Information Systems2003

Website

Information Systems2003 Practical Knowledge for better success

Information Systems Program Structure
02/07/2026

Information Systems Program Structure

Internal Review for National Accreditation═══════ ❁✿❁ ═══════​Department of Information Systems at Debre Berhan Universi...
27/06/2026

Internal Review for National Accreditation
═══════ ❁✿❁ ═══════​
Department of Information Systems at Debre Berhan University conducted an internal review of its educational programs from June 26–27/2026.

የኮምፒውቲንግ ኮሌጅ በአምስት የትምህርት ፕሮግራሞች ብሔራዊ እውቅና ለማግኘት የሚያስችለውን የቅድመ-ምዘና ወርክሾፕ አካሄደ‎═══════ ❁✿❁ ═══════‎​ደብረ ብርሃን - ሰኔ 15/2018...
27/06/2026

የኮምፒውቲንግ ኮሌጅ በአምስት የትምህርት ፕሮግራሞች ብሔራዊ እውቅና ለማግኘት የሚያስችለውን የቅድመ-ምዘና ወርክሾፕ አካሄደ
‎═══════ ❁✿❁ ═══════
‎​ደብረ ብርሃን - ሰኔ 15/2018 ዓ.ም (ደ.ብ.ዩ)
‎​የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የኮምፒውቲንግ ኮሌጅ በኮምፒውተር ሳይንስ፣ ኢንፎርሜሽን ሲስተምስ፣ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ እና ዳታ ሳይንስ በድምሩ በአምስት የትምህርት ፕሮግራሞች ብሔራዊ እውቅና (Accreditation) ለማግኘት የሚያስችለውን ውስጣዊ የቅድመ-ምዘና ወርክሾፕ ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው የህዝብ ግንኙነት አዳራሽ በይፋ አካሄደ።
‎
‎​በወርክሾፑ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ሰብለወንጌል እሰይነው በሂደቱ የኮሌጁን የትምህርት ጥራትና የአሠራር ሂደት ደረጃውን የጠበቀ ለማድረግ እጅግ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
‎
‎ዶ/ር ሰብለወንጌል በአጽኖት እንደተናገሩት የብሔራዊ እውቅና መመዘኛዎችን ማሟላት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን ተማሪዎች በሥራ ገበያ ላይ ተወዳዳሪና ቀጣሪ አካላት የሚፈልጉትን የክህሎት ደረጃ ያሟሉ ብቁ ባለሙያዎች እንዲሆኑ ለማድረግ መሠረታዊ ፋይዳ አለው።
‎
‎​ኮሌጁ የሚያቀርባቸው የትምህርት ፕሮግራሞች የተማሪዎችን ፍላጎትና የማኅበረሰቡን ጥያቄ መሠረት ያደረጉ መሆናቸውን በመግለጽም የኮሌጁ ዲን ለሁሉም ፕሮግራሞች አስቀድሞ ጥራቱን የጠበቀ የፍላጎት ጥናት መካሄዱን ጠቁመዋል።
‎
‎አክለውም ኮሌጁ ለእነዚህ ፕሮግራሞች ውጤታማ አተገባበር የሚረዱ ዘመናዊ ቤተ-ሙከራዎችን እና አስፈላጊ የትምህርት መርጃ መሣሪያዎችን አሟልቶ እየሠራ መሆኑንና ለብሔራዊ እውቅና ማረጋገጫው የሚያስፈልጉ ዋና ዋና የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በአግባቡ መከናወናቸውን አስረድተዋል።
‎
‎​በመድረኩ ከተሳታፊዎች አስተያየቶችና ጥያቄዎች የተሰበሰቡ ሲሆን በሰነዶቹ ላይ ለሚደረጉ ማሻሻያዎች እንደግብአት ያገለግላሉ ብለዋል። አክለውም በየደረጃው በሚገኙ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራር አካላት ታይተው እንደሚጸድቁና ቀጣይ የብሔራዊ እውቅና የማረጋገጥ ሂደቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ዶ/ር ሰብለወንጌል አብራርተዋል።
‎
‎​የወርክሾፑን የቀጣይ አቅጣጫ በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት የኮሌጁ ም/ዲን ዶ/ር ጌታቸው መኩሪያ በቀጣይ የኮሌጁ ትኩረት የሰነዶቹን ጥራት ይበልጥ በማሳደግና የተቀመጡትን መመዘኛዎች በማሟላት ሂደት ላይ እንደሚሆን በመግለጽ ፕሮግራሙን በይፋ ደምድመዋል።
‎
‎​በመጨረሻም ባለፉት አራት ወራት ይህንን ትልቅ ግብ ለማሳካት የተከናወኑት ተግባራት የትምህርት ክፍሎች፣ መምህራን፣ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎችና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ጥረት ውጤት መሆኑን በመጥቀስ ዶ/ር ሰብለወንጌል ለሁሉም አካላት ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
‎
‎​የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈጻሚ See less

30/08/2018 የተማሪዎችን የፈጠራ አቅም ለማሳደግ ያለመ የፕሮጀክት አጻጻፍ ስልጠና በኢንፎርሜሽን ሲስተምስ ዲፓርትመንት ተሰጠ:የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የኮምፒውቲንግ ኮሌጅ የኢንፎርሜሽን...
09/05/2026

30/08/2018
የተማሪዎችን የፈጠራ አቅም ለማሳደግ ያለመ የፕሮጀክት አጻጻፍ ስልጠና በኢንፎርሜሽን ሲስተምስ ዲፓርትመንት ተሰጠ:

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የኮምፒውቲንግ ኮሌጅ የኢንፎርሜሽን ሲስተምስ ዲፓርትመንት፣ ለተመራቂ ተማሪዎች ውጤታማ እና ጥራት ያለው የፕሮጀክት አጻጻፍ ስልጠና ሰጠ። ስልጠናው ተማሪዎች በቆይታቸው ያገኙትን የንድፈ-ሀሳብ እውቀት በተግባር ወደ ሚታይ የፈጠራ ስራ እንዲቀይሩ እና ለነገው የሥራ ዓለም ዝግጁ እንዲሆኑ ለማድረግ ያለመ ነው።
የስልጠናው ዓላማና ፋይዳ
የኢንፎርሜሽን ሲስተምስ ዲፓርትመንት ኃላፊ ወ/ሮ ሂሩት ሸዋቀና በስልጠናው መክፈቻ ላይ እንደገለጹት፣ ይህ ስልጠና ተማሪዎች የመመረቂያ ፕሮጀክታቸውን በከፍተኛ ጥራትና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እንዲያዘጋጁ ትልቅ እገዛ ያደርጋል። ወ/ሮ ሂሩት አክለውም፦ የዲፓርትመንታችን ዋነኛ ግብ ተወዳዳሪና ችግር ፈቺ የሆኑ ባለሙያዎችን ማፍራት በመሆኑ፣ ተማሪዎች የሚያዘጋጇቸው ፕሮጀክቶች ከወረቀት ባለፈ የህብረተሰቡን ችግር የሚፈቱ ቴክኖሎጂዎች እንዲሆኑ እንፈልጋለን ብለዋል።
የስልጠናው ይዘት
ስልጠናውን የሰጡት መምህር ታደሰ በየነ ሲሆኑ፣ በቆይታቸውም ተማሪዎች ከመነሻው የፕሮጀክት ርዕስ አመራረጥ ጀምሮ እስከ መጨረሻው የሪፖርት አጻጻፍ እና የሲስተም ልማት ሂደት (System Development Life Cycle) ድረስ ሊከተሏቸው ስለሚገቡ ሳይንሳዊ መንገዶች ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በተለይም፦
 ትክክለኛውን ችግር መለየት (Problem Identification)፣
 የተጠቃሚዎችን ፍላጎት በጥልቀት መተንተን (Requirement Analysis)፣
 ዘመናዊ የዲዛይን ስልቶችን መጠቀም፣
 እና ጥራት ያለው ሰነድ (Documentation) ማዘጋጀት በሚሉ ነጥቦች ላይ ትኩረት ተደርጓል።
የተማሪዎች ተሳትፎ
በስልጠናው ላይ የተሳተፉ ተመራቂ ተማሪዎች ስልጠናው በፕሮጀክት ሥራቸው ላይ ለነበረባቸው ግርታ ምላሽ የሰጠ መሆኑን ገልጸው፣ በተለይም ከመምህራኖቻቸው ጋር የነበራቸው ውይይት ለቀጣይ ሥራቸው መነሳሳትን እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል።

Below are the 9 standards of the ETA.
24/04/2026

Below are the 9 standards of the ETA.

Information Systems @ College of Computing Accreditation Team
23/04/2026

Information Systems @ College of Computing Accreditation Team

15/08/2018 ዓ/ምየኮምፒውቲንግ ኮሌጅ የኢንፎርሜሽን ሲስተምስ ትምህርት ክፍል የተማሪዎች የዕርካታ ዳሰሳ (Student Satisfaction Survey) የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ...
23/04/2026

15/08/2018 ዓ/ም

የኮምፒውቲንግ ኮሌጅ የኢንፎርሜሽን ሲስተምስ ትምህርት ክፍል የተማሪዎች የዕርካታ ዳሰሳ (Student Satisfaction Survey) የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ
የኢንፎርሜሽን ሲስተምስ የዕውቅና (Accreditation) ኮሚቴ ከተማሪዎች ጋር የነበረውን ግንኙነት ለማጠናከርና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
የመድረኩ ዋና ዋና ኩነቶች፦
• የመክፈቻ ንግግር፡ የትምህርት ክፍሉ ኃላፊ ወ/ሮ ሂሩት ሸዋቀና እና የትምህርት ክፍሉ ሎካል ፐርሰን አቶ ዘሪሁን ጸጋዬ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፤ በንግግራቸውም የተማሪዎች አስተያየት ለትምህርት ክፍሉ ዕድገትና ለውሳኔ አሰጣጥ ያለውን ከፍተኛ ፋይዳ አብራርተዋል።
• ስለ ዕውቅና (Accreditation)፦ ወ/ሮ ቃልኪዳን ጌታመሳይ ስለ አክሬዲቴሽን ምንነት፣ ስለ ጥራት መለኪያዎችና ተቋማዊ ዕውቅና ለተማሪዎች የወደፊት የሥራ ዕድል ያለውን ጠቀሜታ በተመለከተ ሰፋ ያለ ገለጻ አቅርበዋል።
• የዳሰሳ ጥናቱ አስፈላጊነት፦ አቶ ታደሰ በየነ ስለ 'Student Satisfaction Survey' ምንነት፣ ተማሪዎች ቅጻቸውን እንዴት መሙላት እንዳለባቸውና ጥናቱ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ያለውን ሚና የሚዳስስ የውይይት ሃሳብ አቅርበው ከተማሪዎች ጋር ውጤታማ ቆይታ አድርገዋል።
ይህ መድረክ ተማሪዎች በትምህርት ሂደቱ ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ከማሳደጉም በላይ፣ የትምህርት ክፍሉ ሀገርአቀፍ የጥራት ደረጃውን ጠብቆ እንዲቀጥል ትልቅ እገዛ ያደርጋል።
"የተማሪዎቻችን ድምፅ ለጥራት መሻሻል መሰረት ነው!"

13/08/2018 ዓ/ምየኮምፒውቲንግ ኮሌጅ ኢንፎርሜሽን ሲስተምስ ት/ክፍል የእውቅና ኮሚቴ ከት/ክፍሉ ጋር በመሆን በቀን 12 እና 13  ባደረጉት የኮምፒውተር ላብራቶሪዎች ያሉበትን ሁኔታና ወ...
21/04/2026

13/08/2018 ዓ/ም
የኮምፒውቲንግ ኮሌጅ ኢንፎርሜሽን ሲስተምስ ት/ክፍል የእውቅና ኮሚቴ ከት/ክፍሉ ጋር በመሆን በቀን 12 እና 13 ባደረጉት የኮምፒውተር ላብራቶሪዎች ያሉበትን ሁኔታና ወደፊት ለላቦቹ መማሟላት እና መስተካከል ያለባቸውን ስራዎች የልየታ ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡ ይህን በተመለከተ ለቀጣይ 2 ወራት የት/ት ክፍሉ ከኮሌጁ ጋር በመተባበር አስፈላጊ ግብዓቶችን በማሟላትና በማስተካከል የተሻል ስራ እንደሚሰራ ተስፋ እናደርጋለን፡፡

Address

Debre Berhan
Debre Birhan

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Information Systems2003 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category