Memihir-መምህር

Teachers are corner stones in society building. Better teachers are believed to bear better generati

Operating as usual

Photos from Memihir-መምህር's post 07/09/2022

#ህይወት መምህርህ ስትሆን ቦታህን ታገኘዋለህ😎

#አካል ጉዳተኝነት ታሪክ ያደረገዉ ግለሰብ✅

🙏

Photos from Memihir-መምህር's post 02/09/2022

የኦሮምያ መምህራን ማህበር ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር በዛሬው እለት በአዳማ ከተማ 4ተኛውን የትምህርት ጥራት ኮንፈረንስ እያካሄደ ይገኛል ።

የጥናትና ምርምር ስራዎቹ በምሁራን ቀርበው በታዳሚዎች ውይይት ከተደረገባቸው በኋላ ማህበሩ በፕሮሲዲንግ አሳትሞ ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እንዲደርስ ያደርጋል ።

በኮንፈረንሱ ላይ ዶ/ር ዮሀንስ በንቲን ጨምሮ የኢትዮያ መምህራን ማህበር አመራሮች፣ የኦሮምያ ክልል ት/ቢሮ አመራሮችና የሚመለከታቸው ባለሙያዎች የክልሉና ከተለለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች የተጋበዙ የማህበር አመራሮች ፣ መምህራንና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ኮንፈረንሱን ላዘጋጀው ለኦሮምያ መምህራን ማህበር ፣ ድጋፍ ላደረገው የክልሉ ትም/ቢሮ ፣ ለጥናት አቅራቢዎችና ተሳታፊዎች ሁሉ ምስጋናውን እያቀረበ ኮንፈረንሱ የተሳካ እንዲሆን መልካም ምኞቱን ይገልፃል ።

#ሲዳማ ክልልም ከዚህ ልምድ መዉሰድ አለበት😎

Photos from Memihir-መምህር's post 01/09/2022

አሳዛኝ ዜና😭

#ለጥንቃቄ ያክል🤔

የቤት ሠራተኛዋ ሁለት እህትማማቾችን በአሰቃቂ ሁኔታ ገደለች😭😭😭😭

በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ በምትሰራ ሠራተኛ እና የተባሉ የ2 ዓመትና የ3 አመት ህፃናት ህይወት አልፏል፡፡

የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮምሽን ም/ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለኢትዮ ኤፍኤም እንደተናገሩት ወንጀል ፈፃሚው በቁጥጥር ስር መዋሉዋን በመጥቀስ የህፃናቱ ህይወት በወንጀል ፈፃሚዋ እንዴት እንዳለፈና ሌሎችንም መረጃዎች ፓሊስ ተጨማሪ መረጃ እያጣራ እንደሚገኝ እና ህብረሰተቡም እንዲረጋጋም ም/ ኮማንደር ማርቆስ አደራ ብለዋል፡፡

Via: ኢትዮ ኤፍ ኤም

Photos from Memihir-መምህር's post 31/08/2022

እኛ መምህራን በሀገራችን ላይ የተቃጣዉን አዉዳሚ ጦርነት በያለንበት ሆነን በተሠማራንበት ዜጎች ግንባታ ሥራችን መመከት ይጠበቅብናል።

31/08/2022

የኬኒያ መምህራን ደመወዝ(ከ1ኛ-12ኛ ክፍል): ክራቫት ያሳስራል!
******************************
(ከ9ሺ እስከ 70ሺ)
---------------------
ለሁሉም የ 5,000 ሽልንግ የመንገድ ርቀት አበል (commuting allowance) አለ፡፡

መኖሪያቸው ከ10ኪሜ በላይ ከትምህርት ቤታቸው ለሚርቅ የሚከፈል አበል ነው፡፡ እንደ ትራንስፖርት አበል ማለት ይቻላል፡፡ በኬኒያ ለሁሉም መመህራን፣በቅርብም በሩቅም ላሉት እኩል ይከፈላል፡፡

በአጠቃላይ መልኩ አምና በተሻሻለው የደመወዝ ስኬል መሰረት የኬኒያ መመህራን ደመወዝ ከ1ኛ ደረጃ እስከ ሁለተኛ ደረጃ(በእኛ ሀገር ከ1-12) እንደሚከተለው ነው፡፡ የትምህርት ቤት ዳይሬክተር ከሆንክ(ትምህርትና ልምድ
ይጠይቃል) ደመወዝህም፣ጥቅማጥቅምህም ይጨምራል፡፡ ፕሪንስፓሊስት ተብለህ የአካደምክ ማዕረግ ይኖርሃል፣ወደ ኋላ መመለስ የለም፡፡

•121,814 - 157,656 በኢትዮጵያ ብር፡ 51ሺ ብር እስከ 65 ሺ ብር
•109,249 -118,169
•93,850 -102,807
•82,717 -87,900
•74,703 - 82,717
•51,632 - 62,272.
•45,287 - 51,632.
•43,154 -53,943
•31,242 -33,97
•31,000 -43,000
•19,000 -33,000.
•16,000 -27,000 በኢትዮጵያ ብር፡ 7ሺ ብር እስከ 12ሺ ብር
------------------------------
አንድ ጀማሪ የአንደኛ ደረጃ መምህር በትንሹ 7ሺ ብር መደበኛ ደመወዝና 2ሺ ብር የትራንስፖርት አበል ይከፈለዋል፡፡

27/08/2022

ከኢመማ የተላለፈ የጥንቃቄ መልዕክት

የጥንቃቄ መልዕክት

ለተከበራችሁ የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላትና መምህራን በሙሉ

ለነሀሴ 21/2014 ዓ.ም በኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አስተባባሪነት " የመምህራን ባንክ ምስረታ " ተብሎ መገናኛ አካባቢ አሊፍ ሆቴል የተጠራውን ስብሰባ የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር የማያውቀው መሆኑን እየገለፅን መምህራን ተታላችሁ ገንዘባችሁን እንዳትጭበረበሩ ኢመማ ያሳውቃል።

ኢመማ

26/08/2022

ተብለዉ በፌዴራል ሲቭል ሰርቪስ ኮሚሽን የወረደዉ የደመወዝ እርከን የመምህራን ትምህርት ኮሌጅ መምህራንን የትምህርት ዝግጅትና ሥራ ጫናን ታሳቢ ያላደረገ ነዉ😎

24/08/2022
24/08/2022

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ፒኤችዲ) ስለዩኒቨርሲቲ መምህራን!...
***

"... የዩኒቨርስቲ መምህራን እናንተም መገንዘብ ያለባችሁ ኢትዮጵያ ደሃ አገር ናት። አሜሪካ እንኳን ዩኒቨርስቲ ተማሪ አስገብታ አትቀልብም። ዩኒቨርስቲ ሰው ከደረሰ ራሱን ነው ማስተማር ያለበት እንጂ ለአስተማሪም ደመወዝ፣ ለተማሪም ቀለብ አይነት ጥያቄ እንደኢትዮጵያ ላሉ አገራት ኢኖቬተርስ አይፈጥርም። ዩኒቨርስቲዎች ኦቶነመስ ሆነው ራሳቸውን ማስተዳደር አለባቸው። ሃይስኩል ላይ ኢንቨስት ካደረግን እኛ እሱ እንደ በቂ መወሰድ አለበት። ዩኒቨርስቲ ሆኖ ገንዘብ አምጥቶ የራሱን ደመወዝ መክፈል የማይችል ከሆነ ኢትዮጵያን ማሳደግ አይችልም ማለት ነው።

ሃርቫርድ መንግሥትን አይጠይቅም በጀት፣ ኦክስፎርድ አይጠይቅም በጀት፣ ኬንያም ዩጋንዳንም ብትሄድ አይጠይቅም በጀት፣ እዚህ ግን ቀለቡም፣ ደመወዙም ሁሉም ነገር የሚጠየቅ ከሆነ ችግር አለ።
ሁለተኛ የዩኒቨርስቲ መምህር ስታንዳርድ አለው። በሴሚስተር አራት ክሬዲት አወር፣ አምስት ክሬዲት አወር አስተምረህ የዩኒቨርስቲ መምህር ነኝ አይባልም። ተጋባዥ መምህር ነኝ ነው የሚባለው።

አሁን ችግር የሆነው በጅምላ መታየት የለበትም። የዩቨርስቲ መምህራን አርሶ አደር ጋር የሚውሉ፣ የሚመራመሩ፣ ግቢ የሚቀይሩ፣ ለመንግስት ሀሳብ የሚያቀርቡ ታምር የሚሰሩ ሰዎች አሉ። እነዚህን ማመስገን ያስፈልጋል። ሶስትም አራትም ክሬዲት አወር እያስተማሩ፣ በሳምንት አንድ ቀን ዩኒቨርስቲ ግቢ ውስጥ እየተቀመጡ፣ ሌላውን ቀን ደግሞ ሌላ ቦታ እየዋሉ፣ ፌስቡክ ላይ እየቆዩ የዩኒቨርስቲ መምህር ነኝና አድማ አደርጋለሁ የሚሉ ሰዎች ደግሞ አሉ። ይሄ ጥሩ አይደለም ለነሱም ጥሩ አይደለም። አድማ ቢደረግ ዩኒቨርስቲ ይዘጋል፣ አድማ ቢደረግ የበለጠ ገንዘብ ይከስራል። ከዚያ ምን እናገኛለን? ጥቅም አናገኝም! ደረጃ በደረጃ ጥያቄ እየመለስን ብንሄድ። ለሁላችን ጠቃሚ ይሆናል፣ የሁላችን ችግር ነው። ሁላችን በየደረጃው እየፈታን መሄድ አለብን። ከአገር አቅም ጋር መታየት አለበት።

ኢትዮጵያን በሚያሳድግ መልኩ መታየት አለበት። በዚህ አግባብ ከታየ ጥያቄው አግባብ አይደለም፣ በቂ ደመወዝ አላቸው፣ ለምን ጠየቁ የሚባል አይደለም። ችግር አለ እውነታቸውን ነው።

መታረም ያለበት ነገር አለ። ባለፈው ዓመት ተኩል ጂኤጂ ስንወስን ጂኤጂ በጣም ብዙ ዓመት ቆይቷል። ከ30 ቢሊየን ብር በላይ በጀት ጠይቆናል። ቀላል ነገር አይምሰላችሁ። በአገር ደረጃ ስለሆነ አጠቃላይ በጀት ይወስድብናል። በጀቱን በሙሉ ደመወዝ ከፍለን ልማት የማንሰራ ደግሞ ከሆነ ትክክል አይመጣም። እና ጥያቄያቸው ፌር የሆነበት አለ። አቅም በፈቀደ መጠን እንመልሳለን። ከእነሱ ግን ብዙ እርዳታ፣ ብዙ ድጋፍ እንደምንፈልግ ከወዲሁ ግንዛቤ ቢወሰድ ጥሩ ነው። ከዚያ ውጪ ያለው የፖለቲካ መጠቀሚያ መሆን ብዙ ፋይዳ የለውም። ነገር እየተካረረ ስለሚሄድ ያለውንም እያሳጣ ነው የሚሄደውና ትክክል ስለማይመጣ ቆም ብሎ ማሰብ ያስፈልጋል። የዩኒቨርስቲ አመራሮች፣ ፕሬዚዳንቶች፣ ቦርዶች መፈተሽ አለባቸው። ማነው መምህር፣ ማነው መምህር ያልሆነው፣ ማነው እያገዘ ያለው፣ ማነው እያገዘ ያልሆነው? መለየት ያስፈልጋል። ያንን ካደረግን መልካሞችን እየደግፍን የማይሰሩ ደግሞ እንዲሰሩ የምናደርግበት እድል ይፈጠራል።..."

23/08/2022

የትኛዉም መምህር በአንድ ጀምበር ጠቅላይ ሚንስትር፣ አዛዥ እና መሪ ልሆን ይችላል። ማንም ሰዉ ግን ከሌላ ሙያ ተነስተዉ መምህር መሆን አይችልም።

#በመምህር ተምረዉ ያለፈ ሰዉ ደግሞ መምህራንን አያንቋሽሽም።

Want your school to be the top-listed School/college in Awassa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address

Awassa
Other Colleges & Universities in Awassa (show all)
Abirham Kabeso Abirham Kabeso
Cm
Awassa, NABK

Hawassa Polytechnic College Hawassa Polytechnic College
Hawassa
Awassa

Hawassa polytechnic is public TVET College established in 1990 E.C to offer technical and vocational

Liya Fikir Liya Fikir
Awassa

Life have money wey

Cheek tse Cheek tse
Sdf
Awassa

Aaaaaa

Gorfu Goshu coach Gorfu Goshu coach
South
Awassa

This page help us to recognize our area and self profile

Tesfaye Destaw Tesfaye Destaw
Jinka
Awassa

Personal blog

Evangelist Makit Abera Eba Evangelist Makit Abera Eba
Oromia
Awassa

Great commision

Teme Teme
Awassa

Ethio beautiful girl Ethio beautiful girl
Yes
Awassa

A page which describes beautiful girls in Ethiopian

Mesfin Ayenete Pages Mesfin Ayenete Pages
Awassa, MESFIN

tiktok.com/@mesfinayenete https://www.youtube.com/@mesfinayeneteTube6851 🤳I Belong To Jesus❗️

Diguna Fango Woreda youth  league Diguna Fango Woreda youth league
Washigton
Awassa, 091648

ድጉና ፋንጎ ወረዳ ብልግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ