14/09/2022
Economics
Bisness
14/09/2022
14/09/2022
በኢትዮጵያ 7 ትሪሊዮን ኪዪቢክ ጫማ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት መኖሩ ተረጋገጠ ዓለም አቀፍ ጥናቱ የኢትዮጵያን የመደራደር አቅም ያሳድገዋል ተብሏ
11/09/2022
🌀✅ በጨጓራ ህመም የምትሰቃዩ እህቶቼ እና ወንድሞቼ ካነበብኩት ምክር ይዤ መጣሁ!!!
✳ መንስኤ!!
1. ባክቴሪያ
2. ከፍተኛ አልኮል መጠጦችን መውሰድ
3. ለረዥም ጊዜ የሚወሰዱ አንዳንድ መድሃኒቶች
4. ከልክ ያለፈ መጨናነቅ
5. የመመገቢያ ሠአትን ጠብቆ አለመመገብ
✳ የጨጓራ ህመምን በቤት ውስጥ እንዴት ማከም እንችላለን?
1. ዝንጅብል!
አነስተኛ የዝንጅብል ክፍል ወስዶ ከምግብ በፊት መውሰድ የምግብ ልመትን ያፋጥናል በተጨማሪም የጨጓራ ባክቴሪያን ያክማል፡፡
2. እርጎ!
በባክቴሪያ ምክንያት ለሚከሠት የጨጓራ ህመም ተመራጭ ነው፡፡
3. ድንች!
ግማሽ ብርጭቆ የድንች ጁስን በቀን 3 ጊዜ ምግብ ከመመገብ 15 ደቂቃ በፊት መጠጣት።
4. ቆስጣ እና ካሮት!
የቆስጣ ጁስ እና የካሮት ጁስን በመደባለቅ መጠጣት።
5. ውሃ!
በቀን ከ8-10ብርጭቆ ውሃ መጠጣት።
6. በፆም ወቅት ፍሬሽ የሆኑ የፍራፍሬ ጁሶችን መጠቀም ለምሳሌ ወይን ብርቱካን አፕል ፓፓያ…
7. ብዙ ምግብ በአንድ ጊዜ አለመመገብ ምክንያቱም ብዙ ምግብ በአንድ ጊዜ መመገብ የምግብ ልመትን ስለሚያዘገይ ትንሽ ትንሽ ምግብ ሠአትን ጠብቆ መመገብ።
8. ሁል ጊዜ በባዶ ሆድ የሞቀ ውሃ መጠጣት።
9. በአንድ ገበታ ላይ የተለያዩ ምግቦችን አደባልቀው አለመመገብ።
10. ከመተኛቶ 2 ሠዓት በፊት እራት መመገብ።
11. በቫይታሚን ቢ12 እና አይረን የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ።
12. ሥጋና የስጋ ተዋፅዎ መቀነስ በተለይ ለእራት አለመጠቀም።
13. አልኮል ሲጃራና ጫትን አለመጠቀም።
14. ቡናና ሻይ መቀነስ።
15. ኬክ እና በፋብሪካ የተቀነባበሩ ምግቦችን አለመጠቀም።
16. በሀኪም ያልታዘዙ መድሀኒቶች አለመውሰድ።
17. ቅመማ ቅመም መቀነስ ናቸው።
መልካም ጤንነት!!
ምርጥ መጣጥፎች
#ሼርርርር ያድርጉት
"የልጆች የሳምባ ምች (ኒሞኒያ) ምንድነው?" - በዶ/ር ፋሲል መንበረ : የህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም
[ብርድ የሚባል በሽታ አለ ወይስ የለም?]
ብዙ ጊዜ እናቶች ልጄን ብርድ መታው እና በጣም ያስላል ይላሉ:: እውነት ብርድ የሚባል የልጆች በሽታ አለ? ይሄንን ጥያቄ ከመመለሳችን በፊት እስኪ ስለ ሳምባ ምች የተወሰነ ነገር ልበል::
ሳምባ ምች (ኒሞኒያ) ማለት የሳምባችን የታችኛው እና የመጨረሻው ክፍል መቆጣት እና መታመም ነው::
.
ሳምባችን ለሰውነታችን ኦክስጅን የሚባለውን ጠቃሚ አየር የምናስገባበት እና ካርቦንዳይ ኦክሳይድ የሚባለውን የተቃጠለ አየር የሚናስወግድበት አካላችን ሲሆን ይህ አካል ደሞ ኒሞኒያ በሚባለው በሽታ ሲጠቃ ሳምባችን ዉስጥ ያሉ ህዋሳት በከፍተኛ መጠን ስለሚቆጡ አየር የሚቀያየርበት የሳምባ ቅንጣት አካላት(Alveolus) በፈሳሽ ነገር ይሞላል በዚህም ምክንያት ሰውነታችን በቂ የሆነ ኦክስጅን አያገኝም:: የልጆች ሳምባ ደሞ በደምብ ያልዳበረ እና ጠባብ ስለሆነ በወቅቱ ካልታከመ እስከ ሞት ሊያደርስ ይችላል::
እንደ ዓለም የጤና ድርጅት (WHO) መረጃ መሰረት በ2017 ብቻ በዓለም ላይ 808,694 እድሜያቸው ከ 5 ዓመት በታች ያሉ ህፃናት በሳምባ ምች ምክንያት ህይወታቸውን አተዋል:: ይህም ከአጠቃላይ የልጆች ሞት 15% ይይዛል::
👉 ሳምባ ምች (ኒሞኒያ) መንስኤው ምንድነው?
ይህ በሽታ ብዙ ጊዜ በአይን በማይታዩ የበሽታ አምጭ ጀርሞች ማለትም በቫይረስ, በባክቴርያ, በፕሮቶዝዋ አልፎ አልፎም በፓራሳይት አማካኝነት ሊመጣ ይቻላል:: ከነዝህም ዉስጥ በአብዛኞቹ ጀርሞች በሳል ወይም በንጥሻ ወቅት በትንፋሽ የሚተላለፉ ናቸው:: ከነዚህ በሽታ አምጭ ጀርሞች በተጨማሪም ኒሞኒያ በተለያዩ ኬሚካሎችም ሊመጣ ይቻላል:: ለምሳሌ የጨጓራ አሲድ በድንገት ወደ ሳምባ ከገባ ኒሞኒያ ሊያስከትል ይችላል:: ከ5 ዓመት በታች ያሉ ልጆች ላይ የሳምባ ምች ብዙ ጊዜ መንስኤው ቫይረሶች ሲሆኑ የሚጀምረውም ከጉፋን መሰል ምልክቶች ነው::
🛑ልጆችን ለሳም ባምች(ኒሞኒያ) የሚያጋልጡ ነገሮች
1. የላይኛው የትንፋሽ አካላት ኢንፌክሽን ለምሳሌ ጉፋን፤ የቶንሲል ኢንፌክሽን እና የመሳሰሉት
2. ቤት ዉስጥ የሚጨሱ ማንኛዉም የጭስ አይነቶች ለምሳሌ የሲጋራ የከሰል እና የእንጨት ጭሶች በሀገራችን በከፍተኛ መጠን ብዙ ህፃናትን ለሳምባ ምች እያጋለጣቸው ይገኛል::
3. ዝቅተኛ የበሽታ መከላከል አቅም(በምግብ እጥረት ወይም በተለያዩ በሽታዎች ምክንያት)
4. በጣም ተጠጋግቶ መኖር እና በቂ የሆነ የአየር ዝውውር በሌለበት ቤት እና አካባቢ መኖር
5. የሳምባ የተፈጥሮ ችግሮች
6. የቫይታሚን ዲ እጥረት(ሪኬትስ)፦ በተለይ ፀሐይ በደምብ ያልሞቁ ህፃናት ለሳምባ ምች ተጋላጭ ናቸው::
ምልክቶቹ ምንድናቸው?
➡️ ቶሎ ቶሎ መተንፈስ
➡️ ትንፋሽ ማጠር እና ለመተፈስ መቸገረ
➡️ ትኩሳት
➡️ ማቃሰት
➡️ ትውከት
➡️ የደረት ውጋት ወይም ህመም
➡️ ህፃናት ሲተነፍሱ የታችኛው ደረት ክፍል ወደ ዉስጥ ግብት ግብት ማለት ናቸው::
🛑 ልጆት ላይ እነዚህ የተጠቀሱት ምልክቶች ካሉ ባፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም መውሰድ እና ማሳከም ይኖርቦታል::
🛑 ልጆች ሳምባምች(ኒሞኒያ) እንዳይዛቸው ምን እናድርግ መከላከያ መንገዶችስ ምንድናቸው?
📌ክትባት
📌ቤት ዉስጥ ማንኛዉም ጭስ አለማጨስ
📌 ቤት ዉስጥ በቂ የ አየር ዝውውር እንዲሮር ማድረግ
📌የተመ ጣ ጠ ነ ምግብ መመገብ
📌 እስከ 6 ወር ያሉ ህፃናት የእናት ጡት ወተት ብቻ እንዲወስዱ ማድረግ
📌ልጆች የፀሀይ ብርሃን በበቂ ሁኔታ እንዲያገኙ ማድረግ
📌ልጆችን ጉፋን ከያ
07/09/2022
The Health Benefits of Peanuts New research has just been published about peanuts and their health benefits. The study indicates that peanuts aid weight loss.
07/09/2022
07/09/2022
04/09/2022
በመተከል ዞን ወንበራ ወረዳ መነሲቡ ቀበሌ የቡና ምርት
አንድ ሰው ሲመክረኝ "የቤተሰቦቼ ጊቢ ውስጥ አንድ ክፍል ቤት ሰርቻለሁ፤ ኮንደሚኒየም ቤት ደርሶኝ እዳውን ለመክፈል ብዙ ቢቀረኝም ለማደስ የሚስቴ ወንድም እያገዘኝ ነው!" አለኝ "እና ለልጆች አንድ ቋሚ ነገር ለማድረግ መጣር ግድ ነው ሲል ሊመክረኝ ሞከረ!
እድልን ተሞርኩዞ እንደ ውጤታማ ትጉ ሰው ሌሎችን ለመምከር መሞከር ሙሉ አይደለም!
የቤተሰቡ ግቢ ያለው ቤት ካኮረፉት የሚያባርሩት! በእድል እጁ የገባው ኮንደሚኒየም ቤት እዳውን ከፍሎ መጨረስ ካለመቻሉ በተጨማሪ ለዓመታት ለማደስ እንኳን የሚስቱን ወንድም ችሮታ እየጠበቀ ነው።
ውጤታማነት መለኪያው የተዛባ መሆን የለበትም! እድል አንድ ጥሩ ነገር ነው (ግን እሴት ካልተጨመረበት ለሌሎች እንደ ብቃት ሊቆጠር አይችልም) በተመሳሳይ ካደረጉት ባልተናነስ ያደርጉት የነበረን ክፍተት ማየትም ተገቢ ነው!
ባጠራቀመው 300ሺ ብር Ph.D የሰራ ሰው እና ባጠራቀመው 300ሺ ብር ገጠር ላይ መሬት የገዛ ሰው ለተሞክሮ ቢቀመጡ ስለሆነ ጥረት ስለተጨመረ እድል ሊለዋወጡ ይችላሉ።
በርግጥ በኢኮኖሚክስ አስተምሮት ውስጥ ይዞ መገኘት እንጂ ይዘው የተገኙበት መንገድ ዋጋ የለውም! ብዙ አትርፍ እንጂ ህጋዊ መንገድ ተከትለህ ተገቢውን ብቻ መጠን አትርፍ የሚል ግልፅ መርህ የለም!
በሎተሪ እድል 10 ሚሊየን ብር ያገኘ ሰው እድለኛ ነው! ነገር ግን ውጤታማ የሚሆነው ገንዘቡን ማባዛት ሲችል ነው! ስለዚህ ሌሎችን መምከር መጀመር ያለበት ያገኘሁትን ብር እዚህ ደረጃ ላይ አደረስኩት እያለ መሆን አለበት።
ስኬት ዘርፈ ብዙ ነው! ሰዎች ህይወትን የሚጀምሩት እኩል ላይሆን ይችላል (የሃብታም ልጅ ከውርስ ቢነሳ እና የድሃ ልጅ ታናናሽ ወንድሞችን ከማሳደግ ቢጀምር እንደማለት ነው) ስለዚህ ውጤታማነት አሳማኝ እንዲሆን በየአጋጣሚው የሚያገኙት እድል ላይ የጨመሩትን ውስን ጥረት ማሳየት አለበት ባይ ነኝ።
01/09/2022
Image: Project Management Process Groups Found on Google from pmwares.com
01/09/2022
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the school
Telephone
Website
Address
Asosa