Yebikat Drivers Training center

Yebikat Drivers Training center we make special professionals

21/12/2025
መንገድ ትራንስፖርት ትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ ቁጥር 557/2016 ስር የተዘረዘሩ የሚያስቀጡ ስህተቶች እነ የቅጣት ደረጃዎች ከስር ተቀምጧል።የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክ መቆጣጠሪያ የሚኒስት...
25/11/2025

መንገድ ትራንስፖርት ትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ ቁጥር 557/2016 ስር የተዘረዘሩ የሚያስቀጡ ስህተቶች እነ የቅጣት ደረጃዎች ከስር ተቀምጧል።

የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክ መቆጣጠሪያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ በአሽከርካሪዎች የሚፈጸሙ ጥፋቶችን በመዘርዘር ያስቀመጠ ሲሆን ለጥፋቶቹም ደረጃዎችን አስቀምጧል፡፡

ቀላል የሆኑ ጥፋቶች ማለትም እንደ ተሽከርካሪን ያለአግባብ መጎተት፣ ሄልሜት ሳያደርጉ ብስክሌት መንዳት፣ የተሟላ የመጀመሪያ እርዳታ መስጫ ኪትና የእሳት ማጥፊያ ሳይኖር የንግድ ተሽከርካሪ ማሽከርከር፣ የሚበኑ ወይም የሚበተኑ ነገሮችን ጭኖ ያለአግባብ ማሽከርከር፣ በትራፊክ መብራ ወይም መስቀለኛ መንገድ ላይ በልመና ለተሰማሩ ሰዎች ገንዘብ መስጠት፣ ከ13 አመት በታች የሆነን ህፃን ከአሽከርካሪው ጎን በሚገኘው አስቀምጦ ማሽከርከር የመሳሰሉ ጥፋቶች ሲሆኑ ለዚህም ጥፋት ለመጀመሪያ ጊዜ ከሆነ ለጥፋቱ1 ነጥብ ተመዝግቦበት እስከ 500 ብር የገንዘብ ቅጣት እንደሚጣልበት ተደንግጓል፡፡

በደረጃ ሁለት ላይ ተቀመጡ ጥፋቶች በመካከለኛ ደረጃ ላይ ያሉ ጥፋቶች ሲሆኑ እነሱም የተሟላ የጭነት ማቀፊያ /እስፖንድ/ ሳይኖር ጭነት ጭኖ ማሽከርከር፣ ጥሩንባ ያለአግባብ መጠቀም፣ በመንገድ ላይ ተሽከርካሪ ማጠብና ማሳጠብ፣ በተከለከለ ስፍራና ሁኔታ ተሽከርካሪን ማቆም፣ ከመጠን በላይ የሆነ ድምጽ እያሰሙ ወይም በጆሮ ማዳመጫ እያዳመጡ ማሽከርከር፣ በእግረኛ ላይ ውሃ መርጨት፤ ለእግረኛ ቅድሚያ መከልከል የመሳሰሉ ጥፋቶች ሲሆኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሆነ ለጥፋቱ 2 ነጥብ ተመዝግቦበት እስከ 1,000 ብር የገንዘብ ቅጣት ይቀጣል፡፡

ሌላው በሶስተኛ ደረጃ ላይ ያሉ ጥፋቶች ከባድ ጥፋቶች ሲሆኑ ይህም የጉዞ ረድፍን ወይም መስመርን ሳይጠብቁ ማሽከርከር፤ ከተሽከርካሪው የመጫን አቅም በላይ ትርፍ ሰው መጫን፣ ተንቀሳቃሽ ስልክ በእጁ ይዞ እያነጋገሩ ወይም መልእክት እየተጻጻፉ ወይም እያነበቡ ማሽከርከር፣ በጭነት ተሽከርካሪ በህግ ከተፈቀደው ውጪ ሰውን መጫን፣ የደህንት ቀበቶ ሳያስሩ ወይም ተሳፋሪዎች ማሰራቸውን ሳያረጋጋግጡ ማሽከርከር፣ ቀይ የትራፊክ መብራት መጣስ፣ በተከለከለ መንገድ ወይ አቅጣጫ ማሽከርከር፣ ጫት እየቃሙ ወይም አደንዛጅ እጽ ወስዶ ማሽከርከር የመሳሰሉ ጥፋቶች ሲሆኑ ለዚህም ጥፋት ለመጀመሪያ ጊዜ ከሆነ ለጥፋቱ 3 ነጥብ ተመዝግቦበት እስከ 1,500 ብር የገንዘብ ቅጣት እንደሚጣልበት በደንቡ ላይ ተደንግጓል፡፡ ነገር ግን አሽከርካሪው ለሁለተኛ ጊዜ እና ከዛ በላይ ያጠፋ እንደሆነ የቅጣት ነጥቦቹ እየተደመሩ የሚጣለውም ቅጣት ከፍ እያለ የሚሄድ ይሆናል፡፡

ሌላው በዚህ ደንብ ላይ ልዩ ደረጃ ያላቸው ጥፋቶችን የተቀመጡ ሲሆኑ እነዚህም ጥፋቶች ተሽከርካሪ በማሽከርከር በሰው ሕይወት፣ አካል እና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ፣ የአልኮል መጠጥ ጠጥቶ ማሽከርከር፣ በህግ ከተፈቀደው የፍጥነት መጠን በላይ በፍጥነት ማሽከርከር፣ አፈር፣ አሸዋ ድንጋይና ተመሳሳይ ነገሮችን የሚመለከተው አካል ሳይፈቅድ በተሽከርካሪ ወይም በእግረኛ መንገድ ላይ ማራገፍ፣ ጉዳት አድርሶ በቦታው ያለመቆም ወይም ባደረሰው የትራፊክ ጉዳት የተጎዳውን እና ሕክምና የሚያስፈልገውን ሰው ወደ ሕክምና በመውሰድ እንዲታከም አለማድረግ የመሳሰሉ ጥፋቶችን እንደየ ጥፈቱ ቅለት እና ክብደት መጠን እንዲሁም የጥፋቱ ነጥብ ከ8 እስከ 21 ነጥብ በሚሆንበት ጊዜ ከብር 1,500 አስከ 10,000 ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲሁም ከ6 ወር እስከ 1 አመት ከ6 ወር የሚደረስ እግደን ያካተተ ቅጣትን አካቷል፡፡

ደንቡ ሌሎች የደንብ መተላለፍ ጥፋቶችን አብዛኛውን ግዜ አሽከርካሪ ባልሆኑ ሰዎች የሚፈጸሙ ጥፋቶችን ያካተተ ሲሆን ይህም ከሚመለከተው አካል ፍቃድ ሳያገኙ በእጅ የሚገፋ ጋሪ በመንገድ ላይ መንዳት፣ በመንገድ ላይ እንስሳትን መንዳት፣ በተሽከርካሪ ላይ ተገቢ ያልሆነ አካል መጨመር ወይም ከተፈቀደለት ወንበር ውጪ መቀመጫ መጨመር፣ ከሚመለከተው አካል ፍቃድ ሳያገኝ ተሽከርካሪዎችን ወይም እግረኞችን የሚያውክ ቁሳቁስ ወይም ሸቀጥ በእግርኛ ወይም በተሽከርካሪ መንገድ ላይ ማስቀመጥ፣ የንግድ ሥራ መስራት፣ ያለፍቃድ የእግረኛ ወይም የተሽከርካሪ መንግድ መቆፈር፣ የአሽከርካር ብቃት ማረጋገጫ ሳይኖረው ተሽከርካሪ ማሽከርከር፣ ከፖሊስ በተሽከርካሪው ላይ የደረሰውን የጉዳት አይነት የሚገልጽ የጽሑፍ ማስረጃ ሳይቀበሉ ጥገና ማከናወን የመሳሰሉ ጥፋቶችን የሚያካትት ሲሆን እንደየ ጥፋቱ ቅለት እና ክብደት ከብር 100 እስከ ብር 20,000 በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እንደሚያስከጣ ተደንግጓል፡፡

ደንቡ በእግረኞች የሚፈጸሙ ጥፋቶችንም ያካተተ ሲሆን ተገቢ ጥንቃቄ ሳያደርጉ መንገድ ማቆረጥ፣ ለተሽከርከሪ የተፈቀደ መንገድ ላይ ያለበቂ ምክንያት መቆም ወይም መጓዝ፣ እግረኛ መንገድ በሌለበት መንገድ ቀኝ ጠርዝ ይዞ መጓዝ፣ ለእግረኛ መንግድ ተብሎ ከተከለለ መንግድ ውጪ መጓዝ፣ በብረትም ሆነ በግንብ ተለይተው የታጠሩ መንገዶች ዘሎ መንገድ ማቋረጥ፣ በጆሮ ማዳመጫ የተለያዩ ድምጾችን እያዳመጡ ማንገድ ማቋረጥ፣ ለእግረኛ ክልከል ነው የሚል ምልክት ባለበት መንገድ ወይም እግረኛ እንዳያቋርጥ በተከለከለበት የማሳለጫ ወይም የቀለበት መንገድ ማቋረጥ ከብር 100 እስከ በር 150 የሚያስቀጣ ነው፡፡
Via👉ፍትሕ ሚኒስቴር

With LEMI National Cement PLC – I'm on a streak! I've been a top fan for 6 months in a row. 🎉
29/10/2025

With LEMI National Cement PLC – I'm on a streak! I've been a top fan for 6 months in a row. 🎉

With LEMI National Cement PLC – I'm on a streak! I've been a top fan for 4 months in a row. 🎉
31/08/2025

With LEMI National Cement PLC – I'm on a streak! I've been a top fan for 4 months in a row. 🎉

10/05/2025

የመኪና እና የቤት ስም ዝውውርን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ የወጣ አዲስ መመሪያ! 01/09/2017

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የትኛውም የቤት መኪናም ሆነ የቤት ሽያጭ የሚያከናውን ሰው የገቢዎች ቢሮ ታክስ ክሊራንስ የማቅረብ ግዴታ የሚያደርግ መመሪያ አውጥቷል፡፡

ከዚህ በፊት ለ ኮድ3 ተሸከርካሪ ብቻ ሲጠየቅ የነበረው የታክስ ክሊራንስ በአዲሱ መመሪያ መሠረት የቤት መኪናም ሆነ የግል መኖሪያ ቤት ለመሸጥ ከአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ ግዴታ መሆኑን ከመመርያው አግኝተናል።

07/05/2025

በብቃት ምዘና‼️
" የሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ ያልያዘ አሽከርካሪ ማሽከርከር አይችልም " - የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር‼️

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ፥ " ከያዝነው ዓመት ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ የአሽከርካሪዎች የሙያ ብቃት ምዘና ይጀመራል " ሲል አሳወቀ።

የብቃት ምዘናውን መስጠት ያስፈለገው 83 በመቶ በሀገሪቱ እየደረሰ የሚገኘው የትራፊክ አደጋ ከአሽከርካሪዎች እና ተሽከርካሪዎች ጋር የሚያያዝ በመሆኑ ነው ብሏል።

ይህን ተከትሎም በዚህ ዓመት ምዘናው ሥራ ላይ ባሉ አሽከርካሪዎች እንደሚጀመር አረጋግጧል።

በዚሁ መሠረት በሕዝብ እና ደረቅ ጭነት ከ1 እስከ 3 ባሉ ደረጃዎች እንዲሁም ለፈሳሽ 1 እና 2 አሽከርካሪዎች የሙያ ብቃት ምዘና እንደሚሰጥ ተገልጿል።

የሙያ ብቃት ምዘና ከመሰጠቱ በፊት ለአሽከርካሪዎቹ የሙያ ስልጠና ይሰጣቸዋል ተብሏል።

ከስልጠናው በኋላ የሙያ ብቃት ምዘና (ሲኦሲ) እንደሚወስዱ እና ፈተናውን ያለፉት መንጃ ፈቃዳቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት እንደሚኖረው ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በሌላ በኩል የሙያ ብቃት ምዘና ፈተናውን ወስደው ያላለፉ አሽከርካሪዎች እንደገና ስልጠና ወስደው ድጋሚ ይፈተናሉ ብሏል።

የሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ ያልያዘ አሽከርካሪ ማሽከርከር እንደማይችልም አሳውቋል።
በቀጣይም የሙያ ብቃት ምዘናው ታክሲን ጨምሮ በሌሎቹም አሽከርካሪዎች ላይ ይተገበራል ተብሏል።
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉
************************
ትኩስ ያልተሰሙ ዜናዎችን ማግኘት ከፈለጉ ቻናላችንን join አድርጉ+ለሌሎች ጋብዙ👇
https://t.me/debrebirhanviews
https://t.me/debrebirhanviews

With LEMI National Cement PLC – I just got recognized as one of their top fans! 🎉
07/05/2025

With LEMI National Cement PLC – I just got recognized as one of their top fans! 🎉

07/05/2025

" የሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ ያልያዘ አሽከርካሪ ማሽከርከር አይችልም " - የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ፥ " ከያዝነው ዓመት ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ የአሽከርካሪዎች የሙያ ብቃት ምዘና ይጀመራል " ሲል አሳወቀ።

የብቃት ምዘናውን መስጠት ያስፈለገው 83 በመቶ በሀገሪቱ እየደረሰ የሚገኘው የትራፊክ አደጋ ከአሽከርካሪዎች እና ተሽከርካሪዎች ጋር የሚያያዝ በመሆኑ ነው ብሏል።

ይህን ተከትሎም በዚህ ዓመት ምዘናው ሥራ ላይ ባሉ አሽከርካሪዎች እንደሚጀመር አረጋግጧል።

በዚሁ መሠረት በሕዝብ እና ደረቅ ጭነት ከ1 እስከ 3 ባሉ ደረጃዎች እንዲሁም ለፈሳሽ 1 እና 2 አሽከርካሪዎች የሙያ ብቃት ምዘና እንደሚሰጥ ተገልጿል።

የሙያ ብቃት ምዘና ከመሰጠቱ በፊት ለአሽከርካሪዎቹ የሙያ ስልጠና ይሰጣቸዋል ተብሏል።

ከስልጠናው በኋላ የሙያ ብቃት ምዘና (ሲኦሲ) እንደሚወስዱ እና ፈተናውን ያለፉት መንጃ ፈቃዳቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት እንደሚኖረው ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በሌላ በኩል የሙያ ብቃት ምዘና ፈተናውን ወስደው ያላለፉ አሽከርካሪዎች እንደገና ስልጠና ወስደው ድጋሚ ይፈተናሉ ብሏል።

የሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ ያልያዘ አሽከርካሪ ማሽከርከር እንደማይችልም አሳውቋል።

በቀጣይም የሙያ ብቃት ምዘናው ታክሲን ጨምሮ በሌሎቹም አሽከርካሪዎች ላይ ይተገበራል ተብሏል።

መረጃው የኤፍ ኤም ሲ ነው።

Celebrating my 8th year on Facebook. Thank you for your continuing support. I could never have made it without you. 🙏🤗🎉
14/04/2025

Celebrating my 8th year on Facebook. Thank you for your continuing support. I could never have made it without you. 🙏🤗🎉

Address

Near Debre Birhan Referral Hospital
Debre Birhan
03STREET

Telephone

+251911776969

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yebikat Drivers Training center posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category