18/10/2023
Dr seifu T
Anesthesiology ,critical care,pain medicine specialist
18/10/2023
ገና ከመወለዱ ሱስ አስቸገረው!
ሲወለድ ክብደቱም ሆነ ጤንነቱ ኖርማል ነው። ድንቡሽቡሽ ያለ ነው። በሁለተኛው ቀን "እሪ" ብሎ ማልቀስ ጀመረ። እናቱ ብታባብለው ብታባብለው ለቅሶው አልቆም አለ። በተደጋጋሚ አስመለሰው። ላብበላብ ሆነ። ሰውነቱ መንቀጥቀጥ ጀመረ። ሀኪሞቹ ያሉትን ምርመራዎች ሁሉ ቢሰሩለትም ምንም ሊገኝ አልቻለም። እናቱንም መመርመር ጀመሩ። ከዛ እሷ ሄሮይን የተባለው ዕፅ ሱሰኛ እንደሆነች ደረሱበት።
ለካ ህፃኑ ማህፀን ውስጥ እያለ እናቱ ሄሮይን ስትጠቀም እሱም በደሟ አማካኝነት ይደርሰው ነበር። ከተወለደ በኋላ ግን ወተት ውስጥ መጠኑ በጣም ዝቅተኛ ስለሆነ የለመደውን አላገኘም። ገና ከመወለዱ ሱስ አስቸገረው።
እናቶች የሚወስዷቸው ሱስ አስያዥ ነገሮች (ከቡና ጀምሮ) ከእነሱ አልፎ ልጆች ላይም ተፅእኖ እንደሚያደርስ አስታውሶ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። ሱስ የሚታከም የአእምሮ ህመም ነው የምንለው በምክኒያት ነው።
ያለ አእምሮ ጤና ፤ ጤና የለም!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው
Mental wellness የአእምሮ ጤና
08/07/2022
ማንሳት የማልፈልገው ርዕስ ነበር ። ነገር ግን ብዙ አካባቢዬ ላይ ያሉ ሰዎች በዚህ ነገር ተከፍተው ስላየሁና ሰዉም እንደ እውነት እየተቀበለው ስለሆነ ትንሽ ልበልበት።
ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ነው የተመረኩት ሀኪም ነኝ ብሎ በተገነጣጠለ እንግሊዘኛ የሆነ ፌዝ ይሁን ምር ያለየለት ቪዲዮ የሰራው ልጅ ማነው? ምን ቻናል ላይ ነው ኢንተርቪው የሰጠው? ማይክ ወይ ሪከርደር ያጣ የትኛው ሚዲያ ነው በስልክ ቃለመጠይቅ ያደረገለት? የትኛው ሀኪም ነው "graduation" ለማለት "congratulation" የሚለው?
ምን እንግሊዘኛ ባይችል "patient" የሚልን ቃል ጠፍቶበት በስድ አማርኛ ታካሚን "በሽተኛ" ብሎ የሚጠራ ሀኪም ከየት ተገኘ? ምን ቃል ቢጠፋበት በህክምናው አለም በቀን "50" ጊዜ ሳይጠራ የማይውል ቃል "patient" አይደለም እንዴ?
ህክምና እንደሌላ ትምህርት ቲዮሬቲካል አይደለም። ለስድስት ሰባት አመታት በየቀኑ seminar, morning, bedside, round እየተባለ በፈረንጂኛው ስንተካተክ አይደለም እንዴ እድሜያችንን የጨረስነው?
በየቀኑ በእንግሊዘኛ presentation ሳያቀርብ… በዚሁ ቋንቋ መልስ ሳይሰጣጥ … ሳይጨቃጨቅ የተመረቀ የትኛው ሀኪም ነው? "eachother … together" እያለ በግድ እንግሊዘኛ ለመስበር መታገልስ አላማው ምንድነው ?
በነገራችን ላይ ለመጨረሻ ጊዜ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጠቅላላ ሀኪም ያስመረቀው ያለፈው ዐመት ሚያዚያ ላይ ነው። በዚህ ዙር አዲስ የተመረቀ ሀኪም የለም።
ይሄን አይነት የሀኪምን ስም የሚያጎድፍ ስራ መስራት አላማው ምንድነው? ህዝቡስ በሀኪሙ ላይ ያለው አመኔታ እንዲሸረሸር ማድረግ ማንን ይጠቅማል። ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲስ ይሄን ልጅ በስም ማጥፋት ወንጀል ሊጠይቅ አይችልም ወይ? አስቸኳይ ይቅርታ ለባለሞያውም ለተቋሙም ማድረስ ግዴታው ነው ባይ ነኝ ።
Dr. YosephWorkneh
ቴሌግራማችን: t.me/HakimEthio
Click here to claim your Sponsored Listing.