24/02/2026
ሶሻል ሚዲያ መነጋገሪ የሆነው ትንሹ ዝንጀሮ "ፑንች" ልብ የሚነካ ታሪክ
በጃፓን ኢቺካዋ ሲቲ መካነ አራዊት (Ichikawa City Zoo) ውስጥ የተወለደው ትንሹ የጃፓን ማካክ "ፑንች" በአሁኑ ሰዓት በአለም ዙሪያ የብዙዎችን ቀልብ ስቧል። ታሪኩ ግን እንደ አጀማመሩ ቀላል አልነበረም።
ታሪኩ እንዲህ ነው...
ፑንች እንደተወለደ እናቱ ልትቀበለውና ልትንከባከበው ፍቃደኛ አልሆነችም። በዚህም ምክንያት ህይወቱን ለማዳን የእንስሳት ጠባቂዎቹ ጣልቃ መግባት ነበረባቸው።
ፑንች ገና ጨቅላና የፍቅር ረሃብ የነበረበት በመሆኑ፣ ጠባቂዎቹ አንድ የሚገርም መፍትሄ አመጡ— አንድ ትንሽ አሻንጉሊት ሰጡት።
ከዚያ በኋላ የሆነው ነገር ግን አለምን አስለቅሷል። ፑንች አሻንጉሊቱን ልክ እንደ እናቱ አጥብቆ ማቀፍ ጀመረ።
አብሮት ይተኛል፣ የትም ቦታ አይለየውም። ይህንን የሚያሳይ ቪዲዮ በፌስቡክና በቲክቶክ ላይ በመሰራጨቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በዝንጀሮው ሁኔታ ተንክተዋል።
በአሁኑ ሰዓት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ "ታዋቂ ሰዎች ሊያድኑት መጡ" ወይም "ተወሰደ" የሚሉ የተጋነኑ ወሬዎች እየተሰራጩ ቢሆንም፣ እነሱ ግን ሀሰት ናቸው። መካነ አራዊቱ እንዳረጋገጠው ፑንች በባለሙያዎች ጥበቃ ስር በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛል።
ይህ ታሪክ ምን ያስተምረናል?
* እንስሳትም እንደ ሰው የብቸኝነት ስሜት ይሰማቸዋል።
* ማንኛውም ትንሽ ልብ ፍቅርና እንክብካቤ ያስፈልገዋል።
* አንዳንዴ መፅናኛ የምናገኘው በቀላል ነገሮች ውስጥ ነው።
አንዳንዴ ስንገፋ እና በወለዱን ዘመዶቻችን እንኳ ስንተወው፣ ፈጣሪ መፅናኛ የሚሆን ሌላ ነገር አያጣም። ፑንች ከእናቱ ቢገፋም፣ በዛ አሻንጉሊት ውስጥ የእናትነትን ሙቀት አግኝቷል።
በአሁኑ ሰዓት 'ፑንች' በጣም ታዋቂ በመሆኑ፣ በቀን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እየመጡ ይጎበኙታል።
🙏🙏🙏
ጉርሻ page
🌴🌴🌴