Laha Construction And Industrial College

Laha Construction And Industrial College

Share

በጎፋ ዞን የመሎ ከዛ ወረዳ ላሃ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኮሌጅ

Photos from Laha Construction And Industrial College's post 20/11/2025

በላሃ ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ ዓለም አቀፍ የኢንተርፕሪነርሽፕ ሳምንት በዓል በድምቀት ተከብረ።
‎=========================
ላሃ 11/03/2018ዓ/ም

‎የማናጅመንት አባላት የአስተዳደር ሰራተኞች አሰልጣኞች እና ሰልጣኞች በበዓሉ ታድመዋል።

‎ስለ ዓለም አቀፍ የኢንተርፕሪነርሽፕ ቀን ማብራሪያና ስለ ኢንተርፕሪነርሽፕ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጥቷቸዋል።

‎የአለም አቀፍ የኢንተርፕሪነርሺፕ ሳምንት ኢትዮጵያ ብራዚልን በመብለጥ መሪ ተደርጋ መመረጧ ይታወቃል።

Photos from Laha Construction And Industrial College's post 18/10/2025

እንኳን ለአድሱ የሥልጠና ዘመን በሰላም አደረሰን!!
‎የ2018 ዓ.ም የቴክኒክ እና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ።

‎በ2018 ዓ.ም ወደ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ የተደረገ ስሆን በዚሁ መሠረት ኮሌጃችን አድስ ሠልጣኝ ቅበላ ከዚህ ቦኋላ የምጀምር መሆኑን እናሳውቃለን።

‎ #ብቁና ተነሳሽነትን የተላበሰ ዜጋ እንፈጥራለን!!
‎ ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም

Photos from Laha Construction And Industrial College's post 24/06/2025

የቅጥር ማስታወቂያ |👇👇👇👇👇👇👇👇

የላሃ ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ በተለያዩ ዲፓርትመንት
ባለው ክፍት የስራ መደብ አሰልጣኝ መምህራን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታ የምታሟሉ አመልካቾች እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኃል፡፡

ምዝገባ:- እስከ 17/10/2017 እስከ 30/10/2017ዓ/ም
ፈተና የሚሰጥበት ቀን 01/11/2017 ዓ/ም ከጥዋቱ 3፡00 ስዓት
የምዝገባና የፈተና ቦታ:- የላሃ ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ ግብ
* በአካል ቀርባችሁ መመዝገብ የማትችሉት በማስታወቂያው ላይ የተጠየቁ ዶክመንቶችን በመላክ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

Photos from Laha Construction And Industrial College's post 07/06/2025

በላሃ ከተማ አስተዳደር የላሃ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ የ2017 በጀት ዓመት የ11 ወራት የስራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ አካሄደ

ላሃ ፣ ግንቦት 30/2017

በጎፋ ዞን ላሃ ከተማ አስተዳደር የላሃ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ የኮሌጁ የ2017 በጀት ዓመት የ11 ወራት የስራ አፈጻጸም ግምገማ አካሂዷል ።

የኮሌጁ ዋና ዲን የ11 ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡ ስሆን በሁሉም ዲፓርትመንቶች ታቅደው በተከናወኑ ዝርዝር ተግባራት ፣ የተመዘገቡ ውጤቶች ፣ ያጋጠሙ ችግሮች ፣ የተወሰዱ መፍትሔዎቸና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች እንደዚሁም ደግሞ የ2016 እና የ2017 በጀት ዓመት የኦዲት ሪፖርት አቅርበዋል ።

የጎፋ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ ኃላፊ አቶ ታደለ ያዕቆብ ሪፖርቱን መነሻ በማድረግ በኮሌጁ በርካታ ውጤታማና ተስፋ ሰጪ ስራዎች መሠራታቸውን ተናግረው ኮሌጁ በበጀት ዓመቱ በርካታ ተግባራትን በማከናወን የተሻለ አፈጻጸም ደረጃ ላይ መሆኑን ተናግረዋል ።

በበጀት ዓመቱ ተቋሙ ያከናወናቸው ተግባራት የሚያስመሰግን መሆኑን የተናገሩት የመምሪያው ኃላፊ በ11 ወራት ያሳካናቸውን ተግባራትን በማጠናከር በታዩ ክፍተቶች ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት በቀጣይ የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ከዚህኛውም በይበልጥ በርትቶ መሥራት ይጠበቅብናል ስሉ አሳስበዋል ።

የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ እንዳለ ኡታ በበኩላቸው ባለፉት 11 ወራት ኮሌጁ የተሰጠውን ተልዕኮዎችና ግቦችን ለማሳካት በርካታ ስራዎችን እያከናወነ መቆየቱን አንስተው ይህ የአፈጻጸም መድረክ በስልጠና ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በአጠቃላይ ከተልዕኳችን አንጻር የተሰሩ ስራዎችን አፈጻጸም በዝርዝር በማየት ክፍተቶች ላይም በመመካከር በቀጣይ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብና የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ይረዳናል ስሉ ተናግረዋል ።

በአካባቢው ብቁ ፣ ተነሳሽነትና የፈጠራ ክህሎት ያለው የሰው ኃይል ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን ያነሱት አቶ እንዳለ በቀጣይ ለማህበረሰቡ ዕድገት ቁልፍ ሚና ባላቸው የስራ መስኮች ስልጠና በመስጠት ሰልጣኞችን የሙያ ባለቤት በማድረግ የስራ ፈጣሪ ባህል በማጠናከር የፈጠራ ተነሳሽነትን በመደገፍ ከፍተኛ ሚናውን እንደሚወጣም አብራርተዋል ።

በቀረቡ ሪፖርቶች ላይ ሀሳብና አስተያየት ተሰጥቶባቸው የማጠቃለያ ሐሳብና ምላሽ በመሠጠት የአፈጻጸም ግምገማ መድረኩ ተጠናቋል ።

በመጨረሻም የመምሪያ ኃላፊና የማኔጅመንት አካላት በኮሌጁ በተለያዩ ወርክሾፖችና ዲፓርትመንቶች የመስክ ምልከታ አድርገዋል ።

በመድረኩ ላይ የጎፋ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ ኃላፊ አቶ ታደለ ያዕቆብ ፣ የመምሪያው ማኔጅመንት አካላት ፣ የኮሌጁ ዋና ዲን ኢ/ር እንዳለ ኡታ ፣ ምክትል ዲን ኢ/ር ማሞ ኛቦ እና የማኔጅመንት አካላት ተሳትፈውበታል ።

Photos from Laha Construction And Industrial College's post 12/03/2025

ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ቢሮ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር ጋር ውይይት ተደረገ ፡፡

መጋቢት 03/2017 ዓ.ም
ላሃ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር በአርባ ምንጭ ክላስተር በመገኘት ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቴ/ሙያ ትም/ሥ/ቢሮ ኃላፊ ከክቡር አቶ አብዮት ደምሴ፣ ከም/ቢሮ ኃላፊዎች ከአቶ ዳዊት ፋንታዬና ከአቶ በዛብህ ገበየሁ ጋር የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት መ/ር አማኑኤል ጳውሎስ እንዲሁም የክልሉ መምህራን ማህበር ሁሉም ሥራ አስፈጻሚዎች በተገኙበት
1. በአሰልጣኝ መምህራን የደረጃ እድገት፣ ትምህርት ለውጥ እንዲሁም ዝውውርና ምደባ
2. የኑሮ ማሻሻያ ደመወዝ ጭማሪ በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ
3. በኮሌጅ ደረጃ በሚደረገው ሥር ነቀል መሰረታዊ መም/ማህበር ምርጫ ዙሪያ
4. በመልካም አስተዳደር ችግሮችን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት እንዲሁም በቀጣይ በጋራ በምንሰራቸው ሥራዎች ሰፊ ውይይቶች በማድረግ ከላይ በተደረጉ ውይይቶችና አሰልጣኝ መምህራንን በሚመለከቱ ጉዳዬች ከዚህ ቀደም ከነበረው በተሻለ ሁኔታ ለመስራት ተወያይተዋል ።

Photos from Laha Construction And Industrial College's post 02/03/2025

የላሃ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ የ2017 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የስራ አፈጻጸም በተመለከተ የኮሌጁ ስራ አመራር ቦርድ መድረክ አካሂዷል ።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

ላሃ ፣ የካቲት 2017 ዓ.ም ፤ የላሃ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ የ2017 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የስራ አፈጻጸም በተመለከተ የኮሌጁ ስራ አመራር ቦርድ መድረክ አካሂዷል ።

የአፈጻጸም ግምገማው ተቋሙ ያለበትን ደረጃ ለመለየትና በቀጣይ የተግባራትን ሰላም ስኬታማነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እንዲሁም የታዩ ጉድለቶችን በማስተካከል ለቀጣይ አቅም አድርጎ ለመጠቀም ያለመ የአፈጻጸም መድረክ ነው የተካሄደው ።

የላሃ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ አሸናፊ ጮራ በንግግራቸው ዘመኑ የሚፈልገውን የሰው ኃይል በማፍራት ረገድ ኮሌጁ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑን አንስተው በአካባቢው የሰልጣኝ ቁጥር ከፍተኛ ባለመሆኑና አብዛኛው በኮሌጁ ለመማር ፈላጎታቸው ዝቅተኛ ስለሆነ ይህንን የአመለካከት ችግር መስበር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል ።

ክቡር ከንቲባው ጨምረውም እንደገለፁት በቀሪ ስድስት ወራትም ያልተከናወኑ ወሳኝ ስራዎችን እንዲተገበሩ ይህ የአፈጻጸም ግምገማ መድረክ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ብለዋል ።

የኮሌጁ ዋና ዲን እንዳለ ኡታ የ 6 ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡ ስሆን በቀረበው ሪፖርት ላይ ግምገማና ውይይት ተደርጓል ።

በዚህም ኮሌጁ ባለፉት 6 ወራት የተሰጠውን ተልዕኮና ግቦችን ለማሳካት በርካታ ስራዎችን እያከናወነ የቆየ ስሆን በርካታ ተልዕኮዎችን ከመፈጸም አንጻር የተከናወኑ ስራዎች አፈጻጸም በመገምገም ጉድለቶች ላይ ለመመካከር እና ቀጣይ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንዲሁም የመፍትሔ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ወሳኝ የአፈጻጸም ግምገማ መሆኑ ተጠቁሟል ።

በአፈጻጸም ግምገማ መድረኩ ላይ የጎፋ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ ኃላፊ አቶ ታዬ ታደሴ ፥ የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ሳውላ ካምፓስ ፕሬዘዳንት ተወካይ ዘለቀ ዶሳ ፣ የሳውላ ፖሊ ቴክኒክ ሙያ ኮሌጅ ዋና ዲን ግንዳ ባህሩ ፣ የላሃ ከተማ ከንቲባና የኮሌጁ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አሸናፊ ጮራ ፣ የኮሌጁ ዲን አቶ እንዳለ ኡታን ጨምሮ የማኔጅመንት አካላት ተሳትፈውበታል ።

Photos from Laha Construction And Industrial College's post 14/02/2025

የላሃ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጆችን
ያሉንን ፀጋዎች አሟጠን በመጠቀም የተሻለ ተቋም እንገነባለን....!

ላሃ፦ ያካትት 07/2017 ዓ.ም

የላሃ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ከምሰጣቸው ስልጠናዎች ጎን ለጎን የውስጥ ገቢን ለማሳደግና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የኮሌጁ ማህበረሰብ እና የአከባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ በአራት ሄክታር ማሳ ላይ የተለያዩ የሰብልና የጓሮ አትክልቶችን በመዝራት ማሳውን መሸፈኑ ታውቋል።

የኮሌጁ ማኔጅመንት በመወያየት ከትምህርትና ሥልጠና ጎን ለጎን በአረንጓዴ አሻራ(Green Tvet) በከተማ ግብርና ልማት ሥራዎች ትኩረት ሠጥቶ በመሥራት የኮሌጁን የውስጥ ገቢ ለማሳደግ ሁሉም የተቋሙ ሠራተኛ በመረባረብ በተለያዩ ዘርፎች በመሳተፍ የገቢ ምንጭ ለማሳደግ በተሻለና በተቀላጠፈ መንገድ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል። በጓሮ አትክልት፣ በሰብልና ፍራፍሬ ምርት የተሻለ ስራ በመስራት በተመጣጣኝ ዋጋ ምርት በማቅረብ ተጠቃሚ ለማድረግ በቅንጅት እየተሠራ ነው።

አሁን በርካታ የማንጎ ምርት ለሸማቾች በተመጣጣኝና የአከባቢው ገብያ ሁኔታ በምያረጋጋ ዋጋ ማቅረቡ ተገልጿል።

📸
ብቁና ተነሳሽነት ያለው ስራ ፈጣሪ ዜጋን እንፈጥራለን !!

Photos from Laha Construction And Industrial College's post 09/12/2024

በላሃ ቴክንክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ ሰልጣኝ ቅበላ እስካሁን ያለበትን ደረጃና በቀር ቅበላ ስራዎች ዙርያ ከአጠቃላይ ኮሌጅ አባላት ጋር ውይይት ተደርገ፡፡
*************************
ላሃ፤ ህዳር 30/2017 ዓ.ም
በላሃ ቴክንክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ አዲስ ሰልጣኝ ቅበላ ዙሪያ ከአጠቃላይ ኮሌጅ አባላት ጋር ውይይት የተደረገ ስሆን ዉይይት መድረኩ የመሩት ኮሌጁ ዲን ኢ/ር እንዳለ ኡታ በ2017 ዓ.ም ቅበላ አቅማችን ለማሳደግ ቅድሚያ ሁነታዎችን በማመቻቸት ብዙ ተግባራት የተከናወኑ መሆኑን አንስተው ነገር ግን እስካሁን የመጣው ሰልጣኝ ከዕቅድ አንጻር ዝቅተኛ በመሆኑ የቅስቀሳ ስራዎችን ከተለመደው ስልት በመውጣት አድስ ስልቶችን በመጠቀም ተግባራትን ማከናወን እንዳለበት ገልጸዋል።

ዲኑ በመድረኩ እንዳሉት የሙያ ዕውቀት የማይሞት የማይጠፋ ሀብት በመሆኑ ትምህርታቸውን ጨርሰው ቤት የሚገኙ ተማሪዎች ወደ ቴ/ሙያ መጥተው በመሰልጠን ሥራ ፈጥረው የተሻለ ውጤታማ መሆን እንደሚቻል አውቀው ወደ ተቋም እንድመጡ በልዩ ትኩረት ልሰራ እንደሚገባ የእስካሁን አፈፃፀም በመገምገምና አዋጭና ወጭ ቆጣቢ፣ ሰነድ በማዘጋጀትና ልዩ ልዩ ሲልት መዘየድና መምራት አስፈላጊ እንደሆን አሳስበዋል፡፡

የኮሌጁ ም/ዲንና ሰ/አ/አ/ል/ሥራ ሂደት አስ/ሪ ተውካይ የሆኑት ኢ/ር በረከት ሰጉ ነባር ሰልጣኝ ቅበላ አፈጻጸም ጥሩ ብሆንም አድስ ሰልጣኝ ቅበላ የዓመቱ ዕቅድ 422 ለመቀበል ታሲቦ 65 ወጭ መጋራት ከፊሉ መመዝገባቸውንና አፈፃፀም 16% በላይ መሆኑን ገልጾታል።ነገር ግን ወደ ኮሌጁ መምጣት ያለባቸው በርካታ የ12ኛ አጠናቃቂ ተማሪዎችን ውጭ ስለሆኑ እኔዚያን በማምጣት የትምህርት ስብራት ለመቀልበስና ዜጎች የሙያ ባለቤት ሆነው የሀገሪቷ የኢኮኖሚ እድገት እስከሚረጋገጥ ተጋግዘን መትጋት አለብን ብለዋል።

ቅበላ አቅማችን ማሳደግ ሁላችንም ሃላፊነትን ያሉት ተሳታፊዎቹ ወጣቱን ትውልድ የመቅረጽ አባላቱ ሀላፊነት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኮሌጁ ማህበርስብ ሀላፊነት ብለዋል። በውይይቱ ላይ የተለያዩ ለተማሪ ቅበላና ለሥራው ውጤታማነት ተግዳሮት የሚሆኑ ችግሮች ዙሪያ ሀሳቦችን በሰፊው ተነስቶ በቀጣይ የቅስቀሳ ስራዎችና የትኩረት አቅጣጫዎች ዙርያ ውይይት በማድረግና የስራ ስምርት በመከፋፈል ተጠናቋል፡፡

ብቁና ተነሳሽነት ያለው ስራ ፈጣር ዜጋ እንፈጥራለን!!

Photos from Laha Construction And Industrial College's post 05/12/2024

በተግባር፣ በክህሎትና በመልካም ስብዕና የተገነባና ከሥራ አጥነት ችግር የተላቀቀ ዜጋን ማፍራት የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ቁልፍ ተግባር ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ።

ላሃ ኮ/ኢ /ኮሌጅ፣ ኅዳር 26/2017 ዓ.ም በተግባር፣ በክህሎትና በመልካም ስብዕና የተገነባና ከሥራ አጥነት ችግር የተላቀቀ ዜጋን ማፍራት የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ቁልፍ ተግባር ሊሆን እንደሚገባ የጎፋ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ታደለ ያዕቆብ ገለጹ።

በዞኑ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት ነባርና አዲስ ሰልጣኝ ቅበላ አፈፃፀምና አዲሱ የመንግስት ሠራተኞች የኑሮ ማሻሻያ መመሪያ ቁጥር 77/2017 ከኮሌጅ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ ተካሂዷል።

የመምሪያው ኃላፊ አቶ ታዬ ታደሰ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ታደለ ያዕቆብ መንግስት ቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ትኩረት ሰጥቶ እየመራ መሆኑን ገልጸው በቴክኒካል ክህሎት የበለጸገ ብቁና ውጤታማ ራሱን በሁሉም ዘርፍ ያሻሻለ ወጣት እያፈራ ያለ ተቋም ስለሆነ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ አንስተዋል።

አዳዲስ ሰልጣኞች ወደ ኮሌጆች እንድመጡ በማድረግ የሰልጣኝ ቅበላ አፈፃፀማችንን ከፍ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

በተያዘው በጀት ዓመት በዞኑ የሚገኙ በርካታ ቁጥር ያላቸውን ወጣቶችን በተግባር፣ በክህሎትና በመልካም ስብዕና የተገነባ ከሥራ አጥነት ችግር ተላቀው ፊት የወጡ ዜጎችን ማፍራት የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ቁልፍ ተግባር ሆኖ መመራት እንዳለበት ጠቁመዋል።

በምክክር መድረኩ በዞኑ የሚገኙ የሁሉም ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ዲኖችና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

Photos from Laha Construction And Industrial College's post 22/11/2024

በላሃ ኮንስትራክሽንና ኢንዳስትሪያል ኮሌጅ የዲጅታል የመረጃ አስተዳደር ስይስተም መጠቀም የሚያስችል ስልጠና ተሰጠ።
======================
ላሃ ህዳር 13 2017/ኮሌጁ ኮምኒኬሽን /

ላሃ ኮንስትራክሽንና ኢንዳስትሪያል ኮሌጅ በሥራና ክህሎት ሚንስትር በኩል ተበልጽጎ ለኮሌጆች የተሰጤው ዲጅታል የመረጃ አስተዳደር ስይስተም ዙርያ ለስልጠና ክፍል ባለሙያዎች፣ዘርፍ ተጠሪዎች ፣ ማናጅመንት አካላት ፣ አሰልጣኝ መምህራንና አስ/ሪ ሰራተኞች በተገኙበት ስልጠና ተሰጠ።

ዲጂታል የመረጃ አስተዳደር ሲስተም በመጠቀም አገልግሎትን ማቀላጠፍ፣ ስልጣኞች ስልጠና ሂደቱ ማዘመንና በቅ ዕውቀት ከማስገኘት አንጻር ከፍተኛ ፋይዳ ስላለውና ለሁሉም ተቋሙ ማህበርሰብ ግንዛቤን በመፍጠር አገልግሎቱን በላቀ ሁኔታ መጠቀም እንዲቻል ለማድረግ እንደምያስችል ተገልጿል ።

መጨረሻም ኮሌጁ ላይ የሚሰጡ ስልጠናዎችና አገልግሎቶቹን ዲጂታላይዝ በማድረግ የሞደርናይዜሽንና የተቋም ግንባታን የማጠናከር አንድ የሪፎርም ሀሳብ አድርጎ እየተሰራ እንደሚገኝና የመረጃ አያያዝ ስርዓታችንን በማዘመን የጊዜ፣ የሐብት፣ የጉልበት ብክነትን ለመቅረፍ እንደምያግዝ ተገልጿል።

=====

Photos from Laha Construction And Industrial College's post 22/11/2024

በላሃ ኮንስትራክሽንና ኢንዳስትሪያል ኮሌጅ አለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን "
አስመልክቶ ''ሙስናን የሚፀየፍ ትውልድ ለኢትዮጵያ ብልጽግና " በሚል መሪ ሐሳብ በኮሌጁ በፓናል ውይይት ተከበረ ።

ላሃ ፣ ህዳር 13/2017
በላሃ ኮንስትራክሽንና ኢንዳስትሪያል ኮሌጅ የፀረ ሙስና ቀን " አስመልክቶ ሙስናን የሚፀየፍ ትውልድ ለኢትዮጵያ ብልጽግና "በሚል መሪ ሐሳብ በፓናል ውይይት ተከብሯል ። በውይይቱም ሙስናን መከላከል ላይ ትኩረት ያደረገ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል ።

ሁሉም የኮሌጅ ሰራተኞችና የኮሌጅ አመራሮች ሙስናን መጸዬፍ እንደሚያስፈልግ ተገልጾ ሙስናን መጠቆም ፣ ማጋለጥና መከላከል ከሁሉም እንደሚጠበቅና መንግስት ሙስናን ለመከላከል በሚያደርገው ትግል ሁሉም የኮሌጁ ሰራተኞችና የኮሌጅ አመራሮች ተሳትፎ እንዲያድግና ግንዛቤ እንዲኖር ማድረግ ያስፈልጋል ተብሏል ።

21/11/2024
Want your school to be the top-listed School/college in Arba Minch'?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address

Melo Koza
Arba Minch'