እውነተኛ እራስህን ማወቅ ልትይዘው የምትችለው በጣም አስፈላጊው ችሎታ ነው። ማን እንደሆንክ ስታውቅ፣ የሌሎችን ፍቃድ ከመፈለግ ይልቅ ምን ማድረግ እንዳለብህ ታውቃለህ። ለተሳሳቱ ነገሮች ጊዜን በመስጠት ብዙ ብስጭቶች እንዲያልፉ ማድረግ ይቻላል። አዎ፣ ህይወት በሙከራ እና በስህተት የተሞላ ነው ተብሎ ይታሰባል፣ ነገር ግን አንዴ እራስህን ካወቅክ የበለጠ በራስ መተማመን ይኖረሀል፣ አላማህን ትረዳለህ እና በአለም ላይ ትልቅ ተጽእኖ መፍጠር ትጀምራለህ።
ስለዚህ ማን እንደሆንክ እና በህይወት ውስጥ ምን ማድረግ እንዳለብህ እንዴት ማወቅ ትችላለህ? እውነተኛ ማንነትህን/ሽን ለማወቅ የሚከተሉትን እርምጃዎች መውሰድ ያስፈልጋል።
1,ለራስህ ጌዜ ስጥ
ለራስ ጊዜ መስጠት አስፈላጊና ዋና ነገር ነዉ። ለራስህ ገዜ እስካልሠጠህ ድረስ እራስህን ማወቅ አትችልም።እና ብዙ ሰዎች እራሳቸውን አያውቁም ምክንያቱም ማንኛውም ዓይነት ዝምታ ያስፈራቸዋል; እያንዳንዱ እንከን ወደ እነርሱ ዞር ብሎ እያየ ብቻውን መሆን በጣም ምቹ አይደለም። ነገር ግን ብቻህን እስክትሆን፣ እራስህን ገምግመህ ከራስህ ጋር ሙሉ በሙሉ እውነት እስክትሆን ድረስ ሁሉንም የሕይወትህን ገጽታዎች ማለትም ጥሩውን እና መጥፎውን ማየት የምትችለው። ለራስህ ጊዜ ሠጥተህ እውነተኛ ማንነትህን እወቅ።
2,ማን መሆን እንደምትፈልግ ሳይሆን ማን እንደሆንክ እወቅ።
በተስፋ መቁረጥ ዉስጥ ማን መሆን እንዳለብህ እንደምትፈልግ እሙን ነዉ፣ ነገር ግን ማን ለመሆን ታስባለህ ላይሆን ይችላል። ማን እንደሆንክ ስታውቅ አንተ እና ልዩ ስጦታዎችህ ወለል ብለዉ ይታዩሀል።ለዚህ ደግሞ ሁል ገዜ በጠንካራ ባህሪህ ላይ አተኩር ።
ይቀጥላል......
Yonas
አሁን ላይ ስወስን ሁሉን ማድረግ እችላለሁ
ምርጫችን ምንድን ነዉ?
ራሳችንን ማወቅ ከጀመርንበት ጊዜና ሠዓት ጀምሮ ብዙ አማራጮች እንዳሉን የማይካድ ሀቅ ነዉ።ዋናዉ ነገር ምርጫችን ምንድን ነዉ ? የሚለዉ ጥያቄ ነዉ ።ብዙዎቻችን ምርጫችንን ለማግኘት አማራጮችን እናያለን።ነገር ግን ደስተኛ ሁነን ለመኖር አንድ ነገር ብቻ መምረጥ አለብን የህን ለማድረግ ደግሞ አሁን ባለን ህይወት ደስተኛ ነን?ካልሆነ ምርጫችን ትክክል አይደለም።ምርጫ ማለት ወደን የምናደርገዉ (በፍቅር የወደቅንበት)በችግሮች የሚፈተን ግን ፈተናዉን የሚያልፍ፣ የሚደናቀፍ ግን የማይወድቅ፣በምንም ሁኔታዎች ዉስጥ አብሮን የሚሆን በሌላ አገላለፅ የህይወት ዓላማ ማለት ነዉ።በምንም ሁኔታዎች ዉስጥ እንሁን አንድ የሚያስደስተንን እንምረጥ የሚከፈለዉን መስዋዓትነትን እንክፈል ዉጤቱ ያስደስተናልና።
ሠናይ አዳር
በየያንዳንዷ የህይዉት እንቅስቃሴአችን ዉስጥ እኛን ሳይነካ የማያልፍ ጊዜ የለንም:በተለምዶ ጊዜ ብለን የምንጠራዉ ትናንትን፣ዛሬን እና ነገን ነዉ ።በህይወታችን የምናቅዳቸዉን ነገሮችን ለማሳካትም ሆነ የለፈዉን ስህተታችንን ለማረም ወይም ለማስተካከል በነዚህ የጊዚ መለኪያዎች ዉስጥ ማለፋችን ግድ ነዉ።ዋናዉ ነገር ግን ትናትን፣ነገን እና ዛሬን የምናስበዉ አሁን ላይ ሁነን ነዉ ።አሁን ማለት ቀን፣ሰዓት፣ደቂቃና ሠከንድ የሚወሰን ወይም የሚለካ ሳይሆን በቅፅበት ከምናስበዉ፣ከምንወስነዉ እና ከምናደርገዉ ጋር የሚገናኝ ነዉ።ስላለፈዉ፣ስለዛሬም ሆነ ስለነገ የምንናስበዉ አሁን ላይ ነዉ ( A moment that we think) ስለዚህ በምንም ነገሮች ዉስጥ እንሁን አሁናችን አዎነታዊ ዉስጥ መሆን አለበት አሁን ደስተኛ ከሆንን ቀጣዩ አሁናችን ደስተኛ ያደርገናል በተቃራኒው አሁን ደስተኛ ካልሆንም አሁናችን ይበላሻል።ለማጠቃለል ያህል ስኬታችንን ሆነ ዉድቀታችንን የምንወስነዉ አሁን ዉስጥ ነዉና አሁናችንን አንጠቀምበት ።
አብዛኛዉን ጊዜ ህይወት ተመሰቃቅሎብን ይሆናል ወይም የምንፈልገዉን ህይወት እየኖርን እንዳልሆነ ይሰማናል እነዚህ ጥያቄዎች የሚመነጩት ዉስጣችን ያለዉ ማንነትና በየቀኑ የምናደርጋቸዉ ነገሮች ስለማይገናኙ ነዉ የኛ ማንነት የተፈጠረዉ ከራሳችን አልፈን ለሌሎች ሠዎች እንዴት መፍትሔ እንደምንሆን ነዉ የሚያስበዉ በተቃራኒዉ በየቀኑ የምናረጋቸዉ ድርጊቶች ዉስጣችን ከሚፈልገዉ ነገር ጋር ይጋጩብናል ስለዚህ አሁን የምንኖረዉን ህይወት የወሰድነዉ ካደግንበት ማህበረሰብ እንዲሁም በዙሪያችን ካሉ ሠዎች ነዉ። ታድያ ይህን ህይወት እንዴት መቀየር እንችላለን? መልሱ አዎ መቀየር እንችላለን አንዴት ለሚለዉ አነዚህን ጥያቄዎች ለራሳችን መመለስ አለብን።
1,WHO I AM(እኔ ማን ነኝ) ማንነታችንን እና ምን እንደምንፈልግ እንድናዉቅ ይረዳናል
2,What I AM DOING NOW? አሁን ላይ የምናረገዉ ነገር መኖር ከምንፈልገዉ ህይወት ጋር መልስ የሰጠናል።
3, WHERE I AM GOING (ወዴት እየሔድኩ ነዉ)? እዉነት ወደ ምንፈልገዉ ህይወትና ለተፈጠርንበት አለማ አንዴት ወደፊት መሔድ እንዳለብን እንድናስብ ፍንጭ ይሰጠናል። እነዚህን መሰረታዊ ጥያቄዎች እራሳችንን ጠይቀን መልስ ካገኘን ህይወታችንን እኛ ወደ ምንፈልገዉ መዉሰድ እንችላለን ምክንያቱም ህይወታችን በኛ እጅ ላይ ነዉ ያለዉና።።።።
ሕይወታችንን መቀየር ከፈለግን አሁን እንወስን
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the school
Telephone
Website
Address
Ambo
MARANATA