Dejen Polytecnic College

Call

Dejen Polytecnic College Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dejen Polytecnic College, College & University, dejen, Dejen.

የቴክኒክና ሙያ የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ እንደደረሰን በቅርቡ ምዝገባ እንጀምራለን።እስከዚያ ግን ምርጫዎ ብዙ ነዉ።ይምረጡ ያማክሩ ይወስኑ
22/09/2026

የቴክኒክና ሙያ የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ እንደደረሰን በቅርቡ ምዝገባ እንጀምራለን።እስከዚያ ግን ምርጫዎ ብዙ ነዉ።ይምረጡ ያማክሩ ይወስኑ

የደጀን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2018 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀምና የ2019 ዓ.ም ዕቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ::​የደጀን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የምስራቅ ጎጃም ዞን ስራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ አቶ ...
21/09/2026

የደጀን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2018 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀምና የ2019 ዓ.ም ዕቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ::

​የደጀን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የምስራቅ ጎጃም ዞን ስራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ አቶ ፀሐይ ቦጋለ፣ የኮሌጁ የማኔጅመንት አባላትና የዘርፍ ተጠሪዎች በተገኙበት የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2019 ዓ.ም ዕቅድ ትውውቅ መድረክ አካሂዷል።

​በመድረኩ የኮሌጁ ዲን አቶ ይትባረክ ገነት ባቀረቡት ሪፖርት፤ ባሳለፍነው በጀት ዓመት የተከናወኑ መልካም ተግባራትን እና አጋጥመው የነበሩ ማነቆዎችን አብራርተዋል። ዲኑ አክለውም የኮሌጁ ማህበረሰብ ያጋጠሙ ችግሮችን ተቋቁሞ አበረታች ተግባራትን ማከናወኑን ገልፀው፣ የ2019 ዓ.ም ዕቅድን ለማሳካት ከምንጊዜውም በላይ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
​የምስራቅ ጎጃም ዞን ስራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ አቶ ፀሐይ ቦጋለ በበኩላቸው በቀጣይ ትኩረት ሊሰጣቸው በሚገቡ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ ያስቀመጡ ሲሆን፣ ከነዚህም መካከል፡-
​አካታችነት ላይ በትኩረት መስራት፣
​ለተለያዩ ኢኒሸቲቮችና ልማቶች ትልቅ ትኩረት መስጠት፣
​የሰልጣኞች ልማት (ስልጠናና ክህሎት) ላይ አተኩሮ መስራት፣
​ተግባራትን በተሳካ ሁኔታ ለመከወን በቅንጅት መስራት፣
​እስካሁን ያልተፈታውና ትኩረት የሚሻው የኢንተርፕራይዝ አለማቋቋም ችግር ላይ በልዩ ሁኔታ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

​መስከረም 11/2019 ዓ.ም
የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኑኬሽን

ደጀን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ 2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የነባር ሰልጣኞች ምዝገባ ማካሄድ መጀመሩን ያበስራል።​📅  የምዝገባ ቀን፡ ከመስከረም 7 እስከ 11/2019 ዓ.ም📍  የምዝገባ ቦታ፡...
17/09/2026

ደጀን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ 2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የነባር ሰልጣኞች ምዝገባ ማካሄድ መጀመሩን ያበስራል።
​📅 የምዝገባ ቀን፡ ከመስከረም 7 እስከ 11/2019 ዓ.ም
📍 የምዝገባ ቦታ፡ ደጀን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሬጅስትራር ቢሮ
​⏰ ማሳሰቢያ፦ የምዝገባ ጊዜው የተወሰነ ስለሆነ በተጠቀሱት ቀናት ውስጥ በአካል በመቅረብ ፈጥነው እንዲመዘገቡ እናሳስባለን።
​«ለውጥን በሙያ፡ እድገትን በክህሎት!»
​ደጀን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሬጅስትራር

10/09/2026
28/08/2026

🎉 የምስራች ለደጀንና አካባቢዋ ስራ ፈላጊዎች! 🎉
​ቀደም ሲል ወደተለያዩ የአረብና መሰል ሀገራት ለስራ ለመሰማራት በደብረማርቆስ ከተማ በመሄድ የሳይኮሜትሪክ ቴስት (አሻራ) ይሰጡ እንደነበርና በደጀን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ስልጠና ይወስዱ እንደነበር ይታወቃል።
​ይህን እንግልት፣ የጊዜና የወጪ ብክነት ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት ሲባል አሁን አሻራ የመስጠት አገልግሎቱ በራሳችን በደጀን ከተማ ስራና ክህሎት ፅህፈት ቤት መጀመሩን በደስታ እናበስራችኋለን!
​📌 አሁንው መጥተው ይመዝገቡ!

🎓 ደጀን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ‎‎  ​🌟 የ2019 ዓ.ም የስልጠና ጥሪ ለ12ኛ ክፍል      አጠናቃቂዎች! 🌟‎‎​በዘመናዊ የስልጠና ቁሳቁሶችና በምቹ የመማሪያ ክፍሎች የተዘጋጀው ኮሌጃችን፤ ከደ...
27/08/2026

🎓 ደጀን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
‎
‎ ​🌟 የ2019 ዓ.ም የስልጠና ጥሪ ለ12ኛ ክፍል አጠናቃቂዎች! 🌟
‎
‎​በዘመናዊ የስልጠና ቁሳቁሶችና በምቹ የመማሪያ ክፍሎች የተዘጋጀው ኮሌጃችን፤ ከደረጃ 1 እስከ 5 በመደበኛ እና በማታ መርሃ-ግብር ስልጠና ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቋል።
‎​⚠️ ማሳሰቢያ፦ የቦታችን መጠን ውስን በመሆኑ ቀድመው እንዲዘጋጁ እናሳውቃለን!
‎​🔹 የረጅም ጊዜ መደበኛ እና የማታ ስልጠና ዘርፎች
‎​🌾 የግብርና ዘርፍ
‎​💻 የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (IT) ዘርፍ
‎​🏗️ የኮንስትራክሽን ዘርፍ
‎​🏭 የኢንዱስትሪያል ዘርፍ
‎​⚙️ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ
‎​🚗 የአውቶሞቲቭ ዘርፍ
‎​(የቴክኒክና ሙያ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ እንደደረሰን ዝርዝር የሙያ ዓይነቶችን በማስታወቂያና በሚዲያዎቻችን የምናሳውቅ ይሆናል።)
‎​⚡ የአጫጭር ጊዜ የስልጠና መርሃ-ግብሮች
‎​🖥️ ልዩ ልዩ ዲጂታል ስኪሎች (Digital Skills)
‎​🥬 የከተማ ግብርና
‎​🧵 የልብስ ስፌት
‎​🧱 የኮንስትራክሽን ስራዎች
‎​💼 ኢንተርፕረነርሺፕ (የስራ ፈጠራ) እና ሌሎችም...
‎
‎ለበለጠ መረጃ
‎
‎​📞 0587760056
‎
‎ facebook:https://www.facebook.com/profile.php?id=100083226282837
‎
‎Telegram:https://t.me/+rjoBdZj4nUBlMTM0​
‎
‎​📍 ደጀን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
‎ የብቃትና የክህሎት መገኛ!

በህዝብግንኙነትና ኮሙኑኬሽን

University

📌 በደጀን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የአሰልጣኞችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች የሱፐርቪዥን ስራ ተጀመረ!ሰኔ 15/2018 ዓ.ም (ደጀን)በደጀን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የክትትልና ድጋፍ ስርዓቱን ይበልጥ በማጠናከር...
22/06/2026

📌 በደጀን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የአሰልጣኞችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች የሱፐርቪዥን ስራ ተጀመረ!
ሰኔ 15/2018 ዓ.ም (ደጀን)
በደጀን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የክትትልና ድጋፍ ስርዓቱን ይበልጥ በማጠናከር የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ ያለመ የሱፐርቪዥን ፕሮግራም ዛሬ ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ተጀምሯል።
🎯 የሱፐርቪዥኑ ዋና ዓላማ፦
ይህ የሱፐርቪዥን ስራ በኮሌጁ ስር የሚገኙ አሰልጣኞችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ካስቀመጡት ተቋማዊ ዕቅድ አኳያ እስካሁን ምን ያህል ስራዎችን እንዳከናወኑ፣ አሁን ላይ ያሉበትን ተጨባጭ ደረጃ ለመገምገም እና በቀሪዎቹ ቀናት ምን ምን ተግባራትን በማከናወን ዕቅዳቸውን ሙሉ በሙሉ ማሳካት እንደሚችሉ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ነው። በተጨማሪም በስራ አፈጻጸማቸው እጅግ የላቁ እና ኮከብ የሆኑ ሰራተኞችን በመለየት ተገቢውን እውቅና ለመስጠት ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
👥 ሱፐርቪዥኑን የሚመሩት አካላት፦
ይህንን ወሳኝ የክትትል ስራ በዋናነት የተቋሙ ዋና ዲን እና የጥራት አረጋጋጭ ቡድን የሚመሩት ሲሆን፣ በአባልነት ደግሞ፦
ሁለት ምክትል ዲኖች፣
የሰው ሀብት ቡድን መሪ እና
የውስጥ ኦዲት ባለሙያዎች ተካተውበታል።
💡 ቀደም ሲል የተሰሩ ስራዎች፦
ይህ የሱፐርቪዥንና የኢንስፔክሽን ስራ ከመጀመሩ አስቀድሞ፣ አጠቃላይ የኮሌጁ ማህበረሰብ ስለ ሱፐርቪዥንና ኢንስፔክሽን ፅንሰ-ሀሳብ በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው ሰፊ የማስተማር እና ግንዛቤ የመፍጠር ስራ መከናወኑ ይታወሳል። ይህም አሁን ላይ እየተደረገ ያለው ድጋፍ በስኬት እንዲከናወን ትልቅ መሰረት ጥሏል።
ኮሌጁ በዚህ የሱፐርቪዥን ሂደት ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል፣ የታዩ ክፍተቶችን በጋራ በመሙላት እና በላቁ ሰራተኞቹ ላይ ተነሳሽነትን በመፍጠር የተቋሙን የትምህርትና ስልጠና ጥራት ይበልጥ ለማሳደግ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል።

ህዝብግንኙነትና ኮሙኑኬሽን

የደጀን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የአንድነት እና የጋራ መግባባት ፕሮግራም“አብሮ የበላን ጷግሜ አይሽረውም!”የደጀን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተቋሙን አንድነት ይበልጥ ለማጠናከር እና የጋራ የሥራ ስሜትን...
29/05/2026

የደጀን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የአንድነት እና የጋራ መግባባት ፕሮግራም
“አብሮ የበላን ጷግሜ አይሽረውም!”

የደጀን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተቋሙን አንድነት ይበልጥ ለማጠናከር እና የጋራ የሥራ ስሜትን ለመገንባት የሚያስችል የ “ጌት ቱጌዘር” (Get-together) ፕሮግራም ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም አካሂዷል።
የፕሮግራሙ ዋና ዋና ዓላማዎች፦

ተቋማዊ አንድነትን መፍጠር፦
በሠራተኞች መካከል ያለውን መተማመን እና የመቀራረብ ስሜት ማሳደግ።
የስትራቴጂ ግብ መምታት፦ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ፖሊሲና ስትራቴጂን በኮሌጃችን ውጤታማ በሆነ መንገድ ተግባራዊ ለማድረግ የጋራ መግባባት ላይ መድረስ።
የሥራ ተነሳሽነት፦ በአብሮነት የሚመነጨውን የሥራ ጥራት እና ውጤታማነት ከፍ ማድረግ።

ይህንን ጠቃሚ የጋራ ልብ ለማሳካት ትልቅ አቅም እንደሚሆን ታምኖበታል።

የደጀን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለላቀ የትምህርት ጥራትና ዲጂታላይዜሽን ቅድሚያ ሰጥቷል::የደጀን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የውስጥ ጥራት አረጋጋጭ ቡድን ለኮሌጁ ማህበረሰብ በሁለት ቁልፍ የቴክኒክና ሙያ ስ...
26/05/2026

የደጀን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለላቀ የትምህርት ጥራትና ዲጂታላይዜሽን ቅድሚያ ሰጥቷል::

የደጀን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የውስጥ ጥራት አረጋጋጭ ቡድን ለኮሌጁ ማህበረሰብ በሁለት ቁልፍ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና አጀንዳዎች ማለትም በሱፐርቪዥንና ኢንስፔክሽን እንዲሁም በዲጂታል ቤተ መጽሐፍት እሳቤዎች አደረጃጀትና አጠቃቀም ዙሪያ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጅቷል።

ኢንስትራክተር ካሳሁን ወንድሙ ባቀረቡት ሰነድ፡
የሱፐርቪዥንና ኢንስፔክሽን ዓላማዎች፣ የባለሙያ ሥነ-ምግባር እና መርሆች፣
የእነዚህ ሁለት ተግባራት አንድነትና ልዩነት፣
የዲጂታል ቤተ መጽሐፍት አስፈላጊነትና ውጤታማ የቤተ መጽሐፍት ባህሪያት በዝርዝር ቀርበዋል።

በመድረኩ የተገኙት የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ይትባረክ ገነት፣ ስልጠናው የኮሌጁን ጥራትና ደረጃ ለማሳደግ ያለውን ፋይዳ በመጠቆም፣ የኮሌጁን አቅም ለመገንባት እና ተወዳዳሪ ሆኖ ለመውጣት በሙያዊ ብቃት መታጠቅና የውስጥ አቅምን ማጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል። በተለይም ኮሌጁ ራሱን የቻለ ገቢ ማስገኘት እንዲችልና ከበጀት ጥገኝነት ለመላቀቅ የውስጥ አረጋጋጭ ቡድኑ እና መላው የኮሌጁ ማህበረሰብ በትኩረት እንዲሠሩ መልእክት አስተላልፈዋል።
በዕለቱ ከተሳታፊዎች የተነሱት ገንቢ ሀሳቦች ኮሌጁን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር የሚረዱ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፤ ይህ መድረክ ለኮሌጁ ቀጣይ የትምህርት ጥራት ማረጋገጥ ጉዞ ትልቅ አቅም የፈጠረ ሆኗል።

ግንቦት 18/2018ዓ.ም
ደጀን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ህዝብግንኙነትና ኮሙኒኬሽን

Address

Dejen
Dejen

Telephone

+251587760056

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dejen Polytecnic College posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share