Amir Mussa

Amir Mussa

Share

Quality Education is required for the country's development

Photos from Ordin Bedri's post 03/08/2023
29/04/2023

ጅብ ጉዳት ያደረሰበት የ7 ዓመት ዕድሜ ያለው ታዳጊ ህይወቱ አለፈ፡፡

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ትናንት ሚያዝያ 19/2015 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት አካባቢ ህፃን ኢፋ አባድር አደም ስራ ቦታ የነበረውን አባቱን ፍለጋ ሲሄድ ነው ጅቡ መንገድ ላይ ጉዳት ያደረሰበት፡፡

ህፃን ኢፋ አባድር አደም በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ የሚገኘውን ራሬ የእርሻ ምርምር ቦታ በማቋረጥ ገንደ ጄይ ወደሚባለው ሰፈር አቅጣጫ በመጓዝ ላይ ሳለ ጅቡ ከነበረበት ቦታ በመውጣት ታዳጊውን በማባረር ህፃኑም ማምለጥ ባለመቻሉ ሆዱ እና ጭንቅላቱ ላይ ከባድ ጉዳት አድርሶ ጅቡ ወደ ሚኖርበት ጉድጓድ ይዞት መሄዱን ከርቀት የተመለከቱ የዩኒቨርሲቲው የጥበቃ አባላት ህፃኑን ከጅቡ በማስጣል የሕክምና ድጋፍ እንዲያገኝ ወደ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ጤና ጣቢያ ወስደውታል፡፡

ታዳጊው በጅብ የደረሰበት ጉዳት ከፍተኛ ስለነበር የተሻለ ሕክምና እንዲያገኝ ሀረር ወደሚገኘው የሕይወት ፋና ስፔሻላይዝድ አጠቃላይ ሪፈራል ሆስፒታል ተወስዶ ሕይወቱን ለማትረፍ የህክምና ሲደረግለት እንደነበር የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የጥበቃና ደህንነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር አባድር ዩያ ለሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያ ሐ.ዩ. ኤፍ ኤም 91.5 ተናግረዋል፡፡

ጅቡ በታዳጊው ላይ ያደረሰው ጉዳት ከባድ በመሆኑና የፈሰሰበትንም ደም ለመተካት ደም በመስጠት የህክምና ድጋፍ በማድረግ ሕይወቱን ለማትረፍ ርብርብ ቢደረግም ከምሽቱ 3፡30 አካባቢ የታዳጊው ሕይወቱ ማለፉን በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የሕይወት ፋና ስፔሻላይዝድ አጠቃላይ ሪፈራል ሆስፒታል የድንገተኛና አደጋዎች ህክምና ማዕከል ተረኛ የህክምና ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥና አካባቢው የሚኖሩ ሰዎች ህፃናት ልጆች ብዙ የሰዎች እንቅስቃሴ በማይኖርባቸው አካባቢዎች ብቻቸውን እንዳይሄዱ መምከርና ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸውና የዩኒቨርሲቲው ጥበቃም ጅቦች በሚኖሩባቸው አካባቢዎች በሚገኙ መንገዶች ላይ አስፈላጊውን ጥበቃ እንደሚያደርግ ኮማንደር አባድር ጠቁመዋል፡፡
በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የሚኖሩ ጅቦች ከማህበረሰቡ ጋር በሰላም አብረው ሲኖሩ እንደነበርና ከዚህ ቀደም በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ እንደዚህ አይነት መሰል አደጋ እንዳልደረሰ ኮማንደር አባድር ዩያ ለሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ሬዲዮ ኤፍ ኤም 91.5 ተናግረዋል።

የታዳጊ ህፃን ኢፋ አባድር አደም የቀብር ስነስርዓት ዛሬ ሚያዚያ 20/2015 ዓ.ም ረፋድ ላይ ሐረማያ ባቴ ቀበሌ ተፈፅሟል፡፡

ዘጋቢ፡- ሽመልስ በቀለ
ምስል፡- ከክምችት
ሚያዚያ 20/2015 ዓ.ም

23/11/2022
23/11/2022

Our college have recieved 20 latest computers as initiation of stablishment of Health Science education eLearning center Stablishment from director of JSI Digital Health Acitivity Project Mr Teshome Deres.
JSI DHA is supporting HHSC through instructors and students training for several years.
Health Informatics, pharmacy and health extension department students will be the primary participants of the eLearning courses.

03/11/2022
30/10/2022

Amir M***a Ahmed Quality education is the education that best fits the present and future needs of the learners.

14/10/2022

13/10/2022

አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ

አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል።

አምባሳደር ሽፈራው ከጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መሾማቸውን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ በተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊነት ከዚህ ቀደም ማገልገላቸው ይታወሳል፡፡

ካገለገሉባቸው ኃላፊነቶች አምባሳደር ሽፈራው በቀድሞ ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በኦዲትና አቅም ግንባታ ቢሮ ኃላፊነት፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድርነት እና በርዕሰ መስተዳደርነት መርተዋል፡፡

በተጨማሪም የትምህርት ሚኒስትር፣ የግብርና እና የእንስሳት ሀብት ሚኒስትር እና በደቡብ ኮሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን አገልግለዋል፡፡

Photos from Amir M***a's post 13/10/2022

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አዲስ ዋና
ዳይሬክተር ተሾመለት
***** ***** ***** ***** *****
*****

ክቡር አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ ከጥቅምት
2 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የትምህርትና ስልጠና
ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው በኢፊዲሪ
ጠቅላይ ሚኒስትር በክቡር ዶ/ር አብይ
አህመድ ተሾመዋል፡፡
ክቡር አምባሳደር ሽፈራው በቀድሞ ደቡብ
ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በኦዲትና
አቅም ግንባታ ቢሮ ኃላፊነት፤ በምክትል ርእሰ
መስተዳደርነት እና ለሰባት ዓመታት ክልሉን
በርእሰ መስተዳደርነት
መርተዋል፡፡በተጨማሪም የኢፌዲሪ
የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር፤ የግብርና እና
የእንስሳት ሀብት ሚኒስቴር ሚኒስትር እና
በኮሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን
አገልግለዋል፡፡

የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
ሠራተኞች እና አመራሮች መልካም የሥራ
ዘመን እንዲሆንላቸው እንመኛለን፡፡

የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና
ባለሥልጣን

13/10/2022

በህይወት የሌሉና በውጪ ሀገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በባንክ ያላቸውን ለረጅም ጊዜ ሳይንቀሳቀስ የቆየ ሂሳብ ደንበኞቹ እንዳሉና እንደቀረቡ አስመስለው በማንቀሳቀስ ገንዘቡን ለሌሎች ሰዎች በማስተላለፍ በድምሩ ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ በመውሰድ ለግል ጥቅማቸው አውለዋል የተባሉ ሰባት የአዋሽ ባንክ ሰራተኞች ላይ ዐቃቤ ህግ ክስ መሰረተ፡፡

ተከሳሾቹ 1ኛ አቶ ሐብታሙ ደረሰ ጅማ (በአዋሽ ባንክ የዋናው መ/ቤት ቅርንጫፍ የደንበኞች አገልግሎት መኮንን የነበረ)
2ኛ አቶ ወርቁ ኃይሉ ጫሊ ( በአዋሽ ባንክ የዋናው መ/ቤት ቅርንጫፍ የደንበኞች አገልግሎት ሥራ አስኪያጅ የነበረ)
3ኛ አቶ ፈጠነ ገ/እግዚአብሔር ነጋ (በአዋሽ ባንክ የዋናው መ/ቤት ቅርንጫፍ የደንበኞች ግንኙነት መኮንን የነበረ)
4ኛ አቶ ደበላ ንጉሴ ወርቅነህ ( በአዋሽ ባንክ የዋናው መ/ቤት ቅርንጫፍ የደንበኞች አገልግሎት መኮንን የነበረ)
5ኛ አቶ ምስጋናው ያረጋል አንለይ ( በአዋሽ ባንክ የዋናው መ/ቤት ቅርንጫፍ የደንበኞች አገልግሎት መኮንን የነበረ )
6ኛ አቶ ሮባ ታደለ ዲንቃ ( በአዋሽ ባንክ የዋናው መ/ቤት ቅርንጫፍ ሂሳብ ሹም የነበረ)
7ኛ ተከሳሽ ጉግሳ ( በአዋሽ ባንክ የዋናው መ/ቤት ቅርንጫፍ የደንበኞች አገልግሎት መኮንን የነበረ)
ሲሆኑ የተሰጣቸዉ ሥልጣን እና ኃላፊነት አላግባብ በመገልገል በህይወት የሌሉ ደንበኞችን ጨምሮ የሂሳብ ባለቤቶቹ ሳይቀርቡ እንደቀረቡ በማስመሰል እና ሂሳቡን ተንቀሳቃሽ (Active) በማድረግ አጠቃላይ ከስድስት ሚሊዮን ብር በላይ ወስደዋል በሚል ዐቃቤ ህግ 4 ተደራራቢ ክስ መስርቶባቸዋል፡፡ የዐቃቤ ህግ ክስ እንደሚያሳየው ተከሳሾቹ
1ኛ ወ/ሮ ብርሃን ዳባ በተባለች የባንኩ ደንበኛ ለረዥም ጊዜ ያልተንቀሳቀሰ ገንዘብ ደንበኛዋ በህይወት ሳትኖር ቀርባ ሂሳቡን ያንቀሳቀሰች በማስመሰል እ.ኤ.አ ከ23/10/20 እስከ 30/10/2020 ዓ.ም ባሉት 7 ቀናት ውስጥ በ3 የሂሳብ ዝውውሮች የሂሳብ እንቅስቃሴውን በመቀበል እና በማጽደቅ 1ኛ፣ 2ኛ፣ 3ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች ከማይንቀሳቀስ ሂሳብ 10,000 (አስር ሺ) ብር በማስተላለፍ ሂሳቡ ተንቀሳቃሽ (Active) እንዲሆን እና ሌሎች የሂሳብ ዝውውሮች እንዲፈፀሙ በማድረግ 1,603,000 (አንድ ሚሊዮን ስድስት መቶ ሦስት ሺ) ብር፤ 5ኛ ተከሳሽ ደግሞ 1,593,000 (አንድ ሚሊየን አምስት መቶ ዘጠና ሦስት ሺ) ብር እንዲሁም 6ኛ ተከሳሽ 795,000 (ሰባት መቶ ጠና አምስት ሺ) ብር ከወ/ሮ ብርሃን ዳባ ሂሳብ ተቀናሽ አድርገው ወደ ሌላ ቅርንጫፍ እና ባንክ በማስተላለፍ ዝውውር እንዲፈፀም በማድረግ ፣

2ኛ በውጪ ሃገር በምትኖረው ወ/ሮአስናቁ ተሾመ ገ/ማርያም በተባለች ደንበኛ ለረዥም ጊዜ ያልተንቀሳቀሰ ሂሳብ ደንበኛዋ ቀርባ ሂሳቡን ያንቀሳቀሰች በማስመሰል 1ኛ፣ 2ኛ፣ 6ኛ እና 7ኛ ተከሳሾች ከማይንቀሳቀስ ሂሳብ 10,000 (አስር ሺ) ብር በማስተላለፍ ሂሳቡ ተንቀሳቃሽ (Active) እንዲሆን በማድረግ እ.ኤ.አ በ11/11/20 እና በ12/11/2020 ዓም በ2 ቀናት በተካሄዱ 2 የሂሳብ ዝውውሮች ከወ/ሮአስናቁ ተሾመ ሂሳብ አንድ ሚሊዮን አራት መቶ ሁለት ሺህ (1,402,000) ብር ተቀናሽ በማድረግ የሂሳብ ዝውውር እንዲፈፀም በማድረጋቸው፣

3ኛ ኦመር መሀመድ ደዋም የተባለ ደንበኛ በተንቀሳቃሽ ሂሳብ የሚገኝን ለረዥም ጊዜ ያልተንቀሳቀሰ ገንዘብ ደንበኛው ሳይቀርብ ቀርቦ ሂሳቡን ያንቀሳቀሰ በማስመሰል እ.ኤ.አ 10/09/20 (5/13/12ዓም) በተዘጋጀ ሐሰተኛ የሐዋላ መላኪያ ቅጽ በመጠቀም ከኦመር መሀመድ ሂሳብ ተቀናሽ አድርገው ወደ ሌላ ቅርንጫፍ በማስተላለፍ 191,000 (አንድ መቶ ዘጠና አንድ ሺ) ብር ዝውውር እንዲፈፀም በማድረግ እና
4ኛ ከዚህ ዓለም በሞት በተለዩት በወ/ሮ አስቴር ምህረቱ ስም በተከፈተ የቁጠባ ሂሳብ የሚገኝን ለረዥም ጊዜ ያልተንቀሳቀሰ ገንዘብ ደንበኛዋ ቀርባ ሂሳቡን ያንቀሳቀሰች በማስመሰል ከእ.ኤ.አ 24/11/20 እስከ 07/12/20 ዓም ባሉት አጭር ቀናት በተካሄዱ 3 የሂሳብ ዝውውሮች የሂሳብ እንቅስቃሴውን በመቀበል እና በማጽደቅ 3ኛ ተከሳሽ ደግሞ ከማይንቀሳቀስ ሂሳብ 10,000 ብር በማስተላለፍ ሂሳቡ ተንቀሳቃሽ (Active)እንዲሆን በማድረግ ከአስቴር ምህረቴ ሂሳብ 2,510,000 (ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ አስር ሺ) ተቀናሽ አድርገው ወደ ሌላ ባንክ እና ቅርንጫፍ በማስተላለፍ የባንኩ ንብረት ጉዳት እንዲደርስበት ያደረጉ በመሆኑ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌድሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1) (ሀ)፣ የሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ (9)(2) ላይ የተደነገገውን መተላለፍ በፈፀሙት በሥልጣን አላግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል በ4 ተደራራቢ ክሶች ተከሰዋል፡፡
ፍርድ ቤቱ የዐቃቤ ህግ ክስ ለተከሳሾች እንዲደርሳቸው ያደረገ ሲሆን ክሱን ለማንበብ ለጥቅምት 8/2015 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡

Want your school to be the top-listed School/college in Alemaya?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address

Alemaya