Yared'man Sisay

Yared'man Sisay Success is the fruit of hard work and efforts. success cannot come in aday!

06/05/2026

እውነት ፣ፍትህ ፣ርትዕ፣ህሊና
ከእነዚህ ማንነቶች ጋር እንደመኖር ሌላ ሠላም የሚሰጥ ነገር ይኖር ይሆን?
🙏🙏🙏

20/12/2025

Success demands these 6 things..

(The Secret Formula)

1. Hard Work

Don't believe in luck, believe in hard work.

Stop trying to rush the process or searching for a shortcut.

There is none.

2. Patience

If you are losing the patience, you are losing the battle.

First nothing happens, then it happens slowly and suddenly all at once.

Most people give up at stage one.

3. Sacrifice

If you don't sacrifice for what you want, then what you want becomes the sacrifice.

Everything has its price. The question is: Are you ready to pay it for the life you desire?

4. Consistency

Consistency is what transforms average into excellence.

Without consistency, you will never achieve greater success.

5. Discipline

Motivation gets you going, but discipline keeps you growing.

There will be days when you don't “feel” like doing it.

You have to push through those days regardless of how you feel.

6. Self Confidence

Confidence is, I'll be fine if they don't like me.


ስለ ስኬት  በፍልስፍና እይታ። ኣንብቡት ታተርፉበታላችሁ 📚 ✍️ ---ስኬት ምንድነው?ስኬት ማለት ሰው የራሱን ዓላማ መድረስ ነው።ለአንዳንድ ሰዎች ገንዘብ ነው፣ለሌሎች ሰላም ነው፣ለሌሎች ደግ...
20/12/2025

ስለ ስኬት በፍልስፍና እይታ። ኣንብቡት ታተርፉበታላችሁ 📚 ✍️

---

ስኬት ምንድነው?

ስኬት ማለት ሰው የራሱን ዓላማ መድረስ ነው።
ለአንዳንድ ሰዎች ገንዘብ ነው፣
ለሌሎች ሰላም ነው፣
ለሌሎች ደግሞ ራሳቸውን መሆን ነው።
👉 ስኬት አንድ መጠን ያለው ነገር አይደለም፤ የግል ነው።

---

የስኬት መሠረቶች

1️⃣ ግልፅ ዓላማ

ያለ ዓላማ ሰው እንደ መርከብ ያለ አቅጣጫ ነው።
“ምን እፈልጋለሁ?” የሚለውን ጥያቄ ለራስህ መመለስ አስፈላጊ ነው።

---

2️⃣ ትዕግስት እና ቀጣይነት

ስኬት በአንድ ቀን አይመጣም።
ቀን ቀን ትንሽ ትንሽ መሄድ በመጨረሻ ትልቅ ለውጥ ያመጣል።

---

3️⃣ ስህተትን መቀበል

ያልተሳሳተ ሰው አልተሞከረም።
ስህተት መውደቅ አይደለም፤
ትምህርት ነው።

---

4️⃣ ራስን መቆጣጠር

ስኬታማ ሰዎች ስሜታቸውን እንጂ ስሜታቸው አያስመራቸውም።
ጊዜ፣ ሀሳብ፣ ቃል መቆጣጠር ስኬትን ያቀርባል።

---

5️⃣ እምነት በራስ

“እችላለሁ” ብለህ ማመን የጉዞው ግማሽ ነው።
ሌሎች ቢጠራጠሩህም፣ አንተ በራስህ ካመንህ በቂ ነው።

---

አጭር የህይወት ጥቅስ

> “ስኬት መድረሻ አይደለም፤ መንገድ ነው።”

-፣👉ከወደዳችሁት like & follow for more

ስለ ዝምተኛ ሰዎች እውነታዎች1. ዝም ያሉ ሰዎች በልባቸው ውስጥ ብዙ ያወራሉ፣ አንዳንዴ ብቻቸውን ያወራሉ።2. አንዴ ካንተ ጋር ከተግባቡና  ከተመቻቹህ በኋላ ግን እብዶች/ ተማኞች ይሆናሉ። ...
20/12/2025

ስለ ዝምተኛ ሰዎች እውነታዎች

1. ዝም ያሉ ሰዎች በልባቸው ውስጥ ብዙ ያወራሉ፣ አንዳንዴ ብቻቸውን ያወራሉ።

2. አንዴ ካንተ ጋር ከተግባቡና ከተመቻቹህ በኋላ ግን እብዶች/ ተማኞች ይሆናሉ።

3. በሃሳብ እና በልብ ይናገራሉ።

4. አብዛኞቹ ዓይን አፋር ናቸው, የአይን ግንኙነትን ብዙ መጠበቅ አይችሉም

5. በጣም ብዙ ንዴት አለባቸው አታናድዱአቸዉ። ነገር ግን ቁጣቸውን እንዴት እንደሚቆጣጠሩ ያውቃሉ.

6. ጠንካራ እና በጣም ብልህ ናቸው.
በራሳቸው ይተመማናሉ

7. በማህበራዊ ሚዲያ (አንዳንድ ጊዜ) በጣም ብርቱ ናቸው. አልፎ አልፎ ይፖስታሉ፣ ይፅፋሉ፣ ያደንቃሉ አስፈላጊ መስሎ ከታያቸውም ይተቻሉ

8. በጣም አሪፍ ስብዕና አላቸው እና ከነርሱ ጋር አብረው መሆንም አስደሳች ነው።

9. በጣም ያሰላስለሉ, ከመጠን በላይ ያስባሉ።

10. ታማኞች ናቸው እና በግንኙነቶች ውስጥ በጣም ይወዳደሉ. እንደዚህ ያሉ ሰዎች በግንኙነት ውስጥ ሲሆኑ በሙሉ ልባቸው ሠዉን ይወዳሉ። ጥልቅ ፍቅርም አሏቸው . እነሱ ካልወደዱህ ግን ፍቅራቸው በጣም ጠንካራ ስለሆነ ሙሉ ለሙሉ ልተውህ ይችላሉ።

11. በውስጥ ስሜታቸው ቢጎዳና ቢሆኑም እንኳን፤ሕመማቸውን ፈጽሞ አያሳዩም, ምንም እንዳልሆኑ አስመስለው, በጥልቅ ብቻቸውን መሆን ይሰማቸዋል, ስሜታቸዉን ለመግለፅ አይፈልጉም።

12. በጣም ደስ የሚል/ቆንጆ ፈገግታና ሳቅ አላቸው ።

13. አብዛኞቹ እውነትን ይወዳሉ: ለእውነትም ይኖራሉ።

20/12/2025
 #ኤረርና ሣልሳዊ  #ቴዎድሮስ‼️ #አለም ላይ ካሉ ሚስጥራዊ ቦታወች አንዱ እና ዋናው ኤረር(የረር)‼️  ‼️ #በተለያየ የዓለም ክፍል ከሚገኙ መንሳዊ ምስጢራዊ መዓከላት አንዱ ነው ቅዱሱ ኤ...
05/11/2025

#ኤረርና ሣልሳዊ #ቴዎድሮስ‼️
#አለም ላይ ካሉ ሚስጥራዊ ቦታወች አንዱ እና ዋናው ኤረር(የረር)‼️ ‼️

#በተለያየ የዓለም ክፍል ከሚገኙ መንሳዊ ምስጢራዊ መዓከላት አንዱ ነው ቅዱሱ ኤረር ተራራ ከሰሜኑ መአከል የቅዱስ ያሬድ ቀመር ካለበት ከዳሽን ተራራ የሚገናኝበት መንገድ እንዳለ የሚነገር ሲሆን ኤረር የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ቅዱስ ቦታ ነው። በምሥራቅ ኢትዮጵያም ሌላ ምስጢራዊ ቦታ እንዳለ ይነገራል።

በህወኃት ዘመን በኤረር የሚገኙ ባህታውያን ግድያና ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል፦ ይህም የሆነው አንድ ባህታዊ የሣልሳዊ ቴዎድሮስን መምጣት በመናገራቸው ነበር።

#አሜሪካ በሩዝቬልት ዘመን በኤረር ተራራ ላይ ዜጎቿን ለማስፈር ሞክራ ነበር።

በዚህ ቦታ እመቤታችን ጌታን ይዛ መጥታ እንደነበር ጌታም ከደቀመዛሙርቱ ጋር እንደነበረበት ይነገራል። አዳም ከገነት ያመጣቸው ቁሶች፣በራሪ ፈረሶች፣ የሙሴ በትር፣ የህይወት መጽሃፍ(መጽሃፈ ራዝኤል) እዚህ ይገኛሉ። ተራራው ውስጡ ከተማ ሲሆን ፒራሚዶችን እንደያዘም ይነገራል።

ከተለያዩ ሰማያትና ፕላኔቶች የሚመጡ እንግዶች እንዲሁም ከአለም ዙሪያ የተውጣጡ መንፈሳውያን ይገናኙበታል ይባላል።

ስለ መምጣቱ በራዕይ ሲኖዳና ሳቤላ፣በገድለ ፊቅጦር፣ በፍካሬ ኢየሱስ የተነገረለት ሣልሳዊ ቴዎድሮስ በየገዳማቱ ትምህርቱን አጠናቆ የሚሾምበት የሚባለው የሰማዕቱ የወታደሩ ቅዱስ ቴዎድሮስ ቤተክርስቲያን ኤረር ተራራ ላይ ይገኛል። የባዕታ ማርያም፣ የሥላሴና ሌሎች ቤተክርስቲያናትም የሚገኙ ሲሆ፤በርካታ ገዳማውያን ዋሻዎች ውስጥ በዓት ሰርተው ይኖራሉ፣ የአብርሃ አጽብሃ ቤተመንግስት ፍርስራሽም በዚህ አለ።

፦ መልከ መልካምና ረጅም በጡቶቹ መሃል የመስቀል ንቅሳት ያለው ነው ተብሏል...የሮማን ሃይማኖት ሃሰትነት በማረጋግጥ ሥራውን ይጀምራል። በዘመኑ ጠማማ እንጨት እንኳ አይኖርም ተብሏል፤ 40 ዘመን በተድላ በደስታ ይገዛል፤ ከሱ በዃላ ሰባት ነገስታት ይነግሳሉ ሠባተኛው ከጌታ በፊት የሚመጣው ሃሳዊ መሲህ ነው። ከዚያ በዃላ ጌታ ይመጣል አለምም እንዳልነበረች ሆና ታልፋለች።

ታሪካዊና መንፈሳዊ የሆነው ይህ ቦታ ከደብረዘይት ጥቂት ኪሎሜትሮች ርቆ ይገኛል። የታሪኩን ያክል ታዋቂ አለመሆኑ ግርምትን ይፈጥራል።

በስተደቡብ በኩል እንደሚገኝ የሚነገረው እጅግ ሚስጥራዊው ኤረር-ተራራ በጥቅሉ የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ቦታ እንደሆነ ድርሳናት ይናገራሉ። በእርግጥ ከዚህ ከፍ ብሎም ኤረር ተራራ የአዳም ርስት ሀገር ማዕከላዊ ቦታም እንደሆነ ይነገርለታል። #ኢትዮጵያ የአዳም ርስት ሀገር በምንለው ምድር ወስጥ የምትገኝ እንደመሆኗ በአዳም ርስት ሀገር አሉ ተብለው ከሚነሱ ሰባት ታላላቅ ስፍራዎች መካካል ሶስቱ በኢትዮጵያ ይገኛሉ። እነዚህ ስፍራዎች የጥንታዊ ኢትዮጵያ ስልጣኔ መውጫ ለሆነው መንፈሳዊ ክፍል እንደ ማዕከል የሚያገለግሉ ነበሩ። ከእነዚህ ሶስት ስፍራዎች መካካል የመጀመሪያው በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ሲገኝ ሁለተኛው ምስራቁ የሀገራችን ክፍል ላይ የሚገኝ ሆኖ ሶስተኛው በመካከለኛው ኢትዮጵያ ላይ የሚገኝ መለኮታው ሃይል ያላቸው ቦታቸወች ናቸው።

#እንግዲህ ኤረር ከእነዚህ ሶስት ስፍራዎች አንዱ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም የሁሉም ማዕከላዊ ቦታ ነው። ስለ ኤረር ተራራ በርካታ ንግርቶች (Myths) ይነገራሉ። ሆኖም ከእነዚህ ንግርቶች መካካል ትልቁን ስፍራ የሚይዘው አዳም ከገነት ሲመለስ ስድስቱን የክብር ዕቃዎች ከኤረር ማዕከላዊ ስፍራ አስቀምጦታል የሚለው ነው። ይህ በኤረር ተራራ ላይ የምናገኘው ማእከላዊ ስፍራ በተራራው መካካል ላይ የጉልላት ቅርጽ ይዞ ይታያል። ከዚህም ስፍራ አሁንም በርካታ መንፋሳዊ ሰዎች በስውር ይኖራሉ። በዚህ ስፍራ እንዚህን በርካታ የሆኑ መንፈሳዊ ሰዎችን ያሰባሰባቸው ይህ ማዕከላዊ የሆነው ስፍራ ነው። በዚህ ስፍራ ላይ በግልጽ እንዲሁም በስውር ኢትዮጵያኖች እንዲሁም ኢትዮጵያዊያን ያልሆኑ መንፋሳዊ ሰዎች ከአለም ዳርቻ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ተሰባስበው ይገኛሉ። ንግርቱ(Myth) እንደሚለው እውነት አዳም ይዟቸው የመጣው ስድስቱ የክብር ዕቃዎች እዚህ ይሆን የሚገኙት? ይህንን ጥያቄ ይህ ትውልድ ሊጠይቀው እና እውነቱን አነፍንፎ ሊያገኝ የሚጋባ ነው። የዚህ ሚስጥራዊ ኤረር ተራሮችን ለማወቅ የቅድስት ቤተክርስቲያናችንን ህንጻ አሰራር ማወቅ የግድ ይላል፤ በዚህም መሰረት የህንጻ ቤተክርስቲያናችንን ተምሳሌታዊ አወቃቀር ይዘን ኤረር ተራሮች ላይ ስንሄድ ተራራው ሁለት ክፍሎችን ይዞ እናገኘዋለን፤ #የመጀመሪያው ክፍል ከተራራው በላይ የሚገኘውና በአይን ሊታይ የሚችለው በሥጋ ባህሪ የሚመሰለው ክፍል ነው።

#ሁለተኛው የተራራው ክፍል የውስጠኛው ስውር ከተማ ሲሆን ይሄውም በነፍስ ባህሪ የሚወከልው ነው፤ ወደዚህ ወደ ሁለተኛው ወይንም ወደ ውስጠኛው የተራራው ክፍል ለመግባትም ልክ እንደ ህንጻ ቤተክርስቲያናችን በአጠቃላይ ሦስት በሮችን ይዟል፤ የመጀመሪያው በር በምስራቁ አቅጣጫ የሚገኘውና ከተራራው በላይም የቅዱስ #ቶዎድሮስ ቤተክርስቲያን የሚገኝበት በር ነው፤ ሁለተኛው በሰሜናዊው የተራራው አቅጣጫ የሚገኘውና ከበላዩም በደን የተሸፈነው እንዲሁም የባህታ ለማርያም ቤተክርስቲያን የሚገኝበት ሲሆን ሦስተኛውና የመጨረሻው በር በደቡባዊው አቅጣጫ በኮራ ማርያም ቤተክርስቲያን በኩል ይገኛል። ወደዚህ #ስውር ከተማ በምስራቁ በር ከብሔረ ህያዋን ብሎም በምድር የበቁ ታላላቅ አባቶቻችን የሚጠቀሙበት በር ሲሆን የሰሜናዊውን በር ወንድ ነገስታት እስከ አሥራ ሦስተኛው ክ/ዘመን ድረስ ሲጠቀሙበት ኖረዋል፤ ይህንን በር ለዘመናት ሲናፈቅ የኖረውና የኢትዮጵያን ትንሳኤ ያመጣል ተብሎ የሚጠበቀውና የገዢነት ክብሩን ይዞ የተወለደው ካህኑ ዳግም ይጠቀምበታል ተብሎም ይነገራል፤ ሦስተኛውን በር እና በደቡባዊው አቅጣጫ በኩል የሚገኘውን በር ሴት ነገስታት ሲጠቀሙበት እንደኖሩ። ይሄንን አቀማመጥ ወደ ህንጻ ቤተክርስቲያናችን ከ300 በላይ የሚሆኑ ዋሻወች እንዳሉና ከመላው አለም የመጡ ቅዱሳን መነኮሳት እግዚአብሄርን እያመሰገኑ እንደሚኖሩበት ይታመናል፡፡ #በአለም ካሉት 7ቱ ሚስጥራዊ ቦታወች 3ቱ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚገኙ ከሶስቱ አንዱም ኤረር ተራራ እንደሆን አየን፡፡ መላእክት ከእግዚአብሄር ዘንድ ሲላኩም ሆነ ለተልእኮ ሲወጡ እና ሲወርዱ ከሚያርፉባቸው 7ት ሚስጥራዊ እና ስውር ስፍራዎች አንዱ ነው።

‼️
√ ይህ ስፍራ በበርካታ የበቁ አባቶች የተከበበ ነው። እነኚህ አባቶች ከመንፈሳዊ ብቃታቸው የተነሳ የተሰወሩ ቅዱሳን ሲሆኑ ብዙሃኑ በአለማዊ የትምህርት ደረጃቸው ዶክተሮች፣ ኢንጀነሮች ፣ ፓይለቶች ወዘተ እንደሆኑ ይመሰከራል።
√ ይህ ስፍራ በጥንታዊ ዋሻዎች የተከበበ ነው። እነኚህ ዋሻዎች በተሰወሩ ጥንታዊ ቅርሶችና መፃህፍት የተመላ ሲሆን በደጉ ንጉስ ዘመን እንደሚገለጡ ይታመናል።
√ ይህ ስፍራ የኢትዮጵያ ትንሳኤን እውን እንደሚያደርግ የሚታመንበት የሀያሉ ንጉስ ቶዎድሮስ ቤተመንግስት የሚሰየምበት እንደሆነ ይታመናል።
√ ይህ ስፍራ ላይ በንጉስ ሳህለ ስላሴ ዘመን አንድ ቤተክርስትያን ተቆርቁሯል። በዚህ ቦታ ላይ የተቆረቆረው ቤተክርስትያን የሮማዊው ቅዱስ ሰማእት ቴዎድሮስ ነው። ቤተክርስትያኑ በቅዱስ ቴዎድሮስ ስም መሰየሙ ንጉሱ ቶዎድሮስ የሚነግስበት ስፍራ ስለሆነ እንደሆነ አለቃ አያሌው ታምሩ ባዘጋጁት የቅዱስ ቴዎድሮስ ገድል ላይ ተፅፏል።
ይህ ስፍራ ከደብረ ዘይት 13 ኪሜ ርቀት ላይ የሚገኘው የኤረር ቅዱስ ቴዎድሮስ ገዳም ነው።
በዚህ ስፍር ክርስቶስ በምድር ሳለ የተገለገለባቸው እቃዎች እቃዎች ይገኛሉ። እጅግ ጥብቅ ቦታም ነው!

ለአሁኑ ግን አዳም ከገነት ያመጣው የክብር ዕቃ ስለ ሶስተኛው የክብር እቃ ስለሚባለውና በዚህ ስፍራ ስለሚገኘው ልንገራችሁ፡፡ ይህ ሰረገላ ለዘመናት ለኢትዮጵያውያን የሃይላቸው ምንጭ ነበር፡፡ በተጨማሪም አሁን ድረስ አንዳንድ ምስጢራዊ መረጃዎች የሚያመለክቱት ሮም ገናና በነበረችበት ወቅት የኃይል ምንጭ ይህ ገረረ ሰረገላ ነበር ኃላ ግን ከባቢሎዋውያን ጋር ውጊያ ላይ በነበሩበት ወቅት ይህ ገረረ-ሰረገላ ሙት ባህር ውስጥ ይገባባቸዋል በዚህ የተነሳም ተሸንፈው ሮም ለመፈራረስ በቅታለች፡፡ ታዲያ ከዚህ ከሙት ባህር ውስጥ እስራኤል አውጥታ በድብቅ እንዳስቀመጠችው መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ይህ ግን ፈጽሞ ከሀሰት የራቀ ታሪክ ነው ምክንያም የምድራችንን ታሪክ የስማዝያ ወገኖች እና አይሁዶች ድጋሜ ሲጽፉት ሁሉንም የራሳቸው ለማድረግ ካላቸው ምኞት የጻፉት የፈጠራ ታሪክ ነው፡፡ ገረረ ሰረገላ አንድ ብቻ ሲሆን ይኀውም አዳም ከገነት አምጥቶ ርስት በሆነችው ቦታ ያስቀመጠው ነው፡፡ ይህ ገረረ
ሰረገላ ሃይል ብለን ከጠቀስነው ምስጢረ ጥበብ ጋር ተዋህዶ የሚሰራ ነው፡፡ ይህ ሃይል ያልነው ምስጢረ ጥበብ ደግሞ በዘመናችን ሚሊተሪ የምንለው እንደሆነ ልብ ይበሉ ሀይል የተሰኘውን ምስጢረ ጥበብ እና ገረረ ሰረገላ የተባለውን አዳማዊ የክብር እቃ ጠባቂ በምድር ቶዎድሮስ ሲሆን በሰማይ አባታችን የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡
#በአባታችን በቅዱስ ሚካኤል እና ቶዎድሮስ የሚመራው መንፈሳዊ ሃይል ነው ኢትዮጵያን ትንሳኤ ሚያጎናጽፈን!!!

 !እያንዳንዱ ሰው ማድረግ ያለበት ዋና ነገር የስነ-ልቦናዊ እና ስሜታዊ ማዕቀፉን የህይወቱ መሠረታዊ እውነታ በሆነው ማለትም ሟች በመሆኑ ላይ ማዋቀር ነው።ብዙ ሰዎች ሟች መሆናቸውን ለመረዳት...
15/07/2025

!

እያንዳንዱ ሰው ማድረግ ያለበት ዋና ነገር የስነ-ልቦናዊ እና ስሜታዊ ማዕቀፉን የህይወቱ መሠረታዊ እውነታ በሆነው ማለትም ሟች በመሆኑ ላይ ማዋቀር ነው።

ብዙ ሰዎች ሟች መሆናቸውን ለመረዳት ዕድሜ ልክ ይወስድባቸዋል። ያንን ለማስታወስ ምናልባትም የልብ ድካም ወይም የአንድ ችግር ገጽታ እንዲኖር ያስፈልጋቸዋል።

ሞኝ አትሁን!

ህይወት ለአፍታ እንኳን ቆማ አትጠብቅህም፤ ስለዚህ እያንዳንዱን የህይወትህን ደቂቃ ማክበር እና በዚያም መደሰት አለብህ። የማትሞት ብትሆን ኖሮ በእያንዳንዱ ጭንቀት፣ ውጥረት፣ እብደት እና ሰቆቃ ለመቶ አመት ልትደሰት ትችል ነበር።

ግን እንደዛ አይደለም።

ምክንያቱም አንተ ሟች ነህ እና ጊዜህም እየሄደ ነው።

ስለዚህ በዚህ ህይወት ውስጥ ለብስጭት፥ ለድብርት፥ ለጭንቀት፥ ለቁጣ ወይም ለማንኛውም ደስ ለማይል ነገር ጊዜ የለም።

ይልቅ ወዳጄ… መሞትህ ላይቀር ዝም ብለህ በጭንቀት አሁንህን አትግደል፡፡

ከመሞትህ በፊት ፈታ በል!

#2ተኛው ዕትም

በአንድ ወቅት አንድ ገበሬ አህያው ጉድጉድ ውስጥ ትገባበታለች፡፡ ጉድጓዱ ሩቅ ከመሆኑ የተነሳ አህያዋ ለመውጣት በእጅጉ ተቸገረች፡፡ በጣም መጮህ ጀመረች፡፡ ባለቤቱም እሷን ለማውጣት ብርቱ ሙከ...
12/06/2025

በአንድ ወቅት አንድ ገበሬ አህያው ጉድጉድ ውስጥ ትገባበታለች፡፡ ጉድጓዱ ሩቅ ከመሆኑ የተነሳ አህያዋ ለመውጣት በእጅጉ ተቸገረች፡፡ በጣም መጮህ ጀመረች፡፡

ባለቤቱም እሷን ለማውጣት ብርቱ ሙከራ አደረገ አልተሳካለትም ፤ አህያዋ አርጅታለችና እዚያው ጉድጓድ ውስጥ ሊቀብራት አሰበ።

ጎረቤቶቹንም ጠራና ጉድጓዱን በአፈር መሙላት ጀመረ፡፡ አህያዋ ይህንን ስተመለከት እየቀበራት መሆኑን ተረዳችና እጅጉን አዘነች፡፡

ይሁን እንጂ አፈር በተደፋባት ቁጥር አህያዋ አንድ ነገር ታደርግ ነበር። አፈሩን እያራገፈች ከአፈሩ ውስጥ ብቅ ትል ነበር። በተደጋጋሚ በተደፋው አፈር ላይ መቆም ትጀምራለች።

በሂደት በአፈሩ ላይ በቆመች ቁጥር ከነበረችበት ጉድጓድ ከፍ እያለች በመጨረሻም ከጉድጓዱ ውስጥ ሙሉ በሙሉ መውጣት ቻለች፡፡

በሚገርም ሁኔታ አህያዋን ሊቀብሯት የሞከሩት ስዎች ሁሉ በአህያዋ አወጣጥ በእጅጉ ተደነቁ፡፡
የአህያዋ ታሪክ ሁላችንንም ይመለከተናል። የሚጫንብን አፈር በየጊዜው የሚያጋጥሙንና ዝም ብንላቸው በመጨረሻ ሊቀብሩን የሚችሉ ችግሮች ወይም መሠናክሎች ናቸው፡፡
አፈሩን የሚጭኑት ሰዎች በዙሪያችን ያሉ ሰዎች፣ ነገሮች፣ በህይወታችን ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥሩብን አዳዲስ ለውጦች እንዲሁም የራሳችን አፍራሽ ስሜቶች ሊሆኑ ይችላሉ።
ጉድጓዱ ደግሞ አሁን ያለንበት ግራ የተጋባንበት! ተስፋ ቢስ የሆንበት፡ መላ ያጣንበት ህይወት ወይም ገጠመኝ ሊሆን ይችላል፡፡
በእርግጥም እኛ ሰዎች በጤናችን! በኢኮኖሚ ህይወታችን፤ በትዳርና ፍቅር ህይወታችን በተለያየ አጋጣሚ ልክ እንደ አህያዋ ጉድጓድ ውስጥ የመግባት ዕድላችን ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ ጠንካሮች እንደ ጠንካራዋ አህያ ከገቡበት ጉድጓድ ውስጥ መውጣት ሲችሉ አንዳንዶቹ በዚያው ተቀብረው ቀርተዋል፡፡
በህይወታችን ውስጥ ያለው አማራጭ! ወደ ላይ መውጣት አልያም ደግሞ ወደ ታች ወርዶ ከጥልቅ ጉዳጓድ ውስጥ ተቀብሮ መቅረት ብቻ ነው!
ልክ እንደ አህያዋ (የሚጫንባትን አፈር እየረገጠች ወደ ላይ ከፍ እንዳለችው) ሁሉ እኛም በየጊዜው የሚያጋጥሙንን ችግሮች እንደ ድጋፍ እየተጠቀምን በጥንካሬ ወደ ላይ መነሳት ያስፈልገናል።
ከጥልቁ ጉድጓድ ውስጥ ለመውጣት የምንችለው ለመውጣት የምናደርገውን ጥረት ባለማቆም ብቻ ነው!
ምንጊዜም በጠንካራ ውስጣዊ ቁርጠኝነትና እምነት ችግሮችን እንደ መወጣጫ ደረጃ በመጠቀም ከታች ወደ ላይ እንጓዝ!!
እያንዳንዱን ችግር እንደ መሰላል ከተጠቀምክበት ከስኬት ጫፍ ትደርሳለህ!💪💪💪

"According to Psychologists, there are four types of Intelligence: 1) Intelligence Quotient (IQ)2) Emotional Quotient (E...
12/06/2025

"According to Psychologists, there are four types of Intelligence:

1) Intelligence Quotient (IQ)
2) Emotional Quotient (EQ)
3) Social Quotient (SQ)
4) Adversity Quotient (AQ)

1. Intelligence Quotient (IQ): this is the measure of your level of comprehension. You need IQ to solve maths, memorize things, and recall lessons.

2. Emotional Quotient (EQ): this is the measure of your ability to maintain peace with others, keep to time, be responsible, be honest, respect boundaries, be humble, genuine and considerate.

3. Social Quotient (SQ): this is the measure of your ability to build a network of friends and maintain it over a long period of time.

People that have higher EQ and SQ tend to go further in life than those with a high IQ but low EQ and SQ. Most schools capitalize on improving IQ levels while EQ and SQ are played down.

A man of high IQ can end up being employed by a man of high EQ and SQ even though he has an average IQ.

Your EQ represents your Character, while your SQ represents your Charisma. Give in to habits that will improve these three Qs, especially your EQ and SQ.

Now there is a 4th one, a new paradigm:

4. The Adversity Quotient (AQ): The measure of your ability to go through a rough patch in life, and come out of it without losing your mind.

When faced with troubles, AQ determines who will give up, who will abandon their family, and who will consider su***de.

Parents please expose your children to other areas of life than just Academics. They should adore manual labour (never use work as a form of punishment), Sports and Arts.

Develop their IQ, as well as their EQ, SQ and AQ. They should become multifaceted human beings able to do things independently of their parents.

Finally, do not prepare the road for your children. Prepare your children for the road."

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
እንደ ሳይኮሎጂስቶች ገለጻ አራት የማሰብ ችሎታ ዓይነቶች አሉ፡-

1) የማሰብ ችሎታ (IQ)
2) ስሜታዊ ጥቅስ (EQ)
3) ማህበራዊ ዋጋ (SQ)
4) የመከራ ብዛት (AQ)........
Via google.

22/05/2025

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Mamiti Ma, Abdulkariim Umar, Seenaa Asfawuu, Khali Bantu, Asrat Negusu Demise

ታላቁ ፈላስፋ ሶቅራጠስ በአንድ ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር፦“አህያ ቢመታኝ ልከሰው ነው? ወይስ ልሰድበው? አልያም ደግሞ ልረገጠው?”ሁሌም ቢሆን እያንዳንዱን ክርክር ለማሸነፍ ከመነሳታችን በፊት...
22/05/2025

ታላቁ ፈላስፋ ሶቅራጠስ በአንድ ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር፦

“አህያ ቢመታኝ ልከሰው ነው? ወይስ ልሰድበው? አልያም ደግሞ ልረገጠው?”

ሁሌም ቢሆን እያንዳንዱን ክርክር ለማሸነፍ ከመነሳታችን በፊት አዕምሮና ጉልበታችንን ለምን እንደምናባክን እራሳችንን መጠየቅ አለብን።ጨዋታውን ለይቶ ያወቀ አሸናፊነት ራሷ ትመርጠዋለች። ከማይመጥነን ጦርነት መታቀብ የድል ጀንበር ጭላንጭል ነው። ድንቁርና ትጮኻለች ጥበብም ዝም እንዳለች ነው።ማንም ሰው ከስድብና ከጩኸት በቀር የሚያቀርበው ነገር ከሌለው በጣም ሃያሉ ምላሽ ዝምታ ነው።

ግጭት እና ፀብን ወደ ሚፈልግ ሰው ደረጃ አታዘንብሉ።እውነተኛ ብልህነት እራሱን እሳት አይለኩስም፤ በቀላሉ ያበራል…

Address

Bahir Dar

Telephone

+251918659595

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yared'man Sisay posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Yared'man Sisay:

Shortcuts

Share