Chagni TVET College/ቻግኒ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ

  • Home
  • Ethiopia
  • Chagne
  • Chagni TVET College/ቻግኒ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ

Chagni TVET College/ቻግኒ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ የቻግኒ ቴ/ሙ/ማ/ ኮሌጅ በአብከመ በአዊ ብሔ/አስ/ዞን በጓንጓ ወረዳ ውስጥ በቻግኒ ከተማ የሚገኝ የመንግስት ቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛ ኮሌጅ ነው ።

የቻግኒ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የትምህርት መረጃ ቁሳቁስ ችግር ላለባቸው 45 ተማሪዎች ዩኒፎርም እና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።ነሐሴ 7/2018 ዓ/ም ድጋፉን ያስረከቡት የኮሌጁ ...
13/08/2026

የቻግኒ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የትምህርት መረጃ ቁሳቁስ ችግር ላለባቸው 45 ተማሪዎች ዩኒፎርም እና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

ነሐሴ 7/2018 ዓ/ም
ድጋፉን ያስረከቡት የኮሌጁ ዲን አቶ ሚኒችል ዮሐንስ እንደተናገሩት ኮሌጁ ለበርካታ አመታት ተመሳሳይ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን ገልፀው፤ ተቋማችን የትምህርት ተቋም እንደመሆኑ መጠን አንድም ተማሪ በትምህርት ቁሳቁስ ችግር ሳቢያ ከትምህርት ገበታ ውጭ እንዳይሆን አልመን እየስራን ነውም ብለዋል።

አቶ ሚኒችል አክለውም ድጋፉን በየዓመቱ አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል በማለት ተናግረዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናት ወጣቶች ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ፈንታነሽ እንዳለው በበኩላቸው እንደተናገሩት እንደነዚህ አይነት ድጋፍ የተማሪዎች ስነ-ልቦና እንዳይጎዳ ያደርጋል በማለት ተናግረው ፣ ድጋፋችሁ አይለየን በቀጣይ ተጠናክሮ መቀጠ እንዳለ በትም አያይዘው ተናግረዋል።

04/08/2026
‎የቻግኒ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የችግኝ ተከላ አካሄደ፣‎⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳‎‎(ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም) ‎የቻግኒ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የክረምት ...
30/07/2026

‎የቻግኒ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የችግኝ ተከላ አካሄደ፣
‎⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳

‎(ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም)

የቻግኒ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የክረምት ዕቅዶች መካካል 🌹🌹"ተስፋን እንትከል"🌹🌹 በሚል መሪ ቃል ኮሌጁን ይበልጥ ውብና ማራኪ ሊያደርጉ የሚችሉ 1000 በላይ የተለያዩ የውበት እና የችግኝ ዝሪያ አይነቶችን የተከላ ፕሮግራም አካሂዷል።

‎በችግኝ ተከላው ላይ የኮሌጁ ሁሉም አሰልጣኞች እና የአስተዳደር ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

‎የተተከሉ ችግኞች የግራፊሊያ ዛፎች፣ የፖፖያ : የቡና እና ሌሎች ችግኞች ሲሆኑ ይህ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ኮሌጁ በቀጣይ እጅግ በጣም ውበት እንዲኖረውና የሚያስደስት እንዲሆን ስለሚረዳ የተተከሉ ችግኞችን መንከባከብና መቆጣጠር እንደሚገባ በአፅንኦት በማሳሰብ ተጠናቋል።

‎ቻግኒ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ

2018  በጀት ዓመት ለቻግኒ ከተማ የስኬት ዓመት መሆኑ ተገለፀ።በቻግኒ ከተማ የሚገኙ የመንግስት ተቋማት  በብሄረሰብ አስተዳደሩ ካሉ አቻ ከተሞች ጋር ተወዳድረው 1ኛ ወይም ሁለተኛ ደረጃ  ...
21/07/2026

2018 በጀት ዓመት ለቻግኒ ከተማ የስኬት ዓመት መሆኑ ተገለፀ።
በቻግኒ ከተማ የሚገኙ የመንግስት ተቋማት በብሄረሰብ አስተዳደሩ ካሉ አቻ ከተሞች ጋር ተወዳድረው 1ኛ ወይም ሁለተኛ ደረጃ በመያዝ እያጠናቀቁ በመሆናቸው 2018 ዓ/ም የስኬት ዓመት መሆኑን በተግባር አስመስክረዋል።

የቻግኒ ቴክኒክ ሙያ ማሰልጠኛ  ኮሌጅ የ2018 በጀት ዓመት  የሥራ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ።ሀምሌ 9/2018 ዓ/ምበ2018 በጀት ዓመት የቻግኒ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ከተቋቋመበት ዓ...
16/07/2026

የቻግኒ ቴክኒክ ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ።

ሀምሌ 9/2018 ዓ/ም

በ2018 በጀት ዓመት የቻግኒ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ከተቋቋመበት ዓላማ አንጻር በክህሎት እና በዝቅተኛ እና መካከለኛ ደረጃ በሰለጠነ የሰው ኃይል ልማት ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና ኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ፣ በተቋም አቅም ግንባታ ፣ በግዥ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ፣ በሪፎርም እና ዲጅታላይዜሽን ተግባራት በርካታ አበረታች ውጤቶችን አስመዝግቧል። ይህ ሪፖርት በዓመቱ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን በቡድን እና በልዩ አፈጻጸም ይዘረዝራል።

በዘርፍ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራ

1. የትምህርትና ስልጠና ቡድን

የምዝገባና ግንዛቤ ስራ፡ የአዲስና ነባር ሰልጣኞች ቅስቀሳ እና ምዝገባ ስራ ተካሂዷ።
የትብብር ስልጠና (Cooperative Training)፡ ከትብብር መስጫ ተቋማት ጋር በመግባባትና ውል በመያዝ አካባቢው ባሉ ኢን/ዞች ውጤታማ የሆነ የተግባር ስልጠና ተሰጥቷል።
አጫጭር ስልጠናዎች፡ በገበያ ፍላጎት ላይ የተመሰረቱ ስልጠናዎች ተሰጥተዋል። በተለይ ከተማ አስተዳደሩና ወረዳው ከግብረ ሰናይ ድርጅቶች ጋር ውል በመያዝ በስራ ፈጠራ፣ የከተማ ግብርና፣ ልብስ ስፌት ፣ ውሃ ስራዎች ፣ በባልትና እና በተለያዩ ሙያዎች ውጤታማ ስልጠና ለወጣቶች ፣ ሴቶች ፣ አካል ጉዳተኞች እና ተፈናቃዮች ተሰጥቷል።
የውጭ አገር የስራ ስምሪት ሰልጠና/Domestic Work Training/ ፡ ለተከታታይ በ7 ዙር በተሰጠ ስልጠና ከ300 በላይ ሰልጣኞችን በማሰልጠን እና በሙያ ብቃት ምዘና ብቁ በማድረግ ስልጠናውን በተሳካ ሁኔታ በማጠናቀቅ ወጣት ሴቶች በህጋዊ መንገድ የስራ ስምሪት እንዲያገኙተደርጓል ።
ምዘናና የደረጃ ሽግግር፡ ተመራቂ ሰልጣኞች ስልጠናቸውን በብቃት አጠናቀው ተመዘው እኖዲበቁ ተደርጓል።
2. ኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን ቴክ/ሽግግር
ለኢንተርፕራይዞችና አንቀሳቃሾች በአራቱም የድጋፍ ማዕቀፎች ድጋፍ ተደርጓል።
👉በዚህ በጀት አመትም እንደ ዞን ትኩረት ከተሰጣቸው ሂደቶች አንዱ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የተሻለ አፈፃፀም የተመዘገበበት የተሻለ የደረጃ ደረጃ ሽግግር : ሞዴል : የማሽነሪ አቅርቦ ምርጥ ተሞክሮ ቅመራ የተሰሩ ሲሆን በድጋፍ ወቅት አስተማሪ የሆኑ ሞዴል ኢንተርፕራይዞች ተፈጠርዋል።
👉በበጀት አመቱ የተሰሩ ተግባራትን ለቀጣይም ጥራትን መሰረት በማድረግ መከወን እንደሚገባ እና እነዚህ ተግባራትም በጀት ተበጅቶላቸው አመርቂ ወጤት እንዲያስመዘግብና የአካባቢውን ማህበረሰብ የምርትና ምርታማነት እንዲጨምር በትኩረት ሲሰራ እንደሚገባ የተጠቆመበት

3. የሰው ኃይል ቡድን
ዲጂታላይዜሽን፡ የሰራተኞችን ፋይል በዲጂታል መንገድ የመመዝገብ ስራ በከፍተኛ ትኩረት ተከናውኗል።
የሰነድ ማጣራት፡ የትምህርት ማስረጃ ማጣራት ስራዎች ተከናውነዋል።

4. ግዥና ፋይናንስ
የአቅርቦት ሰንሰለት፡ የስልጠና ግብዓቶች በተቻለ አቅም መዘግየት ቢኖርም ህግና አሰራር ተጠብቆ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገዙ ተደርጓል።
የንብረት አስተዳደር፡ ዓመታዊ የንብረት ቆጠራ በተገቢው ሁኔታ ተከናውኗል።
ማጠቃለያ
በ2018 በጀት ዓመት የታዩ ጠንካራ ስራዎችን በማስቀጠል እና የነበሩ ችግሮችን በማረም በቀጣይ በጀት ዓመት የተሻለ ስራ መሸራት እንዳለበት በኮሌጁ ምክትል ቦርድ አቶ ሞገስ ገበየሁ ተሰጥቶ የእለቱ የዕቅድ አፈፃፀም እና የቀጣይ የ90 ቀን ዕቅድ በተገቢወ መንገድ መከናወን እንደሚገባ በማሳሰብ የግምገማ መድረኩ ተጠናቋል።

ቻግኒ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ
ቻግኒ

02/07/2026
በጓንጓ ወረዳ አስተዳደር ስራና ክህሎት ጽ/ቤትና በኒዘርለንድስ ልማት ድርጅት/SNV/ ትብብር  በቀጣይ የስራ እድል ለሚፈጠርላቸው ወጣቶች በተከታታይ አምስት ቀናት ሲሰጥ የነበረው የህይወትና ...
29/06/2026

በጓንጓ ወረዳ አስተዳደር ስራና ክህሎት ጽ/ቤትና በኒዘርለንድስ ልማት ድርጅት/SNV/ ትብብር በቀጣይ የስራ እድል ለሚፈጠርላቸው ወጣቶች በተከታታይ አምስት ቀናት ሲሰጥ የነበረው የህይወትና ንግድ ክህሎት ስልጠና በስኬት ተጠናቀቀ ።

****************//******************
ሰኔ 22/2018 ዓ.ም(ጓንጓ ኮሙዩኒኬሽን)

በጓንጓ ወረዳ አስተዳደር ስራና ክህሎት ጽ/ቤትና በኒዘርለንድስ ልማት ድርጅት/SNV/ ትብብር በቀጣይ የስራ እድል ለሚፈጠርላቸው ወጣቶች በተከታታይ አምስት ቀናት ሲሰጥ የነበረው የህይወትና ንግድ ክህሎት ስልጠና በስኬት ተጠናቀቀ ።

በስልጠናው ማጠቃላያ በቦታው ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የጓንጓ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰለሞን ቦጋለ እንደገለፁት ወጣቶች ስራ ጠባቂ በመሆን ለኢኮኖሚ ጥገኝነት መጋለጣቸው ያሳሰባቸው የተለያዩ ድርጅቶች ችግሩን ለመቅረፍ ከመንግስት ጋር በመተባባር እየለፉ ቢሆንም ችግሩ በተለያዩ እንክፋቶች በዘላቂነት ሊፈታ አለመቻሉን ጠቅሰው ወጣቶች ጎታች አመለካከትን በስልጠና ቀርፈው የስራ ፈላጊ ሰይሆኑ የስራ ፈጣሪ በመሆን እራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ብሎም ሀገሪቷን በኢኮኖሚ ማሳደግ እንዳለባቸው ተናግረዋል ።

ዋና አስተዳዳሪው ስለጠና የሰጠውን SNV ፕሮጀክት በማመስገን የስልጠና እድል ተጠቃሚ የሆኑ ወጣቶች ስልጠናውን በአግባቡ በመተግበር እራሳቸውን ለስራ እድል ፈጠራ መዘጋጀት እንዳለባቸውና አደራጅ ተቋም ድጋፍና ክትት እንዲያደርጉ ፕሮጀክትል ።

የጓንጓ ወረዳ ስራና ክሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እሱባለው ይሁን በበኩላቸው ስልጠናውን ላጠናቀቁት ወጣቶች አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍና ክትትል በማድረግ የሰለጠኑትን ስልጠና ወደ ተግባር ለመቀየር እንደሚሰሩ በመግለፅ ወጣቶችም በትናንሽ እንቅፋቶች ሳይደናቀፉ ወጣትነት ጊዜያቸውን በፅናት ታግለው ስራ ዕድል ፈጥረው እራሳቸውን በኢኮኖሚ እንዲያሳድጉ አስገንዝበዋል ።

በጓንጓ ወረዳ አስተዳደር ስራና ክህሎት ጽ/ቤትና በኒዘርለንድስ ልማት ድርጅት/SNV/ ትብብር  በቀጣይ የስራ እድል ለሚፈጠርላቸው ወጣቶች የህይወትና ንግድ ክህሎት ስልጠና እና የሙያ ስልጠና ...
25/06/2026

በጓንጓ ወረዳ አስተዳደር ስራና ክህሎት ጽ/ቤትና በኒዘርለንድስ ልማት ድርጅት/SNV/ ትብብር በቀጣይ የስራ እድል ለሚፈጠርላቸው ወጣቶች የህይወትና ንግድ ክህሎት ስልጠና እና የሙያ ስልጠና መስጠት ጀመረ።

****************//******************
ሰኔ 18/2018 ዓ/ም(ጓንጓ ኮሙዩኒኬሽን)

ስልጠናውን በቦታው ተገኝተው ያስጀመሩት የጓንጓ ወረዳ ስራና ክሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እሱባለው ይሁን እንደገለፁት ወጣቶች የስራ ፈላጊ ሰይሆኑ የስራ ፈጣሪ በመሆን እራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ብሎም ሀገሪቷን በኢኮኖሚ ማሳደግ እንዳለባቸው ተናግረዋል ።

አቶ እሱባለው ይሁን አያይዘውም SNV ከማስተር ኳርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ራዕይ 2 የተባለ ፕሮጀክት በጓንጓ ወረዳ በዚህ አመት ወደ ትግባራ የገባ መሆኑን በመግለፅ ዛሬ የተጀመረው የህይወትና ንግድ ክህሎት ስልጠና እና የሙያ ስልጠና የፕሮጀክቱን መመልመያ መስፈረት አሞልተው ለተመለመሉት በቀጣይ የስራ ዕድል ለሚፈጠርላቸው ለመጀመሪያ ዙር ሰልጣኞች መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይም በሁሉም ቀበሌ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልፀዋል ።

የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ መሆን የሚችሉት እድሜያቸው ከ18-35 ዓመት የሆኑት 90% ሴት ሁኖ የአካል ጉዳተኞችን ፣ተፈናቃይና የስደት ተመላሽ ስራ አጥ ወጣቶችን በግብርና እሴት ሰንሰለት/በዶሮ ፣ማድለብ ፣የወተት ልማት ፣ እርባታ፣ አትክልትና ፍራፍሬ /የስራ ዘርፍ የስራ እድል ለመፍጠር የሚሰራ ፕሮጀክት መሆኑንም ጨምረው ገልፀዋል ።

አቶ እሱባለው ይሁን ቀጥለውም ፕሮጀክቱ የህይወትና ንግድ ክህሎት ስልጠና እና የሙያ ስልጠና፣ የብድር አቅርቦት ፣የንግድ ልማት አገልግሎት (BDS) ፣የገበያ ትስስርና ተጋላጭ ለሆኑ ወጣቶች የስራ ማስጀመሪያ ድጋፍ በመስጠት ለስራ እድል ፈጠረው ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያበረክት መሆኑን ገልፀው የዚህ ምቹ እድል ተጠቃሚ የሆኑ ወጣቶች ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል እራሳቸውን ለስራ እድል ፈጠራ መዘጋጀት እንዳለባቸው አሳስበዋል ።

ስልጠናውን የጀመሩት ወጣቶች መካከል ያነጋገርናቸው እንደገለፁት በስልጠናው እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው ፕሮጀክቱ የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል ።

Address

የቻግኒ ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ በአብከመ በአዊ ብሔ/አስ/ዞን በጓንጓ ወረዳ ውስጥ በቻግኒ ከተማ የሚገኝ የመንግስት ቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛ ኮሌጅ ነው ።
Chagne

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Chagni TVET College/ቻግኒ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share