ፍቅር by eben

ፍቅር by eben ስለ ፍቅር ብቻ

19/10/2022
25/08/2022
12/05/2022

!

1. ደካማ ጎኖችዎን ይለዩ፦

ደካማ ጎኖቻችሁን ችላ ማለት እንዲጠፉ አያደርጋቸውም። ስለዚህ ጣፋጮችን መብላት የክብደት መጨመሮ ምክንያት ነው? ማህበራዊ ሚዲያ ማዘውተር ምርታማነትዎን ቀንሶታል? ድክመቶችዎን ይወቁ። ድክመቶችዎን ማወቅ አዎንታዊ ለውጥን ለመፍጠር የመጀመሪያው እርምጃ ነው።

2. ግልፅ የሆነ ስልት ይቀምሩ፦

ከፍ ያለ ራስን የመግዛት አቅም በድንገት አይመጣም። ይልቁንም የአእምሮ ጡንቻን ለመገንባት የሚያግዝዎት ስልት ማበጀት ያስፈልግዎታል። ብዙ ጊዜ ወደ ጂም እንደመሄድ ያሉ ጥሩ ልምዶችን መጨመር አልያም ብዙ ሶሻል ሚዲያ መጠቀምን የመሰሉ መጥፎ ልምዶችን ማስወገድ ከፈለጉ እነዚህን ዓላማዎችዎን ወደ ተግባር ለመቀየር ዕቅድ ያስፈልግዎታል። በየቀኑ መውሰድ የሚያስፈልጎትን እርምጃዎችን በግልጽ ይዘርዝሩ።

3. የሚፈታተኖትን ነገሮች ያስወግዱ፦

ቤትዎ ጣፋጮች ምግብ ከተከማቹ ክብደትን ለመቀነስ ራስን የመግዛትን አቅም ያዳክማል። ይልቁን እያንዳንዱን ኩኪስ፣ ቺፕስ እና ሌሎች ጣፋቾችን ላለመብላት በመሞከር ጊዜዎን ያባክናሉ። ድክመትዎ በየሁለት ደቂቃዎች ማህበራዊ ሚዲያዎችን መፈተሽን የሚያካትት ከሆነ ፌስቡክን የሚያግድ መተግበሪያ ይፈልጉ። ፈተናዎችን መገደብ በጊዜ ሂደት የበለጠ ራስን የመግዛትን አቅሞን እንዲገነቡ ይረዳዎታል።

4. ምቾት ማጣትን ይለማመዱ፦

ምቾት ማጣትን ለማስወገድ መሞከር ተፈጥሯዊ ነው። ነገር ግን የአጭር ጊዜ ምቾትን መሻት ብዙውን ጊዜ የረጅም ጊዜ ችግሮችን ያስከትላል። እናም በተሸነፉ ቁጥር ጭንቀትን መቋቋም እንደማይችሉ ለራስዎ ያሳምናሉ። ምቾት ማጣትን ይለማመዱ፤ ያ ማለት እርስዎ ከሚያስቡት በላይ ለተጨማሪ ደቂቃ መሮጥ ወይም ጣፋጭ ምግቦችን የመብላት ፍላጎትን መቃወም ባጠቃላይ ምቾት ማጣት ጠላት አለመሆኑን እንዲያምን አዕምሮዎን ያሰልጥኑ።

5. ግቦቾን ያስታውሱ፦

ፈተናን ሲጋፈጡ ሊያገኟቸው የሚችሏቸውን ነገሮች ለራስዎ ያስታውሱ። ከግቦችዎ ጋር ሲጣበቁ የሚያገኟቸውን ነገሮች ሁሉ ዝርዝር ይፃፉ፤ ተስፋ ለመቁረጥ በሚፈተኑበት ጊዜ ዝርዝሩን ያንብቡ።

6. ለውድቀት ያለዎትን አመለካከት ይቀየሩ፦

መሻሻል ብዙውን ጊዜ በቀጥታ መስመር ላይ አይመጣም። ስህተት ሰርተዋል ማለት ከዚህ በኋላ አይሳካሎትም ማለት አይደለም። ስህተት የመሻሻል ሂደት አካል ነው። ከእነዚህ ስህተቶች የሚመለሱበት መንገድ ነው በጣም አስፈላጊው ነገር፤ ከተሳሳቱት እርምጃዎችዎ በመማር በሚቀጥለው ጊዜ የተሻለ ለማድረግ ቁርጠኛ ይሁኑ።

Source:- Keleme consulting plc

25/08/2020

አዳድስ ነገር ላለማቅረባችን ይቅርታ እየጠየቅን: ከተለያዩ መጽሐፍት ለናንተ ይጠቅማል የምንላቹን ነገር አንካፍላቿለን።

Address

Chire
Awassa

Telephone

+251912435556

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ፍቅር by eben posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share