13/03/2026
የሕጻናትን ጤነኛና ጠንካራ መሰረት ከምንገነባበት ዋና መንገዶች አንዱ አዎንታዊና ገንቢ ንግግር ነው።
ቃላት የማይታይ አስተሳሰባቸውን የመቅረጽ አቅም ስላለው ስለምንለውን ነገር በህጻናት ፊት መጠንቀቅ ያስፈልጋል።
ፈጽሞ ማለት የሌሉብንን ቃላቶች እንመልከት
🚫
👉“አንተ/አንቺ መጥፎ ነህ/ነሽ።”
ይህ ሕጻኑ እንደማይወደድ እንዲሰማው ያደርገዋል።
✔ ይልቁን እንዲህ ማለት “ይህ ባህሪ ጥሩ አይደለም።”
👉“አታልቅስ!” (Stop crying)
ታናሽ ልጆች ስሜታቸውን ለመግለጽ እንዲቸገሩ ያደርጋቸዋል።
✔ ይልቁን እንዲህ ማለት፡ “እንዳዘንክን አይቻለሁ፤ ምን ሆነህ ነው?”
👉“ለምን እንደ ወንድምህ/እህትህ አትሆንም?”
ልጆችን ማነፃፀር ለራሳቸው ያለውን ግምት እንዲያሳንሱ ያረጋል።
✔ ይልቁን እንዲህ ማለት፡ “እያንዳንዱ ሰው በራሱ ፍጥነት ይማራል፤ ሞክር”
👉“ምንም ነገር ትክክል አታደርግም።”
ይህ ልጁን ከማበሳጨቱ በላይ ተስፋውንና መነሳሳቱን ይገላል።
✔ ይልቁን እንዲህ ማለት፡ “እንደገና ሞክር እንጂ፤ ቀላል ነው።”
👉“ትቸህ እሔዳለሁ”
ይህ ፍርሃት እና አልፎ አልፎ እርግጠኝነት ማጣት ያመጣል።
✔ ይልቁን እንዲህ ማለት፡ “ከኔ አጠገብ ቆይ።”
👉“ሕፃን ነህ/ነሽ።”
ይህ ልጁን አፍሮ እንዳይሞክርና መብሰል ባለበት ጉዳይ ወደ ኋላ እንዲቀር ሊያደርገው ይችላል።
✔ ይልቁን እንዲህ ማለት፡ “እየተማርክ እና እያደግክ ነህ።”
✅ : ታናናሽ ልጆች ፍቅር፣ ትዕግሥት እና አበረታች ቃላት ይፈልጋሉ። አዎንታዊ ቃላት የልጆችን መተማመን፣ ደህንነት እና ጤናማ እድገት እንዲኖራቸው ይረዳሉ።
👉በገንቢና አዎንታዊ ቃላት የልጆቻችንን ዓለም እናስውብ!
25/02/2026
ሕጻናት 👭 ከእኩዮቻቸው ጋር ሲጫወቱ የሚያገኙትን እርካታና ጤነኛ ማሕበራዊ እድገት በሌላ በምንም አይተካም!
📌ለልጆቻችን ብሩህ የሕይወት ጅማሬ እንሰራለን!
አድራሻ: ሀዋሳ
ከአቤም ሆስፒታል 70 ሜ ገባ እንዳሉ ያገኙናል
06/02/2026
ሕጻናት በተፈጥሯዊና ጤናማ የጨዋታ አይነቶች
👉 እየተደሰቱ ይማራሉ
👉አፋቸውን በጊዜ ይፈታሉ
👉ጤናማ ማሕበራዊ ክህሎት ያዳብራሉ
👉በአካል ይጠነክራሉ
👉 አዕምሯቸው የሚረጋጋበትን ምቹ ሁኔታ ያገኛል
👉ጤንነታቸው ይጨምራል
ሁሉንም እዚህ ያገኛሉ!
ለተጨማሪ መረጃ +25107227750
ሀዋሳ: ከአቤም የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል 70 ሜ ገባ ብሎ ያገኙናል።
ብሩህ ጅማሬ ጉልህ ፍጻሜ አለው!
04/02/2026
ልጆች ከልክ ያለፈ ስልክ ሲጠቀሙ በአእምሮአቸው ውስጥ ምን ይከሰታል?
🧠 1) የዶፓሚን መጨመር
👉በስልክ የተለያዩ ነገሮችን ማዬት የደስታ ኬሚካል (dopamine) ስለሚጨምር የአእምሮ ሱስ ይሆናል።
ውጤት
👉እውነተኛ ነገር ስለማይስባቸው ፤
በፍጥነት ይሰለቻሉ
🗣 2) የቋንቋ እድገት መዘግየት
ልጆች ቋንቋ የሚማሩት:በዓይን ግንኙነት፣በፊት መግለጫ፣በመስማት
በመመልስ ነው።
📉 ስክሪን ግን:
እውነተኛ ግንኙነት የለውም ፣መመልስ የለም እና ስሜታዊ ግንኙነት የለውም
👉 ውጤት:
ዘግይቶ መናገር ፣ዝቅተኛ ቃላት መኖር ፣ የንግግር ችግር ፣የመግባባት እጥረት
🎯 3) የትኩረት ስርዓት መበላሸት
፣ አእምሮ በፈጣን ምስል ፣ በፈጣን ደስታ እና ቀጣይ ማነቃቂ ፍላጎት ይጠመዳል።
ውጤቱ 👉አጭር ትኩረት፣አደገኛ ፍጥነት ፣የመማር ፍላጎት ችግር
😡 4) ስሜታዊ እድገት መዘግየት
📉 ቁጣ ፣ትዕግስት እጥረት፣ጭንቀት ፣ብስጩነት ፣ርህራሄ እጥረት
🤝 5) የማህበራዊ አእምሮ እድገት መዘግየት
ልጅ ማህበራዊ ግንኙነት የሚማርባቸውን መንገዶች እንደ
ጨዋታ፣ ንክኪ ፣ውይይት፣ግንኙነት ነው
📉 ውጤት:
የዓይን ግንኙነት እጥረት፣ማህበራዊ ሕይወት መጥፋት ፣መገለል እና ብቸኝነት
👉ኦቲዝም የሚመስል ባህሪ
ምልክቶች ማሳየት (Signs)
የዓይን ግንኙነት/ትኩረት ማጣት
አለመናገር / ዘግይቶ መናገር
ለስም መልስ አለመስጠት እና ሰው አለመፈለግ
ይቀጥላል....
13/01/2026
We are surrounded by nature for countless valuable reasons that cannot be fully measured or counted. When we engage with nature in ways that respect its balance and diversity, it provides us with immeasurable benefits.
When a person’s early life is shaped in connection with nature, it helps develop emotional regulation, strengthens patience, encourages sharing and cooperation, enhances the body’s ability to fight disease, and supports the growth of a healthy mind.
Therefore, when children are allowed to play—under proper supervision—with soil, sand, water, and similar natural materials, they become beneficiaries of all the advantages mentioned above.
Natural play is a type of play in which children relax with full joy and genuine inner motivation.
And here is the beauty of it: when children are playing, time seems to run out quickly—but the play continues at home
25/12/2025
ሕፃናትን ከመጠን በላይ መንከባከብ እና የሚገባ እንክብካቤን መንፈግ ምን ያስከትላል?
1. ከመጠን በላይ እንክብካቤ መስጠት (Overcare)
ከመጠን በላይ እንክብካቤ ማለት፣ ሕፃናት በዕድሜያቸውና በችሎታቸው ሊሰሩ የሚችሉትን ነገር እንኳን ራሳቸው እንዳይሞክሩ፣ ከመጠን በላይ እገዛ፣ ጥበቃ ወይም ቁጥጥር ሲደረግባቸው ማለት ነው። ይህ በመጀመሪያ በጎ እንክብካቤ የሚመስል ቢሆንም፣ በእውነቱ ሕፃናት በውስጣቸው ያለውን አዳጊ እምቅ ችሎታ እንዳያወጡ ይከለክላል።
ተፅእኖዎቹ፦
እጅግ የሚንከባከባቸው ሰው በማይኖርበት ጊዜ መቋቋም አለመቻል ፣ፍርሃትና ተስፋ መቁረጥ፣
ዝቅተኛ ራስ-መተማመን፣
ጭንቀትና ስህተትን መፍራት
ደካማ የችግር መፍትሄ ክህሎት
ልፍስፍስነት (በሰዎች ላይ ጥገኛ መሆን)
2. እንክብካቤ እጥረት (Undercare)
እንክብካቤ እጥረት ማለት፣ ሕፃናት ለጤናማ እድገት የሚያስፈልጋቸውን ስሜታዊ፣ አካላዊ ወይም ስነ-ልቦናዊ ድጋፍ ሲነፈግባቸው የሚፈጠር ሁኔታ ነው።
ሕፃኑ ምን እንደሚሰማው፣ ምን እንደሚበላ፣ ህይወቱ እንዴት እየተጓዘ እንደሆነ ለማወቅ ፍላጎትና ቁርጠኝነት ከወላጆቹ/ ከተንከባካቢዎቹ ሲጎድል ይከሰታል።
ተፅእኖዎቹ፦
የደህንነት አለመሰማት፣
ዝቅተኛ ራስ-እምነት፣
ሰዎችን መተማመን መቸገር፣
የባህሪ ችግሮች (ጥቃት መሰማት ወይም ብቸኝነት)
የስሜትና የማህበራዊ እድገት መዘግየት ናቸው።
አጠቃላይ
ከመጠን በላይ እንክብካቤና የእንክብካቤ እጥረት ተቃራኒ ቢመስሉም፣ ሁለቱም የሕፃኑን ችሎታና ራስ-መተማመን ያዳክማሉ። አንዱ በብዙ መስጠት ያገድላል፤ ሌላው በጥቂት መስጠት ይጎዳል።
የተመጣጠነ፣ ከዕድሜ ጋር የሚስማማ እንክብካቤ ሕፃናትን ለራስ-መተማመን፣ ለጽናትና ለጤናማ እድገት ቁልፍ ሚና ይጫወታል።