10/04/2026
እንኳን አደረሳችሁ ጥበብ በእሱ ኮሌጅ
"ትምህርት የፈጠራ ውጤት ነው!"
ለጥበብ በእሱ ኮሌጅ ተማሪዎች፣ ለመማር ማስተማር ሂደቱ ስኬት ሌት ተቀን ለምትተጉ የአስተዳደርና የድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች፣ ዕውቀታችሁን ለምታካፍሉ መምህራን እንዲሁም ሁልጊዜም ከጎናችን ለቆማችሁ ደጋፊዎቻችን በሙሉ፤
እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ!
የትንሳኤው በዓል ለተቋማችን አዲስ ጥንካሬን፣ ለተማሪዎቻችን ብሩህ ተስፋን፣ ለሠራተኞቻችንና ለመምህራኖቻችን ደግሞ የሥራ መነሳሳትን ይዞ እንዲመጣ እንመኛለን። በዓሉ የፍቅር፣ የሰላምና የደስታ ይሁንላችሁ!
• ለተማሪዎቻችን፦ የትንሳኤው ብርሃን ለትምህርታችሁ ስኬትና ለነገው ብሩህ ተስፋችሁ መሠረት ይሁንላችሁ።
• ለአስተዳደርና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች፦ ተቋማችን ውጤታማ እንዲሆን ለምታደርጉት ያልተቆጠበ ጥረት ምስጋናችን የላቀ ነው። እንኳን አደረሳችሁ።
• ለጥበብ በእሱ ኮሌጅ መምህራን፦ በትውልድ ግንባታ ሂደት ላይ ለምታሳዩት ትጋትና ለምታካፍሉት ዕውቀት ትልቅ አክብሮት አለን።
• ለደጋፊዎቻችን፦ በጉዟችን ሁሉ አጋር ለሆናችሁን ሁሉ በዓሉ የበረከት ይሁንላችሁ።
የትንሳኤው ብርሃን ቤታችሁንና ልባችሁን በደስታ ይሙላው!
ጥበብ በእሱ ኮሌጅ - ዳንግላ