አይከል ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ Aykel tvet collage

አይከል ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ Aykel tvet collage

Share

የሙያ ባለቤት መሆን ያስከብራል

Photos from አይከል ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ Aykel tvet collage's post 31/03/2026

አይከል ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ በ Sanitary (የንጽህና አጠባበቅ) ዘርፍ ለከተማችን ወጣቶች ያዘጋጀውን የ45 ቀናት አጭር ስልጠና በይፋ ጀምሯል!
የኮሌጁ ምክትል ዲን ከፍተኛ ኢንስትራክተር አለምነው ዋኘው ​ዛሬ ስልጠናውን የጀመሩ ሰልጣኞች በንድፈ-ሀሳብና በተግባር የታገዘ እውቀት በመቅሰም ራሳቸውን ለስራ ዓለም ብቁ የሚያደርጉበት ጉዞ ጀምረዋል ብለዋል። ም/ዲኑ አክለውም ኮሌጃችን ወጣቶች የክህሎት ባለቤት እንዲሆኑ ለተከታታይ 45 ቀናት ውስጥ የበኩሉን ጥረት እያደረገ ይገኛል።
ም/ዲኑ በመጨረሻም ​የከተማችን ወጣቶች በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ የሚሰጠውን ስልጠና በአግባቡ በመከታተል የነገ ህይወታቸውን የሚቀይር ሙያ እንዲጨብጡ መልእክት አስተላልፈዋል ።
​አይከል ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ

Photos from አይከል ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ Aykel tvet collage's post 31/03/2026

አይከል
"ዘውዲቱ የሴቶች ፀጉርና ውበት ስራ ማሰልጠኛ ተቋም" አይከል ከተማ ላይ በዘርፉ የመጀመሪያ የሆነ የማሰልጠኛ ተቋም ነው

Photos from አይከል ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ Aykel tvet collage's post 24/03/2026

ፀደይ ባንክ እና የአማራ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ትብብራቸውን የሚያጠናክር ስምምነት ተፈራረሙ
አዲስ አበባ | መጋቢት 5 ቀን 2018 ዓ.ም
ፀደይ ባንክ እና የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሥራ እና ክህሎት ቢሮ በሥራ ዕድል ፈጠራ እና በብድር አቅርቦት ዙሪያ የነበረውን ስምምነት ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችል አዲስ ስምምነት ተፈራረሙ።
➡️የስምምነቱ ዓላማና ተፈራራሚዎች
ዛሬ በፀደይ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት በተከናወነው የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ላይ፦
⤴️ከባንኩ በኩል፦ አቶ ተዋበ አይሸሽም (የባንኩ ምክትል ፕሬዝዳንት-የፕሬዝዳንት ልዩ ረዳትና የፕሬዝዳንቱ ተወካይ)
⤴️ከቢሮው በኩል፦ ስቡህ ገበያው (ዶ/ር) (የአማራ ክልል ሥራ እና ክህሎት ቢሮ ኀላፊ) ስምምነቱን ፈርመዋል።
ሁለቱ ተቋማት ከዚህ ቀደም በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በብድር አቅርቦት እና በተለያዩ የልማት ዘርፎች የነበራቸውን ውጤታማ የጋራ ጉዞ በዚህ ስምምነት ይበልጥ ለማሳደግ ቃል ገብተዋል።
ፀደይ ባንክ በቁጥር
ባንኩ በተለይ ለጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች (MSMEs) የሰጠው ትኩረት የሚከተሉትን ስኬቶች አስመዝግቧል፦
⤴️የብድር አቅርቦት፦ ከጠቅላላው 49.5 ቢሊዮን ብር ብድር ውስጥ 80 በመቶው (ከ39.5 ቢሊዮን ብር በላይ) ለኢንተርፕራይዞች ተደራሽ ሆኗል።
⤴️ተጠቃሚነት፦ ከ 1 ሚሊዮን ለሚልቁ ዜጎች ብድር በማቅረብ የኑሮ ደረጃቸውን ማሻሻል ችሏል።
⤴️ተደራሽነት፦ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ 632 በላይ ቅርንጫፎች እና ከ 12 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች አሉት።
የልማት ዐሻራ
ፀደይ ባንክ ለፋይናንስ አካታችነት ቅድሚያ በመስጠት፣ ዘመናዊ እና ደኅንነታቸው የተጠበቀ የዲጂታል ባንኪንግ አማራጮችን በመጠቀም የዜጎችን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ ይገኛል። ይህ ስምምነትም በክልሉ ያለውን የሥራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ እና የምርት እድገትን ለማፋጠን ትልቅ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።
#የሁሉም ባንክ! | Bank of All!
#የክህሎት ልማት ለኢኮኖሚ እድገት

24/03/2026
Photos from ANRS Labour and Training Bureau's post 13/03/2026
Photos from አይከል ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ Aykel tvet collage's post 12/03/2026

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ስራና ስልጠና መምሪያ ለአይከል ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ የድጋፍ መድረክ ውይይት አካሄደ።
በመድረኩ የኮሌጁ አጭር የተግባራት ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጓል ። የተግባራት አፈፃፀም ከቁልፍ እና አበይት ተግባራት በሚል ተከፍለው በውይይቱ ተነስተዋል።
የመምሪያው የድጋፍ ልዑክ መሪው አቶ ገብሬ አሻግሬ ትምህርት እና ስልጠና ተግባሮቻችን እንዲሁም የኢንተርፕራይዝ የድጋፍ ተደራሽነታችን በሚጠበቅብን ልክ መስራትና ሰልጣኞቻችን ላይ እና ኢንተርፕራይዞች የሚታይ ለውጥ ማምጣት አለብን ተብለዋል። አክለውም አቶ ገብሬ አሻግሬ የአፈፃፀም ጉድለት የሚታዩብነን የትብብር ስልጠና የብቃትና ምዘና የአዲስ ተማሪ ቅበላ በሁሉም ዘርፍ በአራቱም ማዕቀፍ ውጤታማ የኢንተርፕራይዞች ድጋፍ ልናሻሽላቸው የሚገቡ ተግባራት ናቸው ብለዋል።
በመጨረሻም የኮሌጁ ሰራተኞች በትብብር እና ቅንጅታዊ ስራን ተግባራዊ በማድረግ እና የተለያዩ የሃብት ማፈላለጊያ ፕሮጀክቶችን በማዘጋጀት እና የውስጥ ሀብት ማግኛ ስራዎችን በመከወን የተጀመረውን የኮሌጅ የህንፃ ግንባታ በማጠናቀቅ ኮሌጁን ወደ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለማሳደግ አልማችሁ መስራት ይገባል ተብሏል።
የመምሪያው የድጋፍ ልዑክ በኮሌጁ ውይይት ላይ የተነሱ ችግሮችን በመያዝ ለጭልጋ ወረዳ ለነባሩጭልጋ ወረዳ እንዲሁም ለአይከል ከተማ አስተዳደር ማቅረብና የጋራ ማድረግ ተችሏል።

Photos from አይከል ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ Aykel tvet collage's post 11/03/2026

የፀረ ኤች አይ ቪ ኤድስ ክበብ ውይይት አደረገ
የአይከል ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ የፀረ ኤች አይ ቪ ኤድስ ክበብ ውይይት አደረገ በውይይቱ የኮሌጁ ሰራተኛች ስለ ኤች አይ ቪ አሁን ላይ መዘናጋቶች የበዙ ነገር ግን ግን የማህበረሰብ ጤና በመጉዳት በሁለነንታዊ ልማት ላይ ሰፊ ችግር እየፈጠረ መሆኑን ተወያዮች አንስተዋል ።
በመሆኑም ሁሉም ዜጋ ሳይዘናጋ እራሱንና ቤተሰቡን መጠበቅ አለበት

Photos from አይከል ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ Aykel tvet collage's post 10/02/2026

03/06/2018
አይከል ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ የ2018 ዓ ም የስድስት ወራት የተግባራት አፈፃፀም ስራዎችን ገመገመ።
ኮሌጁ የ2018 ዓ ም የተለያዩ ተግባራት እቅዶችን በማቀድና ከሰራተኞች ጋር የጋራ በማድረግ ወደ ስራ መግባቱ ይታወቃል በመሆኑም በስድስት ወራት ውስጥ ተግባራትን ለመፈፀም ሰፊ ጥረት ተደርጓል።
በስራ አፈፃፀም ግምገማው ሪፖርቱን ያቀረቡት የኮሌጁ እቅድና በጀት ዝግጅት ባለሙያ ወ/ሮ ማሪቱ ጥላሁን ሲሆኑ በሪፖርቱ የቁልፍ ተግባራት አፈፃፀሞች በጥንካሬና በድክመት የቀረበ ሲሆን አበይት ተግባራትንም ክግብ እና ከአላማ እንፃር በመተንተን የተሻሉ የተከናወኑ ስራዎችን ሲቀርቡ መሻሻል ያለባቸውም ተለይተው ቀርበዋል። በግማሽ አመቱ ያጋጠሙ ችግሮችም ተጠቅሰዋል
ከተሳታፊዎችም የተለያዩ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸው የጋራ ሃሳብ ተይዟል
በመጨረሻም የኮሌጁ ዲን ገብረመድህን አለሙ በውይይት ላይ የተነሱትን ፍሬ ሃሳቦች በቀሪ ወራቶች ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል። ዲኑ አክለውም ትምህርት እና ስልጠናችን ውጤታማነት ማረጋገጥ የምንችለው በንድፍ ሃሳብና በተግባር ውጤታማ ሰልጣኝ ፈጥረን መብቃት የቻለ ዜጋ ስንፈጥር ነው ብለዋል። ብመሆኑም ሁሉም ሰራተኛ በትብብር የተሻለ ኮሌጅ መፍጠር አለብን።
በሌላ በኩል ኢንተርፕራይዞቻችንን በአራቱም የድጋፍ ማዕቀፍ በቅንነት በመደገፍ የሚያመርቱና የበለፀጉ እንተርፕራይዝ መፍጠር አለብን ብለዋል።

26/01/2026

ሞክረው

Photos from አይከል ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ Aykel tvet collage's post 14/08/2025

የአይከል ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ የተጀመሩ የኮሌጁ ህንፃ ግንባታ ለማስጨረስ ሰፊ ስራዎችን እያከናወነ ነዉ።
ባለፈዉ አመት አስር የማሰልጠኛ ክላስ ያለዉ ግንባታ ከአሰሪ ኮሚቴው ጋር በመተባበር የተሻለ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው በዚህ አመት 9 ክፍሎች ያሉት የአስተዳደር ቢሮ ግንባታውን ለማስጨረስ ስራ አስጀምሯል።
ኮሌጃችን ዜጎችን በንድፈ ሃሳብና በተግባር የሙያ ባለቤት እያደረገ ያለ አንጋፋ ኮሌጅ ነው። በመሆኑም በመንግስትና ህዝብ በተባበረ ክንድ ግንባታው እየተከናወነ ያለው የኮሌጃችን ግንባታ መጨረሻ ደረጃ ላይ የደረሰ ቢሆንም ሌሎች ቀሪ ስራዎችን የኮርኒስ እና የመስታውት ስራ የቀረ በመሆኑ ባለድርሻና አጋር አካላት የተለመደ ሰፊ ድጋፋችሁን እድታደርጉልን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ያሉት የኮሌጁ ዲን አቶ ገ/መድህን አለሙ ናቸው።

Want your school to be the top-listed School/college in Amhara Region?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address

Amhara Region