Rehomed Primary &Medium School

Rehomed Primary &Medium School

Share

Quality is the symbole of Us

Photos from Benishangul Gumuz Education Bureau's post 06/07/2025
02/07/2025

📢📢📢
ውድ የትምህርት ቤታችን ወላጆች፤ተማሪዎችና ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች ሰላም ለእናንተ ይሁን እያልን!!!
🌿 🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
የ2017 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የመዝጊያ ፕሮግራም በቀን 29/10/2017 ዓ.ም የአሶሳ ከተማ አስተዳድር(መዘጋጃ)አዳራሽ ይካሄዳል::ስለሆነም ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች፣ወላጆችና ተማሪዎች በተጠቀሰው ቀን 2:30 ተገኚታችሁ የፕሮግራሙ ተሳታፊ እንድትሆኑ በአክብሮት ተጋብዛችኋል🙏🙏🙏

Photos from Rehomed Primary &Medium School's post 08/03/2025

በዛሬው ዕለት ርሆሜድ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፤ እንዲሁም አፀደ ህፃናት ጭምር ከወላጆች ጋር አንድ ለአንድ ውይይት ተካሂዷል።
‎
‎ ርሆሜድ ት/ት ቤት በዋናነት በትምህርት ዓመቱ መግቢያ ላይ ተማሪዎች ያስቀመጡትን ግብ ለመገምገም፣ በተጨማሪም የተማሪው ዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ በጥልቅ ለመወያየት የወላጅ እና የመምህራን አንድ ለአንድ ውይይት አዘጋጅቶ ነበር።
‎
‎ዝግጅቱም ከ2:30 እስከ 6:30 የቆየ ሲሆን በመምህራን በተዘጋጀ የተማሪዎች ጠንካራ እና ደካማ ጎን ፕሮፋይል (profile ) ከወላጆች ጋር ጥልቅ ወይይት ተካሂዷል።
‎
‎በተማሪዎች ፕሮፋይል (Students profile) ተማሪዎች በትምህርት ዓመቱ በትምህርት ቤቱ የነበራቸው ጠንካራ ጎኖች፣ ደካማ ጎኖች፣ እንዲሁም ባህሪያቶች ከእያንዳንዱ መምህራን ተሰብስቦ የተቀመጠበት ሲሆን በተጨማሪም በቅጹ ላይ ተማሪው መሻሻል የሚገባው ነገሮች፣ ከቤት የሚያሳያቸው ልዩ ልዩ ባህሪያቶች ለመመዝገብ የወላጅ አስተያየት ቦታም የተካተተበት ነው።
‎
‎በነበረው ወይይትም ስለእያንዳንዱ ተማሪ ልዩ ልዩ ጉዳዮች የተነሱበት ሲሆን በቀጣዩ ትምህርት ቤቱ እና ወላጆች በመናበብ ሀላፊነት የሚወስድ ያቀደውን የሚያሳካ ወይም ከግብ የሚያደርስ ትውልድ ለመፍጠር ወሳኝ እንደሆነ እንደሚያስችል በመተማመን ነው ውይይቱ የተካኸደው።
‎
‎
‎ርሆሜድ የዕውቀት ማዕድ!!
‎

Photos from Rehomed Primary &Medium School's post 24/12/2024

እንኳን ደስ አላችሁ!!
‎
‎ለርሆሜድ ትምህርት ቤት ማህረሰብ በሙሉ!!
‎
‎
‎ስራችን አፍ አውጥቶ ብቻውን ይናገራል።
‎
‎ርሆሜድ ትምህርት ቤት በ'እኛ መልቲ ሚድያ' አስተባባሪነት በመላው አሶሳ ውስጥ በሚገኙ የመንግስት እና የግል ት/ቤቶች በተደረገ የ3ኛ እና የ5ኛ ክፍል የጥያቄ እና መልስ ውድድር በአንደኝነት አጠናቅቋል።
‎
‎ውድድሩ በጣም ከፍተኛ ፉክክር የታየበት ሲሆን ርሆሜድ ትምህርት ቤት በሁለቱም የክፍል ደረጃዎች ማለትም፤ ከሶስተኛ ክፍል ተማሪ ሀዩ ሰለሞን የወርቅ ሜዳልያ፤ ከ5ኛ ክፍል ተማሪ ሳሮን ሽባባው በሚያስደንቅ ብቃት አንደኛ በመውጣት ለትምህርት ቤታቸው የወርቅ ሜዳልያ አስገኝተዋል።
‎
‎በተጨማሪም በተደረጉ የተለያዩ የስፖርት ውድድሮች የትምሀርት ቤታችን ተማሪዎች 1 የወርቅ 4 የብር እና 3 የነሐስ ሜዳልያዎችን በጥቅሉ 8 ሜዳሊያዎችን ለትምህርት ቤታቸው በማስገኘት ውድድሩን ከተሳተፉ ትምህርት ቤቶች ከፍተኛውን የሜዳልያ ቁጥር የግላቸው ማድረግ ችለዋል።
‎
‎ይህ ውድድር ርሆሜድ ትምህርት ቤት በምን አይነት አቋም ላይ እንደሚገኝ ማሳያ ከመሆኑም በተጨማሪ የስራው እና የትጋቱ ውጤት ነው ተብሏል።
‎
‎ርሆሜድ ትምህርት ቤት የትምሀርት ጥራት እና የተማሪዎችን ስነ-ምግባር መርህ አድርጎ የሚከተል በመሆኑ ውጤቱ ከእሱ እንደሚጠበቅ የሚያምን ቢሆንም አቅዶ ማሳካት ደግሞ ሌላኛው ስኬት ነውና ለዚህ ስኬት ባለድርሻ አካላትን ማለትም መምህራን ወላጅ የትምህርት ቤቱ ባለቤቶች እንዲሁም በውድድሩ ተሳትፈው ማሸነፍ የቻሉትን ጀግና ልጆቹን በትልቁ ሊያመሰግን ይፈልጋል።
‎
‎
‎ርሆሜድ የጥራት ምልክት!!
‎ጥራት ያለው ት/ት ለሁሉም!!
‎ርሆሜድ!!
‎
‎
‎
‎

Photos from Rehomed Primary &Medium School's post 08/12/2024

‎በርሆሜድ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት እና ውይይት በአሶሳ ከተማ አስተዳደር አዳራሽ ተካሂዷል።
‎◌◌◌◌◌
‎
‎በርሆሜድ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት እና ውይይት መምህራን፣ የት/ት ቤቱ ር/መምህር፣ የት/ት ቤቱ ባለቤቶች እና የተማሪ ወላጆች በተገኙበት በድምቀት በአሶሳ ከተማ አስተዳደር አዳራሽ ተካሂዷል።
‎
‎
‎ውይይቱ በትምህርት ቤቱ ባለቤት በአቶ ሰለሞን የመክፈቻ ንግግር ተደርጎ የተከፈተ ሲሆን፣ አቶ ሰለሞን ትምህርት ቤቱ እያበረከተ ያለውን ዘርፈ ብዙ አስተዋፅዖ በማተት የትምህርት ስራ ትውልድ የማዳን ስራ መሆኑን እንዲሁም ብዙ ተጨማሪ አንኳር እና ገንቢ ሀሳቦችን አንስተዋል።
‎
‎በንግግሩም ፤ የትምህርት ስራ የሁሉም ማህበረሰብ ሀላፊነት እንደመሆኑ ትውልድ በመገንባቱ ሂደት ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንደሚገባ በአንክሮ አሳስበዋል።
‎
‎
‎በመቀጠል የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር የሆኑት አቶ አዲሱ ጋሻው የሩብ ዓመት ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በተያዘው 2017 የትምህርት ዘመን፤ ምንም እንኳን ትምህርት ቤቱ የሶስት ዓመት ዕድሜ ቢኖረውም ከአንጋፋ ትምህርት ቤቶች መሳ ለመሳ መቆም የቻለ ብሎም በስነምግባራቸው እና በትምህርት አቅማቸው የተሻሉ ልጆችን ማፍራት እየቻለ መሆኑን ገልጿል።
‎
‎ርሆሜድ ፩ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤ/ት ዕውቀት እና የተማሪ ስነ-ምግባር መርህ አድርጎ እየተንቀሳቀሰ በመሆኑ ይኸን ዓላማ ለማሳካት ዘርፈ-ብዙ ስትራቴጂዎች እና ቴክኒኮችን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝና በዚህም አመረቂ ውጤት እንደተመዘገበ በሪፖርቱ አንስቷል።
‎
‎
‎ከውጤቶችም ርሆሜድ ት/ት ቤት በሚሳተፍባቸው የክላስተር ውድድሮች ሁሉ የተሻለ ውጤት የሚያስመዘግብ እንዲሁም አምና ባስፈተናቸው የስምንተኛ ክፍል ብሔራዊ ተፈተኞች በክልል ደረጃ የተሻለ ውጤት የተመዘገበበት መሆኑን ገልፀዋል።
‎◌
‎
‎ከሪፖርት በተጨማሪ በቀጣይነት ሊሰሩ ስለታሰቡ በተለይም የ8ኛ ክፍል ብሐራዊ እና የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ልጆችን ለፈተናው ዝግጁ ከማድረግ አንፃር ወላጅ ከመምህራን ጎን በመሆን እና በመናበብ መስራት እንደሚገባቸው ለወላጆች በአደራ ጭምር መልዕክት አስተላልፈዋል።
‎
‎በመቀጠልም ወላጆች በትምህርት ቤቱ ባለፍት ሶስት የትምህርት ወራት ስለነበረው ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች እንዲሁም በቀጣይነት ቢደረጉ ብለው ስላመኑባቸው ጉዳዮች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
‎
‎በአስተያየታቸው ብዙ ገንቢ ሃሳቦች የተነሱ ሲሆን ልብ በሚያሞቅ መልኩ በትምህርት ቤቱ ደስተኞች እንደሆኑና በቀጣይነትም ከመምህራን ጋር በማበር የተሻለ ጎበዝ፣ ንቁ እና መልካም ስነ-ምግባር የተላበሱ ተማሪዎችን ለማፍራት መጠንከር እንደሚገባ አንስተዋል።
‎
‎ርሆሜድ ት/ት ቤት!!
‎ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም!!

Photos from Rehomed Primary &Medium School's post 30/11/2024

በትናንትናው ዕለት ማለትም አርብ 20,2017 ዓ/ም በርሆሜድ አንደኛኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ት ቤት ለ19ኛጊዜ የሚከበረውን ሀገራዊ የብሔር ብሔርሰቦች በዓል በድምቀት ተከብሯል።

በዓሉም ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሄ
ራዊ አንድነት በሚል ሀገራዊ መሪ ቃል የተከበረ ሲሆን ዝግጅቱ በት/ት ቤቱ ርዕሰ መምህር በሆኑት አቶ አዲሱ ጋሻው የመክፈቻ ንግግር የተጀመረ ሲሆን በፕሮግራሙ ላይ በተማሪዎች የተለያዩ ግጥሞች፣ መነባነቦች እና ጭውውቶች ቀርበዋል።

በትምህርት ቤቱ ከተለያዩ ማህበረሰብ ከተለያዩ ብሔረሰብ እንዲሁም እምነት የመጡ ተማሪዎች በመቻቻል በንፁህ አንድነት የሚኖሩ መሆናቸውን በተለያዩ ዝግጅቶች አሳይተዋል።

ከዝግጅቱም በተጨማሪ ተማሪዎች በለበሱት ያሸበረቀ ማንነት ገላጭ አለባበሳየው አምረው እና ተውበው በየምርጫቸው ማንነታቸውን በኩራት ያሳዩበት ቀን ሆኖ ተከብሯል።

በርሆሜድ ሁሉም እኩል ሁሉም ውብ ነው።

ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም!!

Photos from Rehomed Primary &Medium School's post 30/11/2024

ባሳለፍነው ሀሙስ በገመሃሩ ክላስተር ስር ባሉ የመጀመሪያ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ት ቤቶች መካከል በተደረገ ውድድር የርሆሜድ መጀመሪያ ደረጃ ት/ት ቤት ውድድሩን በበላይነት አጠናቅቋል።

ውድድሩ የተካኸደው በስድስተኛ እና የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሆን ከርሆሜድ ትምህርት ቤት የስምንተኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ተማሪ ኤልዳና ደመቀ አንደኛ በመሆን፣ ከስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች ደግሞ ተማሪ የአብስራ ደሳለኝ አንደኛ በመሆን ውድድሩን በመጀመሪያነት አጠናቅቀዋል።

የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ውድድሩ ጥሩ እንደነበረ እና በተማሪዎች ውጤት ደስተኛ ቢሆንም በቀጣይነት ከዚህ የበለጠ በመስራት በመሰል ውድድሮች ከዚህ የበለጠ እንደሚያስመዘግቡ በመናገር አክለውም ይኸን ውድድር ያዘጋጀው የገመሃሩ ክላስተርን እጅግ አመስግነዋል።

በውድድሩ የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ጥሩ ማስመዝገባቸው ለቀጣይ የክልላዊ ፈተና ተማሪዎች በጥሩ ሁኔታ እየተዘጋጁ መሆኑ እና የትምህረት ቤቱ መምህራን በጋራ በመረባረብ ተማሪዎች ላይ እየሰሩ መሆኑን ያሳየ ቢሆንም ውጤቱ ሳያዘናጋ ጥረታቸውን እንዲቀጥሉበት ወላጅም ከልጆች ጎን በመሆን እንዲከታተሉ የት/ት ቤቱ ርዕሰ መምህር በአፅንኦት አሳስበዋል።

ርሆሜድ ት/ት ቤት!!
ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም!!

Photos from Rehomed Primary &Medium School's post 16/11/2024

በ2017 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ባሳለፍናቸው 'ቅዳሜ የዕረፍት ቀናት' ለስምንተኛ እና ስድስተኛ ክፍል ክልላዊ ተፈተኞች የማጠናከሪያ ትምህርት በትምህርት ቤቱ መምህራን ከፍተኛ ዝግጅት ተደርጎ እየተሰጣቸው ይገኛል።

እንደምናስታውሰው በ2016 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ርሆሜድ ትምህርት ቤት ከፍተኛ ውጤት በማምጣት በስኬት የተጠናቀቀ ዓመት ነበር።

ይህ ስኬት ሊመዘገብ የቻለው ሁሉም ባለድርሻ አካላት በመናበብ እና በተለየ ትኩረት በመስራቱ ስለሆነ በዘንድሮ ዓመትም የተሻለ ወይም ተመሳሳይ አስደሳች ውጤት ለማምጣት ወላጆች ከትምህርት ቤቱ ጎን በመቆም እና በመናበብ ልጆችን በማስጠናት፣ በመምከር እንዲሁም በተለያዩ መንገዶች እንዲያግዟቸው ትምህርት ቤቱ ከወዲሁ ሊያስታውስ ይፈልጋል።

በተጨማሪም እንሚታወቀው ቅዳሜ የዕረፍት ቀናት ማጠናከሪያ ትምህርት በተለየ አሰጣጥ የሚሰጥ በመሆኑ ማለትም ዋና ትኩረቱ ለክልላዊ ፈተና ማዘጋጀት በመሆኑ ተማሪዎች የተለያዩ ጥያቄዎችን በመስራት የሚለማመዱበት ነው፤ በዚህ ቀን ተማሪዎች ተዘጋጅተው እንዲገኙ የወላጆች ድጋፍ ስለሚያስፈልግ እንዲከታተሏቸው እንላለን።

ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም!!!

ርሆሜድ!!

Photos from Rehomed Primary &Medium School's post 19/10/2024

የት/ቤታችን ሳምንታዊ ዋና ዋና ክንውኖች የሚያሳይ ፎቶ

Photos from Rehomed Primary &Medium School's post 18/09/2024

እንኳን ደስ አላችሁ!!! ለት/ቤታችን ማህበረሰብ በሙሉ!!!! ይህ ለርሆሜድ ትምህርት ቤት የድል ዜና ነው።

በርሆሜድ ት/ቤት የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የክልሉ ሁለተኛ ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል። በትሁት ባህሪዋ እና በጉብዝናዋ ትጠበቅ የነበረችው ተማሪ ፌቨን ሰለሞን የክልላዊ ፈተና 93 አማካይ ውጤት እና 99.99 ፐርሰንታይል በማምጣት ከክልሉ ተማሪዎች ሁለተኛውን ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ት/ት ቤቷን፣ እና ወላጆቿን አኩርታለች።

ምንም እንኳን የክልሉ ማለፊያ ነጥብ 45 አማካይ ውጤት ቢሆንም፣ ርሆሜድ ት/ቤት ካስፈተናቸው ተማሪዎች 95% ተማሪዎችን የሀገር አቀፍ ማለፊያ ነጥብ ማለትም ከ50 አማካይ በላይ ማምጣት ችለዋል

እንደሚታወቀው ት/ት ቤቱ ከተመሰረተ ገና ሁለት ዓመት እንደመሆኑ ከተለያዩ ት/ት ቤቶች የተለያየ ዕውቀት ይዘው የተሰባሰቡት ተማሪዎችን አብቅቶ ያስፈተነ እንደ መሆኑ በሁሉም ባለድርሻ አካላት ያላሰለሰ ጥረት ይኸን ውጤት መመዝገብ መቻሉ ት/ት ቤቱን ልዩ ያደርገዋል።

ይህ ውጤት ሊመዘገብ የቻለው በመምህራን፣ በወላጆች፣ በት/ት ቤቱ ባለቤቶች እንዲሁም በከተማ አስተዳደሩ ት/ት መምሪያ በጎ እገዛ በመሆኑ ርሆሜድ ት/ቤት ሁላችሁንም እንኳን ደስ አላችሁ ይላችኋል።

Photos from Rehomed Primary &Medium School's post 28/05/2024

ባሳለፍነው ቅዳሜ በገመሃሩ ክላስተር ስር ባሉ ስድስት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ት ቤቶች መካከል በተደረገ ውድድር ከስድስት ተሸላሚ ተማሪዎች መካከል ሶስቱን በማሸለም የርሆሜድ አንደኛና መካ/ ደረጃ ት/ት ቤት ውድድሩን በበላይነት አጠናቅቋል።

ውድድሩ የተካኸደው በአራተኛ እና የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሆን ከርሆሜድ ትምህርት ቤት የስምንተኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ተማሪ ፌቨን ሰለሞን አንደኛ በመሆን፣ ተማሪ ናናት ሰሎሞን ደግሞ ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ ውድድሩን አጠናቅቀዋል። ከአራተኛ ክፍል ተማሪዎች ደግሞ ተማሪ ኢክራም ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ ውድድሩን አጠናቅቃለች።

የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ውድድሩ ጥሩ እንደነበረ እና በተማሪዎች ውጤት ደስተኛ ቢሆንም በቀጣይነት ከዚህ የበለጠ በመስራት በመሰል ውድድሮች ከዚህ የበለጠ እንደሚያስመዘግቡ በመናገር አክለውም ይኸን ውድድር ያዘጋጀው የገመሃሩ ክላስተርን እጅግ አመስግነዋል።

በውድድሩ የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ጥሩ ማስመዝገባቸው ለቀጣይ የክልላዊ ፈተና ተማሪዎች በጥሩ ሁኔታ እየተዘጋጁ መሆኑ እና የትምህረት ቤቱ መምህራን በጋራ በመረባረብ ተማሪዎች ላይ እየሰሩ መሆኑን ያሳየ ቢሆንም ውጤቱ ሳያዘናጋ ጥረታቸውን እንዲቀጥሉበት ወላጅም ከልጆች ጎን በመሆን እንዲከታተሉ የት/ት ቤቱ ርዕሰ መምህር በአፅንኦት አሳስበዋል።

Photos from Rehomed Primary &Medium School's post 04/04/2024

በርሆሜድ ትምህርት ለትምህርት ቤቱ መምህራን ከፍተኛ ልምድ ባካበቱ ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል።

°°°°°°

በርሆሜድ ትምህርት ለትምህርት ቤቱ መምህራን ከፍተኛ ልምድ ባካበቱ ባለሙያዎች ልዮ ፍላጎት የሚሹ ተማሪዎችን በምን አይነት መንገድ ሊያግዙ እንደሚችሉ እና እንዴት እንደሚያግዙ እንዲሁም ስምንተኛ ክፍል ብሔራዊ ተፈታኝ ተማሪዎችን እንዴት ማዘጋጀት እንደሚገባቸው ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል።

በትምህርት ቤቱ ጋባዥነት ስልጠና የሰጡት ባለሙያዎችን አቶ ያደታ በቀለ የገመሀሮ ሪሶርስ ማዕከል ተጠሪ ;ወ/ሮ ዘሪቱ ምህረቱ የአሶሳ 1ኛ/መ/ደ/ ሪሶርስ ማዕከል ሴንተር እና አቶ አሸናፊ ፍቃዴ የአሶሳ ከተማ አስ/ት/መምሪያ የልዩ ፍላጎት ባለሙያ ትምህርት ቤቱ ከልብ እያመሰገነ መምህራን የተሰጣቸውን የክህሎት እና ተግባራዊ ስልጠና ወደ ስራ እንደሚያስገቡ ነው የተናገሩት።

የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ስልጠና የሰጡት ባለሙያዎች በራሳቸው ተነሳሽነት ያለማንም ውጫዊ ግፊት ትውልድ ለማነፅ በማሰብ ላሳዩት በጎ ምላሽ መመስገን እንደሚገባቸው ተናግረዋል። በተጨማሪም፣ ተማሪዎቻችን የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጎች በመሆናቸው ሌሎችም በተለያዩ ስራ ሂደት ውስጥ ክህሎት እና ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች በተለያየ መንገድ እንዲህ ቢያግዙ መልካም እንደሚሆን እና ጥሩ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ነው አበክረው የተናገሩት።

መምህራንም በበኩላቸው ስልጠናው ከስነልቦና እስከ ምልክት ቋንቋ የዘለቀ በመሆኑ ብዙ ግንዛቤዎችን እንዳገኙ እና በዚህም ጥሩ ለውጥ ማምጣት እንደሚችሉ ነው የተናገሩት።

Want your school to be the top-listed School/college in Asosa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Website

Address

Near To World Vission
Asosa