New seen currently and Truth educational media

New seen currently and Truth educational media The Darkest night is end when the sun is rise! welcome

25/06/2026
23/06/2026

‼️ውጤትዎን ይመልከቱ!

ከሰኔ 04-12/2018 ዓ.ም የተሰጠው የ2018 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤት መታየት ጀምሯል።

ውጤትዎን ለማየት ከስር ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ 👇

ሊንኩን ከተጫኑ በኋላ 'Exit Examination' ላይ 'View Results' የሚለውን በመጫንና Username በማስገባት ውጤትዎን ይመልከቱ።

23/06/2026

‼️የምርቃት ቀን

በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን በዚህ ሳምንት ያስመርቃሉ። ከማክሰኞ ሰኔ 16/2018 ዓ.ም ጀምሮ ተማሪዎቻቸውን ከሚያስመርቁ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል ተከታዮቹ ዩኒቨርሲቲዎች ይጠቀሳሉ፦

➫ አርሲ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 16/2018 ዓ.ም)
➫ ራያ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 16/2018 ዓ.ም)
➫ ሠመራ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 17/2018 ዓ.ም)
➫ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 18/2018 ዓ.ም)
➫ ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 18/2018 ዓ.ም)
➫ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 18/2018 ዓ.ም)
➫ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 18/2018 ዓ.ም)
➫ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 18/2018 ዓ.ም)
➫ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም)
➫ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም)
➫ ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም)
➫ ጅማ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም)
➫ ዲላ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም)
➫ ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም)
➫ ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም)
➫ አክሱም ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም)
➫ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም)
👉 ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም)
👉 ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም)
👉ጂንካ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም)
👉 ወራቤ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም)
👉 አሶሳ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም)
👉 ወልድያ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም)
👉ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሰኔ 20/2018 ዓ.ም)

23/06/2026

የ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት የጊዜ ሰሌዳ ይፋ ሆነ።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበትን የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አድርጓል። በዚሁ መሠረት በኦንላይን (Computer-based Testing (CBT) የሚፈተኑ ተፈታኞች በስድስት ዙር የሚፈተኑ ሲሆን ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ይፈተናሉ። ከአራተኛ እስከ ስድስተኛ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች የሚፈተኑ ይሆናል።

ፈተናውን በወረቀት የሚፈተኑ ተፈታኞች የተፈጥሮ ሳይንስ በሶስተኛ ዙር ላይ የሚፈተኑ ሲሆን የማህበራዊ ሳይንስ በአራተኛ ዙር በዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚፈተኑ ይሆናል። ዝርዝሩን ከሚከተለው ሠንጠረዥ ይመልከቱ።

የፈተና ስርቆትንና ኩረጃን በጋራ እንከላከል!
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

21/06/2026

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሲሰጥ የሰነበተው የሬሜድያል እና የመውጫ ፈተና (Exit Exam) በሰላም ተጠናቀቀ።

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ሲሰጥ የሰነበተው የሬሜድያል እና የመውጫ ፈተና በሰላም፣ በሥርዓት እና በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን የዩኒቨርሲቲው ተቋማዊ ጥራት ማረጋገጫ አስታወቀ።

በሬሜዲያል ፈተና 2,226 ተማሪዎች የተፈተኑ ሲሆን፣ በመውጫ ፈተና ደግሞ 8084 ተፈታኞች የዩኒቨርሲቲው ተመራቂ ተማሪዎች፣ ከግል ኮሌጆች፣ ከደብረ ማርቆስ መምህራን ኮሌጅ እና ከፍኖተ ሰላም መምህራን ኮሌጅ በመሳተፍ ፈተናውን ወስደዋል።

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተቋማዊ ጥራት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑትና የመውጫ ፈተና እና የሬሜድያል ፈተና አስተባባሪ አባትሁን አለኸኝ (ዶ/ር) እንደገለጹት ፈተናዎቹ በጥብቅ ቁጥጥር፣ በተቀናጀ አስተዳደር እና ያለምንም የጸጥታም ሆነ የአስተዳደር ችግር በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል ሲሉ ገልጸዋል።

አባትይሁን (ዶ/ር) ለፈተናዎቹ ስኬታማ አፈጻጸም አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተማሪዎች፣ መምህራን፣ የፈተና ተቆጣጣሪዎች እና
ሁሉንም አጋር አካላት በዩኒቨርሲቲው ስም ከልብ አመስግነዋል።

በአጠቃላይ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በበይነ መረብ ሲሰጡ የቆዩት የሪሚዲያልና የመውጫ ፈተናዎች በሰላምና በስኬት የተጠናቀቁ ሲሆን ከሰኔ 23/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሚሰጠው ተማሪዎች የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ከወዲሁ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ፡፡

15/06/2026

ለሚመለከተው ሁሉ

13/01/2026

ማስታወቂያ

የመዉጫ ፈተና ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ ተማሪዎች በሙሉ፣

የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርታችሁን አጠናቃችሁ በ2018 ዓ.ም ጥር መጨረሻ ላይ የሚሰጠዉን የመዉጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የምትወስዱ ተማሪዎች ፈታናዉን ለመውሰድ በብሄራዊ መታወቂያ (National ID) በመጠቀም የመለያ ማረጋገጫ (Identity verification) ማረጋገጥ የሚጠበቅባችሁ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አግልግሎት የገለፀ በመሆኑ ከዚህ በታች ባለው ሊንክ እየገባችሁ የሞላችሁት መረጃ ትክክለኛ መሆኑን እንድታረጋግጡ እናሳስባለን፡

ሊንክ፡

Ministry of Education | Exit Exam Verification

Address

Bure
Bure

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when New seen currently and Truth educational media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to New seen currently and Truth educational media:

Shortcuts

Share