅነት የተካሄደ ሲሆን ይህንን የጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ሐሰን ወርቁ የመክፈቻ ንግግር እና የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ አስጀምረውታል፡፡

የኮሌጁ ዲን እንደተናገሩት በዛሬው ዕለት በሚካሄደው የጥናትና ምርምር ሲምፖዚየም የሚቀርቡት ጥናቶች በመማር ማስተማር፣ በአካቶ ትምህርት፣ በማህበረሰብ አገልግሎት እና በስርዓተ-ትምህርት ግምገማ ዙሪያ ላይ ያተኮሩ እንደሚሆኑም ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም የኮሌጁ ዲን በክልሉ ፖለቲካዊ አለመረጋጋቶች ቢኖሩም ኮሌጁ ያለውን ጫና በመቋቋም መደበኛ ስራውን እየከወነና እንዲህ አይነት ሲምፖዝየም በማዘጋጀቱ የላቀ ደስታ እንደሚሰማው ተናግረው ወቅታዊ ሁኔታውን ተቋቁመው ከተለያዩ አካባቢወች ለመጡ ተሳታፊወችም ትልቅ አክብሮት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

ከወሎ ዩኒቨርሲቲ በተጋባዥነት የተገኙት የዕለቱ የፕሮግራሙ ጭብጥ መልዕክት አስተላላፊ ዶ/ር አሊ ያሲን በመማር ማስተማር ላይ ያተኮሩ ጥናትና ምርምሮች ላይ ከራሳቸው ተሞክሮና ልምድ በመነሳት ሰፋ ያለ ግንዛቤወችን ፈጥረዋል፡፡

በስተመጨረሻም ከተለያዩ የአገራችን ክፍል መጥተው በጥናትና ምርምሩ ላይ ተሳታፊ ለነበሩት በ ኮሌጁ ጥናትና ምርምር ዩኒት መሪ አስተባባሪነት የምስክር ወረቀት በኮሌጁ ዲንና ም/አካዳሚክ ዲን አማካኝነት በመስጠት በተከታታይ ለ ሦስት ቀናት ሲካሄድ የነበረውን የኮሌጁና አገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ሲምፖዝየም በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡

Photos from ደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ /Dessie College Of Teachers Education's post 03/07/2024

13ኛው ዓመታዊ የጥናትና ምርምር ሲምፖዝየም በደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በዛሬው ዕለት ተጀመረ
26/10/2016 ዓ.ም ደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ፡-

13ኛው ዓመታዊ የጥናትና ምርምር ሲምፖዝየም በዛሬው ዕለት በደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ዲን ዶክተር ሀሰን ወርቁ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የተከፈተ ሲሆን ከወሎ ዩኒቨርሲቲ የመጡ ምሁራኖችም በዳኝነት እየተሳተፉበት ይገኛሉ፡፡

የኮሌጁ ዲን በመክፈቻ ስነስርዓቱ እንደተናገሩት ይህ የጥናትና ምርምር ሲምፖዝየም በየዓመቱ የሚካሄድ መሆኑን ገልጸው በዚህ ዓመት የጥናትና ምርምር ተሳታፊዎች ቁጥር በተወሰነ መልኩ እንደቀነሰና ለዚህም ምክንያቱ በክልሉ ያለው ወቅታዊ ሁኔታመሆኑን አስታውሰው በዚህ ጫና ውስጥ ሆኖ ይህንን ጥናትና ምርምር ማከናወን የሚያበረታታና ለሌሎችም አርአያ ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል፡፡

ዶ/ሐሰን ወርቁ እንደተናገሩት የዚህ ሲምፖዝየም ዓላማ የጥናት ውጤቶችን ማጋራትከመሆኑም ባሻገር ተሳታፊወች ልምድ የሚያዳብሩበትና ሀሳብና አስተያየታቸውን በመግለጽ ለጥናትና ምርምሩ ዕድገት የላቀ ሚና እንዲጫወቱ ማድረግ መሆኑንም ገልጸዋል፤
ይህ በእነዲህ እያለ በነገው ዕለትም 4ኛው አገራዊ የጥናትና ምርምር ሲምፖዝየም እንደሚካሂያድ የኮሌጁ ጥናትና ምርምር ዩኒት መሪ አቶ ሙሐመድ ሰኢድ ገልጸዋል፡፡

የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ የሕዝብ ግንኙነት
ሰኔ 2016 ዓ.ም

Want your school to be the top-listed School/college in Dessie?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address

Dessie
Dessie