Mao and Komo Special Woreda Educational Office

Mao and Komo Special Woreda Educational Office Mao and Komo Special woreda educational office is Govermental organization

25/08/2026
‎ .        +++=====____======+++ .‎በማኦ እና ኮሞ ልዩ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ከ3ቱ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የተወጣጡ በዉጤታቸዉ የተሻሉ ተማሪዎች በቶንጎ ሁለተኛ ደረጃ ሚኒ...
25/08/2026

‎ .
+++=====____======+++
.

‎በማኦ እና ኮሞ ልዩ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ከ3ቱ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የተወጣጡ በዉጤታቸዉ የተሻሉ ተማሪዎች በቶንጎ ሁለተኛ ደረጃ ሚኒ ቦርድንግ ማዕከል ተቋቋሞ በ2018 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ (Entrance) ዉጤት እንድያመጡ ለማምደረግ በተመረጡ መ/ራን ስሰጥ ከነበሩት #6 ተማሪዎቹ አበረታች ውጤት ማስመዝገባቸውን አስታወቀ።
**************‎******
በ‎ማዕከሉ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን በአንድ ቦታ ሰብስቦ፣ ምቹ የመማሪያ አከባቢን በመፍጠርና አስፈላጊውን የማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠት ተማሪዎች እንድዘጋጁ መደረጉ ይታወሳል።
# # # #====+++++===== # # # # #
‎የዚህ ያላሰለሰ ጥረት ውጤት የሆነው የዘንድሮው የፈተና ውጤት ይፋ ሲደረግ፣ እስካሁን ባለው መረጃ መሠረት #6 ተማሪዎች የማዕከሉ ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግባት የሚያስችል ዉጤት ማምጣታቸዉ ማወቅ ተችሏል።

‎ይህ አበረታች ስኬት የተማሪዎች ጠንካራ ጥረት፣ የመምህራን ትጋትና እገዛ፣ እንዲሁም የልዩ ወረዳው አስተዳደር፣ የትምህርት ጽ/ቤት እና ሌሎች በለድርሻ አካላት ያደረጉት የተቀናጀ የጋራ ርብርብ ዉጤት መሆኑ መረዳት ተችሏል።

‎ውጤቱ በቀጣይ ዓመታትም መሰል የቦርዲንግ ትምህርት ቤቶችን አጠናክሮ በማስቀጠል በልዩ ወረዳው ወደ ዩኒቬርሲቲ የሚገቡ የተማሪዎች ቁጥር ለማሳደግ እና የተሻለ የትምህርት ስኬት ለማስመዝገብ ለሚሰራው ስራ ትልቅ ተስፋ እና መነሳሳትን የፈጠረ በመሆኑ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑ የትምህርት ጽ/ቤቱ አስታዉቋል።

‎እንኳን ደስ ያላችሁ!

  #በማኦ እና ኮሞ ልዩ ወረዳ በዜባ መጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለተማሪዎች ምቹ የት/ቤት ሁኔታ ለመፍጠር የአጥር ጥገና ሥራ በህብረተሰብ ተሳትፎ ተሰርቷል!!!(ቶንጎ፣ነሐሴ 19/201...
25/08/2026


#በማኦ እና ኮሞ ልዩ ወረዳ በዜባ መጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለተማሪዎች ምቹ የት/ቤት ሁኔታ ለመፍጠር የአጥር ጥገና ሥራ በህብረተሰብ ተሳትፎ ተሰርቷል!!!

(ቶንጎ፣ነሐሴ 19/2018 ዓ,ም)በማኦ እና ኮሞ ልዩ ወረዳ በዜባ መጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ በክረምት ወራት የትምህርት ስራዎች የ2019 የትምህርት ዘመን የዝግጅት ምዕራፍ በማከናወን ወደ ት/ቤት የሚመጡ ተማሪዎች ምቹና ሳቢ አከባቢ ለመፍጠር በህብረተሰብ ተሳትፎ የት/ቤቱ የአጥር ጥገና ሥራ ተሰርቷል።

በማኦ እና ኮሞ ልዩ ወረዳዉ የትምህርት ዘርፍ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎች ''በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ'' በሚል ተጠናክሮ ቀጥሏል።‎        @ =====*++======@‎(ቶንጎ...
24/08/2026

በማኦ እና ኮሞ ልዩ ወረዳዉ የትምህርት ዘርፍ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎች ''በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ'' በሚል ተጠናክሮ ቀጥሏል።
‎ @ =====*++======@
‎(ቶንጎ፦ነሀሴ 18/2018 ዓ.ም) የማኦ እና ኮሞ ልዩ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት አንደኛ ከእሽሞሎ ድንባር ተሻጋሪ በጎ አድራጎት ማህበር ጋር በመተባበር የክረምት በጎ ፍቃድ ስራዎችን በሚል ምቹ የት/ቤት አካባቢን ለተማሪዎች ለመፍጠር የመማሪያ ክፍሎች እድሳት እና የተማሪዎች መቀመጫ ዴስክ ጥገና ስራ ተከናዉኗል ።
‎ ======+++======
‎በታጃ ጃሊስ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የማጠናከሪያ ትምህርት የተማሪዎች ማንብ፣ መጻፊና ማስላት፣ የመማሪያ ክፍሎች እድሳት እና የተማሪዎች መቀመጫ ዴስክ ጥገና እየተከናወነ ስሆን ቀጣይ በሌሎች ት/ቤቶች የበጎ አድራጎት ስራዎች ለማስራት በእቅድ ተይዟል።
‎ ====--__--====
‎በበጎ አድራጎት ስራዎች የትምህርት ጽ/ቤት ማኔጅሜንት አባላት፣ በለሞያዎች፣ የእሽሞሎ ድንበር ተሻጋሪ በጎ አድራጎት ማህበር አበላት፣መ/ራን እና የት/ቤት አመራሮች የተገኙ ስሆን ለስራ ስኬታማነት ጉልህ ሚና ለተጫወጡት አካላት ሁሉ ጽ/ቤቱ ምስጋና አቅርቧል።

በማኦ እና ኮሞ ልዩ ወረዳዉ የትምህርት ዘርፍ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎች ''በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ'' በሚል ተጠናክሮ ቀጥሏል።‎         =====*++======‎(ቶንጎ፦ነ...
21/08/2026

በማኦ እና ኮሞ ልዩ ወረዳዉ የትምህርት ዘርፍ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎች ''በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ'' በሚል ተጠናክሮ ቀጥሏል።
‎ =====*++======
‎(ቶንጎ፦ነሀሴ 15/2018 ዓ.ም) የማኦ እና ኮሞ ልዩ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ከዋንጋ ጊቴን ቀበሌ በጎ አድራጎት ወጣቶች በጋር በመተባበር አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የክረምት በጎ ፍቃድ ስራዎችን #በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ በሚል ለተማሪዎች ምቹ የት/ቤት አካባቢን ለመፍጠር የመማሪያ ክፍሎች እድሳት እና የተማሪዎች መቀመጫ ዴስክ ጥገና ስራ ተከናዉኗል ።
‎ 1️⃣2️⃣3️⃣🇪🇹🇪🇹📚📚📚
‎በት/ቤቱ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ-ግብር የማጠናከሪያ ትምህርት፣ የመማሪያ ክፍሎች እድሳት እና የተማሪዎች መቀመጫ ዴስክ ጥገና እየተከናወነ ስሆን ቀጣይ በሌሎች በጎ አድራጎት ስራዎች ለማስራት በእቅድ ተይዟል።
‎ ====--__--====
‎በበጎ አድራጎት ስራዎች የትምህርት ጽ/ቤት ማኔጅሜንት አባላት፣ በለሞያዎች፣ የዋንጋ ቀበሌ በጎ አድራጎት ወጣቶች እና የት/ቤት አመራሮች ተገኝቷል።

‎በመጨረሻም ለስራ ስኬት ጉልህ ሚና ለተወጡት አካላት ሁሉ ጽ/ቤቱ ምስጋና ያቀርባል።

በማኦ እና ኮሞ ልዩ ወረዳዉ የትምህርት ዘርፍ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎች ተጠናክሮ ቀጥሏል።‎         =====*++======‎(ቶንጎ፦ነሀሴ 13/2018 ዓ.ም) የማኦ እና ኮ...
20/08/2026

በማኦ እና ኮሞ ልዩ ወረዳዉ የትምህርት ዘርፍ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎች ተጠናክሮ ቀጥሏል።
‎ =====*++======
‎(ቶንጎ፦ነሀሴ 13/2018 ዓ.ም) የማኦ እና ኮሞ ልዩ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የክረምት በጎ ፍቃድ ስራዎችን የተማሪዎች ማጠናካሪያ ትምህርት ተጠናክሮ ቀጥሏል።

 . #የማኦ እና ኮሞ ልዩ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት የ2018ዓ.ም  #የክረምት ወራት በጎ አድራጎት የትምህርት ስራዎችን ለመፈጸም የተማሪዎች ማጠናካሪያ ትምህርት   መስጠት ተጠናክሮ ቀጥሏል። ...
18/08/2026

.
#የማኦ እና ኮሞ ልዩ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት የ2018ዓ.ም #የክረምት ወራት በጎ አድራጎት የትምህርት ስራዎችን ለመፈጸም የተማሪዎች ማጠናካሪያ ትምህርት መስጠት ተጠናክሮ ቀጥሏል።
‎ 📖📖📖📖🖍🖊🖋📖📖📖📖
‎በክረምት ወራት የትምህርት ስራዎች በዉጤታማነት ለመፈጸም አንደኛ ደረጃ ት/ቤት በተመረጡ መ/ራን በእንግልዘኛ፣ በሂሳብ እና በአካባቢ ሳይንስ ትምህርት ዓየነቶች የማጠናካሪያ ትምህርት በመስጠት የትምህርት ጥራት ችግሮችን ለማፍታትና ትውልድን በእውቀትና በሥነ ምግባር ለመገንባት እየተሰራ ይገኛል።
‎በቀጣይም በት/ቤቱ እና በሌሎች ት/ቤቶች የክረምት ወራት በጎ አድራጎት ስራዎች ተጠናክሮ ይቀጥላል።

fans

በማኦ እና ኮሞ ልዩ ወረዳዉ የትምህርት ዘርፍ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎች ተጠናክሮ ቀጥሏል።‎         =====***++**======‎(ቶንጎ፦ነሀሴ 6/2018 ዓ.ም) የልዩ ወ...
12/08/2026

በማኦ እና ኮሞ ልዩ ወረዳዉ የትምህርት ዘርፍ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎች ተጠናክሮ ቀጥሏል።
‎ =====***++**======
‎(ቶንጎ፦ነሀሴ 6/2018 ዓ.ም) የልዩ ወረዳዉ ትምህርት ጽ/ቤት፣ ከክልሉ ትምህት ቢሮ እና የልዩ ወረዳዉ አስተዳዳር ም/ቤት ጋር በመሆን በዌፄ ቀበሌ የክረምት በጎ ፍቃድ ስራዎችን አስጀምሯል ።

‎በልዩ ወረዳዉ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በትምህርት ዘርፍ አበረታች ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ ።

‎የክልሉ ትምህርት ቢሮ ከፍተኛ በለሞያ አቶ ስራጅ ኢብራሂም እንደገለጹት በ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሐ-ግብር በትምህርት ዘርፍ የማጠናከሪያ ትምህርት፣የትምህርት ቁሳቁሶች ድጋፍ፣ የአረንጓዴ አሻራ እና የአቅመ ደካማ ወላጆች ድጋፊ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑ ገልጾ በሌሎች ትምህርት ቤቶች ተጠናክሮ እንድያስቀጥሉ ጥሪ አቅርቧል።

‎የልዩ ወረዳዉ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ሀብቴ በበኩላቸዉ በበጎነት ክፍያ የማይጠየቅበት ነገር ግን የህሊና እርካታ የሚገኝበት ብሎም የሀገርን ከፍታ የሚያረጋግጥ ትልቅ ሀገራዊ ሀብት በመሆኑ በትምህርት ዘርፍ አበረታች ተግባራት መሆናቸዉ አስረተድቷል።

‎አክሎም የእሽሞሎ ድንበር ተሻጋር በጎ አድራጎት ማህበር ከትምህርት ጋር በመሆን አበረታች ስራዎች ስያከናወኑ ቆይተዉ አሁንም በጋራ ማስራት ባህላቸዉ አጠናክሮ ቀጥሏል ብሏል።

‎በመርሀግብሩም በዌፄ ቀበሌ የተማሪዎች ማጠናከሪያ ትምህርትን በማስጀመር የችግኝ ተከላ እና ለአቅመ ደካማ ሰብዓዊ ድጋፍ ተደርጓል ።

‎በመርሀ ግብሩ የልዩ ወረዳዉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የክልል ትምህርት ቢሮ ከፍተኛ ባለሙያዎች ፣የትምህርት ጽ/ቤት ማኔጅሜንት ኮሚቴ፣ የእሽሞሎ በጎ አድራጎት ወጣቶች፣ የቀበሌ አመራሮች፣ ተማሪዎች እና የቀበሌው ማህበረሰብ ተሳትፏል ።

ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ የሚተገበሩ 11 አዳዲስ የሙያ ዓይነቶችን ይፋ ሆኑ‼​የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በ11ኛ ክፍል ተግባራዊ የሚደረጉ 11 የሥራና ተግባር ...
11/08/2026

ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ የሚተገበሩ 11 አዳዲስ የሙያ ዓይነቶችን ይፋ ሆኑ‼

​የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በ11ኛ ክፍል ተግባራዊ የሚደረጉ 11 የሥራና ተግባር የሙያ ዓይነቶችን ይፋ በማድረግ፣ የክልልና የከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች የመምህራን ቅጥርን ጨምሮ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ መመሪያ አስተላለፈ።

​አዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ የሙያ ትምህርትን ለማካተት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት፣ በሁለተኛው ዙር ለሚተገበሩት በእነዚህ 11 የሙያ ዓይነቶች የመርሐ ትምህርት፣ የተማሪ ሞጁል እና የመምህራን መምሪያ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገልጿል።

​ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረጉት 11 የሙያ ዓይነቶች፦
📌​ብረታ ብረት ሥራ ቴክኖሎጂ
📌​አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ
📌​አልባሳት ቴክኖሎጂ
📌​ህንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋት
📌​ቧንቧ ስራ
📌​ሶፍትዌር ማበልጸግ
📌​ሰብል አመራረት
📌​ጤና ክብካቤ አገልግሎት
📌​ሆቴል አገልግሎት
📌​ፀጉር ሥራና ውበት አገልግሎት
📌​ምግብ ዝግጅት ናቸው። MoE

11/08/2026

Address

Asosa
Asosa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mao and Komo Special Woreda Educational Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category