Afar National Regional State Education Bureau

Afar National Regional State Education Bureau Welcome to the official Page of Afar National Regional State Education Bureau
(1)

Rakaakayak Baritto biiro kee xisnee kee konstraction biiroh koobaahissol Qafar rakaakayih doolataak geytime maali qokolu...
24/08/2026

Rakaakayak Baritto biiro kee xisnee kee konstraction biiroh koobaahissol Qafar rakaakayih doolataak geytime maali qokolut xisne akak takkuwayta 35 takke madabak nahar barittoh buxaaxik xisne taama Elle takku waytah tan arooca xisne abta konterakterwal tabsaanamih taama tekke.

Rakaakay baajetik ossotinah ETOl cugaysot 35 takke barittoh buxaaxih xisne taama axcih Rakaakay caddol sittat 70 takke barittoh buxaaxik xisne taama xayi uddurih addat qemmiselem timixxige.

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት “በአብዛኛው ደስተኞች ነን” ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ። ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ከተፈታኝ ...
23/08/2026

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት “በአብዛኛው ደስተኞች ነን” ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ። ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ከተፈታኝ ተማሪዎች መካከል 87.2 በመቶው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያሳልፋቸው ውጤት ማምጣት ሳይችሉ በቀሩበት እና 565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አለማሳለፋቸውን ካስታወቁ በኋላ ነው።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ የትምህርት ሚኒስትርነት ኃላፊነት ከተረከቡ ወዲህ ለአምስተኛ ጊዜ የተካሄደውን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት ያሳወቁት ትላንት ቅዳሜ ነሐሴ 16፤ 2018 ዓ.ም ነው። ባለፈው ሰኔ ወር መጨረሻ በበይነ መረብ፣ በሐምሌ ወር መጀመሪያ ላይ ደግሞ በወረቀት አማካኝነት የተሰጠውን ፈተና የወሰዱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ብዛት 550,210 ነው።

ከእነዚህ ተፈታኞች መካከል ወደ ዩኒቨርሲቲ ማሳለፍ የሚያስችለውን 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡት 70,544 ተማሪዎች መሆናቸውን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ተናግረዋል። በዚህ መሰረት ዘንድሮ ለዩኒቨርሲቲ ያለፉ ተማሪዎች ምጣኔ 12.8 በመቶ ሆኗል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ የትምህርት ሚኒስትርነት ኃላፊነትን ከተረከቡ ካለፈው አምስት ዓመት ወዲህ፤ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያልፉ ተማሪዎች ምጣኔ 15 በመቶ እንኳ መሻገር አልቻለም። እርሳቸው ወደ ሚኒስትርነት በመጡበት በ2014 ዓ.ም ከ50 በመቶ በላይ የፈተና ውጤት ማስመዘገብ የቻሉ ተማሪዎች ብዛት 3.2 በመቶ ነበር።

🔴ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/18603/

በአፋር ክልል ከ700 በላይ  ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት አስመዘገቡ     ሰመራ ፣ነሀሴ 17፣2018 (አፋ.ብ.መ.ድ) በአፋር ክልል ባለፈው የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ...
23/08/2026

በአፋር ክልል ከ700 በላይ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት አስመዘገቡ

ሰመራ ፣ነሀሴ 17፣2018 (አፋ.ብ.መ.ድ)

በአፋር ክልል ባለፈው የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ከ4 ሺህ በላይ ተማሪዎች ውስጥ ከ700 በላይ የሚሆኑት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ማስመዝገባቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ የተማሪዎቹን ውጤት በማስመልከት ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ባለፈው የትምህርት ዘመን 4 ሺህ 685 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በክልሉ በተመረጡ የፈተና ማዕከላት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና መውሰዳቸውን ገልጿል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ሙሳ አደም እንደገለጹት፣ ከተፈተኙት ተማሪዎች ውስጥ ከ700 በላይ የሚሆኑት የዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል።

ይህም አፋር ክልል በዚህ ዓመት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ካስመዘገቡ ክልሎች መካከል በአማካይ በቁጥር ሦስተኛ የሚሆኑ ተፈታኞችን ያሳለፈ ክልል እንዲሆን አድርጎታል ብለዋል።

በዚህ የውጤት ሂደት 25 ትምህርት ቤቶች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ያሏቸው ሲሆን፣ አንድ ትምህርት ቤት ደግሞ ከተፈተኑ ተማሪዎቹ ሁሉንም በማሳለፍ ታሪክ መስራቱን ኃላፊው ገልጸዋል።

እንደ አቶ ሙሳ ገለጻ፣ የተገኘው ውጤት በትምህርት ዘመኑ በቀድሞ የፈተና ውጤቶች ላይ የተለዩ ክፍተቶችን በመለየት የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠት፣ የአይሲቲና ተያያዥ የሳይንስ ላብራቶሪ ማዕከላትን ማጠናከር እንዲሁም የተማሪዎችን የአይሲቲ አጠቃቀም ለማሻሻል ስልጠና መስጠት በመቻሉ ነው።

በተጨማሪም የትምህርት መርጃ ግብዓቶችና የመማሪያ መጽሐፍት ስርጭትን ማሻሻል እና የተማሪ ወላጆች በትምህርት ሴክተሩ የበለጠ ተሳትፎ እንዲኖራቸው የሚያስችል አደረጃጀት መዘርጋቱ ለተገኘው ውጤት ጉልህ አስተዋጽዖ ማበርከቱን አብራርተዋል።

ኃላፊው አክለውም፣ ለተገኘው ውጤት ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጀምሮ እስከ ትምህርት ሴክተሩ ተራ ፈጻሚዎች ድረስ ያሉ አካላት ጉልህ አስተዋጽዖ ማበርከታቸውን ገልጸው፣ ለሁሉም ምስጋና አቅርበዋል።

🫴 መሀመድ አሊ

🫴 አፋር ብዙሀን መገናኛ ድርጅት

Qafar Rakaakayak Barittô Biirok Naharsi Saqal Xoktor, Muusa Adam 2018 liggidak agat caddoh aqayyaare / 12 hayto footimah...
23/08/2026

Qafar Rakaakayak Barittô Biirok Naharsi Saqal Xoktor, Muusa Adam 2018 liggidak agat caddoh aqayyaare / 12 hayto footimah aqayyaare xalu wagittaamal maybalaalaqa yecee.

Ximolik, 17/12/2018 I.l.l

Asaaki macsenta Rakaakayak Barittô Biirok Naharsi Saqal xoktor Muusa Adam agat caddoh aqayyaare wagsiisak yeceeh yan maybalaalaqal iyyeemih 2018 baritto liggidal 4,685 yakkeh yan barteenitih agat caddoh aqayyaare Rakaakay caddoh Semera Jaamiiqat edde anuk 11 aqayyaare fanteenaanil Onlaayinil yeceenih sugeenim qaddaysak, 2018 agat caddoh aqayyaare xaluy Baritto malaak yeyyeeqeh yan Qafar Rakaakayak agat caddol Addis ababa kee hararak ciggiilak sidoc hayto awaquk axcih addis ababa 32.4% Harar 22.6% Qafar Rakaakay kaadu 15.6% gaba baahak agat caddol sidoc haytooy, Rakaakayittel wagiteenih enek haytoh awaquk 25 barittoh buxaaxil 705 yakkeh yan barteenit Jaamiiqat culmah ximmô baahak tatrem qaddoyse.

Ossotinah Qafar Rakaakayih caddol inki barittoh buxa inkih yan barteenit tatrusem kee Qafar Rakaakay agat Top 5 addat / yayse xalu baaheh yan 5 addat culeh yanim qaddoyse.

Tama aracal Rakaakayak Barittô Biirok Naharsi Saqal Xoktor, Muusa Adam Qafar Rakaakay ta caddoh yawquk kaxxa doori digirteeh qokol abteh tan dagortih kulsale gadda gacise.

Gadda akah yecsen dagortih tu-gactek

Aakamal 🫴 Qafar Rakaakayih president Massakaxxale Cajji Awwal Qarba kee xiinissoh abbah kutbeh buxaay,

🫴 Rakaakayak Ciggiila president Massakaxxale Qumar Nuur Qarbaay,

🫴 Rakaakayak Leeda massoynah kutbeh buxah Saqal, Massakaxxale Macammad Cuseen Qalisaay,

🫴 Rakaakayak Ciggiila presidentih bilhadal ayyuntiino Kilasterih saqalaay, Qa/ Qun/ Sporti Biirok Naharsi Saqal Massakaxxale Caamid Duulaay,

🫴 Rakaakayak koraan ayfafayaay,
🫴 Rakaakayak teleey
🫴 Samara Jaamiiqataay, kalali qandeh adoytit kee federal police adoytit kee Rakaakay polisiiy.

🫴 Sekter birooraay, axcih Rakaakayak kabxaa kee sanaqtta biirooy, Merrayti Biirooy, Qaafiyat Biirooy kalah tan baxabaxsale birooray gammit nek gatek inkihiiy,

🫴Rasitte kee daqorti Miraaciinuuy, baritto maktabawah saqoltiiy,
🫴 Biirok Miraaciini Makaadoh adoytit kee mihratleelaay ICT mihratleelaay, Gawwaani kee adda xaali kolleejiteh, axcih inkih nee qokolteh tan dagortih Rakaakayak Barittô Biirok migaaqal kulsale gadda gacsa iyye.

70 Alfiiy 544 Takke Barteenit Jaamiqat Culmah Ximmo Bahte-Baritto MalaakSamara,Ximoli-Alsak 16/2018 (AFMMA)12 Haytoh Foo...
22/08/2026

70 Alfiiy 544 Takke Barteenit Jaamiqat Culmah Ximmo Bahte-Baritto Malaak

Samara,Ximoli-Alsak 16/2018 (AFMMA)

12 Haytoh Footimah Aqayyare Beyte 550 Alfiiy 210 Takke Barteenitik 70 Alfiiy 544 Takke Barteenit Jaamiqat Culmah Ximmo Bahtem Baritto Malaak Qaddose.

Baritto Malaak P/r Birhanu Negga Sanat 2018 Liggidak 12 Hayto Fotimah Xalu Wagsiisak Yece Maybalalqal Iyyemihi Asanat Yayse Xali Edde Yunkuttube Sanat Kinnim Yescesse.

A sanat Aqayyare Beyte Bartenitik Tatur Ximmo Bahtem 70 Alfiiy 544 Takkem Tatur Ximmo Bahtem Yiysixxige.

Aqayyare Beyte Barteenik Addak 12 Ximmoy 8 Gaba Takke Barteenit Booluk 50 Gaba Kee Tohuk Dagah Xalu Bahtem Yiysixxige.

Asanat 12 Hayto Footimah Aqayyare 563 Alfiiy 960 Takke Barteenit Ankuttubuk 550 Alfi 210 Takke Barteenit Aqayyare Beytem Kassise.

Addis Ababah Magaalah Xinisso 32 Ximmoy 3 Gaba Booluk Tatrusak Qimbih Caddol Geytimtamat Yaabe.

Asanata Aqayyare Beyte Bartenitik Fanak 62 Gaba Takkem Aqayyare Waqinak (Onlinel) Beytem Yescesse.

88 Takke Baritto Buxaaxi Barteenit Inki Tanuuk Tatrussem Kee 565 Barittoh Buxaaxi Hebelto Barteenit Tatrusewaytem Kassise.

Taturte Bartenitik Fanak Gino Saynis 16 Ximmoy 5 Gaba Takkem Kee Ayyuntiino Aaynisik Kaadu 8 Ximmoy 33 Gaba Kinnim Qaddose.

👉 Afar Mass Media Agency

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከ 12.8 በመቶ   ወይም 70, 544 ተማሪዎች የማለፊያ ወጤት ማምጣታቸው ተገለጸ።በዘንድሮው ፈተና ከ600 ከፍተኛ ውጤት...
22/08/2026

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከ 12.8 በመቶ ወይም 70, 544 ተማሪዎች የማለፊያ ወጤት ማምጣታቸው ተገለጸ።

በዘንድሮው ፈተና ከ600 ከፍተኛ ውጤት 591.64 በተፈጥሮ ሳይንስ ሆኖ ተመዝግቧል።

------------ // ----------

‎(ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤትን በማስመልከት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከ 12.8 በመቶ ወይም 70, 544 ተማሪዎች 50% እና በላይ ወጤት ማስመዝገባቸውን አብራርተዋል።


‎ባለፈው ዓመት በተሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና 8.9 በመቶ ተማሪዎች ማለፋቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ በዚህ ዓመት የማለፊያውን ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ቁጥር ከአምናው ጋር ሲነጻጸር ከ20 ሺህ በላይ ብልጫ እንዳለው ተናግረዋል።


‎በዚህ ዓመት ከ50 በመቶ በላይ ያመጡ ተማሪዎች በተፈጥሮ ሳይንስ 16.58 በመቶ እንዲሁም በማህበራዊ ሳይንስ 8.33 በመቶ መሆኑንም ተናግረዋል።


‎በተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 ከፍተኛ ውጤት 591.64 በወንድ ፤ 583.03 በሴት ሆኖ የተመዘገበ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ከ600 ከፍተኛ በወንድ 576.25 በሴት 569.17 ሆኖ መመዝገቡን አብራርተዋል።


‎ በዚህ ዓመት ተማሪዎችን ካስፈተኑ ት/ቤቶች መካከል 88 ት/ቤቶች 100% ተማሪዎቻቸውን ማሳለፋቸውን እና 565 ትምህርት ቤቶች ደግሞ ምንም ተማሪ አለማሳለፋቸውን ተናግረው ከባለፈው ዓመት ምንም ካላሳለፉ 1232 ት/ቤቶች ጋር ሲነጻጸር የተሻለ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህ ዓመት ለፈተና ከተመዘገቡ 563,960 ተማሪዎች ውስጥ 550,210 ተማሪዎች ፈተናቸውን ወስደዋል።


‎በአጠቃላይ በትምህርት ዘርፉ እየነተገበሩ ባሉ የሪፎርም እርምጃዎች የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መምጣቱን የዘንድሮው ውጤት ማሳያ መሆኑንም ክቡር ሚኒስትሩ አብራርተዋል።

🫴 ትምህርት ሚኒስቴር

Rakaakayak Baritto Biirok Miraaciini Makaadoh adoytit Baritto Sekterik 2019 Mizaaniyat ikraaro kee 2019 taama liggidal h...
21/08/2026

Rakaakayak Baritto Biirok Miraaciini Makaadoh adoytit Baritto Sekterik 2019 Mizaaniyat ikraaro kee 2019 taama liggidal hangisso akah yeceen taamoomil walal gudgud gexsen.

Ximolik 15/12/2018 I.l.l

Tama aracal Rakaakayak Barittô Biirok Naharsi Saqal xoktor, Muusa Adam Miraacisak 2019 taama liggidih Mizaaniyat kee baritto Sekterik Qusba Santal hangisso akah yeceen taamoomiiy, Biirok Istraateeji Caagiidal baar leh yan walal abak 2019 Mizaaniyat inki xongolol faaticisen.

Carruki Daqaarak Naharsi caddoh barittoh buxal coox daabisiyyi taddeera gexsen.Carruki Daqaarak Naharsi caddoh barittoh ...
20/08/2026

Carruki Daqaarak Naharsi caddoh barittoh buxal coox daabisiyyi taddeera gexsen.

Carruki Daqaarak Naharsi caddoh barittoh buxal Maaqiddah takke cooxuk 50 iraawoh yakke cooxuk 150 Daqaarak Baritto kutbeh buxah Saqal Gifta, Qabdu Macammad kee Daqaarak buqree kee gino Daddoosih maktabih Saqal Gifta, Qali Caysamah kobaahissol coox dabisaanamih taama asaaki macsenta aben.

ከ80 በመቶ በላይ ያመጡ ተማሪዎችን በአዳሪ ትምህርት ቤቶች የመመዝገብ ስራ ተጀመረ********************  │በ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከ80 በመቶና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎችን ...
19/08/2026

ከ80 በመቶ በላይ ያመጡ ተማሪዎችን በአዳሪ ትምህርት ቤቶች የመመዝገብ ስራ ተጀመረ
********************

│በ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከ80 በመቶና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎችን በአዳሪ ትምህርት ቤቶች ለመቀበል ምዝገባ መጀመሩን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የአዳሪ ትምህርት ቤቶች የተማሪ ምዝገባን አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የሚኒስትሩ አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ክንድዬ ገብረሕይወት (ፕ/ር)፤ በ8ኛ ክፍል ከ80 በመቶና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎችን በማወዳደር ምዝገባ የተጀመረ ሲሆን፤ ከገጠራማ እና ከአርብቶ አደር አካባቢዎች ለሚመጡ ተማሪዎች ልዩ ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል፡፡

ምዝገባው በሚኒስቴሩ በይነ-መረብ በኩል ያለምንም ክፍያ እንደሚከናወን ጠቁመው፤ ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ውጤታቸውን በፒዲኤፍ (PDF) ስካን በማድረግና የፈተና መለያ (ID) ቁጥራቸውን በመጠቀም ባሉበት ሆነው በመመዝገብ ወደ አዲስ አበባ ሳይመጡ ባሉበት ክልል ሆነው በበይነ-መረብ ፈተናውን ይወስዳሉ ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በአምስት አካባቢዎች (ጂጂጋ፣ ጋምቤላ፣ ቦንጋ፣ ቡኢ እና ወሊሶ) አገልግሎት እየሰጡ ካሉት አራት አዳዲስ ትምህርት ቤቶች ማለትም በባህር ዳር፣ አርባ ምንጭ፣ ድሬደዋና አሶሳ መቀበል እንደሚጀምሩ ጠቁመዋል፡፡

በሁሉም ክልሎች የተገነቡ 13 የፌደራል አዳሪ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት ሲጀምሩ፣ እያንዳንዱ አዳሪ ትምህርት ቤት እስከ 1,000 ተማሪዎችን በመቀበል በየዓመቱ 13 ሺህ አዳዲስ ተማሪዎችን የማስተናገድ አቅም ይኖራቸዋል ሲሉ ተናግረዋል።

ለትምህርት ቤቶቹ የሚያስፈልጉ ዳይሬክተሮችና መምህራንም በፌደራል ደረጃ በልዩ ሁኔታ ተመርጠው እየተቀጠሩ ይገኛሉ ሲሉ ገልጸዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፕሮግራሙ ከፍተኛ አገራዊ ሀብት እየፈሰሰበት የሚገኝ በመሆኑ፣ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ብቁ ተማሪዎች የዚህ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።

በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ፕሮግራሞች ጥራት ማሻሻል መሪ ስራ አስፈፃሚ ዮሐንስ ኦጋሶ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች በተግባር የተደገፈ ትምህርት በመስጠት በፈጣራ የጎለበተ ዜጋ እያፈሩ ነው፡፡

"አዳሪ ትምህርት ቤት ላይ የሚማሩ ልጆች መጀመሪያውንም በጣም ጎበዝ፣ ፈጣን የመማር ችሎታና ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ልጆች የሚማሩ በመሆኑ በቀጣይ እነዚህ ልጆች የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው" ብለዋል፡፡

ባለፈው ዓመት በአምስት አዳሪ ትምህርት ቤቶች በእያንዳንዱ 250 ተማሪዎች፣ በአጠቃላይ 1,250 ተማሪዎች የ9ኛ ክፍል ትምህርታቸውን አጠናቀዋል።

በታደሠ ብናልፈው

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት #አዳሪትምህረትቤቶች #ምዝገባመጀመር #ትምህርት

በትምህርት ዘርፍ ባለን አቋምና በምንሰራው ሥራ እንኮራበታለን - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
17/08/2026

በትምህርት ዘርፍ ባለን አቋምና በምንሰራው ሥራ እንኮራበታለን - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Address

Afar National Regional State Education Bureau
Afar

Opening Hours

Monday 07:00 - 18:00
Tuesday 07:00 - 18:00
Wednesday 07:00 - 18:00
Thursday 09:00 - 18:00
Friday 07:00 - 18:00
Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00

Telephone

+251911272806

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Afar National Regional State Education Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Afar National Regional State Education Bureau:

Shortcuts

Share