17/02/2023
Sometimes you think people are stopping you from getting to the top and forget it's your mouth.
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Derry Desalegn, Awassa.
17/02/2023
Sometimes you think people are stopping you from getting to the top and forget it's your mouth.
11/08/2022
If you feel comfortable by being alone,congratulations,You understood life.
16/02/2022
ትንሽ ወግ ላጫውታችሁ
👉ሰውዬው ስማቸው አባ እንሂድ በመባል ይታወቃሉ።በሚኖሩበት መንደር ሰዉን በመርዳት ቀዳሚውን ድርሻ ይወስዳሉ።ሰዎች ወደወንዝ ስወርዱ ካዩ ''ወዴት ትሔዳላችሁ?''።እነርሱም ''ውሀ ልንቀዳ።? ይላሉ።ሰውዬውም ''እንግዲያስ እንሂዳ'' ይሉና አብሯቸው ውሀውን ይቀዳሉ።በሌላ ጊዜም ''ወዴት ትሔዳላችሁ?'' ''እንጨት ለቀማ''።ከዚያም ''እንሂዳ'' ብለው ቀኑን ሙሉ ስለቅሙ ውለው ይገባሉ።በዚህ ሁኔታ እየኖሩ ሳለ አንድ ቀን ቅዱስ ሚካኤል በሰው ተመስሎ ከመንገድ ያገኙታል።''ወዴት ትሔዳለህ?'' ''ወደ ገነት'' ሰውዬውም ''እንሂዳ''።የሰውየው ታሪክም እዚህ ላይ ያበቃል።ሰውየው አልተመለሰም።
10/10/2021
ወሬ ቀንሰህ ዝምታ ባበዛህ ቁጥር ዋጋህ እየጨመረ ይመጣል!!!
25/09/2021
የአንድ ሰው እውነተኛ ማንነት ያለው በሚነግርህ ነገር ላይ ሳይሆን በማይነግርህ ላይ ነው።ስለዚህ ፀባዩን በደንብ ለማወቅ ከፈለክ የሚነግርህን ነገር ሳይሆን የማይነግርህን አድምጥ።
13/07/2021
👉ብልህነት👈
አንድ ንጉሥ ነበር። በህልሙ ጥርሶቹ ሁሉ ሲረግፉ ያያል። በዚህ ግዜ ህልም የሚፈታለት ሰው ያስጠራና ህልሙን ይነግራል። ህልም ፈቺውም በመገረም..
“ይህን ህልም ያዩት እርሶ ኖት ንጉስነቶ? እርግጠኛ ነዎት” ሲል ይጠይቃሉ።
ንጉሡም “አዎን እኔ ነኝ”.. ይለዋል፡፡
የህልሙ ፈች “ቤተሰቦችህ በሙሉ በፊት ለፊትዎ ዐይንኖት እያየ ይሞታሉ” ብሎ ነገረው። በዚህ ግዜ ንጉሡ ተቆጣ.. “ይሄን ቀባጣሪና ሙዋርተኛ እስር ቤት ወርውሩልኝ” ሲል አዘዘ። ትዕዛዙም ተግባራዊ ሆነ።
ሌላ ህልም ፈቺ ተጠራ። ህልሙንም ነገረው። የዚህም ሰውዬ ፍቺ የመጀመሪያው አይነት በመሆኑ ንጉሡ ተበሳጨ። እሱንም ወደ እስር ላከው።
ሶስተኛ ህልም ፈቺ ተጠራ እንደተለመደው ህልሙን ተናገረ። ህልም ፈችውም ረጋ ብሎ
“ንጉሥ ሆይ … ይህን ህልም ያዩት እርሶ ኖት ክቡርነቶ”.. በማለት ጠየቀ ህልም ፈችው።
“አዎን ምነው?”.. ሲል አተኩሮ ተመለከተው።
“እንኳን ደስ አለዎት ንጉስነቶ!”.. በማለት ተናገረ ህልም ፈችው።
“ለምኑ?”.. ሲል ንጉሡጠየቀ።
“የዚህ ህልም ፍቺ ይህ ነው ፡፡ከቤተሰቦችህ ሁሉ ረዥም እድሜ ምትኖሩት እርሶ በመሆንዎ ነው።
እናም እንኳን ደስ ያልዎት በድጋሚ” በማለት በደስታ ተናገረ። በዚህ ግዜ ንጉሱ ተደሰተ.. ለህልም ፈቺው ስጦታ በመስጠትም በክብር አሰናበተው።
የንጉሱ እድሜ ከቤተስቡ በለጠ ማለት ቤተሰቦቹ ንጉሱን ቀድመውት ይሞታሉ ማለት አይደለምን? ሆኖም ግን ሃሳቡ አንድ ሆኖ ሳለ የቀረበብት መንገድ የተለየ በመሆኑ ህልም ፈችው ከእስር እና እንግልት ዳነ፡፡
በሕልም ታምናላችሁ
እናንብብ እንወያይ ነጻ እንውጣ
ንበብ ለንባብ
22/06/2021
👉👉የራስህን ኑሮ ኑር👈👈
አንዳንዴ ቁጭ ብዬ ሳስብ የአንዳንዱ ህይወት ይገርመኛል።የራሱን ህይወት መኖር ይተውና የሌላውን ህይወት ሲኖር ይታያል።የራሱን ህይወት በቅጡ ሳይኖር የሌላውን ህይወት ይኖራል።ይህ ማለት ደግሞ ሁለት ሰዎች አንድ ህይወት ይኖራሉ።በአንድ አውሮፕላን ውስጥ አንድ ሽማግሌና አንድ ህፃን ጎን ለጎን ተቀምጠው ይሄዳሉ።ታዲያ በዚህ ጊዜ ልጁ ከኪሱ ቸኮሌት አውጥቶ ሲበላ ሽማግሌው ያየውና እንዲህ ይመክረዋል
''ቸኮሌት ለምን ትባላለህ ጥርስህን ያበላሻል ስለዚህ አትብላ'' ይለዋል።ልጁም መልሶ ''አያቴ 120 ዓመት ነው የኖረው''።ሽማግሌውም ቀበል አድርጎ ''ቸኮሌት ባለመብላቱ ነው አይደል?'' ሲል ልጁም ''አይደለም በማያገባው ስለማይገባ ነው።''ብሎ መልሶለታል። ዛሬም አንዳንድ ሰው በማያገባው እየገባ የሌላውን ህይወት ሲኖር ቆይቶ የራሱ ህይወት ኦና ሆና ይቺን ምድር ይሰናበታታል።እኔ እስከማውቀው ድረስ የራሱንም የሌላውንም ህይወት የምኖረው ብቸኛው 👉ያፈቀረ ሰው👈 ብቻ ነው።እሱም ወዶ ሳይሆን ተገዶ ነው።................ስለዚህ ወደራስህ ተመለስ።
20/06/2021
ህይወት ሹክ ከምትልህ ነገሮች ጥቂቶቹ
1:መታመንን ለመገንባት አመታት ልፈጁ ይችላሉ፤ነገር ግን ለማውደም ጥቂት ሰከንዶች ብቻ እንደሚፈጁ ትገነዘባለህ
2:አንዳንዴ አንድን ሰው ስላፈቀራችሁ ብቻ ያኛውም እንዲያፈቅራችሁ ማድረግ አትችሉም።ማድረግ የምትችሉት ነገር ቢኖር ጥሩ አፍቃሪ መሆን ብቻ ነው።
3፡አንዳንዴ ደግሞ ተንሸራተህ ወድቀህ ከመቸው ረጋገጡኝ ያልካቸው ሰዎች እጅህን ይዘውህ ብድግ አድርገው ሲያነሱህ ማንኛውንም ሰው በውጪው መፍረድ እንድታቆም እያሳሰቡህ እንደሆነ ትረዳለህ።
4፡ምንም እንኳ ቤተሰብ መከታ ቢሆኑም ግን ለሁልጊዜ እንዳልሆኑ፣ጓደኞችህ ምንም ያህል ጥሩ ቢሆኑም አንዳንዴም እንደሚያስቀይሙህ ትረዳለህ።
.
For those who consider education as the main bridge for success.
18/02/2021
''ዝም ስትል የማታውቅ የሚመስላቸው ብዙ ናቸው...ምክንያቱም እነሱ በማውራት ያምናሉና ነገር ግን ያወሩትን አይኖሩም።...አንተ ግን በማውራት አትመን፤ዝም ብለህ ልታወራ የፈለከውን ኑረው ከዛ ባንተ ዝምታ ውስጥ የኖርከው ህይወት ጥሶ ይወጣና አንተ ዝም እንዳልክ ሳታወራ ሰዎች ያወሩልሀል።''
ሳነብ ካገኘሁት(የአና ማስታወሻ)
30/11/2020
👉አይ ሰው ሲገርም👈
1:ስለነገ በመጨነቅ ዛሬን ለመኖር አለመቻሉና ከዛሬም ከነገም ሳይሆን መንከራተቱ ያሳዝነኛልም ያስገርመኛልም
2:ልጆች ሳሉ መሰልቸታቸውና ትልቅ ለመሆን መሮጣቸው......ካደጉ በኃላም ልጅ ሆኖ ለመታየት መሮጣቸው
3:ገንዘብ ለማካበት ጤንነታቸውን ማጣታቸውን.....ጤናቸውን ለመመለስ እንደገና ያንኑ ገንዘብ ማፍሰሳቸው
4:ልክ እንደማይሞት ሰው መኖራቸውና ልክ እንዳልኖረ ሰው ተፅዕኖ ቢስ ሆነው መሞታቸው
ያስገርሙኛል።
29/11/2020
አስተውል!!!!!
ሁሉም ሰው ጂኒየስ(Genius)ነው፤ግን አሳ ከዛፍ ዛፍ በመዝለል ችሎታው ከተመዘነ እድሜ ልኩን የማይረባ እንደሆነ ያምናል ALBERT EINSTEIN እንዳለው።ድክመታችንን ከሌሎች ጥንካሬ ካወዳደርነውማ ሁሌም የበታችነት ይሰማናል፤ከሌሎች ዝቅ ያልን ይመስለናል።እኛን የሚዳኘን የራሳችን መስፈርት ነው።የሌሎች መንገድ የሌሎች ነው።🙏🙏🤞🤞🤞