Ridwan Mudessir Seid

Ridwan Mudessir Seid I haven't

07/04/2026
05/04/2026
18/03/2026

🌙 Crescent Sighting Across the Kingdom

Dammam is known as the first city in the Kingdom of Saudi Arabia where the crescent of Eid al-Fitr can be sighted, due to its eastern location.

Meanwhile, Tabuk becomes the last city where the sighting process ends, as it is among the final regions where the sun sets in the Kingdom.

This sequence allows observation committees across the country to monitor the crescent progressively from east to west.

May Allah allow us to witness the blessed crescent and accept our fasting and prayers.

16/03/2026

“ወድቆ መቅረት የለም”፤ ከሥልጣን እስከ መቄዶንያ
+++++++++++++++++++

| ሕይወት እንዲህ ናት፤ ከፍታን በቀኟ ከያዘች በግራዋ ዝቅታን ይዛ እንካችሁ ማለት ልመዷ ነው።

ይህ አባባል የቀድሞው ባለስልጣን አሁን በመቄዶንያ በጎ አድራጎት ማኅበር አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑት የአቶ መላኩ አሰፋ የሕይወት ምስክርነት ሊሰጡበት የሚያስችል ነው።

አቶ መላኩ አሰፋ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመርቀው ሲወጡ ትልቅ ራዕይ አንግበው ነበር የወጡት።

በኢትዮጵያ ማዕድን ሀብት ልማት ኮርፖሬሽን ውስጥ ለ10 ዓመታት በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች አገልግለዋል። የኢትዮጵያን ሠራተኞች ኮንፌዴሬሽንን በምክትል ፕሬዝዳንትነት መርተዋል፡፡

በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞችን ወክለው ከሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትርና ሚኒስትሮች ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ ተደራድረዋል፤ ተወያይተዋል።

የሰው ልጅ ሕይወት ሁልጊዜ አልጋ በአልጋ አይደለምና በኋላ ግን የአቶ መላኩ ሕይወት በዚህ ልትቀጥል አልቻለችም።

አቶ መላኩን ከባድ የአዕምሮ ሕመም ገጠማቸው። ያ ሁሉ ዝና፣ ያ ሁሉ ሥልጣንና እውቀት በሕመሙ ጥላ ሥር ተሸፈነ።

በአንድ ወቅት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞችን መብትና ጥቅም ለማስከበር የሚሟገቱት ግለሰብ፣ ሕመም አሸንፏቸው ጎዳና ላይ ለመውደቅ በቁ።

ከውድቀትም በኋላ ትንሳኤ ከሕመምም በኋላ ፈውስ አለና አቶ መላኩ በሕመሙ ተሸንፈው አልቀሩም። ወደመቄሄዶንያ ገቡ፡፡

በመቄዶንያ በጎ አድራጎት ማኅበር ባገኙት ፍቅር፣ እንክብካቤና ሕክምና ዳግም ለመወለድም ታደሉ። አእምሯቸው ተመልሶና ማንነታቸውን መልሰው በማግኘት ዛሬ ለመቄዶንያ ትልቅ ውለታ እየመለሱ ይገኛል።

በአሁኑ ጊዜ አቶ መላኩ በመቄዶንያ ውስጥ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያና የስክሪፕት ጸሐፊ ናቸው።

በፋና እና በተለያዩ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች በሚተላለፉ የመቄዶንያ የአየር ሰዓቶች ላይ ከ70 በላይ ስክሪፕቶችን አዘጋጅተዋል። በተጨማሪም ዶክመንተሪዎችንና ቃለ መጠይቆችን በብቃት ያከናውናሉ።

አቶ መላኩ መቄዶንያ ከበጎ አድራጎት ማኅበርነት አልፎ ወደ "ቻሪቲ ቪሌጅ" (Charity Village) እንዲያድግ የራሳቸውን ሙያዊ አስተዋጽኦ ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውን ያስረዳሉ።

"መቄዶንያ የኢትዮጵያውያን የበጎነት ጥግ የታየበት፣ የሀገርን ሸክም የተሸከመ ተቋም ነው" ሲሉ መቄዶንያን ይገልጹታል።

"እኔ ድኜ ዛሬ እዚህ ሥራ ላይ ብገኝም፣ ነገ ለማንም ምን እንደሚመጣ አይታወቅም። ስለዚህ ሰውን አትናቁ፣ መቄዶንያን ደግሞ ደግፉ" ሲሉም መልእክታቸውን ያስተላልፋሉ።

በክቡር ዶክተር ቢኒያም በለጠ የተመሰረተው መቄዶንያ እንደአቶ መላኩ አይነት በርካታ የሕይወት ውጣ ውረድ ያሳለፉ ግለሰቦችን ያስጠለለ ተቋም ነው፡፡

ተቋሙ በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በክልል ከተሞችም ቅርንጫፎችን ከፍቶ ሰውን ከጎዳና እያነሳ እየጦረ ይገኛል፡፡

መቄዶንያ ከመጋቢት 6 ጀምሮ የገበያ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ያዘጋጀ ሲሆን፤ ይህም ተቋሙ ለጀመረው ባለ 15 ወለል ሆስፒታል እና በክልል ከተማ እየተገነቡ ላሉ ቅርንጫፎች ማስጨረሻ የሚሆን ነው፡፡

መላው ኢትዮጵያውያንና ሌሎችም በገቢ ማሳባሰቢያው በመሳተፍ ተቋሙን እንዲያግዙ ጥሪ ቀርቧል፡፡

በሄለን ወንድምነው
++++++++++++++++++++++++++

#መቄዶንያ #ተስፋ #ኢትዮጵያ #ሰብአዊነት

17/01/2025

With Jemush Kemal – I just got recognized as one of their top fans!

ለዳላስ አለመስጠት ይቻላልን?  በእርግጥ ዳሎቻ የሚለው ቃሉ የሶስት ፊደላት ስብስብ ነው። አሻራውንና   የነዚህን ሶስት ቃላት ስብስብ እምቅ አቅም መግለፅ ግን እጅግ በጣም ከባድ ነው።  ስለ...
10/01/2025

ለዳላስ አለመስጠት ይቻላልን?
በእርግጥ ዳሎቻ የሚለው ቃሉ የሶስት ፊደላት ስብስብ ነው። አሻራውንና የነዚህን ሶስት ቃላት ስብስብ እምቅ አቅም መግለፅ ግን እጅግ በጣም ከባድ ነው። ስለዳላስ ከብዙ በጥቂቱ ዬትም ተወለድ/ጂ ዳላስ ግን እደግ/ጊ ነው። የአብሮነትን፣ የመቻቻልን፣ የፍቅር ጥግን ተምረህ/ሽ ታስተምረለህ/ሪየለሽ። ዳላስ ብቻዋን የሙሉ ስልጤ ማንነት ነፀብራቅ ናት። ዳላስ ድሬ ናት መስክሩ የነገዳችሁባት መስክሩ ያስተማራችሁባት መስክሩ የተማራችሁባት፣ መስክሩ ያከማችሁባት፣ መስክሩ ግብርናን የቆረቆረችሁ፣ መስክሩ የያኔው አክሽን ኤይዶችም፣ መስክሩ ለስልጤ ዞን ጎጆ የቀለሳችሁባት (ታላቁ ሰው እና ክቡር አቶ ስራጅ ፈጌሳ፣ ዲፕሎማቱ አንደበተ ርቱ እና ክቡር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፣ ኢንተር ፕረነሯ እና ጊስቲት ሙፈሪያት፣ የግብርናው መሃንዲስ እና ክቡር አቶ ኡስማን ሱሩር ..........) መስክሩ፣ የመራችሁባት/የመራቹሁዋት ለዳላስ ያየ የሰማ ማም ይሁን ማ? አለመስጠት አይቻልም አንድ ላይ በሉና መስክራችሁ መስክሩ በሉ።

ዳሎቻ ትጣራለች ዬት አላችሁ? ዉለታዬን መልሱ! አስመልሱ! ትላለች። እናት ሆኜ! እናንተን ሁሉ አርግዤ! አምጬ ወልጄ! ለወግ ለማእረግ አብቅቼ! ይሀው አለሁ እንደተጎሳቆልኩ! ግን ለምን?

ኡሚ/እማ/ እናትዬ በቃሽ ጉስቁልና! ይመርብሽ! ተዋቢ ተሞሽሪ! በሉ።
ውድ የዳላስ ልጆችና ወዳጆች መኖር ማግኘት መማር መመራመርና ሀያልነት ትርጉሙ ትግበራው ኡሚ/እማ አንቺን ማስዋብ ነዉ ለእኛ በአንድነት በሉ።

ዳሎቻ የእውነትም ልዩ ናት!! የሁሉም እናት!! የመሃንዲሶች፣ የሃኪሞች .....,

ኖረን ሞት ላይቀር በተባበረ ክንድ ዳላስን ሞሽረን ዘመን ተሻጋሪ ታሪክ እንስራ!
መመስከሪያው መሞሽሪያው ቀጥሎ ባሉት ቁጥሮች ነው።

በመጨረሻም ስማችሁን የጠቀስኳችሁ አይከኖቻችን በጣም ይቅርታ

ይህቺ ዳላስ ናት!
07/01/2025

ይህቺ ዳላስ ናት!

መቼም ቢሆን ማንም በእናቱ አይጨክንም የምንችለውን ሁሉ እናድርግ!!  ዳሎቻ ስሟ እንጂ እናትዬ/ታችን ኡሚ ናት ለሁላችን ። እኛ እንኳን ተወልደን ጭቃ አቡክተን ውሃ ተራጭተን ፊደል ቆጥረን  ...
29/12/2024

መቼም ቢሆን ማንም በእናቱ አይጨክንም የምንችለውን ሁሉ እናድርግ!! ዳሎቻ ስሟ እንጂ እናትዬ/ታችን ኡሚ ናት ለሁላችን ። እኛ እንኳን ተወልደን ጭቃ አቡክተን ውሃ ተራጭተን ፊደል ቆጥረን የኖርንባት ያደግንባት የተሞሽረንባት! ይቅርና እምዬ ዳላስ የሁላችንም እናት ናት/ነሽ! ይመርብሽ! ፍክት! ድምቅ በይ ደግመሽ ደጋግመሽ ድመቂ። እውነት ለመናገር መለስ ብዬ ሳስበው አይኖቼ እምባ ያቀረሉ እናታችን ብዙ ወደ ኋላ ቀርታለች ግን ደግሞ የፊቷ ብርሃን ፍክት ያላ ነው። እኔ ይህን እውን ለማድረግ በየወሩ ከዚህ ወር ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ወር አንድ አንድ ሺህ ብር አስገባለሁ የዚህን ወር አሁን አስገብቻለሁ ደጋጎቹ የምዪ ልጆች እናንተስ? በ1000668483438 ት እናምበሽብሻት ይህቺ ድረሱልኝ የምትለው ዳላስ ኡሚ እምዬ ናት።

25/12/2024

Address

Dalocha
46

Telephone

+251911795449

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ridwan Mudessir Seid posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Ridwan Mudessir Seid:

Shortcuts

Share