Diguna Fango Woreda youth league

ድጉና ፋንጎ ወረዳ ብልግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ

Operating as usual

Photos from ሶዶ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ's post 23/04/2022
22/04/2022

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ ብልፅግና ፓርቲ መልካም የስቅለት በአል እንዲሆንላችሁ ይመኛል።

መልካም በአል!!

21/04/2022

ሚያዝያ 13/2014 ዓ/ም

የድጉና ፋንጎ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተፈሪ ኩሣ የ2014 ዓ/ም የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል ።

አቶ ተፈሪ አክለውም ስቅለቱ በዓሉ በመላው የሀገራችን ክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በደማቅ ሁኔታ የሚከበርና ያላቸው ሌለላቸው የሚያስቡበትና የሚደጋገፉበት በዓል መሆኑን ገልጸዋል።

የብልፅግና ፓርቲ መጀመርያ ጉባኤ የተካሄበትና አቅጣጫዎችና ውሣኔዎች የተላለፈበት፣ የውጭና የውስጥ ጣልቃ ገብነት የከሰመበት፣ ኢትዮጵያ በአደባባይ የራሷን ማንነት የገለጸችበት ዓመት በመሆኑ የስቅለት በዓል አከባበርን ላይት እንደሚያደርግ አቶ ተፈሪ አስረድተዋል።

ኢትዮጵያ የብልፅግና ጉዞን ለማሳካት ራዕይን፣ተልዕኮንና እሴትን ለመተግበር አቅዳ መነሳቷን በህዝቦቿ ህብረ-ብሔራዊ አንድነት ለማሳካት በቁርጠኝነት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

የወረዳችን አርሶአደሮች ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የበልግ እርሻ ስራዎች ላይ ትኩረት በመስጠት ድርሻቸውን እንዲወጡና ሌሎች በተለያዩ ስራዎች የተሰማሩትም ለውጤታማነቱ መረባረብ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ስቅለት በዓሉ የሠላም፣የጤና፣የመተሳሰብና የብልፅግና እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል።

Photos from የወላይታ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት- Wolaita Prosperity Party office's post 21/04/2022
Photos from በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ's post 19/04/2022
Photos from Wolaita Zone Prosperity party youth league's post 19/04/2022
Photos from የድጉና ፋንጎ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ  ጽ/ቤት ገፅ's post 16/04/2022
Photos from ወላይታ ዞን ዳሞት ፑላሳ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት's post 16/04/2022
15/04/2022

ከ94 ሺህ በላይ ወጣቶች የሚሳተፉበት መድረክ ቅዳሜ ይካሄዳል፡-የደቡብ ወጣቶች ሊግ ጽህፈት ቤት

ወላይታ ሶዶ፡- ሚያዚያ 6/2014 በደቡብ ክልል 94 ሺህ 200 ወጣቶች የሚሳተፉበት ክልል አቀፍ የውይይት መድረክ ሚያዚያ 8/2014 እንደሚካሄድ የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሰንበቶ አባባ የውይይት መድረኮቹ ወጣቱ በብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ የተላለፉ ውሳኔዎችን በአግባቡ ተረድቶ ወደቀጣዩ ተግባር በእውቀት እንዲገባ የሚያደርጉ ናቸው ብለዋል፡፡

መድረኮቹ ለወጣቱ የተሻለ ግንዛቤ መፍጠር የሚያስችሉ፣መካተትና መሻሻል አለባቸው የሚሏቸውን ጉዳዮች በነጻነት የሚያነሱባቸውና የወጣቱን ወሳኝ ችግሮች ለመፍታት እንደመነሻ የሚሆኑ ሀሳቦች የሚገኙበት እንደሚሆንም ገልጸዋል፡፡

ብልጽግና ፓርቲ ያለወጣቱ ተሳትፎ የትኛውም ጉዳይ ግቡን እንደማይመታ ያምናል ያሉት አቶ ሰንበቶ የጉባኤው ውሳኔዎች ወደተግባር የሚቀየሩት በወጣቱ ስለሆነ ሁሉም ወጣቶች በመድረኮቹ በንቃት እንዲሳተፉም አሳስበዋል፡፡

በመድረኮቹ የፓርቲዉ አባል ያልሆኑ ወጣቶችም ጭምር እንደሚሳተፉ ያስታወቁት ጽህፈት ቤት ሃላፊው የውይይት መድረኮቹ በ157 አካባቢዎች እንደሚካሄዱና ለዚህም የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡

ወጣቱ ለአካባቢው፣ለክልሉና ለአገሪቱ ይበጃሉ የሚላቸውን ሀሳቦች በቅንነት በማንሳት የጸናና ዘላቂ ሰላም ያለው፣ የበለጸገ አገርና ህዝብ ለመፍጠር ለሚደረገው ጥረት የራሱን ሚና እንዲጫወትም አቶ ሰንበቶ ጠይቀዋል፡፡

በመድረኮቹ ማጠናቀቂያ ላይ የኑሮ ውድነቱን ለማስተካከልና የምርት አቅርቦቱን ለማሳደግ የሚያስችል የከተማ ግብርና ማስጀመሪያ መርሃ ግብር የሚካሄድ ሲሆን በከተማ ግብርና መልካም ተሞክሮ ያላቸው ግለሰቦች ጥረትም ጉብኝት ይካሄዳል ብለዋል፡፡

የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ከ840 ሺህ በላይ አባላት እንዳሉት ያመለከቱት አቶ ሰንበቶ አባባ በቀጣይ እስከ ገጠር ቀበሌያት የሚገኙ ሁሉንም ወጣቶች በጉባኤው ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ ለማወያየት እቅድ መያዙንም አስታውቀዋል፡፡

12/04/2022

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዘመናት ያዳበረውን ፍቅር፣ መከባበርና መደጋገፍ እንደገና ወደነበረበት በማስቀጠል አንዱ ጎታች ሌላው ተጎታች ሳይሆን ወይም አንዱ የበላይ ሌላው የበታች ሳይሆን ሁሉም እኩል ለሀገሩ ብልፅግና አሻራውን የሚያሳርፍበት ወቅት እንዲሆን ፓርቲው ፕሮግራሞቹንና ህገ ደንቦቹን ተከትሎ እየሰራ ይገኛል፡፡

ብልጽግና ህልሙ ትልቅና ሰፊ እንጂ በትንንሽ ነገሮች ረክቶ የሚቀመጥ ፓርቲ እንዳልሆነ ካስቀመጣቸው ፕሮግራሞችና ህገ ደንቦች መረዳት ይቻላል፡፡አገራዊ አጀንዳን በአግባቡ መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ብልጽግና ፓርቲ ከማንም የተደበቀ አጀንዳ የለውም፡፡አጀንዳው ልማት፣ብልጽግና እና ዴሞክራሲን ማጽናት ነው፡፡

ትንንሽ ልዩነቶቻችንን በማቻቻል፣ ከጎጠኝነትና ከቡድንተኝነት አስተሳሰብና ድርጊት በመውጣት እና ለሃገርና ለሃገራዊ አንድነት ቅድሚያ መስጠት ከቻልን በእርግጥም የበለጸገች ኢትዮጵያን በጋራ ድካማችን መገንባት እንችላለን፡፡

ብልጽግና ፓርቲ ለአሁኑ ትውልድ ብቻ ሳይሆን ነገን ተሻግሮ ለመጪው ትውልድ የበለጸገች ኢትዮጵያን ለማስረከብ ዛሬን እየሰራ ያለ ፓርቲ ነው፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ ፓርቲው ለአገርና ለህዝብ የማይከፍለው መስዋዕትነት የለም፡፡

12/04/2022

ወጣቶች _የኢትዮጵያ የለዉጥ ተዋኒያንና ተስፋዎች፣

ወጣቶች በሀገራችን የፖለቲካ ታሪክ ዉስጥ ልዩ ሥፍራ አላቸዉ። ከ19 60ዎቹ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች እስከ አዲሱ የሀገራችን የለዉጥ እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ ወጣቶች አሻራ ጉልህ ነዉ።

ብልጽግና ደግሞ በትዉልድ ቅብብሎሽ እየተረጋገጠ የሚሄድ ብሩህ የጉዞ ሂደት ነዉ። ብልጽግና በዜጎች የነቃ ተሳትፎ እዉን እየሆነ የሚቀጥል የትዉልዶች የቤት ስራ ነዉ።

ለዚህም ነዉ ወጣቶች የነገ ሀገር ተረካቢ ብቻ ሳይሆኑ የዛሬዋ ኢትዮጵያ ባለቤትም ናቸዉ የሚለዉ ብልጽግና ፓርቲ።

ወጣቱ የዛሬዋም የነገዋም ኢትዮጵያ የለዉጥ ተዋናይና ተስፋ ነዉ።

ብልጽግና ፓርቲ የወጣቱን ዘርፈ ብዙ ጥያቄዎችና ችግሮች መፍታት የሀገራችንን ችግሮች በወሳኝ መልኩ መፍታት ነዉ ብሎ ያምናል። ኢትዮጵያ የወጣቶች ሀገር ናትና ለወጣቱ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት የሚሠራ ሥራ ፋይዳዉ ከፍተኛ ነዉ።

የበለፀገች ሀገር መፍጠር የወጣቱን ትጋት ይጠይቃል። ወጣቱ ከማህበራዊ ሚዲያዎች ጫና፣ ከፅንፈኛ አስተሳሰብና ተግባር ራሱን በመከላከል ለዘላቂ ጥቅሙ ዘብ መቆም አለበት።

አሁናዊ ሀገራዊ ኢኮኖሚያዊ ፣ የፖለቲካዊና ማህበራዊ ችግሮችን በመፍታቱ ሂደትም ወጣቱ የመፍትሄ ቁልፍ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

የሴራ ፖለቲካ ዉዥንብርና የመጠፋፋት ፖለቲካ ሰለባ ላለመሆንም በምክንያታዊነት መርህና በአስታዋይነት መመራት ይኖርበታል።

ወጣቱ ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት እንዲጎለብት፣ የትብብርና የአብሮነት መንፈስ እንዲያብብ ይበልጥ መጣር ይኖርበታል።

ፅንፈኛ አስተሳሰቦችና ተግባራት ሰለባ እንዳያደርጉት መጠንቀቅ አለበት። አንድነታታቸዉ የተናጋ፣ ግጭት ሰለባ የሆኑ ሀገራት በቀላሉ እንደሀገር እንደማበታተኑ፣ እንደሚፈርሱ፣ ለስደት እንደሚዳረጉ ከነ ሶሪያ፣ የመንና መሠል ሀገራት ትምህርት መዉሰድ ብልህነት ነዉ።

'ብልጥ ልጅ እየበላ ያለቅሳል ' እንዲሉ የጀመርነዉን ለዉጥ ፍሬዉን እያጣጣምን፣ የጎደለዉ እንዲሞላ አየሠራን በስክነት ሀገርን መገንባትና ከሴራ ፖለቲካዊ መታደግ የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት ነዉ።

12/04/2022

ኢትዮጵያ የብዝኃነት ሀገር ናት፡፡ ያለን አንድ ሀገር ብቻ ነው፡፡ ሌላ ተጨማሪ ሀገር የለንም፡፡ ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ነን፡፡ ሀገራችን ለእኛ ለዜጎቿ በቂ ሀብት አላት፡፡ ብዝኃነት ውበት እንጂ ዕዳ አይደለም፡፡ ጽኑ፣ የበለጸገችና በመከራን የምትሻገር ሀገር ለመገንባት ከፈለግን እርስ በእርስ መተቃቀፍ እንጂ መገፋፋት የለብንም፡፡ በወንዴማማችነትና በእኅትማማችነት ስሜት መኖር አለብን፡፡

በመገፋፋት የሚገነባ ሀገርም ሆነ የሚበጽግ ሕዝብ የለም፡፡ የዓለም ታሪክ የሚነግረን እውነት ቢኖር እርስ በእርስ በመገፋፋት ጥፋት እንጂ ብልጽግናም ሆነ ሀገራዊ አንድነት ማምጣት እንደማይቻል ያረጋግጣል፡፡ የሊቢያ፣ የየመንና የሶርያ የቅርብ ታሪክ የሚያሳየን ይህንን ሐቅ ነው፡፡

Photos from Duguna Fango Woreda Government Communication Affairs Office's post 11/04/2022
11/04/2022

መልካም አጋርነት ዘላቂ የሚሆነው በመከባበር ላይ የተመሠረት እኩልነት ሲኖር ነው-አምባሳደር ተሾመ ቶጋ

ወላይታ ሶዶ፣ ሚያዚያ 2፣ 2014 መልካም አጋርነት ዘላቂ የሚሆነው በሁለቱም ወገኖች በኩል በመከባበር ላይ የተመሠረት እኩልነት ሲኖር ነው ሲሉ በቻይና የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ተናገሩ፡፡

በአፍሪካ እና ቻይና ሥልጣኔዎች ዙሪያ ያተኮረ ውይይት በቻይና እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የተሳተፉት አምባሳደር ተሾመ ቶጋ፥መልካም አጋርነት ዘላቂ የሚሆነው በሁለቱም ወገኖች በኩል በመከባበር ላይ የተመሠረት እኩልነት ሲኖር ነው ብለዋል።

አምባሳደሩ የአፍሪካ ቻይና የትብብር መድረክ ዋና መሠረቱ በመከባበር ላይ የተመሠረተ እኩልነት እንደሆነ መናገራቸውንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

መረጃ ምንጫችን (ኤፍ ቢ ሲ) ነው

Want your school to be the top-listed School/college in Awassa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address

Washigton
Awassa
091648
Other Colleges & Universities in Awassa (show all)
Abirham Kabeso Abirham Kabeso
Cm
Awassa, NABK

Hawassa Polytechnic College Hawassa Polytechnic College
Hawassa
Awassa

Hawassa polytechnic is public TVET College established in 1990 E.C to offer technical and vocational

Memihir-መምህር Memihir-መምህር
Awassa

Teachers are corner stones in society building. Better teachers are believed to bear better generati

Liya Fikir Liya Fikir
Awassa

Life have money wey

Cheek tse Cheek tse
Sdf
Awassa

Aaaaaa

Gorfu Goshu coach Gorfu Goshu coach
South
Awassa

This page help us to recognize our area and self profile

Tesfaye Destaw Tesfaye Destaw
Jinka
Awassa

Personal blog

Evangelist Makit Abera Eba Evangelist Makit Abera Eba
Oromia
Awassa

Great commision

Teme Teme
Awassa

Ethio beautiful girl Ethio beautiful girl
Yes
Awassa

A page which describes beautiful girls in Ethiopian

Mesfin Ayenete Pages Mesfin Ayenete Pages
Awassa, MESFIN

tiktok.com/@mesfinayenete https://www.youtube.com/@mesfinayeneteTube6851 🤳I Belong To Jesus❗️