Abuu Diraar

Abuu Diraar �I Need Allah In My Life�

                            ክፍል3አላህም ቀጠል አድርጎ፦"ሙሳ ሆይ! ወደ ግብፅ ተመለስ። ፊርዐውንም ወሰን አልፏል" አለው።ሙሳም፦" ጌታዬ ሆይ! ልቤን አስፋልኝ፡፡ነገሬንም ለ...
22/12/2020



ክፍል3

አላህም ቀጠል አድርጎ፦"ሙሳ ሆይ! ወደ ግብፅ ተመለስ። ፊርዐውንም ወሰን አልፏል" አለው።

ሙሳም፦" ጌታዬ ሆይ! ልቤን አስፋልኝ፡፡

ነገሬንም ለእኔ አግራልኝ፡፡

ከምላሴም መኮላተፍን ፍታልኝ።

ከቤተሰቦቼም ለእኔ ረዳትን አድርግልኝ፡፡

ሃሩንን ወንድሜን፡፡

ኅይሌን በእርሱ አበርታልኝ፡፡

በነገሬም አጋራው፡፡

በብዙ እናጠራህ ዘንድ፡፡

በብዙም እንድናወሳህ፡፡

አንተ በእኛ ነገር ዐዋቂ ነህና" አለው።

አላህም የሙሳን ፍላጎት እንዲሚያሳካለት ቃል ገባለት'ና ሙሳም ወደ ሚስቱ በመሄድ ወደ ግብፅ መሄድ እንዳለባቸው ነግሯት ከሚስቱ ጋር ጉዞ ወደ ግብፅ ጀመሩ።

ግብፅ እንደገቡም ሙሳ የወንድሙን የሀሩን ቤት በመግባት ለሀሩን ሁሉንም ነገር ነገረው።ሀሩንም እጅጉን በመደሰት በሀሳቡ ተስማሙ።

በነጋታው ሙሳ እና ሀሩን ያለ ምንም ፍራቻ ወደ ፊርዐውን ቤተ መንግስት ዘልቀው ገቡ።ከዚያም ፊርዐውንን እንደተገናኙም ወደ አላህ እንዲመለስ'ና በኒ ኢስራኢሎችንም እንዳይበድል፤ ሙሳ እና ወንድሙ ሀሩንም የአላህ መልዕክተኞች መሆናቸውንም አክለው ነገሩት።

ፊርዐውንም ከ10 አመት በፊት እቤቱ ይኖር የነበረውን ሙሳን በትኩረት ሲመለከት አወቀው'ና፦"አንተ ህፃን ሆነህ እቤቴ አላሳደግኩህም እንዴ!!! ያችንም የሠራሃትን ሥራህን አልሠራህምን? አንተም ከውለታ ቢሶቹ ነህ"አለው

ሙሳም፦"ያን ግዜ ተሳስቼ ነው። ከዚያም እናንተ ትገድሉኛላችሁ ብዬ ሩቅ ሀገር ሸሸሁ። እዚያው ጌታዬም ጥበብን ሰጠኝ።ይህችም የእስራኤልን ልጆች ባሪያ በማድረግህ በእኔ ላይ የምትመጻደቅባት ጸጋ ናት" አለው።

ፊርዐውንም፦" (ላከኝ የምትለው) የዓለማትም ጌታ ምንድነው" አለው።

ሙሳም፦" የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ሁሉ ጌታ ነው፡፡ የምታረጋግጡ ብትኾኑ (ነገሩ ይህ ነው)" አለው።

ፊርዐውን ትንሽ ሳቀ'ና ወደ ዙሪያው ያሉትን ሰዎች እየተመለከተ፦"ሚለውን አትሰሙትም እንዴ!" አላቸው።

ሙሳም፦"የምሥራቅና የምዕራብ በመካከላቸውም ያለው ነገር ሁሉ ጌታ ነው፡፡ ታውቁ እንደኾናችሁ (እመኑበት)" አላቸው።

ፊርዐውንም፦"ከእኔ ሌላ አምላክን ብትይዝ በውነቱ ከእስረኞቹ አደርግሃለሁ" አለው።

ሙሳም፦"እኔ ከአላህ ዘንድ የተላክሁ ስለመሆኔ ማስረጃ ባመጣልህስ?" አለው።

ፊርዐውንም፦"እስቲ ማስረጃህን አምጣ እውነተኛ ከሆንክ" አለው።

ሙሳም ይህን ሲሰማ ብትሯን ጣላት፤ወዲያው ወደ እባብነት ተቀየረች።
ጣቱንም በብብቱ አስገብቶ የምታንፀባርቅ ሆና አወጣት።

ፊርዐውን እችን ሲያይ፦" አሀ!!! ይህም ግልፅ ድግምት ነው።እንደውም እንዳንተ ያሉ ድግምተኞች በግዛቴ ብዙ ስላሉ ቀጠሮ እንያዝ'ና እንገናኝ ማን እንደሚያሸንፍ እናያለን"አለው።

ሙሳም በዚህ ተስማምቶ
ትልቅ ህዝባዊ በአል በሚከበርበት ቀን ቀጠሮ ተያይዘው ያን ቀን

በሰላም ተለያዩ።

ቀን ቀንን ወራት ወራትን እየተተካካ ሙሳ እና ፊርዐውን የያዙት ቀጠሮ ወቅቱን ጠብቆ መጣ።

ህዝቡ የዛሬዋን የቁርጥ ቀን ፍፃሜ ሊመለከት ለቁጥር አዳጋች ሆኖ በሰልፍ ተሰብስቧል።ድግምተኞችም እድሜ ልካቸውን ሲጠበቡበት የከረሙትን አስደናቂ ድግምት ይዘው ከሙሳ ሊፋለሙ ሰልፍ ይዘው ቁጭ ብለዋል። የድግምተኞች ብዛት 30,000(ሰላሳ ሺህ) ነበር።

(አስቡት በናታችሁ የድግምተኞቹ ቁጥር 30,000 ከሆነ የተመልካቹ ቁጥር ስንት ሊሆን ነው!!! ብቻ ትዕይንቱን በጭንቅላታችሁ ሳሉት)

ተመልካቹም፣ድግምተኛውም፣ንጉሱም ሙሳም ሁሉም ቦታውን ከያዘ በኋላ ድግምተኞቹ ቀስ ብለው ፊርዐውንን፦"ግን እኛ ካሸነፍን ምንድነው ሽልማታችን?" አሉት።

ፉርዐውንም፦"እኔ ዘንድ የቅርብ ባለሟል ትሆናላችሁ" አላቸው።

አሁን ጫወታው ሊጀመር ነው ፊርዐውን ዙፈኑ ላይ ተቀምጧል፣ሙሳ እና ወንድሙ ከአንድ ጎኑ ሲሆኖ ድግምተኞቹም ከአንድ ጎን ቆመዋል።ህዝቡ የትንቅንቁን ፍፃሚ ለማየት እጅጉን ጓግቷል።

..............

                  ክፍል2ሙሳም የግብፅን ምድር ትቶ በረሀውን እያቆራረጠ እግሩ ወደ መራው ቦታ መጓዝ ጀመረ።ብዙ ተጉዞ ረሀብ፣ጥማት እና ድካም ድንበር አልፈው ካዳከሙት በኋላ መድየን...
06/12/2020



ክፍል2

ሙሳም የግብፅን ምድር ትቶ በረሀውን እያቆራረጠ እግሩ ወደ መራው ቦታ መጓዝ ጀመረ።

ብዙ ተጉዞ ረሀብ፣ጥማት እና ድካም ድንበር አልፈው ካዳከሙት በኋላ መድየን የምትባል ሀገር ደረሰ።

(የሹዐይብ ትረካ ላይ እችን ቦታ እንድታስታውሱ ነግሪያቹ ነበር። አይደል እንዴ....!!! አላስታወሳችሁትም...? አዎ..!!?

አረ በአላህ አስታውሱ እንጂ እንደውም የሹዐይብ እድሜ ሲገፋ በጎችን ማገድ ተሳነው'ና ሁለት ሴት ልጆቹ በጎቹን ማገድ ጀመሩ....ምናምን አላልኳቹም..!!!? አይዋ.....በቃ ኑ ሴቶቹን አሁን ላሳያችሁ።)

ሙሳ በከተማዋ መግቢያ ላይም ሲደርስ የመድየን ከተማ ነዋሪያን በሙሉ እንስሳዎቻቸውን ውሀ የሚያጠጡበትን አንድ ምንጭ ቦታ ደረሰ።

ልክ እዛ ሲደርስ ህዝቡ በሙሉ ውሀ ሲያጠጣ ሁለት ሴቶች ግን በጎቻቸውን ወደ ውሀው

እንዳይጠጉ ሲከለክሉ ተመለከተ።

ሙሳም ወደ ሴቶቹ ጠጋ ብሎ፦

"ለምን በጎቻችሁን ውሀ መጠጣት ትከለክላላች" ሲል ጠየቃቸው።
ሴቶቹም፦

"እኛ በጎቻችንን ይዘን ከወንዶች ጋር እዚህ ግፊያ ውስጥ መግባት ስለምናፍር ሁሉም እንስሳዎቻቸውን አጠጥተው ሲሄዱ ነው እኛ ምናጠጣው።ሚያግዘን ሰው የለም በዚያ ላይ አባታችን ትልቅ ሽማግሌ ነው" አሉት።

ሙሳም የሴቶቹን በጎች ሊያጠጣላቸው በጎቹን እየነዳ ግፊያውን ሰንጥቆ መሀል አስገብቶ አጠጣላቸው።

ሙሳ አቅማም ስለነበረም ማንም ገፍቶ አይችለውም...በጎቹን እስኪጠግቡ ካጠጣላቸው በኋላ ሰብስቦ ለሴቶቹ አስረከባቸው።ሴቶቹም ሙሳን በጣም አመስግነውት በጎቻቸውን እየነዱ ወደ አባታቸው ተመለሱ።

ሁሉም እንስሳቶቹን ካጠጣ በኋላ የምንጩን ቦታ ለቆ ሲሄድ ሙሳ ብቻውን እዛው ቀረ።የትም መሄጃ የለውማ...ከዚያም ወደ አንድ ዛፍ ጥላ ጋ ሄደ'ና፦

"ያ አላህ! እኔ ከመልካም ነገር (ምንም ይሁን ምን) ወደኔ ለምታወርደው ፈላጊ ነኝ" ሲል አላህን ተማፀነው።

ብዙም ሳይቆይ ከቅድሞቹ ሴቶች አንዷ እያፈረች መጣች'ና መሬት መሬቱን እያየች፦" በጎችን ስላጠጣህልን አባቴ ውለታውን ሊመልስልህ ይፈልጋል። ስለዚህ ና እኛ ቤት እንሂድ" አለችው።(ያ ሰላም ደስ አይልም በአላህ!!!)

ሙሳም ብድግ ብሎ ተነሳ'ና መሄድ ጀመሩ።እየሄዱ ሳለ ልጅቷ መንገዱን ለመጠቆም ፊት ፊት ስትራመድ ሙሳ ወጣትም ስለሆነ ከኋላ ሆኖ እሷን መመልከት ስላልፈለገ፤

ጠርቷት ከኋላ ኋላው እንድትራመድ'ና መታጠፊዎችንም ሲደርሱ ወደ ቀኝ ከሆነም ወደ ግራ ድንጋይ በመወርወር እንድታሳውቀው ነግሯት እሱ ከፊት ፊት መራመድ ጀመረ።

አባታቸው(ነቢዩላህ ሹዐይብ) ዘንድም ደረሱ'ና አባታቸው ሙሳን አመስግነውት ከየት እንደመጣ ሲጠይቁት ሙሳም ሙሉ ታሪኩን ተርኮላቸው ወደ መድየን የመጣበትንም ምክንያት በግልፅ ነገራቸው።

ሙሳ ከዚህ በኋላ የትም መሄጃ እንደሌለው የተመለከተውም የሴቶቹ አባት፦"ለ8 አመታት ያህል በጎቼን የምታግድልኝ እንደሆን እኔ ከሁለቱ ሴት ልጆቼ አንደኛዋን እድርልሀለሁ።

ግን አንተን ደስ ካለህ ስምንቷን አመታት 10 ሙላት" አሉት።

ሙሳም በሀሳባቸው ተስማምቶ ለ10 አመታት ያህል በታማኝነት አገለገላቸው።በመጨረሻም አስሩ አመት ሲሞላ ሙሳ ሹዐይብን የገባለትን ቃል እንዲያሟላ(ልጅቷን እንዲዘውጀው) ጠየቀው'ና ወደ ሌላ ሀገርም መሄድ እንደሚፈልግ ነገረው።

ሹዐይብም ሴት ልጁን ሞሽሮ ከተለያዩ ስጦታዎች ጋር ለሙሳ ጀባ አለው።

ሙሳም ሚስቱን እና ከሹዐይብ የተበረከተለትን እንስሳቶች ይዞ ጉዞ ጀመረ።በጉዞ ላይ ሳሉም ሰይናእ የተባለ ቦታ ላይ በሚገኝ የጡር ተራራ ላይ ሲደርሱ መሽቶ ጨለመባቸው።

እዛው ጋ ሳሉ መንገዱም ተወዘጋገበባቸው ወዴት እንደሚሄዱ'ና ከየት በኩል እንደመጡ ሁላ ጠፋባቸው።

በዚህ ጨለማ በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ ከተራራው በስተቀኝ በኩል የሚነድ እሳት ሚመስል ነገር ሙሳ አየ'ና ለሚስቱ፦

"እዚሁ ጠብቂኝ ከተራራው ጫፍ የሚነድ እሳት ስላየሁ ለኩሼ እመጣለሁ። ወይም መንገድ ወዴት እንደሆነ እጠይቃለሁ" ብሏት ሄደ።

ሙሳ እሳቱ ወደሚንቀለቀልበት ተራራ ላይ በጨለማው ከወጣ በኋላ ሲያይ ምንም እሳት የለም።ሙሳም ደነገጠ በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለ ከወደኋላ በኩል፦"አንተ ሙሳ" የሚል ድምፅ ሰማ።

ሙሳ ተደናግጦ ሲዞር፦"እኔ ጌታህ (አላህ) እኔ ነኝ መጫሚያዎችህንም አውልቅ፡፡ አንተ በተቀደሰው ሸለቆ በጡዋ ነህና፤ እኔም መረጥኩህ፤ የሚወረድልህንም ነገር አዳምጥ።

እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና ተገዛኝ፡፡ ሶላትንም (በእርሷ) እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡

ሰዓቲቱ በእርግጥ መጪ ናት፡፡ ልደብቃት እቃረባለሁ፡፡ ነፍስ ሁሉ በምትሠራው ነገር ትመነዳ ዘንድ (መጭ ናት)።

በእርሷ የማያምነውና ዝንባሌውን የተከተለውም ሰው ከእርሷ አያግድህ ትጠፋለህና" አለው።

ሙሳ በድንጋጤ ዝምታ ወርሮታል።አላህም ቀጠል አድርጎ፦"ሙሳ ሆይ! ይህችም በቀኝ እጅህ ያለችው ምንድን ናት?" አለው።

ሙሳም እየተርበተበተ፦"እርሷ በትሬ ናት፡፡ በእርሷ ላይ እደገፍባታለሁ፣ በእርሷም ለፍየሎቼ ቅጠልን አረግፍባታለሁ፣ ለእኔም በእርሷ ሌሎች ጉዳዮች(ጥቅሞች) አሉኝ" አለው።

አላህም፦"ሙሳ ሆይ! በትርህን ጣላት" አለው።

ሙሳም እሽ ብሎ በትሯን ሲጥላት፤ በትሯ የምትሯሯጥ እባብ ሆነች"

ሙሳ እባቡን ሲያያ እግሬ አውጭኝ ብሎ ሲበረግግ አላህ፦"አንተ ሙሳ አትፍራ እባቧን ያዛት እንደነበረች ዱላ አደርጋታለሁ" አለው።

ሙሳም እየተንቀጠቀጠ እባቧን ሲይዛት እንደነበረች ዱላ ሆነች።

ከዚያም አላህ፦"ሙሳ ሆይ! እጅህን በብብትህ ውስጥ አስገባ" አለው።

ሙሳም እሽ ብሎ እጁን በብብቱ ሲያስገባ እጁ እንደ መብራት መብራት ጀመረ።ሙሳ እጁን በዚህ መልኩ ሲያይ በሽታ መስሎት በጣም ተጨነቀ።

ያን ግዜ አላህም፦"ሙሳ ሆይ! አትፍራ ይህ ከኛ የሆነ ተአምር ነው" አለው።

..............

-------------------------------------------------------👇👇🌹🌹----

                 ክፍል1ግዜው ዩሱፍ ዐ ሰ ከሞተ 97 አመታትን አስቆጥሯል።በዩሱፍ አማካኝነት የግብፅን ምድር ገብተው በመንፊስ ከተማ መኖር የጀመሩት የያዕቁብ ልጆች ሁሉ ሞተው አልቀ...
28/11/2020



ክፍል1

ግዜው ዩሱፍ ዐ ሰ ከሞተ 97 አመታትን አስቆጥሯል።በዩሱፍ አማካኝነት የግብፅን ምድር ገብተው በመንፊስ ከተማ መኖር የጀመሩት የያዕቁብ ልጆች ሁሉ ሞተው አልቀው የልጅ ልጆቹ ግን በመተካካት ግብፅን እጅጉን እየሞሏት ነው።

ምንም እንኳን ያኔ በዩሱፍ (ዐ ሰ) ዘመን እነዚህ በኒ ኢስራኢሎች (የያዕቁብ ልጆች) በግብፅ ምድር የተከበሩ ሰዎች ቢሆኑም አሁን ላይ ያለው ንጉስ ግን እጅጉን ይበድላቸው ጀምሯል።

ይሄን ግዜ ነበር እንግዲ አላህ በኒ ኢስራኢሎችን ነፃ እንዲያወጣ ሙሳን የላከው።
የሙሳ የዘር ሀረግ፦
ሙሳ ኢብን...ዒምራን ኢብን...የስሀር ኢብን...ቃሂስ ኢብን...ላዊ ኢብን...ያዕቁብ ኢብን...ኢስሀቅ ኢብን...ኢብራሂም ኢብን....አዛር......ምናምን እያለ ይቀጥላል።

ሙሳ ከመወለዱ በፊት ፊርዐውን አንድ ቀን በህልሙ የሆነች እሳት ከእየሩሳሌም ወደ ግብፅ መጥታ የግብፃውያንን ቤት እየዞረች ታቃጥል'ና የበኒ ኢስራኢሎችን ቤት ስትተው ተመለከተ።

እና ይህ ህልም እረፍት የነሳው ንጉስ በነጋታው ጠንቋዮችን እና ኮከብ ቆጣሪዎችን ሰብስቦ የህልሙን ፍች ሲጠይቃቸው፦"ከነዚህ የያዕቁብ ልጆች(ከበኒ ኢስራኢሎች) አንድ ንግስናህን የሚሽር ልጅ ሊወለድ ነው" አሉት።

ፊርዐውን ይህን ሲሰማ በጣም በመደንገጥ የበኒ ኢስራኢል ወንድ ልጆችን እንዳለ እንዲገደሉ አዘዘ...ምንም አይነት ወንድ ልጅም ቢረገዝ እንደሚገድልም ትዕዛዝ አስተላለፈ።

የፊርዐውን ትዕዛዝ መተግበር ተጀመረ...በጣም ለቁጥር የሚያዳግቱ የበኒ ኢስራኢል ወንድ ልጆች እንደ ገፍ ተገደሉ። በመጨረሻም ይህ ህግ ማሻሻያ መደረግ እንዳለበት የግብፅ ህዝብ አቤቱታ ሲያቀርብ ፊርዐውንም ዘወትር የሚተገበረውን የግድያ ተግባር አንድ አመት ግድያ እንዲቆም እና አንድ አመት እንዲገደል አደረገ.....

በዚህ ሁኔታ ነበር የማይገደልበት አመት ላይ ሀሩን የተባለው የሙሳ ወንድም ተወልዶ፤ በሚገደልበት አመት ደሞ ሙሳ የተወለደው።

ሙሳ ልክ እንደተወለደ የሙሳ እናት ህፃኗን አይኗ እያየ እንዳይገድሉባት በጣም ተጨነከች።ምታደርገው ጠፍቷት በመዋለል ላይ ሳለች አላህም እናትየውን ከእንጨት የሆነ ሳጥን ሰርታ፤በዚያ ሳጥን ውስጥ ህፃኑን እንድታስገባው'ና ሳጥኑንም ከነ ህፃኑ ወንዝ ላይ እንድትጥለው አዟት፤ ይህንንም ህፃን ነቢይ አድርጎ እንደሚመልስላት ቃል ገባላት።

በዚህ መሰረት የሙሳ እናት ህፃን ልጇን በጨርቅ ጠቅልላ በሳጥን አሽጋ ሆዷ እየባባ በናይል ወንዝ አሻግራ ሸኘችው።

ውሀውም ሳጥኑን ከነ ህፃኑ እያንሳፈፈ የልጆችን ግድያ ትዕዛዝ ወደሰጠው ፊርዐን ግቢ ይዞት ገባ።በሰዐቱ የፊርዐውን የሚስቱ አገልጋዮች እዚያ ወንዝ ዳር እየታጠቡ ነበር'ና ይህን ሳጥን ሲመለከቱ በውስጡ ወርቅ ያለ መስሏቸው ለእመቤታቸው ሳጥኑን ሳይከፍቱ በስጦታ መልክ ወስደው አስረከቧት።

የሙሳ እህት እዚያ ቤተ መንግስት ውስጥ ተቀጥራ ትሰራ ነበር'ና እናቷ የጣለችው ሳጥን በገዳዮች እጅ መግባቱን ስታረጋግጥ ወደ እናቷ ስትከንፍ ሄዳ ነገረቻት።እናትም ልጇን ተመልሳ ሄዳ ሁኔታውን እንድታጣራላት ላከቻት። ልጅቷም ሁኔታውን ለማጣራት ቤተመንግስት ተመልሳ መጣች።

ንግስቲቱም አገልጋዮቿ እና ባለቤቷ ባሉበት ቦታ ሳጥኑ እንዲከፈት አዘዘች፤ሳጥኑ ሲከፈትም ልብን የሚያማልል ውብ እና ማራኪ ልጅ በሳጥኑ አገኙ።የፊርዐውን ሚስት ልጅ መውለድ አትችልም ነበር'ና፦"ልጅ ስለሌለን እባክህ ይሄን ህፃን አትግደለው።ወደ ፊትም ልጃችን አድርገን እንይዘዋለን " አለችው።

እሱ ህፃኑን መግደል ቢፈልግም የሚስቱን ሀሳብ መቃረን አልፈለገም'ና በሀሳቧ ተስማማ።

አሁን አስቸጋሪው ነገር መጣ....ይህን ምግብ ያልጀመረ ህፃን ማን ያጥባው??????

የተለያዩ አጥቢ እናቶች ይህን ህፃን ሊያጠቡ ቢሞክሩም ህፃኑ ግን የማንንም ጡት ከአፉ ሊያስጠጋ ፍቃደኛ አልሆነም።ይልቁኑ አጥቢዎቹ ሲመጡ ይባስ ያለቅስ ነበር።

የፊርዐውንም ሚስት እጅጉን ተጨነቀች አላህ በልቧ የሙሳን ፍቅር ስለከተበባትም በህፃኑ ለቅሶ ጭንቀት ምትገባበት ጠፋት።
ይሁ ሁሉ ሲሆን ሁኔታዎችን ትከታተል የነበረችው የሙሳ እህት ምንም እንደማያውቅ ሆና፦"ይህን ህፃን ለናንተ የሚያሳድግላችሁን ቤተሰብ ለመላክታችሁ!! ታማኝም ናቸው" አለቻት።

የህን ስትሰማ የፊርዐውን ሚስት ደስታዋ ወደር አጣ።የፈለጉትን ክፍያም ለአጥቢዋ እንደሚከፍሉም ቃሉ ገቡላት'ና የሙሳ ትክክለኛዋ እናት እንድትመጣ አደረጉ።

የሙሳ እናት ቤተ መንግስት ገብታ ልክ ልጇን ስትመለከት ልቧ ተንሰፈሰፈ...፣እንባዋ ከአይኗ ሊሾልክ ተቃረበ።እንደምንም ራሷን ተቋቁማ ህፃኑን ልታጠባ ስታቅፈው ህፃኑ ለቅሶውን ትቶ ጡቷን ይሞጥሙጥ ጀመር።ፊርዐውን እና ኣሲያ(የፊርዐውን ሚስት) ይህን ሲመለከቱ በጣም ተደሰቱ።
በዚህ ሁኔታ የሙሳ እናት እየተከፈላት ልጇን ለ2 አመታት ያህል አጠባችው።

ግዜ ግዜን እየተካ ሙሳም ትልቅ ልጅ ሆነ።ምንም እንኳን ሙሳ የፊርዐውን ያብራኩ ክፋይ ባይሆንም በህዝቡ ዘንድ ግን የፊርዐውን ልጅ በመባል ነው ሚታወቀው።

ከእለታት አንድ ቀን ሙሳ በጠራራ ፀሀይ ከተማ ውስጥ እየተራመደ ሳለ አንድ ግብፃዊ እና አንድ በኒ ኢስራኢላዊ ሲደባደቡ ተመለከተ። በኒ ኢስራኢላዊውም ሙሳን አድነኝ በማለት ተጣራ።

ሙሳም ይህን ግዜ ግብፃዊው ላይ ገራሚ ቦክስ ሰነዘረበት'ና ሳያስበው የግብፃዊው ህይወት በሙሳ እጅ አለፈች።ይሁን እንጂ ማንም አላወቀበትም ነበር።

ይሄን ግዜ ሙሳ በጣም በመፀፀት አላህን ምህረት ለመነው። አላህም ተውበቱን ተቀብሎት፦"ሙሳ ሆይ! በልቅናዬ እምላለሁ ይህች የገደልካት ነፍስ ለቅፅበት እንኳን በኔ ጌትነት ያመነች ብትሆን ከባድ ቅጣትን አቀምስህ ነበር" አለው።

ሙሳም ከዚያ ቀን አንስቶ የግብፃዊው ሟች ወገን መጥተው እንዳይበቀሉት በጣም ስለሰጋ እንቅስቃሴውን በጥንቃቄ ማድረግ ጀመረ።

በማግስቱም ሙሳ ከተማ ላይ ሳለ ይህ ትናንት ሲደባደብ የነበረው (በኒ ኢስራኢላዊው) የሙሳ ዘመድ ዛሬም ከሌላ ግብፃዊ ጋር ሲደባደብ ተመለከተው።
የሙሳ ዘመድ ሙሳን ሲመለከት ዛሬም የእርዳታ ጥሪውን ለሙሳ አሰማ።

ሙሳም ወገኑን(በኒ ኢስራኢሉን) ሲመለከት፦"አንተ በእርግጥ ግልጽ ጠማማ ነህ" አለው።
ወገኑም፦"በትናንትናው ቀን ነፍስን እንደ ገደልክ ልትገድለኝ ትፈልጋለህን በምድር ለይ ጨካኝ መሆንን እንጅ ሌላ አትፈልግም፡፡ ከመልካም ሠሪዎችም መሆንን አትፈልግም" አለው።

በዚያ አካባቢ የነበሩ የግብፅ ነዋሪያንም ወገናቸውን የገደለው ሙሳ መሆኑን ሲያውቁ እሱን ሊገድሉት መመካከር ጀመሩ።
ይህን የሰማ ሂዝቂል የተባለ ግብፃዊ ሙእሚን ለሙሳ፦"ግብፃውያን አንተን ሊገድሉ እየተመካከሩ ስለሆነ የግብፅን ምድር ለቅቀህ እንድትወጣ እመክርሀለሁ" ብሎ መከረው።

#ይቀጥላል..............

 በድሮ ዘመን አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ ነይነዋ ወደተባለች ምድር ዩኑስ የተባለን ሰው በነቢይነት ይልከዋል።ዩኑስም አላህ እሱን ነቢይ አድርጎ ስለመረጠውም በጣም ተደስቶ ተልዕኮውን መፈፀም ጀመረ...
23/11/2020



በድሮ ዘመን አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ ነይነዋ ወደተባለች ምድር ዩኑስ የተባለን ሰው በነቢይነት ይልከዋል።

ዩኑስም አላህ እሱን ነቢይ አድርጎ ስለመረጠውም በጣም ተደስቶ ተልዕኮውን መፈፀም ጀመረ።

ምንም እንኳም ዩኑስ ያለ እረፍት የነይነዋን ህዝቦች ወደ አላህ ቢጣራም ለጥሪው ምላሽ የሰጠ አንድም ፍጥረት አላገኘም።

ዩኑስ ተስፍ ቆረጠ...የህዝቡን አመፅ እና እንቢተኝነት ሲመለከት የነይነዋን ምድር ትቶ ወደማያውቅበት ሀገር ለመሄድም ወሰነ።ነገር ግን የአላህን ፍቃድ አልጠየቀም ነበር እንዲሁ በብስጭት ነበር ዩኑስ ሀገሩን ሊለቅ የወሰነው።

ዩኑስም በማግስቱ ባህር ዳርቻ በመሄድ መርከብ ጠብቆ መርከቢቱ የትም ትሂድ የት ብቻ መርከቢቱ ወደምትሄድበት ሊሄድ ሂሳብ ከፍሎ ተሳፈረ።

ሰዐቱ ፀሀይ ልትጠልቅ ጀንበርን በመሰነባበት ላይ ነበረች....ጨለማውም ምድርን ሊሸፍን ዝግጅት ላይ ነው።ይሄን ግዜ ዩኑስን እና በርካታ ተሳፋሪዎችን የጫነችው መርከብ በጨለማ ባህሩን እየሰነጠቀች መጓዝ ጀመረች።

ሁሉም ነገር በመርከቢቷ ረግቷል..ሰላም እና ሰጥታም እጅጉን ሰፍኗል።በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ መርከቢቷ ብዙ ከተጓዘች በኋላ ባልታሰበ መልኩ በድቅድቅ ጨለማ መርከቢቷን ከየት እንደመጣ ያልታወቀ ማዕበል ከየአቅጣጫው ያናውጣት ጀመር።

ሁሉም ግራ ተጋባ የመርከቧ ሰራተኞች ሁኔታውን ሊያረጋጉ ቢሞክሩም ምንም ሊረጋጋ ባለመቻሉ የመርከቧ ክብደት እንዲቀንስ እያንዳንዱ ሰው የጫነውን ጭነት ከመርከቧ እንዲጥል አዘዙ።

ምንም እንኳን ተሳፋሪው ሁሉ የያዘውን እቃ ወደ ባህር ቢወረውርም የመርከቢቷ መናወጥ ሊቆም አልቻለም።በመጨረሻም መርከቧ ላይ ያሉ ተሳፋሪዎች፦"እዚህ መሀከላችን አንድ ከአሳዳሪው ያመለጠ ባሪያ አለ ማለት ነው።ስለዚህ ያን ወንጀለኛ ለማወቅ እጣ እንጣል" በማለት ተስማሙ።

እጣው ተጀመረ....ወረቀቱ ሲከፈት ዩኑስ የሚል ስም ወጣ።ዳግም እጣ ጣሉ፤አሁንም ዩኑስ የሚል ስም ወጣ። ለሶስተኛ ግዜም እጣ ሲጥሉ የዩኑስ ስም ወጣ...። ያን ግዜ ዩኑስ እራሱን ከመርከቢቱ ሲወረውር አንድ አሳ ነባሪ አፉን ከፍቶ ጎረሰው'ና ወደ ባህሩ ዝቅተኛ ክፍል ይዞት ወረደ።

አላህም አሳ ነባሪውን፦"አንድም አጥንት እንዳትሰብር አንድም ስጋ እንዳታኝክ" አለው።

ዩኑስም በአሳነባሪው ጉሮሮ ተሽሎክልኮ ሆዱ ላይ እንዳረፈም ያን አሳ ነባሪ እራሱ ሌላ አሳ ነባሪ ዋጠው።ዩኑስም እራሱን የአሳ ነባሪው ሆድ ውስጥ ሲያገኝ የሞተ መስሎት ነበር፤ ድንገት እግሩን ሲያንቀሳቅስ በህይወት እንዳለ ተረድቶ መዘከር ጀመረ።

አስቡ ሌሊት ነው፣በዛ ላይ ዩኑስ አሳ ነባሪው ሆድ ውስጥ ነው፣በዛ ላይ ዩኑስን የዋጠው አሳ ነባሪ እራሱ ሌላ አሳ ነባሪ ሆድ ውስጥ ገብቷል፣ ጨለማ ላይ ጨለማ ተደራርቧል።

ዩኑስ እዛው በአሳ ነባሪዎቹ ሆድ ውስጥ ሆኖ የሆነ ጫጫታ ይሰማል...እና በልቡ፦"የምን ጫጫታ ነው ምሰማው ...!!!" እያለ ሲያሰላስል
አላህም፦"የባህር ውስጥ ፍጥረታት ለኔ የሚያደርጉት ውዳሴ ነው" ብሎ ወህይ አወረደለት።

ያን ግዜ ዩኑስ፦"ላ ኢላሀ ኢላ አንተ ሱብሀነከ ኢኒ ኩንቱ ሚነ ዛሊሚን (ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ጥራት ይገባህ፡፡ እኔ በእርግጥ ከበዳዮቹ ነበርኩ)" ሲል ወደ አላህ ተጣራ።

ዩኑስ እንዲህ ሲል ከሰባት ሰማያት በላይ ያሉ መላዕክት ይሄን ጥሪ ሰምተው አላህን
እንዲህ አሉት፦ያ አላህ አንድ የሚታወቅ ደካማ ድምፅ ከሩቅ ቦታ ይሰማናል"
አላህም፦"እሱ እኮ ዩኑስ ነው። አምፆኝ በአሳ ነባሪ ሆድ ውስጥ አስሬው ነው" አላቸው።
መላዕክቱም፦"እንዴ! ያ ቀን እና ማታ መልካም ስራዎቹ ወደ ሰማይ የሚወጡለት ዩኑስ?"ብለው ሲጠይቁት
አላህም፦" አዎን" አላቸው።

ያን ግዜ መላዕክቱ ለዩኑስ አማላጅ ሆኑለት'ና ዩኑስን የዋጠው አሳ ነባሪ ከአንድ ደሴት ዳርቻ ሄዶ በአላህ ትዕዛዝ ዩኑስን ተፋው።

ዩኑስ ከአሳ ነባሪው ሆድ ወጥቶ ሲወድቅ የአሳ ነባሪው የሆዱ ሙቀት ዩኑስን እጅጉን አሞቅሙቆት ስለነበር ዝንቦች ይረባረቡበት ጀመር።ያን ግዜ አላህ የዱባ ቅጠልን ዩኑስ በተኛበት ቦታ አበቀለለት።

አላህም ዩኑስ እዛው ሳለ ተውበቱን እንደተቀበለው ወህይ አወረደለት'ና ወደ ህዝቡ እንዲመለስ አዘዘው።

(እሺ አሁን አንዴ ወደኋላ ልመልሳችሁ ነው...አንድም ሰው እንዳይቀር ግርርር ብላችሁ ኑ።)

ዩኑስ መጀመሪያ ህዝቡን ትቶ ሲወጣ አላህ በእነዚያ ህዝብ ላይ ከባድ ቅጣትን አምጥቶ አንዣበበባቸው።ሰማዩ ጠቁሯል...ብቻ ከባድ ቅጣት እንደመጣባቸው ታውቋቸዋል ዩኑስን ማስተባበላቸው በጣሙን ፀፅቷቸዋል።

አሁን ሁሉም ጥፋቱን አምኖ የሀዘን ልብስ ለብሰ፣ላሞችን ከጥጃዎቻቸው ለይተው፣በጎችን እና ፍየሎችን ከግልገሎቻቸው ለይተው፣ ግመሎችንም ከግልገሎቻቸው ልይተው፣ ህፃናት ልጆችንም ከእናቶቻቸው ለይተው ሁሉም ኡኡኡ ብሎ ሲጮህ አላህ ያዝንልናል በሚል ሚዳ ላይ ወጥተው ኡኡኡ...እያሉ አላህን በፀፀት እንባ ለመኑት።

አላህም ተውበታቸውን ተቀብሎ ያመጣባቸውን መቅሰፍት መለሰላቸው። ከዚያም ያ የጠፋውን ነቢያቸውን ይቅርታ ሊጠይቁት በጉጉት ይጠባበቁት ጀመር።

(እሺ አሁን ወደ ቅድሙ ቦታ ኑ...አንድም ስው እንዳይቀር...፤ዩኑስን አጅበን እንመጣለን።)

ከዚያም ዩኑስ እዛች የዱባ ቅጠል ስር ሆኖ ካገገመ በኋላ የቀድሞው ህዝቡ ወደሚገኝበት የነይነዋ ምድር ዳግም ዳዕዋ ለማድረግ ጉዞ ጀመረ።

ዩኑስም ልክ ነይነዋ ከተማ ውስጥ ሲገባ ከ 100,000(መቶ ሺህ) ህዝብ በላይ ተገልብጦ በመውጣት ደማቅ አቀባበል አደረጉለት።በህዝቡ መለወጥ በጣምም ተገረም....እነሱም የተከሰተውን ሁሉ በዝርዝር ነግረውት ይቅርታም ጠየቁት።እሱም ሰላሳለፋቸው አሰቃቂ ግዜያት አወጋላቸው።

ከዚያ በኋላ የዩኑስን ትምህር እየተቀበሉ ለረጅም አመታት በሰላም ከኖሩ በኋላ ዩኑስ ይህ ነው ተብሎ በማይታወቅ እድሜው ይህችን አስቸጋሪ አለም በሞት ተገላገለ።
(የአላህ ሰላም እና እዝነት በዩኑስ ላይ ይሁን)

___________________________
ምንጮች፦
القرءان الكريم
ﺍﻟﺒﺪﺍﻳﺔ ﻭﺍﻟﻨﻬﺎﻳﺔ /ﺍﻟﺠﺰﺀ ﺍﻷﻭﻝ /
صحيح مسلم
مسند الإمام أحمد

 እርግጠኛ ነኝ አብዝሀኛዎቻችን ይሄን ነብይ በስም ብቻ ነው የምናውቀው። አይደል እንዴ...!!!ነገሩ እንዲህ ነው...ለአንድ አካባቢ ተልኮ ህዝቡን ሲያገለግል የከረመ አንድ ነቢይ ነበር።ይህም...
22/11/2020



እርግጠኛ ነኝ አብዝሀኛዎቻችን ይሄን ነብይ በስም ብቻ ነው የምናውቀው። አይደል እንዴ...!!!

ነገሩ እንዲህ ነው...
ለአንድ አካባቢ ተልኮ ህዝቡን ሲያገለግል የከረመ አንድ ነቢይ ነበር።ይህም ነብይ መሞቻው ሲቃረብ የአከባቢውን ህዝብ ሰብስቦ፦"እኔ ስሞት የህዝቡን ሀላፊነት ከእናንተ ውስጥ ለአንድ ሰው አስረክቤ መሞት ነው ምፈልገው።ያም ሀለፊነቱን የማስረክበው ሰው 3 ተግባራትን የሚፈፅም ሰው መሆን አለበት።እነሱም...
1፦ቀኑን በፆም የሚያሳልፍ
2፦ሌሊቱን በሰላት የሚያሳልፍ
3፦የማይቆጣ
ስለዚህ ከእናንተ ውስጥ እነዚህን ተግባራት የሚፈፅም ማን ነው" አለ።

ሁሉም ዝም አለ...ነገር ግን ዙል ኪፍል እጁን አውጥቶ፦"እኔ" አለ።
ያ ነቢይም ሀለፊነቱን ለዙል ኪፍል አስረክቦ ዱንያን ተሰናበተ።ዙልኪፍልም ሀገሪቱን በፍትህ ይመራ ጀመር።

ከእለታት አንድ ቀን ኢብሊስ ዙል ኪፍልን በስህተት ሊጥለው ፈልጎ ሸይጣኖችን ሰብስቦ፦"እያንዳንዳችሁ ዙል ኪፍልን በስህተት የመጣል ግዴታ አድርጌባችኋለሁ" አላቸው።

ሸይጣኖችም ዙል ኪፍልን ለማሳሳት ብዙ ከታገሉ በኋላ ተስፋ በመቁረጥ ኢብሊስ ዘንድ በመሄድ፦"አልቻልንም" አሉት።

ኢብሊስም፦"እሽ እኔ እንዴት እንደማሳስተው አሳያችኋለሁ" ብሏቸው ወደ ዙል ኪፍል ዘንድ ሄደ።

ዙል ኪፍል ማታ እየሰገደ ስለሚያድር እንቅልፍ እሚተኛው ከዙህር በኋላ ነው። እና ዙል ኪፍል ቀይሉላ (ከዙህር በኋላ የሚተኛ እንቅልፍ) ሊተኛ ዝግጅት ላይ ሳለ ኢብሊስ በትልቅ ሽማግሌ ሰው ተመስሎ እቤቱን አንኳኳ።

ዙል ኪፍልም፦"ማን ነው?" አለ።
ኢብሊስም፦"እኔ በእድሜ የገፋው ሽማግሌ ነኝ። አንድ ጉዳይ ገጥሞኝ ነው" አለ።

ዙል ኪፍልም ተነስቶ ከፈተለት'ና ጉዳዩን ጠየቀው።ኢብሊስም፦"የሆኖ ሰዎች እንዲ በድለውኝ እንዲ አድርገውኝ....."እያለ የቆጥ የባጡን ለረጅም ሠዐት ማውራት ጀመረ።ዙል ኪፍልም እንቅልፉን ተቋቁሞ በጥሞና ካደመጠው በኋላ ሽማግሌውን፦ነገ ችሎት ላይ ቅረብ'ና እዛ ጉዳይህን እናይልሀለን" ብሎ ሸኘው።ያን ቀን ዙል ኪፍል የእንቅልፍ ሰዐቱ ሳይተኛም አለቀችበት።

በሁለተኛው ቀን ጠዋት ላይ ዙል ኪፍል ችሎት ላይ ሆኖ ያን ሽማግሌ ረጅም ሰዐት ቢጠብቀውም ሊመጣ አልቻለም።ዙል ኪፍልም ብዙ ከጠበቀው በኋላ ትቶት ሄደ።

ከዚያም ማታ ሲሰግድ ያደረው ዙል ኪፍል ጎኑን ሊያሳርፍ ፍራሹ ላይ ገና ከመቀመጡ በሩ ተንኳኳ።
ዙል ኪፍልም፦"ማን ነህ?" ሲል
ኢብሊስ፦"የትናንቱ ሽማግሌ ነኝ" አለው።
ዙል ኪፍል ተነስቶ በሩን ከከፈተ በኋላ፦"ችሎት ላይ ቅረብ ብዬህ አልነበር ለምን ቀረህ?" አለው።
ኢብሊስም፦"አረ በጣም መጥፎ ሰዎች ናቸው የበደሉኝን ላንተ ነግሬ ችሎት ላይ ጉዳያችንን እንደምታይ ሲሰሙ ሀቅህን እንሰጥሀለን አሉኝ።ከዚያም ችሎቱ ሲያልቅ ከለከሉኝ" አለው።
ዙል ኪፍልም፦"በቃ አሁን ሂድ ነገ ችሎት ላይ ግን እንዳትቀር" ብሎ ሸኘው'ና የዛሬዋንም እንቅልፍ መስዋዕት አደረገ።

በማግስቱ ዙል ኪፍል ችሎት ላይ ይሄን ሽማግሌ ቢጠብቀው... ቢጠብቀው ሊመጣ አልቻለም።የቀኑን ችሎት ካጠናቀቀ በኋላ ሌሊት ሲግድ ያደረውን'እና ከሁለት ቀን አንስቶ እረፍት ያጣውን ወገቡን ሊያሳርፍ እቤት ገባ።

ለዘበኞቹም፦"ማንም ሰው ቢመጣ እንቅልፌን ሳልጨርስ በሩን እንዳያንኳኳ" ብሎ ክፍሉን ዘግቶ ተኛ።

ልክ ዙል ኪፍል እንደተኛውም ሽማግሌው ከች አለ'ና ሊየንኳኳ ሲል ዘበኞች ከለከሉት።

ኢብሊስም፦"አይ እኔ ትናንት መጥቼ ጉዳዬን ነግሬዋለሁ አሁን ቀጥሮኝ ነው የመጣሁት" አላቸው።እነሱም በምንም ተዐምር አናስገባህም አሉት።

የን ግዜ ኢብሊስ ከርቀት አንዲት ቀለበት የምታክል ቀዳዳ በሩ ላይ ተመለከተ'ና ተወርውሮ በሷ ሾልኮ ገባ።ከዚያው ከውስጥ በኩል ሆኖ ሲያንኳኳ ዙል ኪፍል ደንግጦ ተነሳ።

ዙል ኪፍል ሽማግሌውን ክፍሉ ውስጥ ሲመለከተው ዘበኛውን ጠርቶ፦"ማንም እንዳይገባ ብዬህ አልነበር!!! ለምን ፈቀድክለት?" ብሎ ሲጠይቀው

ዘበኛውም፦"እኔ አልፈቀድኩለትም ነገር ግን በዚህች ቀዳዳ ነው የገባው" ብሎ የበሩን ቀዳዳ አሳየው።ያን ግዜ ዙል ኪፍል ሽማግሌውን ነቃበት'ና፦"አንተ የአላህ ጠላት ኢብሊስ ነሃ...!!" አለው።

ሽማግሌውም፦"አዎ እኔ ኢብሊስ ነኝ በተለያዩ ነገሮች ፈትኜክ ስላልቻልኩህ ይሄን ስልት ተጠቅሜ ላስቆጣህ ነበር።ይሁን እንጂ አላህ ጠብቆህ አሁንም አልቻልኩህም" አለው።

ለዚያ ነው እንግዲህ አላህም ዙል ኪፍል(ሀላፊነትን የመወጣት ባለቤት) ብሎ የሰየመው።

ማሳሰቢያ፦በሙስነድ የተዘገበው ዙል ኪፍል ይህ እንዳይመስላችሁ።ይኼኛው ዙል ኪፍል እና ዙል ኪፍል (የበኒ ኢስራኢሉ ዓቢድ) ይለያያሉ።
_______________
ምንጭ፦
ﺍﻟﺒﺪﺍﻳﺔ ﻭﺍﻟﻨﻬﺎﻳﺔ /ﺍﻟﺠﺰﺀ ﺍﻷﻭﻝ /

اَلسَلامُ عَلَيْكُم وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ‎ አዩብ ኢብን ሙስ ኢብን ራዚኽ ኢብን ዒስ ኢብን ኢስሀቅ ኢብን ኢብራሂም ይባላል የዛሬው እንግዳችን።እናቱም የ...
18/11/2020

اَلسَلامُ عَلَيْكُم وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ‎



አዩብ ኢብን ሙስ ኢብን ራዚኽ ኢብን ዒስ ኢብን ኢስሀቅ ኢብን ኢብራሂም ይባላል የዛሬው እንግዳችን።

እናቱም የነቢዩላህ ሉጥ ልጅ ስትሆን ባለቤቱ ደግሞ ራህማ ትባላለች የነቢዩላህ ዩሱፍ የልጅ ልጅ ናት

ይህ ነቢይ በጣም ሚገርመው ዙሪያው በነቢያት የታጠረ ነው።እራሱ የነቢያት የልጅ ልጅ ሲሆን ሚስቱ እና እናቱም የነቢያት ልጆች ናቸው።

እናላችሁ ይህ ነቢይ የዘር ሀረጉ በከበርት ቤተሰቦች የተከበበ ከመሆኑም ባሻገር ዱንያ ላይም አላህ ሰፋ አድርጎለት ነበር።

አዩብ የብዙ አገልጋዮች እና የብዙ ማሳዎች ባለቤት ብቻ ሳይሆን በጣም የብዙ ልጆችም አባት ነበር።በሀገሩ ካሉ ባለሀብቶች ውስጥ በደግነቱ እና በላጋስነቱም የሚታወቅ ምርጥ ነቢይም ነው።

በዚህ በተመቻቸ የኖሮ ደረጃ ላይ እሱ እና ቤተሰቦቹ ህይወትን እያጣጣሙ ስላ ነበር አላህ በአንድ ሌሊት ውስጥ ሚስቱ ስትቀር መላ ልጆቹን እና ሙሉ ንብረቱን ያጠፋበት።(ፈተናው ተጀመረ)

ይህም ብቻ አልበቃም አዩብ በቅፅበት በአደገኛ በሽታ ላይም ወድቆ ሰውነቱ እየቆሳሰለ ስጋው ከአከላቱ መራገፍ ጀመረ።
በሰውነቱ ላይም እንደ ሴት ጡት ያለ ነገር ያብጥበት'ና እብጠቱ ሲፈነዳም ምግል እና እዥ ይወጣል።ሽታው ይከብድ ነበር....

ይህን የተመለከቱ የከተማይቱ ነዋሪዎችም ተላላፊ በሽታ ነው በሚል አዩብን ከከተማ በማግለል አንድ ተራራ ላይ ወስደው ጣሉት።

ምንም እንኳም አዩብ በበሽታ ተኮማትሮ የከተማይቱ ህዝብ ተፀይፈው ከመሀከላቸው ቢያገሉትም በፍፁም ፍቅር እና እዝነት የተሞላችው ውድ ባለቤቱ ግን ልክ እናት ለልጇ የምታደርገውን እንክብካቤ አይነት በዚያ ተራራ ላይ ያለ አጋዥ ታደርግለት ነበር።
ቀን ወደ ከተማ ወርዳ በየቦታው ተቀጥራ በመስራት ሲመሽ ለአዩብ ምግብ ገዝታለትም ትመጣ ነበር።

አዩብ የበሽታ ዘመኑ እጅግ ዘገየበት። ይሁን እንጂ አዩብ በዚህ ሁኔታውም ቀን እና ማታ ጌታውን ከማጥራራት ጋር ማመስገንን አልተወም።ትዕግስት አስጨራሽ የሆኑ 7 የእንግልት አመታትን በዚያ ተራራ ላይ ካሳለፉ በኋላ ከእለታት አንድ ቀን ይህች መከራዋ የበዛባት የአዩብ ሚስት ተንሰቅስቃ ማልቀስ ጀመረች።

አዩብም፦"ምን ሆንሽ?" ሲላት...
እሷም፦"መከራህ በዛ። ያለ እረፍት 7 የእንግልት አመታትን አሳለፍን እባክህ ጌታህን ለምን ይህን በላእ እንዲያነሳልም" አለችው።
አዩብም፦"ከዚህ በፊት በድሎት ስንት አመታት አሳልፈናል?" አላት።
እሷም፦"70 አመታት አሳልፈናል" አለችው
አዩብም፦"70 አመታትን በድሎት ሲያንደላቅቀን ከርሞ አሁን ለ7 አመታት ስላሳመመኝ ሰብር አናደርግም እንዴ.. ወላሂ አላህ አፊያ ካደረገኝ 100 ግዜ እገርፍሻለሁ!!!?" አላት።

ከእለታት አንድ ቀን ከተማ ስራ ፍለጋ በወጣችበት በጣም ጣፋጭ ምግብ ይዛ ተመለሰች።እንዲህ አይነት ምግብ ከየት አገኘሽ ሲላት ምንም መልስ ሳትሰጠው አበላችው።

ዳግም በሁለተኛ ቀንም ከተማ ወጥታ የትናንቱ አይነት ጣፋጭ ምግብ ይዛ ስትመጣ ከየት ነው ያመጣሽው ብሎ አጥብቆ ሲጠይቃት ያን ግዜ ፀጉሯን ሸጣ እንዳመጣችለት ነግራው ፀጉሯን ስትገልጥለት አዩብ እጅጉን አዘነ አላህንም ሊማፀን ወሰነ።

በማግስቱ እሷ እንደተለመደው ምናምን ፍለጋ ከተማ በወረደችበት አዩብ እጁን ዘርግቶ ሀራም አይተው በማያውቁት አይኖቹ እንባ እያዘነበ፦"(ጌታዬ ሆይ!!)እኔን መከራ አገኘኝ አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ" በማለት አላህን ተማፀነ።

አላህም የታጋሾችን ጥሪ ምላሽ ይሰጣል'ና፦" በእግርህ (ምድርን) ምታ፡፡ ይህ ቀዝቃዛ መታጠቢያ(እና) መጠጥም ነው" አለው። አዩብም ምድሪቱን በእግሩ ሲመታ ሁለት ምንጮች ወጡ፤አንዱን ጠጥቶ በአንዱ ሲታጠብ አዩብ ሙሉ በሙሉ ከበሽታው በመፅዳት የድሮ ውበቱ እና ግርማ ሞገሱ ተመለሰ።

አዩብ በዚያ ሁኔታ ላይ ሳለ በአጠገቡ ከሰማይ የአንበጣ መንጋዎች መጡ'ና ወርቅ ሆነው መዝነብ ጀመሩ። አዩብም እየተሯሯጠ የሚዘንበውን ወርቅ በልብሱ መሰብሰብ ሲጀምር አላህም፦"አንተ አዩብ ከዚህ ከምትሰበስበው ወርቅ አላብቃቃሁክም እንዴ!!!" ብሎ ተጣራው።

አዩብም አራዳ ነበር'ና፦"ልክ ነህ ጌታዬ፤ግን ካንተ በረከት እንዴት እብቃቃለሁ።አንተ እይጎድልብህ እባክህ ተወኝ ልሰብስብ" ብሎ መሰብሰቡን ቀጠለ።

ከዚያም ሚስት የቀን ስራ ስትሰራ ውላ ለባሏ ምግብ ሸምታ አዩብ የሚገኝበት ቦት ስትደርስ አዩብን አጣችው።እዛ ጋር አንድ ሰው ተመልክታም፦"እዚህ ጋር አንድ በሽተኛ ትቼ ሄጄ ነበር አይተኸዋል? ደሞ ድሮ ከመታመሙ በፊት ልክ አንተን ይመስል ነበር" ስትለው እዛ ጋር የነበረውም ሰው፦"እኔ እኮ አዩብ ነኝ" አላት።

ተቃቅፈው ከተለቃቀሱ በኋላ ያኔ ቃል የገባውንም 100 ግርፊያ እንዲገርፋት አላህም አዘዘው። ነገር ግን፦"ትንሽ አርጩሜ ይዘህ አንድ ግዜ ትንሽ መታ አድርጋት እኔም በመቶ እቆጥርልሀለሁ" አለው።

ከዚያም አላህ ለአዩብ ድሮ ከነበረው ሀብት እጥፍ ድርብ አድርጎ ካሰው።ጠፍተው የነበሩትንም ልጆቹን ሁሉ ሰበሰበለት'ና ድሮ ይኖሩ ከነበረው የድሎት ኑሮ በላይ መኖርም ጀመሩ።
(የአላህ ሰላም እና እዝነት በአዩብ እና በባለቤቱ ላይ ይሁን)
__________________________________
(በታሪካቸው ውስጥ ለአእምሮ ባለ ቤቶች በእርግጥ መገሰጫ ነበረ፡፡ (ይህ ቁርኣን) የሚቀጣጠፍ ወሬ አይደለም፡፡ ግን ያንን በስተፊቱ ያለውን አረጋጋጭ ለነገርም ሁሉ ገላጭ ለሚያምኑ ሕዝቦችም መሪና ችሮታ ነው።) *ሱረቱ ዩሱፍ*
___________________________________
ምንጮቻችን፦"
القرءان الكريم
صحيح البخاري
مسند إمام أحمد
البداية والنهاية

اسلام عليكم ورحمة الله وبركاته                  #ክፍል2ህዝቦቼ ሆይ! ጌታችሁን ማርታ በመጠየቅ ወደ እሱም ተመለሱ እሱ አዛኝ ጌታ ሲሆን ወደ እርሱ የሚመለሱ ባሪያ...
15/11/2020

اسلام عليكم ورحمة الله وبركاته



#ክፍል2

ህዝቦቼ ሆይ! ጌታችሁን ማርታ በመጠየቅ ወደ እሱም ተመለሱ እሱ አዛኝ ጌታ ሲሆን ወደ እርሱ የሚመለሱ ባሪያዎቹን ይወዳል።

አላህም ለእናንተ መልካምን ይሻል...ለዚህም ነው እኔን በመልዕክተኝነት ወደ እናንተ የላከኝ" አላቸው።

ህዝቡም፦"ሹዐይብ አንተ ድግምት የተሰራብህ ሰው ነህ። እኚህ ወገኖችህ(ጎሳዎችህ) ባይኖሩ ድራሽህን እናጠፋህ ነበር" አሉት።

ይህን ግዜ ሹዐይብ ከህዝቦቹ ዛቻን እና ማላገጥን ሲመለከት ተስፋ ቆረጠ።ህዝቡንም፦"ህዝቦቼ ሆይ! እናንተ የታያችሁን ስሩ እኔም የታየኝን እሰራለሁ።ከዚያም ማናችንን አሳፋሪ ቅጣት እንደሚያገኘን እንመለከታለን" አላቸው።

ይህን ግዜ ህዝቦቹ፦"እንደውም ቅጣት ስትል ትዝ አለን እውነት መልዕክተኛ ከሆንክ እስቲ ቅጣት አስወርድብን" በማለት አሾፉበት።

ሹዐይብም፦" እሽ ማን ውሸታም እንደሆነ ታዩታላችሁ!!" ብሎ ህዝቡን ትቶ አል አይካ ወደተባለች አጎራባች ሀገር ሄደ።

ሹዐይብም አል አይካ የተባለችውን ሀገር ሲገባ ህዝቡን ልክ የሀገሩን(የመድየንን )አይነት ኑሮ ሲኖሩ ተመለከታቸው።

በሀገሪቱ ሲዘዋወርም ቅርንጫፎቻቸውን ያንጋለሉ ፍራፍሬዎችን፣የእርሻ ማሳዎችን እያቋረጡ የሚፈሱ ጅረቶችን እና የተንደላቀቁ ቤቶችን ተመለከተ።

ነገር ግን እነዚህም ህዝቦች እንደ መድየን አቻዎቻቸው ሁላ የጣኦታት ተገዢ፣እርስ በርስ አጭበርባሪ፣የሚዘን ዘራፊ እና እራስ ወዳድ ህዝቦች ሁነው አገኛቸው።

ሹዐይብ ምንም እንኳን ለከተማይቱ እንግዳ ቢሆንም ወደ አላህ ለመጣራት ምንም አላፈገፈገም ነበር።እንዲህም ሲል ጥሪ አደረገላቸው፦" አላህን ተጠንቀቁ...ቁጣውንም ፍሩ።

አላህ ብክለትን አይወድም ወንጀለኛ ህዝቦንም አይወድም። ስለዚህም በእኩይ ተግባሮቻችሁ ምድርን አትበክሏት"

ይህን ሲሰሙ ጥሪውን ሙሉ በሙሉ ውድቅ በማድረግ፦"አንተ ውሸታም የምትናገረው ነገር እውነት ከሆነ እስቲ የጌታህን ቅጣት አምጣ" አሉት።

ሹዐይብም፦"እናንተ የምትሰሩትን አላህ ያውቀዋል እኔ ስራዬ መልዕክቱን ማድረስ ብቻ ነው። የቻልኩትን ያህል እናንተንም አስተካክ

ላለሁ ረዳቴም አላህ ብቻ ነው" አላቸው።
እነሱም፦"አንተ ግልፅ ድግምተኛ ነህ።ቆይ አንተ ከኛ በምን ተለይተህ ነው የፈጣሪ መልዕክተኛ የምትሆነው!!!" አሉት።

ይህን ሲመለከት ሹዐይብ የ አል አይካ ህዝቦችን ባሉበት ትቶ ወደመጣበት የትውልድ ሀገሩ መድየን ተመልሶ ሄደ።

መድየን ሲደርስ የመድየን አመፀኛ ህዝቦች ሹዐይብን ማስተባበል አንሷቸው በሱ መልዕክተኝነት ያመኑትን ሲያንከራትቷቸው አገኘ።

ሹዐይብም ወደ አላህ የሚያደርሰውን መንገድ ህዝቦቹ እንዳያቋርጡ እና ካቋረጡም ቅጣታቸው የከፋ እንደሆነም አክሎ ለህዝቡ ነገራቸው።

ከእለታት አንድ ቀን የመድየን ህዝቦች ሹዐይብ ዘንድ በመምጣት፦"ይህን ሀይማኖትህን ልቀቅ እንቢ ያልክ እንደሆን አንተንም ተከታዮችህንም ከሀገር እናባርራችኋለን" ሲሉት

አንድ ሙዕሚን ከሹዐይብ ዘንድ ነበር እና፦"ሰዎች! ከሀገር የሚያስባርር ተግባር እኮ እኛ አልፈፀምንም። ለምንድነው ምታባርሩን!!!" አላቸው።

እነሱም፦"እንግዲያውስ ወደ ድሮው ሀይማኖታችሁ እንድትመለሱ እናስገድዳችኋለን" አሉ።

ሹዐይብም፦"ይሄን መንገዳችሁን ጠማማ መሆኑን አውቀን፤አላህ ትክክለኛውን መንገድ ከመራን በኋላ ወደ ጨለማ የምንመለስ ይመስላችኋልን!!!" አላቸው።

ከዚያም ሹዐይብ በመተናነስ እጁን ወደላይ ዘርግቶ፦"ጌታችን ሆይ! በእኛ እና በህዝባችን መሀክል በእውነት ፍረድ፤ አንተም እውነተኛ ፈራጅ ነህ'ና" ብሎ አላህን ተማፀነ።

ሹዐይብም ከህዝባቸው ጋር ያለውን ንትርክ እርግፍ አድርገው ተዉት።ያመኑትን ብቻ በአንድ ቤት ሰብስበው ትምህርት መስጠት ጀመሩ።ይሁን እንጂ ህዝቦቹ ግን ሹዐይብን'ና ተከታዮቹን መተናኮል አልተዉም።

በመጨረሻም የቁርጥ ቀን ደረሰ።ህዝቡ ሀገር ሰላም ብሎ ለአማልክቱ ከሰገዱ በኋላ በሌሊት ለስራ ወጡ።

እርስ በርስ እየተጭበራበሩ እየተሸዋወዱ ቀኑ ካሳለፉ በኋላ ፀሀይ ገብታ ለተረኛው ጨለማ ቦታ ለቀቀች።

ያን ቀን ማታው ይከብድ ጀመር ሰዉ ሁሉ እርካታ ርቆታል።ሁሉም ተጫጭኖታል...በዚህ ሁኔታ ላይ ሰሉ ከከርሰ ምድር ውስጥ ከፍተኛ ድምፅ ወጣ።

መሬት በከፍተኛ ሁኔታ ድምፁን እያስተጋባች መንቀጥቀጥ ጀመረች።መድየንም በጥቂት ደቂቃዎች ልክ እንደፈራረሰ ቤት ድምጥማጧ ጠፋ።

ከምንም በላይ የነዚህን ለየት የሚያደርገው የመድየን ምድር ስትንቀጠቀጥ ሙእሚኖችም እዛው ከተማዋ ውስጥ ነበሩ።ነገር ግን በአላህ ጥበብ በነጋታው በሰላም ከሀገሪቱ ወጡ።

ሹዐይብም የከተማይቱን መውደም እና በህዝቡ ላይ የደረሰውን መቅሰፍት ባየ ግዜ፦"ህዝቦቼ ሆይ! የጌታዬን መልዕክት አድርሼላችሁ መክሪያችሁም ነበር።ታዲያ በከሀዲያን ህዝቦች መጥፋት እንዴት አዝናለሁ" አለ።

ሹዐይብም ከዚያ በኋላ በወደመችው መድየን ኑሮውን ከሁለት ሴት ልጆቹ ጋር ይኖር ጀመር።

በዚያ ግዜ ሹዐይብ ይተዳደር የነበረውም በጎችን በማርባት ስለነበር ትንሽ እርጅና ሲጫጫነው በጎቹን የማርባቱን ሀላፊነት ሁለቱ ሴት ልጆቹ ተረከቡ።

ብዙ ግዜ በጎችን ውሀ ለማጠጣት ወደ ወንዝ ሲወስዱ እነዚህ ሴቶች አይናፋር ስለሆኑ ሁሌም ከሰዉ በስተመጨረሻ ነበር በጎቹን የሚያጠጡት።

እችን ቦታ የሙሳን ትረካ ስንጀምር በሰፊው እንዳስሳታለን።

ሹዐይብ ከዚያ በኋላ ብዙ አመታትን ከኖረ በኋላ በጆርዳን ምድር ዋዲ ሹዐይብ ተብሎ በሚያወቀው ተራራ ላይ ተቀብሯል።

ግን አንዳንድ የታሪክ መዛግብት ሹዐይብ መሞቻው አካባቢ ከተከታዮቹ ጋር መካ መጥቶ ከሞተ በኋላ በካዕባ በስተ ምዕራብ በኩል

በሚገኙት በ ዳረ-ነድዋ እና በ ዳሩ በኒ ሳህም መካከል እንደተቀበሩ ይዘግባሉ። አላሁ አዕለም.....
(የአላህ ሰላም እና እዝነት በሹዐይብ ላይ ይስፈን)

......❀━┅┉┈ #ተፈፀመ┈┉┅━❀
_____________________
ምንጮቻችን፦
القرءان الكريم
ﺍﻟﺒﺪﺍﻳﺔ ﻭﺍﻟﻨﻬﺎﻳﺔ /ﺍﻟﺠﺰﺀ ﺍﻷﻭﻝ /
ﻗﺼﺺ ﺍﻻﻧﺒﻴﺎﺀ ﻟﻠﺸﻴﺦ ﺍﻟﺸﻌﺮﺍﻭﻯ
ﻗﺼﺺ ﺍﻷﻧﺒﻴﺎﺀ ﻟﻺﻣﺎﻡ ﺍﻟﺤﺎﻓﻆ ﺍﺑﻦ ﻛﺜﻴﺮ

اسلام عليكم ورحمة الله وبركاته              #ክፍል1መድየን በአረንጓዴ እፅዋት የተሸፈነች ለሁሉም አይነት ቡቃያ ምቹ የሆነች እና ህዝቦቿም በድሎት እና በከፍተኛ የኑ...
12/11/2020

اسلام عليكم ورحمة الله وبركاته



#ክፍል1

መድየን በአረንጓዴ እፅዋት የተሸፈነች ለሁሉም አይነት ቡቃያ ምቹ የሆነች እና ህዝቦቿም በድሎት እና በከፍተኛ የኑሮ ደረጃ የሚኖሩባት ለኑሮ ምቹ የሆነች ዐረባዊ ሀገር ናት።

ከዚህች ከተማ አጎራባች ላይ " አል-አይካ" የምትባል በውብ ማሳዎቿ እና በአጓጊ ጅረቶቿም የምትታወቅም ምርጥ ከተማ አለች።

ነገሩ እንዲህ ነው ከዛሬ 3000 ሺህ አመት በፊት ነበር። ኑሮ ሁሉ በነዚህ ሁለቱ ከተማዎች አልጋ ባልጋ ሆኗል።

ዝናብ እንደልብ ይዘንባል ፍራፍሬዎች እና አዝርዕትም ያለ ግዜያቸው ዝም ብለው ያበቅላሉ።ህዝቡም በዚህ በተደላደለ ህይወት ኖሮውን በደስታ ያጣጥማል።

የመድየን ከተማ የነዋሪዎቿ ቁጥር አናሳ ቢሆንም ኑሮዋቸው ከማንም ሚስተካከል አልነበረም።

በተለይ የንግድ እንቅስቃሴ በዘመኑ ከየትኛውም ቦታ ይልቅ እዚህች መድየን ከተማ ላይ ድባቡ ይለያል።

በዚያ ዘመን ሹዐይብ የሚባል መልካም ሰውም በዝህች ሀገር ከነዚያ ሰዎች አብሮ ይኖርም ነበር።

ሹዐይብ ህዝቡን እና ሀገሩን እጅጉን የሚወድ ጥንቁቅ ሰው ነው።

ምንም እንኳም የመድየን እና የአል አይካ ከተማ ነዋሪዎች በድሎት እና በፈንጠዝያ የሚኖሩ ህዝቦች ቢሆኑም ሹዐይብ ፊት ላይ ግን ሁሌም ሀዘን እና ትካዜ ይነበብበታል።

ይህም ሊሆን የቻለው ሹዐይብ ተወልዶ ያደገባት የመድየን ከተማ ነዋሪዎች የተለያዩ ጣኦታት እና የዛፎች አምላኪ በመሆናቸው እና ሲሳይን የሚለግሷቸው፣

ከጠላት የሚጠብቋቸው፣ ብሎም ሀገራቸውን የሚባርኩላቸው እነዚህ ጣኦታት መሆናቸውን ማመናቸው ነው።
ለዚህ ነው እንግዲህ የሹዐይብ መተከዝ ምክንያት የሆነው።

ህዝቡም በከዋክብት ወደ ተሞላው ሰማይ ተመልክቶ ማን እንዳንጣለለው አያስተነትንም ነበር።

ወደ ምድርም ተመልክቶ ማን ምድርን ሰንጥቋት ቡቃያን እንደሚያበቅል እና ለመኖርም ምቹ አድርጎ እንደዘረጋት አያስተውልም ነበር።

በተጨማሪም የመድየን ህዝቦች በንግዱ አለም ከፍተኛ እንቅስቃሴ እንደሚያደርጉ ቢታወቅም በንግድ ላይ ሚዛንን በመስረቅ እጅጉን የተካኑ ህዝቦችም ነበሩ።

ምንም እንኳን አላህ እነዚህን ህዝቦች ኑሮዋቸውን እጅጉን ያመቻቸላቸው ህዝቦች ቢሆኑም ለገንዘብ ያላቸው ስግብግብነት ሚዛን ላይ እንዲያጭበረብሩ አድርጓቸዋል።

ከምንም በላይ እሚገርመው ይህን ተግባራቸውን እንደ ነፃነት መገላጫ ይመለከቱት ነበር።

ይህን ግዜ ነው እንግዲህ አላህ በመሀከላቸው የሚገኘውን በመልካም ስነ ምግባሩ ሚታወቀውን ሹዐይብን ለነሱ በነቢይነት የላከላቸው።

ሹዐይብ ንግግሩ ሚማርክ አንደበተ ርቱዕ ሰው ከመሆኑም ባሻገር ስለ አላህ ሲያወራ ደግሞ ልብን ገዝቶ ትኩረትን ይስባል።

ሹዐይብ በጌታው ትዕዛዝ መሰረት ጣኦታትን በማውገዝ አምልኮን ለብቸኛው እና ለሀያሉ አላህ ብቻ እንዲያደርጉ ህዝቡን መጥራት ጀመረ።

በመቀጠልም ህዝቡን በንግዱ አለም የሚፈፅሙትን ፀያፍ ተግባር እንዲያቆሙ እና በሀቅ እንዲገበያዩ አስረግጦ መምከርም ጀመረ።

ህዝቡንም ሰብስቦ፦"ሚዛንን የምትሰርቁ ከሆናችሁ፣መጥፎውን በጥሩው የምትሸውዱ ከሆናችሁም፣

ገባያ ላይ ገዢን ወይም ሻጭን የምታጭበረብሩም ከሆናችሁ ይህ የጌታችሁን መቅሰፍት ሊያወርድባችሁ ይችላል" በማለት በለዘብተኝነት ጥሪ አደረገላቸው።

የሹዐይብ ንግግር እጅግ ጣፋጭ ነበር።ምክንያቱም ወገኖቹ የተመቻቸን ኑሮ፣ ሰላም በሰፈነባት ሀገር ሲኖሩ ማየት ስለነበር ነው።

ሹዐይብ በቀደምት ህዝቦች በኑህ፣በዓድ፣በሰሙድ፣እና በሉጥ ህዝቦች ላይ የደረሰውን የአላህን ቁጣ ጠንቅቆ ያውቅ ነበር።

ስለዚህም ህዝቦቹን ሲመክር፦"በሉጥ ህዝቦች ላይ የወረደውን በላእ(መከራ) አትመለከቱምን!!!

የከተማቸው መውደም እኮ መልዕክተኛቸውን በማመፃቸው ምክንያት ከፍተኛ መቅሰፍት ወርዶባቸው መሆኑን ያመለክታል" እያለ ነበር።

ይህን ግዜ ህዝቡ በሁለት ተከፈለ። ከፊሉ የሹዐይብን ምክር በመቀበል የሹዐይብ ተከታይ ሲሆን ቀሪው ደግሞ በእኩይ ስራው መዘውተርን መርጦ ሹዐይብን አስተባበለ።

እነዚህም የሹዐይብን መልዕክተኝነት ያስተባበሉት ማስተባበላቸው ሳያንሳቸው ሹዐይብን እና የሹዐይብን ተከታዮች ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ መተናኮል ጀመሩ።

ከዚህም አልፈው፦"ሹዐይብ አንተ የምትለንን ምንም አናውቅም...በዛ ላይ አንተ ደካማ ነህ ጎሳዎችህ በጎንህ ባይኖሩ እንገድልህ ነበር ምንም አታቅተንም" እስከማለት ደረሱ።

ሹዐይብም እጅግ ስነ ምግባርን በተሞላ መልኩ፦"ህዝቦቼ ሆይ! ጎሳዎቼን የምትፈሩ ስትሆኑ ለምንስ አላህን አትፈሩም...!!!

እኔ እኮ ለእናንተ ቅኑን መንገድ ልመራችሁ እንጂ ሌላን አስቤ አይደለም።በዚህም ከናንተ ምንም ክፍያ አልፈልግም።

ህዝቦቼ ሆይ! በዚህ በምትፈፅሙት እኩይ ተግባር የምትዘወትሩ እንደሆን የአላህ ቁጣ እንዳይወርድባችሁ አስጠነቅቃችኋለሁ" አላቸው።

እነሱም፦"እኛ መብታችን ነው በብራችን የፈለግነውን ማድረግ እንችላለን።

አንተ ግን ይህ ዘውትር የምትሰግደው ሰላት ነው እንዴ በብራችን እንደፈለግን እንድንሆን እና አማልክቶቻችንንም እንድንተው የሚያዝህ?" በማለትም ያላግጡበት ጀመር።

ሹዐይብም፦" እኔ ምንም ነገር አልከለከልኳችሁም።

ግን እናንተ ነፃነት ብላችሁ የምታስቡት ሚዛንን በማጉደል፣የሰውን ሀቅ በመብላት፣አንዱ ሌላኛውን በመበደል....ነው እንዴ!!!
እኔ እንኳን ሚዛን ላይ ታማኝ እንድትሆኑ የሰውን ሀቅ እንዳትበሉ እና አንዱ ሌላኛውን እንዳይበድል ነው የመከርኳችሁ።

ህዝቦቼ ሆይ! የአንድ ሀገር ልጆች ሆናችሁ ሳለ ለምን እርስ በርስ ትሸዋወዳላችሁ!!!
እባካችሁ እርስ በርስ በመከባበር አንዳችሁ የአንዳችሁን መብት ጠብቁ።

#ይቀጥላል...... ...
⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️

ምንጮች:-
القرءان الكريم
ﺍﻟﺒﺪﺍﻳﺔ ﻭﺍﻟﻨﻬﺎﻳﺔ /ﺍﻟﺠﺰﺀ ﺍﻷﻭﻝ /

اسلام عليكم ورحمة الله وبركاته                     🌹 #ክፍል4🌹ይህን ግዜ አባታቸው በተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ ሆኖ፦"አይደለም ነፍሶቻችሁ አንዳች ነገርንለናንተ...
10/11/2020

اسلام عليكم ورحمة الله وبركاته


🌹 #ክፍል4🌹

ይህን ግዜ አባታቸው በተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ ሆኖ፦"አይደለም ነፍሶቻችሁ አንዳች ነገርን
ለናንተ ሸለሙላችሁ፤ (ሠራችሁትም) መልካምም

ትዕግሥት (ማድረግ) አለብኝ፤ እነርሱን፣
(ሦስቱንም ልጆቼን) የተሰበሰቡ ሆነው አላህ ሊያመጣልኝ ይከጀላል፤ እነሆ እርሱ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና"
አላቸው።

ያዕቁብም ከአጠጋባቸው ዘወር ብሎ፦" በዩሱፍ ላይ ዋ ሐዘኔ!" እያለ የድሮውን ዩሱፍን በማስታወስ ይንሰቀሰቅ ጀመር።

እነርሱም ፦ "በአላህ እንምላለን፤ ለጥፋት
የቀረብክ እስከምትሆን ወይም ከጠ ፊዎቹ
እስከምትሆን ድረስ፣ ዩሱፍን ከማውሳት
አትወገድም" አሉ።

ያዕቁብም፦"ጭንቀቴንና ሐዘኔን የማስማው፣ ወደ አላህ
ብቻ ነው፤ ከአላህም በኩል የማታውቁትን ነገር ዐውቃለሁ" አላቸው።

ቀን ቀንን እየተካ ቀስ በቀስ ልጆቹ ከግብፅ ይዘው የመጡት ቀለብ አለቀ።ቤተሰቡም አደጋ ላይ ወደቀ። ይህን ግዜ ያዕቁብ ልጆቹን ሰብስቦ፦

"ልጆቼ ሆይ! ሂዱ፤ ስለ ዩሱፍና ስለ ወንድሙም ፊንጭ ሰብስቡ፤ ከአላህም እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፤
እነሆ ከአላህ እዝነት ከሐዲዎች ሕዝቦች እንጂ፣
ተስፋ አይቆርጥም" አላቸው።

እነሱም አባታቸው ባላቸው መልኩ ዩሱፍን እና ወንድሞቹን ፍለጋ ወደ ግብፅ ምድር ለሶስተኛ ግዜ ብቅ አሉ። ዩሱፍ ዘንድም በመግባት፦

" አንተ የተከበርከው ሆይ!
እኛንም ቤተ ሰቦቻችንንም ጉዳት ደረሰብን፤ ርካሽ
ሸቀጥም ይዘን መጥተናል፤ ስፍርንም ለኛ
ሙላልን፤ በኛም ላይ መጽውት አላህ መጽዋቾችን
ይመነዳልና" እያሉ ሲማፀኑት...

ዩሱፍም ማንነቱን ሊነግራቸው ወሰነ'ና፦" እናንተ ባለማወቅ በዩሱፍ እና በወንድሙ የፈፀማችሁትን አውቃችኋልን?" አላቸው።

ይህን ግዜ እነሱም ይህ ሰው ዩሱፍ ይሆን ብለው በመጠትጠር፦" አንተ ግን ዩሱፍ ነህ እንዴ?" አሉት።

ዩሱፍም፦"እኔ ዩሱፍ
ነኝ ይህም ቢንያሚን ወንድሜ ነው አላህ በኛ ላይ በእርግጥ
ለገሰልን፤ እነሆ! የሚጠነቀቅና የሚታገሥ ሰው
(አላህ ይክሰዋል)፤ አላህ የበጎ አድራጊዎችን ዋጋ
አያጠፋምና" አለ።

ያን ግዜ ህፍረትን ተከናነቡ በመተናነስም፦" በአላህ እንምላለን፤ አላህ በኛ ላይ በእርግጥ
አበለጠህ፤ እኛም በእርግጥ አጥፊዎች ነበርን" አሉ።

ዩሱፍም፦"ዛሬ በናንተ ላይ ወቀሳ የለባችሁም፤ አላህ ለናንተ ይምራል፤ እርሱም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነው።

አሁን ይህንን ቀሚሴን ይዛችሁ ከንዓን ሂዱ፤ በአባቴ ፊትም
ጣሉት አይኑም ተፈውሶ የሚያይ ሆኖ ይመጣልና
ቤተሰቦቻችሁንም ሰብስባችሁ አምጡልኝ" አላቸው።

ልጆቹም እህሉን እና የዩሱፍን ቀሚስ ይዘው ወደከንዓን ጉዞ ሲጀምሩ ያዕቁብም፦"እኔ የዩሱፍ ሽታ በእርግጥ እየሸተተኝ ነው፤ ባታቀሉኝ
ኖሮ (ታምኑኝ ነበር)" አለ እዛው ከንዓን ሆኖ።

ልጆቹም ከንዓን ምድር ከገቡ በኋላ ቀሚሱን በያዕቁብ ፊትለፊት ሲጥሉት ያዕቁብም አይኑ በራለት።
ያን ግዜ፦"እኔ ለናንተ
ከአላህ በኩል የማታውቁትን ዐውቃለሁ
አላልኳችሁምን?" አላቸው።

ልጆቹም በዩሱፍ ላይ የፈፀሙትን ጥፋት ሁሉ አምነው አባታቸው አላህን ይቅርታ እንዲለምንላቸው ለመኑት።

አባታቸውም፦"ወደፊት ለናንተ ጌታዬን ምሕረትን
እለምንላችኋለሁ እነሆ! እርሱ መሐሪው አዛኙ
ነውና" አላቸው።

አሁን የዩሱፍ ቤተሰቦች ሁሉም ከንዓንን ትተው ወደ ግብፅ ጉዞ ጀምረዋል።ሁሉም ተሰብስበው ግብፅን ከደረሱ ብኋላ ዩሱፍም መንገድ ላይ ከሀገሪቷ መሳፍንት ጋር ሆኖ ትልቅ አቀባበል አደረገላቸው።

ዩሱፍም ወላጆቹን ለያን እና ያዕቁብን ዙፋን ላይ ሲያወጣቸው ያዕቁብም ልጆቹን ይዞ ለተከበረው ልጁ ለዩሱፍ ሱጁድ አደረጉለት።

ዩሱፍም፦አየህ አባቴ ያኔ ድሮ ህፃን ሳለሁ በህልሜ ያየሁትን ነገር
ጌታዬ በእርግጥ
እውነት አደረጋት፤ ከወህኒ ቤትም ባወጣኝና
ሰይጣንም በኔና በወንድሞቼ መካከል ከአበላሸ

በኋላ እናንተን ከገጠር ባመጣችሁ ጊዜ፣
በእርግጥ ለኔ መልካም ዋለልኝ፤ ጌታዬ
ለሚሻው ነገር እዝነቱ ረቂቅ ነው፤ እነሆ እርሱ
ዐዋቂው ጥበበኛው ነው" ብሎ ከተናገረ በኋላ ለዚህ ደረጃ ላበቃው ጌታም እንዲህ ሲል አወደሰ፦

" ጌታዬ ሆይ! ከንግስና በእርግጥ ሰጠኸኝ፤
ከሕልሞችም ፍች አስተማርከኝ፤ የሰማያትና
የምድር ፈጣሪ ሆይ! አንተ በቅርቢቱና
በመጨረሻይቱ ዓለም ረዳቴ ነህ፤ ሙስሊም ሆኜ
ግደለኝ፤ በመልካሞቹም አስጠጋኝ"

ከዚህ በኋላ ያዕቁብ እና መላ ቤተሰቦቹ መንፊስ በተባለች ከተማ ዩሱፍ ባዘጋጀላቸው አከባቢ ፍፁም ምቾት እና ድሎት በሞላበት ኖሮ ይኖሩ ጀመሩ።ያኔ ያዕቁብ እድሜው 130 ነበር።

በመጨረሻም ያዕቁብ በመንፊስ ከተማ ለ17 አመታት ከኖረ በኋላ በ147 አመቱ ይህችን አለም በሞት ተለየ።

ያዕቁብም ሲሞት የግብፅ ህዝብ ለ70 ቀናት ያህል ለቅሶ ከያዘ በኋላ ዩሱፍ የግብፅ ከበርቴዎችን ባለአባቶችን የሀገር ሽማግሌዎችን አስከትሎ በአባቱ ኑዛዜ መሰረት የኢብራሂም መቃብር ወደሚገኝበት ምድር አባቱ ያዕቁብን ወስዶ ቀበረው።

ዩሱፍም ከዚያ በኋላ ብዙ አመታትን ቆይቶ ከሞተ ሬሳውን የአያቶቹ መካነ መቃብር በሚገኝበት ወስደው እንዲቀብሩት ተናዝዞ በተወለደ በ120 አመቱ ነፍሱን ለጌታዋ አስረከባት።

ይሁን እንጂ ኑዛዜውን አልፈፀሙለትም ነበር።
የአላህ ሰላም እና እዝነት በያዕቁብ እና በዩሱፍ ላይ ይስፈን።

......❀━┅┉┈ #ተፈፀመ┈┉┅━❀

⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️

ምንጮች:-
القرءان الكريم
ﺍﻟﺒﺪﺍﻳﺔ ﻭﺍﻟﻨﻬﺎﻳﺔ /ﺍﻟﺠﺰﺀ ﺍﻷﻭﻝ /

                  #ክፍል3ድርቁን ተከትሎ ከተለያዩ ሀገራት በድርቅ የተመቱ እህል ሸማቾች ወደ ግብፅ ምድርም ይተሙ ጀመር።በዚያ መሀል በከንዓን ይኖሩ የነበሩ የዩሱፍ ቤተሰቦችም የድ...
08/11/2020



#ክፍል3

ድርቁን ተከትሎ ከተለያዩ ሀገራት በድርቅ የተመቱ እህል ሸማቾች ወደ ግብፅ ምድርም ይተሙ ጀመር።

በዚያ መሀል በከንዓን ይኖሩ የነበሩ የዩሱፍ ቤተሰቦችም የድርቁ ሰለባ ነበሩ'ና 10 ወንድሞቹ እህል ፍለጋ የግብፅን ምድር ረግጠው በማያውቁት የወንድማቸው መጋዘን ለእህል ተሰለፉ።

በግዜው ከመንግስት መጋዘን ሁሉም እህል ሲሸምት ስሙን እና የመጣበትን ሀገር እያስመዘገበ ነበር የሚሸምተው።

እነዚህም ወንድሞቹ ስማቸውን እስመዝግበው እህላቸውን ከመረከባቸው በፊት ዩሱፍ የከንዓን ሰዎች መጥተዋል የሚል ወሬ ሰምቶ ሊያጣራ ሲሄድ ወንድሞቹን ተመለከታቸው።

ምንም እንኳን እሱ ቢያውቃቸውም እነሱ ግን በፍፁም ሊያውቁት አልቻሉም።ግን ዝም ብለው በግምት፦" ይህ ፊት አዲስ አልሆነብኝም ይባባላሉ" እርስ በርስ....

ዩሱፍም ከተለያዩ ሀገራት ከመጡ ቁጥር ስፍር ከሌለው ሰልፈኛ መሀል ለ40 አመት የተለያያቸውን ወንድሞቹን የሰሩበትን ተንኮል ወደ ጎን አድርጎ በናፍቆት ተሸንፎ ስለማንነቱ ምንም ሳይነግራቸው ወደሚኖርበት ቤተ መንግስት ይዟቸው ሄድ።

ይህችን ሌሊትም እሱ ጋር አሳልፈው በነጋታው እንደሚሄዱ ካሳመናቸው በኋላ በጥሩ መስተንግዶ እራት አብልቷቸው ያዕቁብ ስለተባለው ነቢይ መጠየቅ ጀመረ።በህይወት እንዳለ እና ዩሱፍ በተባለው ልጁ ሀዘን ምክንያት በጣሙን እንደተጎዳ ነገሩት።

ዩሱፍ ይህን ሁሉ ሲሰማ ሆድ እየባሰው ከእንባው ጋር ትንቅንቅ ቢገጥምም ይህን ሀዘኑን ግን ለወንድሞቹ ግልፅ ሊያደርግ አልፈለገም።ያውቁኛል ብሎ ሰግቶ.....

በነጋታው ዩሱፍ አገልጋዮቹን ጠርቶ፦"ለእህሉ የከፈሉትን ገንዘብ በየከረጢታቸው ውስጥ ደብቁትና ሳያውቁ ስጧቸው" ብሎ አዘዘ።

ዩሱፍ ባዘዘውም መልኩ የከፈሉት ገንዘብ ተመልሶ በየከረጢታቸው ተጨመረላቸው።

በመጨረሻም ሲሸኛቻው፦"በሚቀጥለው ዙር ስትመጡ ከንዓን ትታችሁት የመጣችሁትን ትንሹን ወንድማችሁን ይዛችሁ ኑ። እሱን ካላመጣችሁት ግን ምንም አይነት እህል አንሰፍርላችሁም" ብሎ ሸኛቸው።

እነሱም እንደሚሞክሩ ቃል ገብተውለት ጉዞ ወደ ከንዓን ጀመሩ።

ረጅም ተጉዘው ከንዓንም ሲደርሱም በግብፅ ከተማ የገጠማቸውን ሁሉ ለአባታቸው ያዕቁብ ተረኩለት'ና በቀጣይ ዙር ግን ታናሽ ወንድማቸውን ቢንያሚንን ካላመጡ ምንም አይነት ስፍር እንደማይሰፈርላቸው ነገሩት።

አባታቸው ያዕቁብ ግን ልጆቹ ከዚህ በፊት በልጁ ዩሱፍ የፈፀሙትን በማስታወስ ዳግም ልጁን ቢንያሚንን ለነሱ አምኖ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆነም ነበር።

ይሁን እንጂ ያዕቁብ ምንም እንኳን ውድ ልጁን ቢንያሚንን ከአጠገቡ ማራቅ ቢከብደውም ከፊትለፊቱ የተደቀነው ድርቅ እና ቸነፈር ቢንያሚንን ወደ ግብፅ ለመላክ አስገድዶታል።

ከመላኩ በፊትም ያዕቁብ ልጆቹን ሰብስቦ፦"ካልተከበባችሁ በስተቀር እርሱን(ቢንያሚንን) በእርግጥ
የምታመጡልኝ ለመሆናችሁ ከአላህ የሆነን ቃል
ኪዳን መተማመኛ እስከምትሰጡኝ ድረስ ከናንተ
ጋር ፈፅሞ አልልከውም" አላቸው።
መተማመኛቸውንም ቃል ኪዳን በሰጡት ጊዜ ፦"አላህ
በምንለው ሁሉ ላይ ምስክር ነው" አላቸው።

በገቡት ቃል ኪዳን መሰረትም ቢንያሚንን ከአባታቸው እቅፍ አውጥተው ከከንዓን ምድር ነዋሪዎች ጋር ጉዞ ወደ ግብፅ ከመጀመራቸው በፊትያዕቁብ ልጆቹን ነጥሎ፦" ልጆቼ ሆይ! ባንድ በር አትግቡ፤ ግን

በተለያየ በሮች ግቡ፤ ከአላህም (ፍርድ)
በምንም አልጠቅማችሁም፤ (አልመልስላችሁም)፤
ፍርዱ የአላህ እንጅ የሌላ አይደለም፤ በርሱ ላይ
ተመካሁ፤ ተመኪዎችም ሁሉ በርሱ ብቻ ይመኩ" ብሎ መከራቸው።

በከንዓን እና በግብፅ መሀከል ያሉትን በረሃማ እና አሸዋማ መንገዶችን ካቋረጡ በኋላ የዩሱፍን ታናሽ ወንድም ይዘው ቤተ መንግስት ገቡ።

ዩሱፍም ከመጀመርያው በተሻለ መልኩ ካስተናገዳቸው በኋላ ታናሽ ወንድሙን ለግል አውጥቶ፦"እነሆ እኔ ወንድምህ ነኝ ይሠሩት
በነበሩትም ሁሉ አትቆጭ" ብሎት ነገ እሱን ግብፅ ሊያስቀረው የንጉስ ዋንጫ በሱ ከረጡት እንደሚሸጉጥበትም ጨምሮ ነግሮት ለአዳር ወንድሞቹ ጋ አቀላቀለው።

ጠዋትም ለጉዞ በተዘጋጁ ግዜ ዩሱፍ እቃዎቻቸውን አስጭኖላቸው ሸኛቸው።ብዙም ሳይርቁም ዩሱፍ እና ወታደሮቹ ከአንድ ኮረብታ ላይ ሆነው፦" እናንተ ባለ ግመሎች ሆይ! እናንተ በርግጥ ሌቦች ናችሁ" በማለት ተጣሯቸው።

እነሱም ዞረው፦" ምንድነው የጠፋችሁ?" አሉ።
ዩሱፍም፦" ፦ የንጉሡ መስፈሪያ ጠፍቶናል፤ እርሱንም ላመጣ ሰው የግመል ጭነት ሽልማት አለው፤ እኔም በርሱ ተያዥ
ነኝ" አላቸው።

እነሱም፦" በአላህ እንምላለን በምድር ላይ ለማጥፋት
እንዳልመጣን በእርግጥ ዐውቃችኋል፤ ሌቦችም
አልነበርንም" አሉት።

ዩሱፍም፦" ውሸታሞች ብትሆኑ ቅጣቱ ምንድነው?" አላቸው።

እነሱም፦"ቅጣቱ (በያዕቆብ ሕግ) ዕቃው በጓዙ ውስጥ
የተገኘበት ሰው (ራሱን አገልጋይ አድርጎ መወሰድ) ነው፤ እርሱም
ቅጣቱ ነው። እንደዚሁ በደለኞችን እንቀጣለን" ብለው መለሱለት።

(ፍተሻውን) ከወንድሙም ዕቃ በፊት
በዕቃዎቻቸው ጀመረ፤ ከዚያም (ዋንጫይቱን)
ከወንድሙ ዕቃ ውስጥ አወጣት።ሁሉም ደነገጡ ሚሉት ጠፋባቸው በዚህ አጋጣሚ እራሳቸውን ለማዳን፦"እሱ ቢሰርቅ ምንም አይደንቅም አንድ ታላቅ ወንድሙም እንዲህ ይሰርቅ ነበር" አሉ።

ዩሱፍም በውስጡ፦"እናንተ ሥራችሁ የከፋ
ነው፤ አላህም የምትሉትን ሁሉ ዐዋቂ ነው" አለ።

ከዚያም እነሱ ራሳቸው በተስማሙት መሰረት እቃውን የሰረቀውን ቢንያሚንን ዩሱፍ እና ወታደሮቹ ይዘውት ሊሄዱ ሲሉ፦"አንተ የተከበርከው ሆይ! ፦ ለርሱ(ለቢንያሚን) በእርግጥ ትልቅ
ሽማግሌ አባት አለው፤ ስለዚህ በርሱ ፋንታ

አንደኛችንን ያዝ፤( ይህን ከፈፀምክ) እኛ ከመልካም ሠሪዎች ሆነህ
እናይሃለንና" አሉት።

ዩሱፍም፦"ዕቃችንን እርሱ ዘንድ ካገኘነው ሰው ሌላን ሰው ከመያዝ በአላህ
እንጠበቃለን፤ እኛ ያን ከፈፀምን በእርግጥ በዳዮች ነን" አለ።

ዩሱፍንም ለምነው ለምነው ተስፋ ሲቆርጡ ወደ ጎን ነጠል ብለው መመካከር ጀመሩ።

በመሀልም ታላቅ ወንድማቸው፦" አባታችሁ በናንተ ላይ
ከአላህ የሆነን መታመኛ ቃል ኪዳን በእርግጥ
የያዘባችሁ መሆኑን ከዚህም በፊት በዩሱፍ ላይ
ግፍ የሠራችሁትን አታውቁምን? ስለዚህ አባቴ
ለኔ እስከሚፈቅድልኝ ወይም አላህ ለኔ
እስከሚፈርድልኝ ድረስ የግብፅን ምድር
አልለይም፤ እርሱ ከፈራጆች ሁሉ በላጭ ነው።

ወደ አባታችሁ፣ ተመለሱ፤ እንዲህ በሉትም፦ አባታችን
ሆይ! ልጅህ ሰረቀ ባወቅነውም ነገር እንጂ
አልመሰከርንም፤ ሩቁንም ነገር (ምስጢሩን)
ዐዋቂዎች አልነበርንም፤
ያችንም በውስጧ የነበርንባትን ከተማ ያችንም
በውስጧ የመጣነውን ባለ ግመል ጓድ ጠይቅ፤
እኛም በእርግጥ እውነተኞች ነን በሉ" ብሏቸው እነሱን ትቶ ወደ ከተማይቱ ገባ።

እነሱም ምንም አማራጭ አልነበራቸውምና የጫኑትን እህል ጭነው ወደ ከንዓን ተጓዙ።ልክ ከንዓን ሲደርሱ አባታቸው መንገድ ላይ እየጠበቃቸው ነበር።

ሁሉንም ሰላም ብሎ የልጁ ቢንያሚንን መምጣት በጉጉት ሲጠብቅ ቢንየሚን የውሀ ሽታ ሆነበት።ልጄስ ብሎ ሲጠይቃቸውም የሆነውን ሁሉ ነገሩት።

በ አላህ ፈቃድ #ይቀጥላል.......

Address

Jabal-alnuur
Bati
9192

Telephone

+251919469192

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abuu Diraar posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Abuu Diraar:

Shortcuts

Share

Category