Meba Tube

Meba Tube

Share

Please follow Us in YouTube
Link
https://youtube.com/@mebatube1621

26/03/2026

ይህንን ያዉቁ ኖሯል???

24/03/2026

Machine learning

29/11/2025



"ጽዮን" ማለት "ጸወን አምባ፣ መጠጊያ" ማለት ነው:: ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም፣ ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል፡፡

ኅዳር ፳፩ ቀን በታቦተ ጽዮን የተፈጸሙ ታላላቅ ተአምራት የሚታሰቡበት ቀን ነው፡፡ በዚህ ቀን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የታቦተ ጽዮንን ተአምራት እግዚአብሔር ቃል ቅድስት ድንግል ማርያምን ታቦቱ አድርጎ ከፈጸማቸው ታላላቅ የድኅነት ሥራዎች ጋር በማነጻጸር እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በነገረ ድኅነት ውስጥ ያላትን ድርሻ በስፋት ታስተምራለች፡፡

እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን!

#ኅዳር #ጽዮን

17/11/2025
17/11/2025

PIN stands for
A. Private Inistitution Number
B. Personal Identification Number
C. Personal Imstitutional Node
D. Private international Number

12/11/2025

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Melke Man, Kasahun Danjile, Haimi Ye Mariam, Habtishe Harko

10/11/2025


የልብህን ቁስል ትተው የደረትህን ንቅሳት ያደንቃሉ... የጭንቅላትህን ዋጋ በገዛኸው ኮፍያህ ዋጋ ይተምኑሃል...ጫማ ከሌለህ እግርህ አይታይም... መከራ ተሸክሞ ሲኖር ያላዩትን ትክሻ ኮት ሲለብስ ያጨበጭቡለታል... ታሪክህን ጨርቅህ ላይ...ስምህን ልብስህ ላይ ለማንበብ ይሽቀዳደማሉ...
ጀግና ማለት ታግሎ የጣለ ሳይሆን ነው።
ወንድሜ ሆይ ሁሌም ...!
የምትወድቀው ሌላውን ለመጣል የሞከርክ ቀን ነው...ሌላውን ለመምሰል የሞከርክም ቀን ነው... ሌላው የሚያስበውን የሚያየውን የሚሠራውን መሥራት ከጀመርክ እውነትም ያኔ መውደቅ ትጀምራለህ።
እናም ወዳጄ #ሁሌም ከፈጣሪህ ጋር ራስን መሆን ራስን መምሰልን የመሰለ ነገር የለም።
መልካም ቀን!
#ካነበብኩት

06/11/2025

ሩሲያ ወላጆች የልጆቻቸውን እንቅስቃሴ መከታተል የሚችሉበትን ሲም ካርድ ይፋ አደረገች
*******

ወላጆች የልጆቻቸውን እንቅስቃሴ መከታተል የሚችሉበት ሲም ካርድ ይፋ መደረጉን የሩሲያ ዲጂታል ልማት፣ ኮሙኒኬሽን እና መገናኛ ብዙኃን ሚኒስትር ማክሱት ሻዳዬቭ አስታውቀዋል።

ሲም ካርዱ የሕፃናት ደኅንነትን ለመጠበቅ ታስቦ የተዘጋጀው ነው ተብሏል።

በተጨማሪም ሲም ካርዱ ከ14 ዓመት በታች የሆኑ አዳጊዎች ተገቢ ያልሆኑ የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ይዘቶችን እና የማይመከሩ ድረ-ገጾችን ማየት እንዳይችሉ የሚገድብ እንደሆነም ተገልጿል።

ወላጆች ሲም ካርዱ የሚልክላቸውን መረጃ ተጠቅመው ያለ ፍርድ ቤት ፈቃድ ልጆቻቸው ያሉበትን ቦታ ማወቅ እንደሚችሉም ተመላክቷል።

ሲም ካርዱ የሚሰጠው በወላጆች ፈቃድ ብቻ መሆኑን የዘገበው ቻይና ኒውስ ነው።

ይሁንና ወላጆች የልጆቻቸውን የእንቅስቃሴ መረጃ የሚከታተል ሌላ አካል ከፈለጉ በራሳቸው ፈቃድ ኃላፊነቱን መስጠት ይችላሉ ተብሏል።

05/11/2025

ትራፊክ ባለሙያዎችን ስራ የሚያሳጣ ፈጣን ሮቦት ስራ ጀመረ!

የ1 ሜትር ከ80 ሳ.ሜ ቁመት ያለው ትራፊኩ ሮቦት ዛሬ በይፋ
በቻይና ዤጂያንግ ግዛት፣ ቶንግሺያንግ ከተማ አንድ የትራፊክ ተቆጣጣሪ ሮቦት በይፋ ሥራውን ጀምሯል ይህ በዲህ እንዳለ
ሥራውን መጀመሩን ተከትሎ የቶንግሺያንግ ከተማን የትራፊክ እንቅስቃሴ በማሳለጥ ላይ ይገኛል።

አቅጣጫዎችን እና የተለያዩ የመንገድ ትራፊክ ምልክቶችን እንዲረዳ ተደርጎ የተፈበረከው ሮቦቱ የከተማዋን የትራፊክ ፍሰት በተገቢው መንገድ በመረዳት ሥራውን በአግባቡ እያከናወነ እንደሚገኝ ተገልጿል።

Want your school to be the top-listed School/college in Arba Minch'?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

http://www.YouTube.com/@MebaTube1621

Address

Arba Minch'